Wisdom Books Job

Curses for the Wicked

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 374 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኤልፉዝ፣ በልዳዶስ እና ሶፋር ሁሉም በመጀመሪያዉ ዙር ኢዮብ የነበረበትን ሁኔታ እንዳልወደዱት እንዲያዉቅ ተናገሩ ፡፡ የዛሬዉ ምዕራፍ ለኢዮብ በወዳጆቹን ሁለተኛ ዙር ንግግር ይጀምራል ፡፡ እንደ ገና ኤልፉዝ መጀመሪያ ጀመረ ፤ በኢዮብ (4-5) ለኢዮብ የመጀመሪያ ንግግሩን ከተናገረ በኋላኤልፉዝ ከኢዮብ ጋር አለመስማማቱን ለማስፋት ዝግጁ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ ለአመለካከታቸዉ (ለኤልፉዝ፣ ለበልዳዶስና ለፋሪሶ) የኢዮብ ተቃዉሞና ፀሎቱ/ልመናዉ በተቃዉሟቸዉ ኃይሉን ለመጨመር እንደ ተበረታቱ “ ተመልክቷል ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (15፡ 1-6)፡ ኤልፉዝ ክፉ ሰዎች መጥፎ ነገር እንደሚገባቸዉ እንዲሁም ደግሞ መልካም ሰዎች መልካም ነገር እንደሚቀበሉ ወደ ሚለዉ እምነት በመራው ላይ የቅጣት አስተምሮ ላይ ተተክሏል ፡፡ ኮንስታብል የወዳጆቹ የመጀመሪያዉ ንግግራቸዉ በጣም ምርምር የበዛበት እና እዉነት እንደነበርና ሁለተኛ ንግግራቸዉ ደግሞ የኢዮብን ሀሳብ ለማሳመን በማሰብበጣም ስሜታዊነት የበዛበት እንደ ነበር ፅፏል ፡፡

ኤልፉዝ ኢዮብን ወዳጆቹ በተለያዩ መቅሰፍቶቹ ምክንያት አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ኖሯቸዉ እያለ በሙለ ለፍላፊ በመሆኑ ከሰሰው ፤ ዋይርስቤ የኢዮብ ሁኔታ በወዳጆቹ ላይ ከፍተኛ የስነ መለኮት አስተምሮ ላይ ፈተና እንዳመጣባቸዉ ፅፏል ፡፡ ኢዮብኃጢዓት ሰርቶ ካልነበርና በእግዚአብሄር የተቀጣ ካልነበር “ እግዚአብሄርን እንዲያከብሩ ሰዎችን ምን ያነሳሳቸዋል ? “ ፤ የኤልፉዝ አስተምሮ ስራ ላይ የተመሰረተ ነበር ፡፡ ኢዮብ ትክክል የሆነ ነገር አድርጎ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሄር ለመልካም ነገሮች የራሱ እንዲሆን ያደርግለታል መጥፎ ነገሮችንም ለማስወገድ በእርሱ ስር ይሆን ነበር፤ እንዲህ አይነት አስተምሮ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሄር አያገለግልም ፡፡ ዋይርስቤ እንዳጠቃለለው እንዲህ አይነት እምነት “ ራስ ወዳድነትን የሚያሳይ የኃይማኖት ስርዓት ብቻና እግዚአብሄርን የማያከብር ነው “ ፡፡ በቅደም ተከተሉ ለእኛ ከዚህ አይነት እምነት ለመብለጥ በትክክል እግዚአብሄርንመዉደድ ያስፈልገናል (ዘዳ 6፡ 4-6, 7፡ 7-9) ፡፡ ኤልፉዝ የኢዮብን አመለካከት ገሰፀ ነገር ግን በእዉነቱ የገሰፀበት አመለካከት ለእግዚአብሄር የኢዮብን ፍቅር ነበር ፡፡

ቁጥር 5 እና 6 ኢዮብ በኢዮ (9፡ 20) “ ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል ፤ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል “ ካለዉ ነገር ጋር የምፀታዊ አይነት ስምምነት ነበረው ፡፡ ኤልፉዝ የኢዮብን ቃል በመጠምዘዝ ትርጉሙን ለመጠምዘዝ በቃው፡፡

