Wisdom Books Job

Waiting on the Lord

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 379 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ጌታን መጠበቅ ሁል ጊዜ አስቸጋሪ ይሆናል ፤ በዚህ ምዕራፍ ኢዮብ ለሶፋር ሁለተኛ ንግግር ምላሽ ሰጠ ፡፡ የኢዮብ ንግግር በዚህ ምዕራፍ ለሶፋር ምላሽ ነበር ነገር ግንእየተከናወነ ለነበረዉ ነገር ትልቅ ስዕል ንግግር ነበር ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (21፡ 1-3)፡ ኢዮብ ተስፋ በመቁረጥ ሁኔታ ዉስጥ ቃሉን እንዲሰሙት፣ በእርሱ ባህሪ ላይ መፍረድ እንዲያቆሙና በችግሩ ልቡን እንዲሰሙት ፈለገ ፡፡ ወዳጆቹ ከእርሱ ጋር እንዲያዝኑ ፈለገ ፤ ኢዮብ በኢዮ (13፡ 5) ያለዉን ስሜት ደግሞ በመጥቀስ ይህን ንግግር ጀመረ “ ምነዉ ዝም ብላችሁ ብትኖሩ ! ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር “ ፡፡ ኢዮብ ወዳጆቹን ቸኩሎ ደግሞ ከመናገሩ በፊት ለትንሽ ጊዜ ወደ እርሱ እንዲያደምጡ ገሰፃቸው ፡፡

ኢዮብ (21፡ 4-16)፡ኮንስታብል ኢዮብ በአጭሩ በወዳጆቹ መሰማት ብቻ እንደፈለገ አመለከተ ፡፡ ኢዮብ እንዲሰሙት ስለሆነ ሰዉ ተስፋ ቆርጧል ምክንያቱም እግዚአብሄር እንኳን ወደ እርሱ እያዳመጠ እንዳልነበር ስለ ተሰማው ፤ ይሁን እንጂ ወዳጆቹ ፈፅሞት እንደ ነበር እርግጠኞች በነበሩበት ኃጢዓቱ ላይ ንስሐ እንዲገባ በመሞከር ላይ ያተኮሩ ነበሩ ፡፡

ቁጥር 7 መጀመሪያ ላይ ኢዮብ እንዴት ክፉ ሰዎች ብልፅግና እንደሚገጥማቸው ተናገረ ፤ ክፉዎች በሁሉም ነገር እግዚአብሄርን እዉቅና ለመስጠት እምቢ በማለት መልካም ነገር ይገጥማቸዋል ፤ ዋይርስቤ ይህን “ ተግባራዊ እግዚአብሄርን መከዳ “ በማለት ይጠራዋል ፡፡ ክፉዎች ስለ እግዚአብሄር አይጨነቁም/ጣጣ የላቸዉም ነገር ግን አሁንም የበለፀጉ ነበሩ ፤ ይህ እዉነት ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ክፉዎችን ይቀጣል እንደ እግዚአብሄር ሀሳብ ያሉትን ደግሞ ሁል ጊዜ ይባርካል የሚለዉን የወዳጆቹን ጠቅላላ ትምህርታቸዉን ሸረሸረው ፡፡

ኢዮብ (21፡ 17-26)፡ ኢዮብ እግዚአብሄር እንዴት እንዳመሰቃቀለና ክፉዎችን መቼ እንዳበለፀገ ጠየቀ ፤ በኢዮብ ሀሳብ ዉስጥ ወዳጆቹ እንድትሆን እንዳደረጓት ህይወት ቀላል እንዳልነበረች ነበር ፤ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር ክፉዎች እንዲበለፅጉ እና ፃድቆች ደግሞ እንዲቸገሩ ይፈቅዳል ፤ ሌላ ጊዜ ላይ ደግሞ እግዚአብሄር ክፉዎችን ይቀጣል ፃድቆችን ደግሞ ያበለፅጋል ፡፡ ጉዳዩ ጓደኞቹ እንዲሆን አድርገዉት ከነበረዉ በላይ በጣም ሚስጥራዊና ቀመር የለሽ ነበር ፡፡ የኢዮብ ክርክር የካርማን ሀሳብ ስህተት አሳዬ ፤ እግዚአብሄር መታዘዝን ጨምሮ መልካም ነገር ማድረግ መልካም ነገር ለመቀበል ተደረገ ማለት አይደለም ፤ ኃጢዓትን ጨምሮ መጥፎ ነገር ማድረግ ማለት በተገቢ መጥፎ ነገር ይቀበላል ማለት አልነበረም ፡፡

