Wisdom Books Job

Death Is Not The End

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 376 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በምዕራፍ 16 ኢዮብ ለኤልፉዝ መለሰለት ፡፡ በምዕራፍ 18 በልዳዶስ ሁለተኛ ንግግሩን አደረገ ፤ የበልዳዶስ የመጀመሪያዉ ንግግር በኢዮብ 8 ነበር ፡፡ በዚህ ንግግር ዉስጥ የበልዳዶስ መሰረታዊ ክርክር “ ኢዮብ ወደ እርሱ ሁኔታ መጥቶ እንዲያገኘዉ ነበር “ ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (18፡ 1-4)፡ኮንስታብል እነዚህ ጥቅሶች በኢዮብ ላይ የበልዳዶስን ትችቶች እንደያዙ ተናግሯል ፡፡ ኢዮብና ወዳጆቹ ሁለቱም ሌሎቹ በጣም ብዙ ተናግረዉ እንደ ነበር አመኑ ፤ ማንኛቸዉም ቡድን የሌሎቹን አመለካከት አልወደዱትም፣ ብስጭታቸዉንም ገለፁ (ቁጥር 2) ፡፡ ማንኛቸዉም ቡድን ለሌሎች የሚጨነቁ አይመስሉም ፡፡ በልዳዶስ ተበሳጨ ምክንያቱም ኢዮብ እንደ እንስሳ ስለጠራዉና (ቁጥር 3) (ኢዮ 12፡ 7-9) የተናቀ እንደ ሆነ ስላሰበ፡፡ እንስሳ ነህ ተብሎ መጠራትን እና እንዲሁም ደደብ ነህ ተብሎ መጠራትን አያበረታታም ፡፡ የዚህ ምዕራፍ የመጀመሪያዎቹ አራት ቁጥሮች ከአሽሙር ጋር የታሰሩ ናቸው ፡፡

ኢዮብ (18፡ 5-21)፡ኮንስታብል እነዚህ ቁጥሮች ክፉዎችን በተመለከተ የበልዳዶስን ማስጠንቀቂያ እንደ ነበሩ አጉልቶ አሳይቷል ፡፡ በልዳዶስ ለኢዮብ እንደ ማስጠንቀቂያ የሞትን አራት የወደፊት ስዕሎች አስቀምጧል፡

  1. መብራቱ ይጠፋል (ቁጥር 5-6) – “ የሰዉ መንፈስ የእግዚአብሄር መብራት ነው የሆዱን ጉርጆች ሁሉ የሚመረምር “ ፡፡
  2. ተጓዥም አጠመደው/አሰናከለዉ (ቁጥር 7-10) – “ ለመረብ “ ወይም “ ለወጥመድ “ ይህን ሀሳብ ለማመልከት ስድስት ዕብራዊ ተመሳሳዮች ተጠቅመዉ ነበር ፡፡ መረብ እርሱን ለመያዝ የተዘረጋ፣ በቅርንጫፎች በመሸፈን ለማጥመድ በጉድጓድ ላይ የተደረግ፣ አንድ ዘራፊ በነካዊ ጊዜ በሚፈናጠር ሸምቀቆ የሚጠቅም ወጥመድ፣ በምድር ላይ የተደበቀ ወጥመድና አዳኝን ለመያዝ ለማንኛዉም መሳሪያ የሚጠቅም ጠቅላላ ቃሉ ወጥመድ የሆነ ነበር ፡፡ በልዳዶስ ክፉዎች ወደ ሞት እንደሚመሩ ፍራትን ለማምጣት እነዚህን ሁሉ ምስሎች ተጠቀመ ፡፡ ዋይርስቤ ፍርሀት መልካምና ጤነኛ ድርጊት እንድንወስድ ሊያነሳሳን የሚችል ትክክለኛ ስሜት እንደሆነ ፅፏል ፤ ይሁን እንጂ በልዳዶስ በኢዮብ ዉስጥ ተስፋ የሌለው የሞት ፍርሃት እንደ ነበር ለማስገባት ፈለገ ፡፡
  3. ወንጀለኛ ተከታተለው (ቁጥር 11-15) - በቁጥር 14 በልዳዶስ “ የንጉሱ ፍራት/ማስፈራት “ በማለት ጠቅሷል ፤ ይህ ሞትን ይመስል ነበር ነገር ግን ሰይጣን ሊሆን ይችላል ፡፡ ዮሐንስ በርን ይህ “ የወረርሽኝ የመሴፖታሚያ አማልዕክት እና በኦቶማን አገዛዝ ጊዜ በአለም ስር ከፍተኛ ሰራተኛ ለናማታር ማጠቀሻ ሊሆን እንደሚችል “ ያመለክታል ፡፡
  4. ዛፉ ስሩ ይደርቃል (ቁጥር 16-21) - ኢዮብ ቀድሞ መቅሰፍት ቢኖርም ዛፍ ትንሽ ተስፋ ሊቀረዉ እንደሚችል ገልፆ ነበር ፤ በልዳዶስ ደግሞ አንዴ ዛፍ ስሩ ከደረቅ ከመሬት በታችም ወይም ከመሬት በላይ ቢሆንም ለዛፉ ማንኛዉም አካል ምንም ተስፋ እንደማይኖረዉ ተከራከረ ፡፡ ይህ ምስዕል የቤተሰብ ዛፍን በአይምሮ ዉስጥ አምጥቷል ፡፡ አንድ ክፉ ሰዉ ወደ መጨረሻዉ ከመጣ ሁሉም ቅርንጫፎቹም ይወድቃሉ፡፡