ኢዮብ (15፡ 7-13)፡ ኤልፉዝ ኢዮብ በፍፁም ጥፋት አላደረኩም የሚለዉን አመለካከቱን ለመገሰፅ ስለ አቤቱታዉ ከባድ የሆነ ጥያቄ መጠየቅ ጀመረ ፡፡ የኤልፉዝ ጥያቄ ለኢዮብ በቁጥር 9 “ እኛ የማናዉቀዉን አንተ የምታዉቀዉ ምንድር ነው ? “ በኢዮ (13፡ 2) “ እናንተ የምታዉቁትን እኔ ደግሞ አዉቃለሁ ፤ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም “ ለሚለዉ ለኢዮብ ንግግር ምላሽ ነዉ የሚመስለው ፡፡ በቁጥር 10 ኤልፉዝ ኢዮብን የሽማግሌዎቹን ምክር እምቢ በማለቱ ከሰሰው ፤ ቆይቶም ኢዮብ “ በዕድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም ሽማግሌዎችም ፍርድን አያስተዉሉም “ (ኢዮ 32፡ 9) ፡፡ በቁጥር 12 ኤልፉዝ ኢዮብ ወደ እርሱ ላይ ብስጭትን ለምን አሳይቶ እንደ ነበር ተደነቀ/ጠየቀ ፤ በኤልፉዝ አስተሳሰብ ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ትክክልና ምክንያታዊ እንደ ሆነ ነበር የሚያስበዉ ፡፡

ኢዮብ (15፡ 14-16)፡ ኤልፉዝ ጥቃቱን ማንም በምድር ላይ ፃድቅ እንዳልነበር በማመልከትበኢዮብ ላይ ጥቃቱን ቀጠለ ስለዚህም በዚህ ኃይለኛ ሁኔታ ኢዮብ ራሱም ሊሆን አይችልም ፡፡ እግዚአብሄር “ እምነት ያላስቀመጠባቸው “ “ ቅዱሳን “ ተብለዉ ለመጠቀስ ምናልባት ለወደቁት መለዓክት ማጣቀሻ ሊሆን ይችላል ፡፡

ኢዮብ (15፡ 17-35)፡ የኢዮብን ኃጢዓተኝነት በራሱ ሀሳብ ላይ ለማቋቋም ኤልፉዝየዚህን ንግግሩን ትኩረት የክፉዎችንእጣ በማመልከት አተኮረ ፡፡ የኤልፉዝ መመልመያ በኢዮብ ሁኔታ ዉስጥ ለመናገር በራሱ ልምምድ ላይ (ቁጥር 17) እና በሰዎች ልምድ ላይ የተመሰረተ ነበር (ቁጥር 18) ፡፡ የመጀመሪያ ንግግሩ የእግዚአብሄር ሰዎች የሚገጥማቸዉን በረከት አጉልቶ ሲያሳይ አሁን ደግሞ ኤልፉዝ ኢዮብ ንስሀ የማይገባ ከሆነ ሊገጥሙት የሚችሉትን ሁሉንም የክፉዎችን ሰባት እርግማኖች አጉልቶ ያሳያል፡

  1. ስቃይ ይደርስባቸዋል (ቁጥር 20) - በቁስሉ እና በጤንነቱ ችግር ምክንያት ኢዮብ በጣም ብዙ አካላዊ ህመሞች እየደረሱበት ነበር ፡፡
  2. ቀድመዉ/ያለጊዜአቸዉ ይሞታሉ (ቁጥር 20) - አሁንም ኢዮብ ህያዉ ነበር ነገር ግን ለመሞት ፍላጎቱን እየገለፀ ነበር ፡፡
  3. መሰረተ ቢስ ፍርሀት አላቸው (ቁጥር 21) ፡፡
  4. በሰላም ጊዜ ጥፋት ይገጥማቸዋል (ቁጥር 21) ፡፡
  5. ከጥፋተኝነት ኃሳብ ከፍተኛ ስቃይ ይገጥማቸዋል (ቁጥር 22) ፡፡
  6. የተሳደዱ ሕዝቦች ናቸዉ (ቁጥር 22) ፡፡
  7. ሁልጊዜ ይራባሉ መሰረታዊ ፍላጎትም ይፈልጋሉ/ይመለከታሉ (ቁጥር 23) ፡፡
  8. የተጨነቁና በድብርት ዉስጥ ያሉ ናቸው (ቁጥር 23-24) ፡፡

