Miserable Comforters
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የኤልፉዝን የቃል ክፉ ንግግር ጨረስን ! ለክፉዎች(ያ ማለት ለኢዮብ) 16 ዉጤቶችን አቀረበ ፡፡ ኢዮብ ለኤልፉዝ ሁለተኛ ጊዜ ሀሰቱን ለማረጋገጫነት ለመስጠት ተገደደ ፤ ብዙ ጊዜ ሁሉንም ወዳጆቹን ዉሸታቸዉን ያረጋግጣል ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (16፡ 1-5)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ኮንስታብል “ የኢዮብን ማስጠላት ለወዳጆቹ “ በማለት መግለፁን እናያለን ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ቁጥሮቹን በዚህ መልኩ “ እንደ መልካም መካሪ በችግሬ ልታፅናኑኝ ሲገባችሁ ችግርን በመናገር በተቃራኒዉ ጥያቄአችሁ እያለ ስቃዮን ጨመራችሁት “ ብሎ በመፃፍ መልሶ ፅፎታል ፡፡
ከጥቂት ምዕራፎች በፊት ኢዮብ ወዳጆቹን ምን ብሎ እንደጠራቸዉ ታስታዉሳላችሁ ? ዋጋ የሌላችሁ ሐኪሞች ናችሁ በማለት ጠራቸው ፤ እስከዚህ ስፍራ ድረስ ምንም ነገር አላደረጉም ነበር ነገር ግን ተሳለቁበት፣ ፈረዱበት ተስፋ አስቆረጡትም ፡፡ በቁጥር 2 ኢዮብ ወዳጆቹን “ የምታደክሙ አጽናኞች “ ናችሁ አላቸዉ ፡፡ ማክአርቱር “ የኢዮብ ወዳጆች ሊያፅናኑት መጡ ፤ ሰባት የደስታ ቀናት በዝምታ ተቀምጠው ተልዕኮአቸዉ በአድካሚ ሁኔታ አልተሳካላቸዉም እንዲሁምለኢዮብ ማፅናናታቸዉ ወደ ከፍተኛ ስቃዩ ተቀየረ ፤ የኢዮብን አጣብቂኝ ሁኔታ በመረዳት ለመርዳት የኤልፉዝ በማክበር የጀመረ ጥረት ወደ ጥላቻና ሽሙጥ ተቀየረ “ በማለት ፅፏል ፡፡ ኢዮብ ሁሉንም ወዳጆቹን የጠራባቸዉን ስሞች ለመመልከት ተመልሰን ኢዮ (6፡ 15, 8፡ 2, 13፡ 4) ላይ እንሂድ ፡፡
ኢዮብ በመዝ (22፡ 7) እንዳለዉ ወዳጆቹ በእርሱ ስፍራ ሆነዉ ቢሆን ኖሮ በወዳጆቹ ላይ ሊፈርድባቸዉና ራሱን ሊነቀንቅባቸዉ እንደሚችል ጠቆመ ፤ ነገር ግን ኢዮብ ህመማቸዉን በማበረታታት ያፅናናቸዋል ፡፡ በኢዮብ ስፍራ የሆነን አንድን ሰዉ እንዴት ትንከባከቡት/ታዩታላችሁ ? ሌሎችን ለማበረታታትና ለመርዳት ለማየት ማቴ (7፡ 22) መረዳት አስፈላጊ ነው ፤ በዚያ ስፍራ ላይ እንዲደረግልን የምንፈልገዉን ለሌሎች ማድረግ እንዳለብን እናያለን ፡፡ ይህ ጥቅስ “ ወርቃማዉ ህግ “ በመባል ይጠቀሳል ፡፡ ፀሀፊ ገርግ ፋዉልስ በወርቃማ ህግ/ትዕዛዝ ለመኖር አምስት መንገዶችን ለይቷል ፡፡
አምስቱ መንገዶች እነዚህ ናቸው፡
- ይቅር እንድትባሉ ይቅር በሉ ፡፡ (ማቴ 6፡ 12, ቆላ 3፡ 13) ፡፡ ለኢዮብ ወዳጆቹን ለማበረታታት በክፉ ንግግር ያለማቋረጥ ለደበደቡት ይቅርታ ያደርግላቸዋል ፤ ይቅርታ በእዉነት ልናደርገዉ የማንፈልገዉ ነገር ነው ፤ በመጉዳት ወይም በጥቂቱ በመቅጣት ከመሄድ ይልቅ ከዚያ ስሜት በመዉጣት ይቅር እንበል ፤ እርስ በእርስ ይቅር ልንባባል ያስፈልገናል ፡፡
- እንዲደረግላችሁ የምትፈልጉትን ለሌሎች አድርጉ ፡፡ (ቆላ 3፡ 13) ፤ ይህ አንዱ ሌላዉን ስለ መቀበል ነው ፤ ሌሎች እንዲረዷችሁ በምትፈልጉበት ሌሎችን ለመርዳት በማየት ፡፡ እርስ በእርሳችን ልንረዳዳ ያስፈልገናል ፡፡
