The Wicked Will Not Prosper
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በቀደመዉ ምዕራፍ ኢዮብ በመጨረሻ በሚያድነዉ ህያዉን ተቤዢ ላይ ያለዉን ተስፋ ገልጻል ፡፡ አሁን ለኢዮብ በምላሹ ሶፋር ሁለተኛ ንግግሩን አቀረበ ፡፡ ሌሎቹ ሁለቱ ወዳጆቹ ኤልፉዝና በልዳዶስ ሁለተኛ ንግግራቸዉን ሰጥተዋል፣ ሶፋርም ምላሹን መስጠት ፈለገ ፡፡ የሶፋር የመጀመሪያዉ ንግግር በምዕራፍ 11 ነበር ፡፡ በዚህ ንግግር ሶፋር “ ኢዮብን የክፉዎችን እጣ እንደ ገና እንዲመለከተዉ አስጠነቀቀው “ ፤ የሶፋር ሁለተኛዉ ንግግርእስካሁን ከተናገሩት ከሌሎቹ በላይ ኢዮብን ይጎዳዋል ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (20፡ 1-3)፡ እነዚህ ቁጥሮች በግልፅ የሶፋርን ብስጭት ያሳያሉ ፡፡ ሶፋር የኢዮብ ግሳፄ እንዳበሳጨዉ ስላረጋገጠ ለመድገም እንዳስገደደዉ ተሰማው ፤ ምናልባትም ይህ ለኢዮብ በኢዮ (16፡ 3) “ በዉኑ ከንቱ ቃል ይፈፀማልን ? ወይስ ትመልስ ዘንድ ያነሳሳህ ምንድር ነው ? “ ለሚለዉ ንግግር ምላሽ ነበር ፡፡ ፊሊፕ ብሩክ “ እምነት አንድ የተጠቃን ሰዉ ከእርሱ ላይ ሸክሙ የማንወስድለትን ነገር ግን መሸከም እንደሚችለዉ ጥንካሬዉን በመጥራት በመሸፈን መርዳት እንደምንችል “ ፅፏል ፡፡
ኢዮብ (20፡ 4-11)፡ ሶፋር የክፉዎችን ብልፅግና በግልፅ ዘረዘረ ፤ አሁን ሆኖ ከነበረዉ ከኢዮብ ደስታ ጋር ተመሳሳይ ክፉ ሰዎች የሚገጥማቸዉ ደስታ በፍጥነት እንደመጣና እንደሄደ አመነ ፡፡ አሽ በእነዚህ ወዳጆቹ ንግግር በተደጋጋሚ ሊሰማን በሚችለዉ መካከል ላይ እንኳን የ2ጢሞ (3፡ 16-17) “ የእግዚአብሄር ሰዉ ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድየእግዚአብሄር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣፅ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለዉ ምክር ደግሞ ይጠቅማል “ በሚለዉ ተስፋ ላይ መደገፍ እንደምንችል ያሳስበናል ፡፡
የኢዮብ መፅሀፍ በተለይም በክፉዎች ላይ ማስጠንቀቂያዎችን ከኤልፉዝ፣ ከበልዳዶስና ከሶፋር የሚደጋግሙት እነዚህ ምዕራፎችለሰዎስት ምክንያቶች ጠቃሚዎች ናቸው፡
- እኛን በማስፈራራት ሌሎች የማያምኑትን ንስሀ የማይገቡ ከሆነ ፍፃሜአቸዉ እንዲህ እንደሚሆን እንድናስጠነቅቃቸው ፡፡ የኃጢዓታችን ዉጤቶች መጨረሻ ላይ ሞትን ማካተታቸዉ እዉነት ነው ፡፡ ኤልፉዝ፣ በልዳዶስ እና ሶፋርቢያንስ ስለ ክፉዎች የዘላለም ዉጤቱን ተረድተዉ ነበር ፡፡
- ጌታ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የደረሰበትን የጨለማን ጥልቀት እና መከራዉን በጥልቀት በመያዝ እንድንረዳዉ ያግዘናል ፤ በጨለማና በመከራ ጊዜያት ዉስጥ በምንሄድ ጊዜ ጌታ በዚያ ዉስጥ ሊያስተምረን እየሞከረ እንደሆነ መመልከት አለብን ፡፡ ክርስቶስ በጨለማ ዉስጥና በስቃይ ዉስጥ ተወስዷል ስለዚህምህይወት አለ (2ቆሮ 5፡ 21) ፡፡ ኢዮብ ኢየሱስ በራሱ ላይ በማድረግ ህይወት ለኛ የሰጠበትን ችግርና ጨለማ ጥልቀት ስዕል ሳለዉ ፡፡