የእግዚአብሄር ምክንያት ለፍርድ በግለሰብ አመፅ ( ቁጥር 25-26) እና በራስ ፍላጎት ማርቃት/ልቅነት (ቁጥር 27-28) ላይ የተመሰረቱ ናቸው ፡፡ እነዚህን ምክንያቶች ከዘረዘረ በኋላ ኤልፉዝ ክፉዎችን የሚገጥሙ ሰባት ፍርዶችን ሰጠ፡

አይበለፅጉም (ቁጥር 29) ፡፡

ይሞታሉ (ቁጥር 30) ፡፡

ስራቸዉ ይወድቃል/አይሳካም (ቁጥር 30) ፡፡

ያላደገ/ያለጊዜዉ የሆነ ነገር ይገጥማቸዋል (ቁጥር 31-32) ፡፡

ኃብታቸዉ ይወድቃል (ቁጥር 32-33) ፡፡

ባዶነት ይደርስባቸዋል (ይሰማቸዋል ) (ቁጥር 34) ፡፡

ራሳቸዉን ያታልላሉ (ቁጥር 35) ፡፡

ኤልፉዝ ኢዮብን ባልታወቅ አደገኛነት መንገድ ግብዝና እግዚአብሄር የሚፈልገዉ አይነት አይደለህም በማለት ጠራው ፡፡ በፍፁም አንድ ጊዜ እንኳን ኢዮብ ይህን ሁሉንም መከራ እየደረሰበት የነበረዉ በግሉ እንደ እግዚአብሄር አይነት ሰዉ ባለመሆኑ እንደ ነበር አልገለፀም ነገር ግን የኤልፉዝ ጠቅላላ ንግግሩ በግልፅ የሚያስበዉ ምን እንደ ነበር ግልፅ ለማድረግ ነበር ፤ ይሁን እንጂ የኤልፉዝ ስነ መለኮታዊ ትምህርት ሁል ጊዜ እዉነት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር “ ….. በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና “ (ማቴ 5፡ 45) ፤ ክፉ ወይም ደግሞ መልካም እናድርግ እግዚአብሄር “ ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሳል “ (2ጴጥ 3፡ 9) ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ በሮሜ (2፡ 4) “ የእግዚአብሄር ቸርነት ወደ ንስሀ ሊመራህ ያሰበ ነዉ “ በማለት ፅፏል ፤ እግዚአብሄር የሚገባን ቢሆንም እንኳን ሊፈርድብንና ሊያጠፋንአይፈልግም ነገር ግን እኛን ወደ እርሱ ለመሳብ ሲል መከራ እንዲደርስብን በመፍቀድ ፍቃደኛ ነው (1ጴጥ 1፡ 6-8) ፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ ላይ እንድትጣበቁና ተስፋ እንድትይዙ ለማስተማር በችግር ጊዜ ዉስጥ ሊያሳልፋችሁ/ሊወስዳችሁ ይፈልጋል (ሮሜ 8፡ 18-20) ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005) p. 580.

  2. Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes: Job, p. 63; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  3. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Wisdom and Poetry (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 32.

  4. Wiersbe, p. 32.

  5. MacArthur, p. 580.

  6. MacArthur, p. 580.

  7. Constable, p. 65.

    Constable, p. 65.