ኢዮብ (21፡ 27-34)፡ ኢዮብ የወዳጆቹን የፍርድ አስተምሮት ስህተትነቱን ለማሳየት ብዙ ምሳሌዎችን አቀረበ ፡፡ በቀላሉ በዙሪያቸዉ በመጓዝ ክፉ ሰዎች እንዴት በደህንነት በቤታቸዉ እንደሚኖሩ፣ ሰላም የሆነ ቀብር አንደተደረገላቸዉና በሰዎች ቀብራቸዉ እንደሚጠበቅ እና ልጆቻቸዉ ከእነርሱ ኃላ እንደሚኖሩ እንዲመለከቱ ጠየቃቸው ፤ በኢዮብ ሀሳብ ወዳጆቹ ክርክራቸዉ ዉሃ የማያነሳ እንደሆነ እንዲያዩ በዙሪያቸዉ ባለዉ አለም ለማየት አይናቸዉን መክፈት እንደሚያስፈልጋቸዉ ነው ፡፡

በኢዮ (21፡ 4) ሁሉም ነገር በስህተት በሚሄድበት መካከል ላይና በችግሩ ጊዜ እግዚአብሄርን ለመጠበቅ ታገለ ፡፡ ሊንዳ ግሪን ስንቸገር ማድረግ የምንችላቸዉን አስር ምክሮች አቅርቧል፡