በልዳዶስ ንግግሩን ለኢዮብ በመጠቅለል በጥብቅ የኢዮብ የንፅህና ቅሬታዉ ስህተት እንደሆነ በማስረዘም ሄደ ፡፡ በልዳዶስ የኢዮብ ሁኔታ ልጅ ሳይኖረዉ ራሱን ያገኘበት፣ ቅርስ የሌለበት እና ምንም ያልቀረለት ንብረት ሁኔታ “ ትክክል ያልሆነ አንድ ሰዉ “ ምልክቶች እንደ ነበሩና “ እግዚአብሄርን የማያዉቅ “ (ቁጥር 21) አንድ ሰዉ ማስረጃዎች እንደ ነበሩ ተከራከረ ፡፡

በጣም በቅርብ በሆኑ ንግግሮቻቸዉ ኤልፉዝና በልዳዶስ ሁለቱምክፉን በጋራ/በተመሳሳይ ንግግሮች ገልጸዋል፡

ኤልፉዝ

ክፉዎች . . .

በልዳዶስ

15:22–23, 30

ጨለማ ይገጥማቸዋል

18:5–6, 18

15:30b, 32–33

ጤነኛ ያልሆኑ እፅዋቶችን የሚመስሉ ናቸው

18:16

15:30, 34

በእሳት የሚጠፋ ናቸው

18:15

15:27–31

ተፅዕኖአቸዉን ያጣሉ

18:7, 15–16

15:21, 24

በጭንቀት የሚፈሩ ናቸው

18:11, 14

15:34

ቤታቸዉን ያጣሉ

18:6, 14–15

15:4, 13, 25–26

እግዚአብሄርን ይቃወማሉ ወይም አያዉቁም

18:21

15:13

የተጠመዱ ናቸው

18:8–10

መደምደሚያ

ዋይርስቤ “ ሞት ለመሞት ያልተዘጋጁትን የሚያስፈራራ ጠላት ነው “ በማለት አስተዋለ ፡፡ በብዙ መንገድ የኢዮብ ህይወት የእኛን ይመስል ነበር ፡፡ ሰይጣን ብዙ መጥፎ መልዕክቶችን በኢዮብ ላይ ወረወረ እንዲሁም ደግሞ እኛን ለመጣል በየቀኑ በመሞከር ተመሳሳይ ነገር ያደርግብናል፤ ነገር ግን ስናምንና ወደ ክርስቶስ በፍጥነት ስንይዝ ሁሉም የሰይጣን ጥቃት ምንም አይደለም ፡፡ ኢየሱስ “ እዉነት እዉነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለዉ ከሞትም ወደ ሕይወትተሸገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም “ (ዮሐ 5፡ 24) ፡፡

የክርስቶስ በሆንን ጊዜ በዚህ ህይወታችን የሚያስፈራን ምንም አይኖርም ፡፡ ለእኛ በእዉነቱ ሞት ማለት ህይወት ማለት ነው ፤ ሞት ማለት ወደ ቤታችን በመሄድ ከአባታችን ጋር ከመለያየት ይልቅ ከእርሱ ጋር መሆን ማለት ነው ፡፡

7 John B. Burns, “The Identity of Death’s First-Born (Job XVIII 13),” Vetus Testamentum 37:3 (July 1987), pp. 362–64; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Job, p. 72; https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Job, p. 71; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  2. Constable, p. 71.

  3. Constable, p.72.

  4. Warren Wiersbe, The Bible Expository Commentary: Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David Cook, 2004) pp. 37–38.