እንዲያበረቷችሁ በምትፈልጉት ሌሎችን ማበርታት ፡፡ (ዕብ 3፡ 13) ፤ ምናልባትም ኢዮብ የወዳጆቹን ስም መጥራት ያቆማል ፡፡ ይቅር ማለት ካልቻላችሁ ማበረታታት ትችላላችሁ ብዬ አላስብም ፡፡ ፋዉልስ “ ቤን ፍራንክሊን አንድ ጊዜ አብዛኞቹ ሰዎች 25 ሀያ አምስት አመታቸዉ ላይ ከመንቃታቸዉ ላይ ይሞታሉ ምክንያቱም ማለም ሲያቆሙ “ ፤ ይህ ይሆናል ምክንያቱም ሰዎች እርስ በእርስ መደጋገፍ ስላቆሙ ፡፡
እንዲረዱዓችሁ የምትፈልጉትን ሌሎችን መረዳት ፡፡ (ዮሐ 8፡ 7) ፤ የኢዮብ ወዳጆች ለኢዮብ መረዳት ወይም ችግርን እንደ ራስ ማየትን አላሳዩም ፤ ኢዮብን ለመረዳት ፍላጎት አልነበራቸዉም ፡፡
በዙሪያችሁ ያሉትን የሚባርኩና የሚጠቅሙ ነገሮችን መመልከት ፡፡ (ፊል 2፡ 4) ፤ የጎዷችሁን ማበረታታት ደረጃ ላይ እንዴት ትደርሳላችሁ ? ለሌሎች ዋጋ ለመስጠትና ለመጠንቀቅ ከራሳችሁ መንገድ መዉጣት አለባችሁ ፡፡ በሁኔታዉ ላይ በመመልከት እንዴት ልረዳ እችላለሁ ? በማለት ጠይቁ ፡፡
ኢዮብ (16፡ 6-17)፡ኮንስታብል እነዚህን ጥቅሶች “ የኢዮብ ጭንቀት በእግዚአብሄር እጅ “ በማለት ይጠቅሰዋል ፡፡ በእግዚአብሄር የኢዮብ አመለካከት እግዚአብሄር በእርሱ ተበሳጭቶበት እንደ ነበር እና በእርሱ የተቀጣ እንደሆነ ነበር ፤ ኢዮብ እግዚአብሄርን እንደ ጠላቱ ጠቀሰዉ ፡፡ ማክአርቱር “ ኢዮብ እግዚአብሄርንእንደ ሰባበረዉ፣ እንደ ቀጠቀጠዉ፣ እንደወጋዉና እንደ ቆራረጠው እንደ ጠላት እንደ ገለፀዉ (ቁጥር 12-14) “ ፅፏል ፡፡ ዋይርስቤ “ የኢዮብ ምላሽ (ለኤልፉዝና ለወዳጆቹ) ሰዎስት የልብ ስሜት ጥያቄዎችንለመናገር/ለመተንፈስ ነዉ፡ መጀመሪያለወዳጆቹ ስለ መፅናናት ለመነ (ቁጥር 1-14) ከዚያም የእግዚአብሄርን ፍትህ ለመነ (ቁጥር 15-22) በመጨረሻምህይወቱን በመጨረስ ከመከራዉ እንዲያርፍ እግዚአብሄርን እንደ ለመነ (ኢዮ 17፡ 1-1) “ ፅፏል ፡፡
ኢዮብ የእግዚአብሄርን ፍትህ ሲለምን እራሱን እንደቆሰለ አንድ እንስሳት አወዳደረ ፤ ኢዮብ እንዲመለስ የቀረዉ ማንም ስላልነበረዉ የማቅ ልብስ ለበሰ፣ ፊቱን በትቢያ በመሸፈን በመዋረድና በፀፀት አለቀሰ ፤ ይህ ተስፋ የሌለዉ ሁኔታ ይመስላል ፡፡
ኢዮብ (16፡ 18 – 17፡ 2)፡ኮንስታብል እነዚህን ጥቅሶች “ የኢዮብ ፍላጎት ለሰማያዊ ወኪል “ በማለት ይጠቅሳቸዋል ፡፡ ኢዮብ ወዳጅ አልነበረዉም እግዚአብሄርም እንደ ተወዉ ተሰማው ፡፡ ኮንስታብል “ ኢዮብ በምድር ላይ ደሙ እንዳይሸፈን ተጣራ (ቁጥር 18) ስለሆነም ወደ እግዚአብሄር እንዲታደገዉ አልቅሷል (ዘፍ 4፡ 10) ፤ ኢዮብ ቢሞት እንኳን ጉዳዪን ሰዎች እንዲረሱት አልፈለገም ፡፡ ስለዚህ ነገር ለመመስከር በህይወት ባይሆን እንኳን ጥያቄዉን እንዲመልስለትና እንዲታደገው አንድን ሰዉ እንደ ፈለገ “ ፅፏል ፡፡ ምንም እንኳን ኢዮብ በጭንቀት ቢሆንም ወደ እግዚአብሄር ብቻ መመለስ ይችላል ፡፡
ማክአርቱር የኢዮብ “ ልመና በዳኞች/በነገስታት ፍርድ ፊት ሲቀመጥ ስለወዳጆቹ ወይም ስለ ጎረቤቶቹ ንፅህናዉን ስለሚያረጋግጥለት/ነፃ ስለሚያወጣዉ አንድ ነፃ አዉጪ/ታዳጊ እንሆንለት “ እንደሆነ ፅፏል ፡፡
መደምደሚያ