  1. ያዳናችሁ እግዚአብሄር ጩኸታችሁን እንደሚሰማ እመኑ ፡፡ ራሳችሁን በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ብታገኙትም ችግር የለም ብቻችሁን ብትሆኑም ወይም ደግሞ ከሌሎች ጋር ብትሆኑም ብቻ እግዚአብሄር እንደሚሰማችሁ እርግጠኞች ሁኑ ፡፡ “ እኔ ግን ወደ እግዚአብሄር እመለከታለሁ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ ፤ አምላኬም ይሰማኛል “ (ሚክ 7፡ 7) ፡፡
  2. በተስፋ ጠብቁ ላልተጠበቀ መልስም የተዘጋጃችሁ ሁኑ ፡፡ “ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እጠብቃለሁም “ (መዝ 5፡ 3) ፤ እግዚአብሄር መልሳችንን ይመልስልናል ነገር ግን ይመልሳቸዋል ባልነዉ መንገድ አይመልስ ይሆናል ፡፡
  3. ተስፋችሁን በቃሉ ላይ አድርጉ ፡፡ ተስፋችንን በብዙ ነገሮች ላይ ልናስቀምጥ እንችላለን ነገር ግን መዝ (130-5-6) “ አቤቱ ስለ ስምህ ተስፋ አደረገሁህ ፤ ነፍሴ በሕግህ ታገሰች ፡፡ ከማለዳዉ ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሄር ታመነች “ ይላል ፡፡
  4. በራሳችሁ ማስተዋል ሳይሆን በእግዚአብሄር ታመኑ ፡፡ “ በፍፁም ልብህ በእግዚአብሄር ታመን በራስህም ማስተዋል አትደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ እርሱም ጋዳናህን ያቀናልሃል “ (ምሳ 3፡ 5-6) ፡፡ በመጨረሻ/በከፍተኛ ስራ በትግል መካከል ላይ ሀሳባችንን ለማረጋጋት ምንም ነገር ማድረግ እንችልም ፤ እምነታችንን በእግዚአብሄር ላይ ለማስቀመጥ ስንወስን ብቻ የምንፈልገዉን መፅናናት እናገኛለን ፡፡
  5. ብስጭትን መቋቋም፣ ንዴትን መቆጣጠር፣ የተረጋጋ በመሆንና በመታገስ ፡፡ “ ለእግዚአብሄር ተገዛ ተስፋም አድርገዉ ፡፡ መንገድም በቀናችለትና ጥመትንበሚያደርግ ሰው አትቅና ፡፡ ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው ፤ እንዳትበድል አትቅና “ (መዝ 37፡ 7-8) ፡፡
  6. ጠንካራ መሆንና ድፍረትን መዉሰድ ፡፡ “ የእግዚአብሄርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ ፡፡ እግዚአብሄርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሄርን ተስፋ አድርግ “ (መዝ 27፡ 13-14) ፡፡
  7. የእግዚአብሄርን ቸርነት እንደማግኛ እንደ እድል ተመልከቱት ፡፡ “ እግዚአብሄር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻዉም ነፍስ መልካም ነው “ (ሰቆ.ኤር 3፡ 25) ፡፡
  8. በራሳችሁ መንገድ ከመሄድ ይልቅ ስለ እግዚአብሄር ተስፋ ጠብቁ ፡፡ “ ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው ነገር ግን ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠዉን የተስፋ ቃል ጠብቁ “ (ሐዋ 1፡ 4) ፡፡
  9. ሳታቋርጡ በፀሎት ቀጥሎ በማመስገንም የምትጠብቁ ሁኑ ፡፡ “ ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ “ (ቆላ 4፡ 1) ፡፡
  10. የሚመጣዉን በረከት አስታዉሱ ፡፡ “ እግዚአብሄርም የፍርድ አምላክ ነዉና ስለዚህ እግዚአብሄር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሳል ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል ፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው “ (ኢሳ 30፡ 18) ፡፡ በዚህ አሁን የእግዚአብሄርን በረከት እንቀበላለን ወይም ደግሞ ለዘላለም እንቀበላቸዋለን ፤ በአንዱ መንገድ እንደምንጠብቀዉ እግዚአብሄር ሊባርከን ተስፋ ሰጥቷል ፡፡

መደምደሚያ

በችግር/በስቃይ መካከል ላይ እግዚአብሄርን እንዴት መጠበቅ እንደምንችል እነዚህ አስር እዉነቶች እንድንረዳ ይረዱናል ፤ ሂደት ወይም ቀመር አይደሉም ነገር ግንበማንኛዉም ሁኔታ በሌላኛዉ በኩል እግዚአብሄርን ለመጠበቅ የሚያስፈልጉን ማግኘታችንን ለማረጋገጥ በእነዚህ እዉነቶች ላይ የሚያዙ ናቸው ፡፡

  1. Dr. Tom Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Job, p. 82; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  2. Constable, p. 82.

  3. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 44.

  4. Linda Green, “What to Do While You’re Waiting on God”; available at https://unlockingthebible.org/2017/08/what-to-do-while-youre-waiting-on-god/.

ጥያቄዎች

  1. ኢዮብ የተናገሩት ወዳጆቹ ሊሰጡት የሚችሉት አንድ መጽናናት ምን ነበር ? ሌሎችን ለመስማት ትታገላላችሁ ? የግል አስተያየታችሁን የምትሰጡ ከመሆንችሁ ይልቅ እንዴት የተሸለ አድማጭ መሆን ትችላላችሁ ?
  2. የኢዮብ እዉነተኛ ቅሬታ ለማን ያተኮረ ነበር ? ይህን እንደ መጥፎ ነገር ታዩታላችሁ ? ግለፁ
  3. የሶፋርና የወዳጆቹ ኢዮብ ስህተት እንደ ነበር ያስረዳዉ ሰዎስት ዋና ዋና ነገሮች ምን ነበሩ ? (ኢዮ 21፡ 7, 17, 22-26)
  4. ስለ ቤተሰቦቹ ኃጢዓት በልጆቹ ላይ በወደቀዉ ቅጣት የኢዮብ አስተሳሰብ ስፍራዉ ምን ነበር ? (ዘዳ 24፡ 16, ሕዝ 18፡ 1-20, ዮሐ 9፡ 1-3)
  5. ኢዮብ (21፡ 7-16) አንብቡ ፤ እግዚአብሄርን የማይቀበሉት ነገር ግን ከችግር ነፃ ሆነዉና በብልፅግና ሕይወት ሲኖሩ ራሳችሁን በመቅናትና በማድነቅ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ሁሉም ነገር ያላቸዉ የሚመስሉትን ሰዎች ወንጌልን እንዴት ትነግሯቸዋላችሁ ?
  6. በኢዮብ 21 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 21:4–5

