Wisdom Books Job

A Living Redeemer

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 377 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሁሉም የመፅሀፍ ቅዱስ መፅኀፍ በመጨረሻም ወደ ኢየሱስ ያመለክቱናል ፤ ኢየሱስ እራሱም “ ነቢያትንና ሕግን ሊፈፅም እንጂ ሊያጠፋ …” እንዳልመጣ (ማቴ 5፡ 17) ተናግሯል ፡፡ ኢዮብ 19 የኢዮብን ተስፋ ስለ አንዱ ተቤዢ በመግለፅ በቀጥታ ወደ መሲሁ ያመለክተናል ፤ ቤተሰቡን፣ ሁሉንም ንብረቱን፣ ጤንነቱን ካጣ በኋላና ከወዳጆቹ ጋር በችግሩ መካከል ላይ በመሆን ኢዮብ በምዕራፍ 18 የተመዘገበዉን ለበልዳዶስ ንግግር ሲመልስለት ወደ ፊት ተስፋ ወደ ተገባለት ተቤዢ ተመለከተ ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (19፡ 1-4)፡ ኮንስታብል እነዚህ ጥቅሶች “ የኢዮብ ከሳሾች ጠላትነትን “ አጉልተዉ እንደሚያሳዩ ተመልክቷል፡፡ ኢዮብ በወዳጆቹ ቅሬታዎች ደከመበት ስፍራ ላይ ደረሰ ፤ ቃላቸዉ ሰብሮት ነበር (ቁጥር 2) በአድራጎታቸዉም እንደ ተዋረደ ተሰማዉ (ቁጥር 3) ፡፡ ኢዮብ ኃጢዓት ያደረገ ቢሆንም እንኳን የወዳጆቹ ጉዳይ እንዳልነበር ተከራከራቸው ፡፡

ኢዮብ (19፡ 5-12)፡ ኢዮብ ወዲያዉኑ የህይወቱን መከራ የሚገልፁ ሰባት ስዕሎችን አመጣ ፡፡ እነዚህ ስዕሎች ከኢዮብ የወዳጆቹን ጠላትነት ለመግለፅ ወደ እግዚአብሄር ጠላትነት ሽግግር አመለከቱ፡

  1. በወጥመድ እንደ ተያዘ አንድ እንስሳ ተሰማው (ቁጥር 6) ፡፡
  2. በፍርድ እንደ አንድ ወንጀለኛ ተሰማው (ቁጥር 7) ፡፡
  3. እንደ ታጠረበት አንድ ተጓዥ ተሰማው (ቁጥር 8) ፤ ኢዮብ መንገዱ በእግዚአብሄር ጨለማ እንደ ተደረገበት ተሰማው ፤ በተቃራኒ ኢሳያስ “ ከእናንተ እግዚአብሄርን የሚፈራ የባሪያዉንም ቃል የሚሰማ ማነው ? በጨለማም የሚሄድ ብርሃንም የሌለዉ ማነው ? ነገር ግን በእግዚአብሄር ስም የሚታመን በአምላኩምየሚደገፍ ማን ነው “ (ኢሳ 50፡ 10) ፡፡
  4. ከስልጣን እንደ ወረደ ንጉስ ተሰማው (ቁጥር 9) ፡፡
  5. እንደ ፈረሰ መዋቅር/አካል ተሰማው (ቁጥር 10) ፡፡
  6. ስሩ እንደ ተነቀለ ዛፍ ተሰማው (ቁጥር 10) ፤ በኢዮብ (14፡ 7) ኢዮብ የተቆረጠ ዛፍ ተስፋ እንዳለዉ ምክንያቱም “ ስሮቹ ስለ ማይሞቱ “ በማለት ተናግሯል ፤ ነገር ግን ስሩ የተነቀለ ዛፍ ግን ተስፋ የለዉም ፡፡ ኢዮብ በሁኔታው ተስፋ እንደሌለዉ አየ ፡፡
  7. እንደ ተከበበች አንድ ከተማ ተሰማው (ቁጥር 12) ፡፡