ኢዮብ አንድ ጠበቃ፣ አንድ አማላጅ እና አንድ መካከለኛ አስፈለገው ፤ እግዚአብሄር እነዚህ ነገሮችን በክርስቶስ በኩል ሰጠ ፡፡
1ዮሐ (2፡ 1-2)፡ “ ልጆቼ ሆይ ኃጢዓትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ ፡፡ ማንም ኃጢዓትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ እርሱም የኃጢዓታችን ማስተሰሪያ ነው ለኃጢዓታችንም ብቻ አይደለም ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢዓት እንጂ “ ፡፡
ሮሜ (5፡ 8)፡ “ ነገር ግን ገና ኃጢዓተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሄር ለእኛ ያለዉን የራሱን ፍቅር ያስረዳል “ ፡፡
ዕብ (7፡ 25)፡ “ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሄር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸዉ ይችላል “ ፡፡
ኢየሱስ የኢዮ (16፡ 21) መፈፀም ይሆናል ፤ ኢየሱስ በክርስቶስ በኩል የሚመጣዉን ማንንም ማዳን ይችላል ፡፡ ከሁላችንም ዉስጥ ለእያንዳንዳችን ህይወትን ሊሰጠን ይፈልጋል !
5 Faulls.
6 Faulls.
7 Faulls.
8 Faulls.
9 Faulls.
13 Constable
14 Constable
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Job (PLANOBIBLE Chapel: https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf), p. 50.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 627.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary: Job (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 581.
Greg Faulls, Five Ways To Live Out The Golden Rule (Prevailing Life with Greg Faulls: http://prevailinglife.com/five-ways-to-live-out-the-golden-rule/, March 3, 2015).
Constable, p. 51.
MacArthur, p. 581.
Warren Wiersbe, The Bible Expository Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), pp. 13–14.
MacArthur, p. 581.
ጥያቄዎች
-
ኢዮብ ወዳጆቹን “ የምታደክሙ አጽናኞች “ ናችሁ በማለት ጠራቸው ፤ እሰከዚህ ስፍራ ድረስ ወዳጆቹ አድርገዉት የነበረዉ የሚያፅናና ነገር ምን ነበር (ኢዮ 2፡ 11-13) ?
-
በኢዮ (13፡ 15-18) እና (19፡ 25) ኢዮብ ስለ እግዚአብሄር የተናገረዉን እና በጥቅስ (16፡ 9-14) ስለ እርሱ እንዴት እንደ ተናገረዉ አነፃፅሩ ፤ በዘፍ ( 32፡ 22-32) ያዕቆብ ከእግዚአብሄር ጋር ታግሎት እንደ ነበረው ኢዮብ አድርጎት የነበረዉ ይመሳሰላል ? በሁለቱ ትግል መካከል የነበረዉ ልዩነት ምን ነበር ?