“As for me, is my complaint against a man? Then why shouldn’t I be impatient? Look at me and shudder; put your hand over your mouth.”

ኢዮብ ለጓደኞቹ መለሰ ፤ ለምንስ ይህንን የመከራ ጊዜ እንደሚያሳልፍ እና ቀንና ሌሊት በቁስል እየተሰቃየ እንደሚኖር አስረዳ ፡፡ የኢዮብ አሳብና ስሜት ተለዋውጦ ነበር ፤ ግን አሁንም ከስቃይ ነጻ የሚሆንባት ቀን ድረስ እግዚአብሔርን መጠበቁን ቀጠለ ፡፡

መጠበቅ ፣ መታገስ ፤ በመንፈስ ስትመላለስ ጌታ በትዕግስት ይሞላሀል ፡፡ በሌላ በኩል በስጋ ስትመላለስ ፣ በተፈጥሮህ ትእግስት አልባ ትሆናለህ ፤ ጭንቀትና ፍርሀት ይወርስሀል ፤ ትናደዳለህ ሚዛናዊነትህንም ታጣለህ ፡፡ ምናልባት ቡና ለመጠጣት እየጠበክ ፤ በምግብ መደብር ውስጥ ተራ እየጠበክ ወይም የትራፊክ መጨናነቅ እንድቀንስ እየጠበክ በቃ በየቀኑ ያለው ሁኔታ ትእግስት አልባ ሊያደርግህ ይችላል ፡፡ ለሳምንት የህክምና ምርመራ ውጤት መጠበቅ ወይም ደግሞ የምትወደው ሰው ከቀዶ ጥገና ክፍል መውጣት ልብህ የምር እረፍትን እንዳያገኝ ሊዳርግ ይችላል ፡፡ ነገር ግን ጌታ እነዚህ እግዚአብሔርን የሚጠባበቁ ኃይላቸውን እንደሚያድሱ ይናገራል ፡፡ የምትጠብቀው ነገር ምንም ይሁን ጸሎትህን ወደ እግዚአብሔር ጸልይ እርሱም እንደሚሰማህ እመን እናም በተስፋ ጠብቅ ! ዛሬ በህይወትህ የሆነ ነገር ስትጠብቅ ፣ አንድ ነገር እመን ጌታ ያውቃል ፡፡ እርሱ ይሰማሀል ፡፡ ስለዚህ በመጨናነቅም ውስጥ ብትሆን እንኳ የእርሱን ጊዜ ተስፋ አድርግ ፡፡ በምስጋና ጠብቅ ፡፡ በእርሱ ተስፋዎች ውስጥ እረፍ ፡፡ ለፍርሀትና ለመበሳጨት የሚሆን ቅስቀሳን ተቃወም ፡፡ በመጠበቅ ውስጥ ሳለህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው ፡፡

“በውኑ የኀዘን እንጉርጕሮዬ ለሰው እናገራለሁን? አለመታገሥ ስለ ምን አይገባኝም ? ወደ እኔ ተመልከቱ፥ ተደነቁም፤ እጃችሁንም በአፋችሁ ላይ አኑሩ ። “

  • ኢዮብ 21፡4-5

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 5:3 — “ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም ። “

ኢሳይያስ 40:31 — “ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም ። “

ሚክያስ 7:7 — “እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል ። “