  5. Wiersbe, p. 37.

  6. Wiersbe, p. 38.

  7. Wiersbe, p. 38.

  8. Constable, pp. 71-72

  9. Wiersbe, p. 38.

ጥያቄዎች

  1. በኢዮ (17፡ 6) የኢዮብ ስለራሱ ገለፃ ወደ መሲሁ እንዴት ያመለክታል (ኢሳ 53፡ 3, 4፣ ሉቃ 18፡ 32) ? ስለ ኢዮብና ስለመሲሁ ስለ ሁለቱም በማስተካከል ዋጋዉ ለማን የተሰጠ ነው ?
  2. በልዳዶስ ኢዮብ እሱንና ሌሎቹን ወዳጆች እንደ “ አዉሬ “ እንደቆጠራቸዉ አመነ ፤ በሚከተሉት መፅሀፍቶች መሰረት ምን ማለት ይሆናል ? ኢዮ (18፡ 3), መዝ (49፡ 20), 57፡ 4, 73፡ 22, መክ 3፡ 18 እና ቲቶ (1፡ 12)
  3. በኢዮብ 18 በልዳዶስ ስለ ክፉ ሰዎች እንዳጋራው ከመፅሀፍት ጋር የሚመሳሰሉት የእዉነት አካሎች ምን ነበሩ፣ በስህተት የነበረዉ የት ላይ ነበር ? (መዝ 11፡ 6, 37፡ 10, 73፣ 1ጴጥ 2፡ 21-23, 3፡ 17)
  4. በኢዮብ (17-18) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 18:21

“Indeed, such is the dwelling of the unjust man, who does not know God.”

ኢዮብ በማዘን ፣ ባለበት መከራ ውስጥ ረዳት አንደሌለው በተናገረ ጊዜ ጓደኛው በልዳዶስ ለሁለተኛ ጊዜ ተናገረ ፡፡ በዚህ ጊዜ እርሱ እስከ ሞትና ጥፋት ድረስ በመጥቀስ በኢዮብ ላይ ትችቱን ሰነዘረ ፡፡ በልዳዶስ እግዚአብሔርን በማያውቁት በአመጸኞች ላይ ምን እንደሚሆን በመናገር ኢዮብን አስጠነቀቀው ፡፡ ነገር ግን እውነቱ ይህ ነው ፡- ኢዮብ እግዚአብሔርን ያውቅ ነበር ፡፡

አስበኸዋል እንደዚህ ያሉ መራራ ቃላትን ከጓደኛህ መስማት ለዚያውም በህይወትህ በጣም በከባድ መከራና ስቃይ ውስጥ እያለፍክ ሳለ ? ምናልባት እንደዚህ ያለ ጓደኛ ማግኘት ያልተለመደ ሊሆን ይችላል ፡፡ ነገር ግን ጠላት እንደዚህ ያለ ጥፋትና ሞት በህይወትህ ላይ ለማስከተል በየቀኑ በዙሪያህ ያደባል ፡፡ ደስታህንና ጓደኝነትህን ሊያቋርጥ ይመጣል ፡፡ አንተ ድብርት ፣ ረዳት አልባነት እናም ተስፋ ቢስነት እንድሰማህ ለማድረግ ውሸት ጭምር ይነግርሀል ፡፡ ነገር ግን ነገሩ እንድህ ነው ፡- አንተ እነዚህን ውሸቶች ታስቆም ዘንድ በውስጥህ ኃይሉ አለህ ፡፡ ኢየሱስ ውጊያውን አሸንፏል ፡፡ አስተውል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት መልሰህ ለመዋጋት የሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ አለህ ፡፡ ስለ ራስህ የምታስበውን ነገር በመቆጣጠርና የእግዚአብሔርን አውነት በማመን ማንኛውንም አሳብ ማርክ ፡፡ ጠላት በህይወትህ ያጠመደው ወጥመድ ውስጥ እንዳትወድቅ ፣ የእምነት እንቅፋትህን አንሳ ፡፡ በድል ተራመድ ምክንያቱም ውጊያው የእግዚአብሔር ነውና ፡፡ ስለዚህም የእግዚአብሔርን ተስፋዎች በማመን በታላቅ እምነት ቀጥል ፡፡

“በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት ፥ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው ። “

  • ኢዮብ 18፡21

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘዳግም 20:4 — “ከእናንተ ጋር የሚሄድ፥ ያድናችሁም ዘንድ ጠላቶቻችሁን ስለ እናንተ የሚወጋ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና ። “

2ኛ ቆሮንቶስ 10:4–5 — “የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው ፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን ፡፡ “

1ኛ ዮሐንስ 5፡4 — “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው ። “