ኢዮብ (19፡ 13-22)፡ የኢዮብ ንግግር ይህ ክፍል ከሌሎች ጓደኞቹ ኢዮብ የገጠመዉን ጠላትነት ይገልፃሉ ፡፡ ኢዮብ ሁሉም የሚቀርቡት “ እንደ ወንድሞቹ፣ እንደ ጓደኞቹ፣ እንደ ቤተሰቡና እንደ አገልጋዮቹም እንኳን ሳይቀሩ እንደ ተዉት ተሰምቶት እንደነበር ቅሬታ አቀረበ (ቁጥር 13-16) ፡፡ አሁን ቤተሰቦቹ የተገፋ ሆኖ አገኙት (ቁጥር 17) ፤ ለኢዮብ ነገሮች ጨልመዉበት ነበር ፡፡ ኦስዋልድ ቻምበር “ የሚያስገርም የጨለማ ሀብት የማይነገር ቡራኬ/ምርቃን ፤ ቆይታቸዉንና በነፍሳቸዉ ላይ የማይለቀዉን ተፅዕኖ የማይተዉበት የፀሀይና የዉበት እንዲሁም የነፃነትና የብርሃን ቀን አይደለም ነገር ግንየመንፈስ ጨለማዎች በእግዚአብሄር እጅ የጨለሙት፣ በአድካሚ ምድር በአለት ቅርፊት ዉስጥ የደበቁት በአይናችን ፊት የሚያልፈዉን የራሱን የዳርቻ ዉበት ስለፈቀደ “ በማለት ፅፏል ፡፡

ሕፃናት ሰዎችም ኢዮብን ማጃጃል ጀመሩ (ቁጥር 18 ) ፤ ኢዮብ የገጠመዉ/የደረሰበት የድጋፍ አቀራረብ የቃል /ከዉሸታሞች /ወዳጆች ጋር ይመስላል ፡፡ ማንም ከእርሱ ጋር ለመስራት ምንም ነገር አልፈለጉም ከእርሱም እርቀታቸዉን ጠበቁ ፤ ወዳጆቹና የሚወዳቸዉ በእርሱ ላይ ፊታቸዉን አዞሩበት ፡፡ የኢዮብ ልምዶች/ችግሮች መሲሁ ከሚቋቋማቸው ጋር በሚያስደንቅ ሁኔታ ተመሳሳይ ነበር ፡፡ ኢሳያስ “ የተናቀ ከሰዉም የተጠላ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያዉቅ ነው ፤ ሰዉም ፊቱን እንደሚሰዉርበት የተናቀ ነው እኛም አላከበርነዉም “ (ኢሳ 53፡ 3) በማለት ተንብዮአል ፡፡

ኢዮብ የወቅቱን የአካሉንሁኔታ ደካማነት ገለፀ (ቁጥር 20) ፡፡ ማክአርቱር ኢዮብ “ ሞትን በቀጭን መስመር/ዳርቻ እንዳመለጠ “ ፅፏል ፡፡ እንዲህ አይነት ሙሉ የሆነ ችግር ከደረሰበት በኋላ ኢዮብ እንደ ገና ወዳጆቹን “ እንዲምሩት “ (ቁጥር 21) ለመናቸው ፡፡

ኢዮብ (19፡ 23-29)፡ አሁን እግዚአብሄርና ወዳጆቹ በእርሱ ላይ በተቃራኒ ሄደዉበት የነበረዉን መንገድ ሁሉ ዘርዝሮ ካቀረበ በኋላ ኢዮብ በእግዚአብሄርን ላይ ያለዉን መተማመን መግለፅ ጀመረ ፡፡ ማክአርቱር “ በኢዮብ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ላይ በታላቅ እምነቱ እንደ ተገለጠ “ ፅፏል ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄር እንደ ሚታደገዉ ያውቃል ፤ እግዚአብሄር እንደ ህያዉ ተቤዢ/ታዳጊ ሆኖ የሚታይበት ሌላ ስዕል በብሉይ ኪዳን የተሰጡ ናቸው፡

“ ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው ፡፡ እኔ እግዚአብሄር ነኝ ከግብፃዊያንም ባርነት አወጣችኋለሁ ከተገዥነታቸዉም አድናችኋለሁ ፤ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ “ (ዘጸ 6፡ 6) ፡፡

“ አቤቱ ረድኤቴ መድኃኒቴም የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን (መዝ 19፡ 14) ፡፡

“ ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸዉን ያድናል ፤ ስማቸዉ በፊቱ ክቡር ነው “ (መዝ 72፡ 14) ፡፡

“ የእስራኤል ቅዱስ የሚቤዣችሁ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ፡፡ ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ ከለዳዉያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ “ (ኢሳ 43፡ 14) ፡፡

ኢዮብ ተስፋ የተገባዉን ተቤዢ/ታዳጊ እንደሚያየዉና እንደሚቀምሰዉ አምኗል (ቁጥር 27) ፡፡ በሁሉም ትርምስ መካከል ላይ ኢዮብ የህያዉ ተቤዢን ተስፋ አስታወሰ ፡፡

መደምደሚያ

ኢዮብ እያደረገ በነበረዉ ነገር ታዋቂ አልነበረምነገር ግን በህያዉ ተቤዢ የተስፋዉ ገለፃ በመሲሁ በኢየሱስ የሚመጣዉ ተስፋ ገለፃ ነበር ፤ ሁኔታችን ምንም ያክል ተስፋ አስቆራጭ ቢሆን ችግር የለም ኢየሱስ ማንኛችንም ሊቤዠን ይችላል፡ “ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነዉ ቤዛነት በኩል እንዲያዉ በጸጋው ይጸድቃሉ “ (ሮሜ 3፡ 24) ፡፡

  1. Tom Constable, Dr. Constable’s Bible Study Notes: Job, p. 73; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  2. Constable, p. 73.