- በዚህ ጊዜ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርቶች በአንዳንድመለኪያዎች የጠጣዉን ፅዋ እንደሚጠጡ እዉነት ከሆነ በመጨረሻ እርሱን ለማክበርከእርሱ ጋር ችግር መቀበለ ፤ በክርስቶስ በኩል በምንወርሰዉ የዘላለም ህይወት ምክንያት በዚህ ህይወት የሚደርስብን ስቃይ አለ ፡፡ ሮሜ 8፡ 17 የሚለው “ ማለት የእግዚአብሄር ወራሾች ነን አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን “ ፡፡
ሶፋር የክፉዎች እጣን /የእግዚአብሄር ፍርድን መግለፁን ቀጠለ ፤ በሶፋር የግል አስተያየት ክፉ በፍጥንት እንደሚጠፋና ልጆቹም ለማኞች እንደሚሆኑና በመጨረሻም የምድርን ሞት እንደሚገጥመዉ ተናገረ ፡፡
ኢዮብ (20፡ 12-19)፡ ሶፋር በኃጢዓት ጥቂት ቅጣቶች ላይ እምነቱን አስቀመጠ/ዘረዘረ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ለጊዜዉ ለክፉዎች ክፋት ጣፋጭ ይሆናልየባህሪያቸዉ ጥቂት ዉጤቶች ዉድቀታቸዉን እንደሚያመጣ “ ይፅፋል ፡፡ ምሳ (20፡ 17) “ የሐሰት እንጀራ ለሰዉ የጣፈጠ ነው ፤ ከዚያ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል “ ፡፡ የሶፋር ዋና ሀሳብ እግዚአብሄር ክፉዎች ላይ እንደሚፈርድ እዉነት ቢሆንም አፈፃፀሙ የተጠመዘዘ ነበር ምክንያቱምእርሱና ወዳጆቹ ኢዮብን በመዝለፋቸዉ ክፉዎችና ኃጢዓተኞች ነበሩ ፡፡
ኢዮብ (20፡ 20-29)፡ በመጨረሻም ሶፋር “ በእግዚአብሄር ፈጣን ፍርድ በክፉዎች ላይ “ ያለዉን እምነት አስቀመጠ/ዘረዘረ ፡፡ የሶፋር የጠበቀዉ ተግሳፁ ለኢዮብ ንስሀ እንዲገባ ወይም ያለዉን ነገር ሁሉ ማጣት እንደሚገጥመዉ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
ስደት/መከራ በአማኞች ላይ ይመጣል ማለት የእግዚአብሄር ፍርድ መጣ ማለት አይደለም ፤ የሶፋር አስተምሮ ስህተት ቢሆንም ሞትን ለመመልከት፣ በክርስቶስ ላይ የደረሰዉን ችግርና ጨለማ ለማስታወስ ፍቃደኞች በመሆን እንድናስታዉስ በማድረግ እናየእግዚአብሄርን ዘላለማዊ ክብር እንድንካፈል የመከራዉን ፅዋ ለመጠጣት ፍቃደኞች እንድንሆን አስጠነቀቀን ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 582.
Tom Constable, Dr. Constable’s Bible Study Notes: Job, p. 78; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.
Constable, p. 78.
Phillip Brooks; quoted in Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 42.
Constable, p. 79.