-
ኢዮብ በአካል ለእግዚአብሄር “ ጥቃት “ እንዴት ምላሽ ሰጠ ? የፀና መንፈሳዊ እምነቱ ምን ነበር (ኢዮ 16፡ 19-21) ?
-
ነገሮች በመንገዳችሁ በማይሄዱ ጊዜ ጠበቃችሁ ማነው (1ዮሐ 2፡ 1-2) ? የሚማልድላችሁ ሊቀ ካህናችሁ ማነው (ዕብ 2፡ 17-18, 4፡ 14-16) ? በእግዚአብሄር ፈቃድ ፍፁም ሊያደርጋችሁ ማን ይፈልጋል (ዕብ 13፡ 20-21) ?
-
በኢዮብ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 16:4–5
“If you were in my place I could also talk like you. I could string words together against you and shake my head at you Instead, I would encourage you with my mouth, and the consolation from my lips would bring relief.”
ኢዮብ ኤልፋዝ ለሁለተኛ ጊዜ በእርሱ መከራ ላይ ለሰጠው ጠንከር ያለ አስተያየት ምላሽ ሰጠ ፡፡ ኢዮብ በታማኝነት መለሰ በተጨማሪም ኤልፋዝ እንዳላጽናናው ተናገረ ፡፡ እርሱም የኤልፋዝን ንግግር ተራ የሆነ የቃላት ስብስብ ፣ ከንቱ ንግግር ብሎ ጠራው ፡፡ ኢዮብ በተጨማሪም በመከራ ውስጥ ያለው ኤልፋዝ ቢሆን ኖሮ ብዙ መጽናናትን እንድሁም ለነፍሱ ተስፋ መቁረጥን ሳይሆን ያሚያጽናኑ ቃላትን ይነግረው እንደነበረ ተናገረ ፡፡
ንግግሮችህ ጠቃሚ ናቸው ፡፡ ያስፈልጋሉ እና ደግሞ ተፅዕኖ አላቸው ፡፡ አንተ የሚያጽናና ጓደኛ ነህን ? ወይስ ፈጥኖ ችግርን ነቅሶ የሚያወጣ እና ሁኔታውን የሚተች ነህ ? እግዚአብሔር አንተ ራስህ መታየት መስተናገድ በምትፈልገው መንገድ ሌሎችንም እንድታይና እንድታስተናግድ ይነግርሀል ፡፡ ከሰማዩ አባትህ ፍቅርን ስትቀበል አንተ ደግሞ ለሌሎች ፍቅሩን አፍስስ ፡፡ ይቅር መባልን እንደምትፈልግ ሁሉ ይቅር በል ፡፡ መረዳት እንደምትፈልግ ሁሉ እርዳ ፡፡ መጽናናት እንደምትፈልግ ሁሉ አጽናና ፡፡ አንተ እንድኖርህ የምትፈልገው አይነት ጓደኛ ሁን ፡፡ ግራ በመጋባት ውስጥ ስትሆን ይህን አስታውስ ፍቅር ታጋሽ ፣ ፍቅር ደግ እንደሆነ ፤ ፍቅር እንደማይቀና ፤ ፍቅር እንደማይኮራ ፤ ፍቅር እንደማይታበይ ፤ ፍቅር ልክ ያልሆነውን እንደማያደርግ ፤ ፍቅር ራስ ወዳድ እንዳልሆነ በተጨማሪም ፍቅር ልክ ያልሆነን ነገር ለማድረግ እንደማይቆጣ ፡፡ ይልቁንም ፍቅር በእወነት ደስ ይሰኛል እንድሁም ፍቅር ፈጽሞ አያልቅም ፡፡ ዛሬ የሚያጽናናንና የፍቅርን ቃል ለጓደኛህ ታካፍል ዘንድ እግዚአብሐርን ጠይቅ ፡፡ ከዚያም መልእክቱን በፍቅር አድርስና የእግዚአብሔርን መገለጥ ተመልከት ፡፡
“እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፤ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር ። በአፌም ነገር ባበረታኋችሁ ነበር የከንፈሬን ማጽናናት ባልከለከልሁም ነበር ። “
- ኢዮብ 16፡4-5
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ13:4–6 — “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም ፥ አይታበይም ፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም ፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም ፡፡ “
ቆላስይስ 3:13–14 — “እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ ፤ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት ። “
ዕብራውያን 3:13 — “ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።