  3. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), pp. 39–40.

  4. Constable, p. 75.

  5. Oswald Chambers; quoted in Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 39.

  6. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005) p. 582.

  7. Constable, p. 75.

  8. MacArthur, p. 582.

ጥያቄዎች

  1. ኢዮብ በበልዳዶስ በመዘለፉ የደከመ ነበር (ኢዮ 19፡ 1-5) ፤ ከራሱ ይልቅ በኢዮብ ኃጢዓት ላይ ያተኮረ ይመስላል ፡፡ ስለ ሌሎች ኃጢዓት ትክክለኛ ምላሽ መፅሀፍት የት ላይ እናገኛለን (ማቴ 7፡ 3-5) ? ይህን የሚመስል አንድ ሰዉ ታውቃላችሁ ?
  2. በኢዮ (19፡ 13-20) ኢዮብ ኃዘኑን ጠቀሰ ፤ ከአንዱ በላይ አስበልጦ ምን ጠቀሰ ?
  3. ኢዮብ 19 መጨረሻ ላይ ኢዮብ “ እኔ ግን የሚቤዠኝ ህያው እንደ ሆነ አዉቃለሁ “ አለ ፤ ያ ንግግር እንዴት ኃይለኛ ነበር ? ኢዮብ እንደ ገጠመዉ ገጥሟችሁ አሁንም እንደምታዩት በማወቅ እግዚአብሄርን እንዳመሰገናችሁ ታስባላችሁ ?
  4. በኢዮብ 19 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 19:25–26

“But I know my living Redeemer, and He will stand on the dust at last. Even after my skin has been destroyed, yet I will see God in my flesh.”

ኢዮብም ለበልዳዶስ በድካም መለሰ እንድህ አለ ፡- “ነፍሴን የምትነዘንዙ፥ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው ?....... ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ ፥ የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ ። …… ሚስቴ እስትንፋሴን ጠላች ፥ የእናቴም ማኅፀን ልጆች ልመናዬን ጠሉ ። “ ቢሆንም ግን ኢዮብ በተስፋ መቁረጥና በድካም ውስጥ ሆኖ እንኳ ፡- “ እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም አውቃለሁ “ በማለት ተስፋን አደረገ ፡፡ በእርግጥ ኢዮብ ህያውን ቤዛ ፣ ሊመጣ ያለውን ፣ እንደሚመጣ የተነገረውን ታዳጊ ኢየሱስን አውቆ ነበር ፡፡ ኢዮብ ተስፋን አገኘ ፡፡

በየቀኑ ተስፋ በሚያስቆርጡ ሁኔታዎች ውስጥ ታልፋለህ ፡ - በኮምፒውተርህ ላይ ቡና መድፋት ፣ ስልክ መጣል ፣ ኪሳራ ፣ ያኮረፈ ጓደኛ ፣ በአልጋህ ወይም በቤትህ ውስጥ መዋል ………. በእያንዳንዱ ቀን ተስፋ ለመቁረጥ የሚዳርጉ በጣም ብዙ አጋጣሚዎች አሉ ፡፡ በእነዚህ አስቸጋሪ አጋጣሚዎች ውስጥ ስታልፍ ሀልጊዜም የሆነ መንገድ እንዳለ አስታውስ ፡፡ ሁሌም እውነታው አለ ፡፡ ህያው የሆነው ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ አለህ ፡፡ አንተን ከኃጢአትና ከሞት ነጻ ያወጣ ዘንድ ህይወቱን ሰጥቷል ፡፡ አሁንም የሚቤዥህ አለ ፡፡ በአስቸጋሪ ቀን መጨረሻ ላይ እንኳ እንድህ ማለትን ምረጥ ፡- “እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ አውቃለሁ ፡፡ “ አሁን ነገን መጋፈጥ ትችላለህ ምክንያቱም የሚቤዥህ ስለላ ፡፡ ጓደኛዬ እግዚአብሔር አግኝቶሀል ፡፡ በክርሰቶስ በሆነው ተስፋ ላይ ተጣበቅ ፡፡

“እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም ፥ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ ። “

  • ኢዮብ 19፡25-26

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 43:1 — “አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ ። “

ሮሜ 8:1–2 — “ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም ። በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና ። “

ኤፌሶን 1:7–8 — “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን ። “