Christopher Ash, Job: The Wisdom of the Cross, ed. R. Kent Hughes (Wheaton: Crossway, 2014), p. 219.
Ash, p. 220.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 628.
ጥያቄዎች
-
ሶፋር ምላሽ ለመስጠት መንፈሱ አነሳሳዉ (ኢዮ 20፡ 3) ፤ በግል አስተያየታችሁ የትኛዉን መንፈስ ነበር እያዳመጠ የነበረዉ፡ መንፈስ ቅዱስ ወይስ የጠላትን መንፈስ ነበር ?
-
ሶፋር ለኢዮብ በፍቅር ተናግሮታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? በጠንካራ ፍቅር ? ኢየሱስ ፍቅር ምን እንደ ሆነና ምን እንደሚመስል የነገረን የት መፅኀፍት ላይ ነው ? (ምሳ 17፡ 17, ዮሐ 15፡ 12, ሮሜ 13፡ 10)
-
በኢዮብ 20 ዉስጥ በአጠቃላይ ሶፋር “ እሱ “, “ እርሱ “ እና “ እነርሱ “ ፤ የምዕራፉ ንግግር ጠቅላላ ነበር ወይስ ሶፋር ኢዮብን ግብዝ፣ እባብ እና ክፉ ነበር በማለት አጠቃዉ ?
-
በኢዮብ 20 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 20:20
“Because his appetite is never satisfied, he does not let anything he desires escape.”
ሶፋር ለሁለተኛ ጊዜ ለኢዮብ መለሰ ፡፡ በዚህ ጊዜ ቁርጥ ያላለ አሳብ ሶፋርን በቁጣ ለኢዮብ እንድመለስ አደረገው ፡፡ ሶፋር ጠንከር አድርጎ እንዴት የኃጢአተኞች ጭፈራ አጭር እንደሆነና የአምላክ የለሾችም ደስታ ለቅጽበት እንደሆነ ገለጸ ፡፡ እርሱም የኃጢአተኞች ፍላጎት ፈጽሞ አይረካም ወደ ማለት አመራ ፡፡
ከኢየሱስ ውጭ የሆኑት እነዚህ ፤ በውስጣቸው ህያው ከሆነው ከእግዚአብሔር መገኘት ውጭ የሆኑት እነዚህ በህይወታቸው ትርጉም ያለው ሕይወትንና ስኬትን ይፈልጋሉ ፤ ነገር ግን ፈጽሞ እርካታን አያገኙም ፡፡ የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ ይከተላሉ ፤ ነገር ግን ፈጽሞ ከልብ የሆነ ሰላምን አያገኙም ፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ መገኘት የተትረፈረፈ ደስታ አለ ፡፡ ህይወት ደረቅና የመጠማት ስትሆን እንኳ ፣ እርሱ ህያው ምንጭህ ይሆናል ፡፡ ብርታትህ ይሆናል ፡፡ ኃጢአትህን ይቅር ይላል ደግሞም በሽታህን ይፈውሳል ፡፡ ህይወትህን ከጉድጓድ ይታደጋል በርህራሄም ያረሰርስሀል ፡፡ በጌታም ደስ ስትሰኝ የልብህን መሻት ይሰጥሀል እንድሁም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የምትፈልገውን ጉልበት ይሰጥሀል ፡፡ ክርስቶስ በቂ ነው ፡፡ ከክርስቶስ ጋር የሆነ ሕይወትን ስትራብና ስትጠማ ፣ ትሞላለህ ፡፡ የአለምን ነገሮች ከመከተል አቁም ፡፡ ክርስቶስ ብቻ ፍጹም ደስታን መስጠት ይችላል ፡፡
“ሆዱ ዕረፍትን አላወቀምና የወደደው ነገር አላዳነውም ። “
- ኢዮብ 20፡20
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 103:2–5 — “ ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ ፥ ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ ፥ ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል ። “
- ኢሳይያስ 58:11 — “እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ ። “
- ማቴዎስ 5:6 — “ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።