ጥያቄዎች

  1. ለኢዮብ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ የኤልፉዝ ምላሽ ምን ነበር ? እንዴት ኢዮብን ከሰሰው ?
  2. የኢዮብ ሰዎስት ወዳጆች ኢዮብ እየተሰቃየ የነበረዉ በኃጢዓቱ ምክንያት ነዉ ብለዉ በማሰብ ለምን የጸኑ እንደነበሩ ምን ታስባላችሁ ? ስለ ጤንነት ወይም ስለ ብልፅግና ዋስትና ለእግዚአብሄር መታዘዝ ነው ? ግለፁ (ማቴ 26፡ 39, ሉቃ 9፡ 58, ፊል 2፡ 8, ዕብ 5፡ 8)
  3. ኢዮብ የፀሎት ሰዉ ነበር (ኢዮብ 1) ? ኤልፉዝ ኢዮብን ፍራትን በማስወገድ በእግዚአብሄር ፊት ፀሎትን እንዳቆመ ነገረው (ኢዮ 15፡ 4 አዲሱ ኪንግ ጀምስ ዕትም) ፤ የሆነ ሰዉ/አንድ ሰዉ በእግዚአብሄር ፊት እንዴት ፀሎት ያቆማል ?
  4. የኤልፉዝ የመጀመሪያ ንግግሩን ቃል (ኢዮ 5፡ 17-26) በዮሐ (15፡ 17-35) ካለዉ ንግግር ጋር አወዳድሩ ፤ የሁለቱ ልዩነት እንዴት ነበር ?
  5. በኢዮ (15፡ 34-35) ኤልፉዝ ኢዮብን በምን ኃጢዓት ከሰሰው ? ኢዮብ ብትሆኑ እነዚህን ወዳጆች እንዴት አድርጋችሁ ትይዟቸዋላችሁ ? በሆነ ነገር በስህተት ተከሳችሁ ታዉቃላችሁ ? እንዴት አድርጋችሁ አስተናገዳችሁት ?
  6. በኢዮብ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 15:17

“Listen to me and I will inform you. I will describe what I have seen.”

የኢዮብ ጓደኞች ሁለተኛ ዙር ምላሽ መስጠት ጀመሩ ፡፡ ኤልፋዝም ቀደመ ፤ በዚህ ጊዜ ምክሩን ጠንከር አድርጎ ኢዮብን ገሰጸ ፡፡ ኢዮብ ይህ መከራ ይደርስበት ዘንድ በእርግጥ አመጻን አድርጓል ብሎ በማመን ለኢዮብ ስቃይ በስራ ላይ የተመሰረተ አስተያየቱን ሰነዘረ ፡፡

እውነቱ ይህ ነው ፡፡ የራስህን መንገድ ለእግዚአብሔር ልታደርግ አትችልም ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት ነጻ ስጦታዎች ናቸው ፡፡ እርሱ መልካምና ታጋሽ ነው ፡፡ ይህ በምታደርገው ወይም ደግሞ በማታደርገው ነገር አይመሰረትም ፡፡ በእርግጥ ለመረጥከው ምርጫ ወይም ለሰራኸው ኃጢአት ውጤቱን የምትቀበልበት ጊዜ አለ ፡፡ ነገር ግን በፈተና ውስጥ ስታልፍ ይህን አስተውል የእግዚአብሔር መንገድ የአንተ መንገድ እንዳልሆነ ፡፡ እግዚአብሔር የጸጋና የምህረት አምላክ ነው ፡፡ በእርግጥ እንደ አማኝ መከራን እንደምትቀበል ጌታ ተናግሯል ፤ ሁሉም አማኝ ማለት ነው ፡፡ ሆኖም ግን በብዙ መከራዎች ውስጥ ብታልፍ እንኳ አይኖችህን በኢየሱስ ላይ ስታደርግ ፣ በእሳቱ ተፈትነህ እንደምትወጣ ከተረዳህ ተስፋ አለ ፡፡ እንደ ወርቅ ትጠራለህ ኢየሱስንም በማመስገን ፣ በማክበርና ከፍ በማድረግ ትጨርሳለህ ፡፡ እግዚአብሔር ትእግስትንና ብርታትን እንድሰጥህ ጸልይ ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር በፍቅሩ ይሸፍንሀል ደግሞም መልካምነቱን በአንተ ላይ ያፈሳል ፡፡

“እገልጥልሃለሁ፥ ስማኝ፤ ያየሁትንም እነግርሃለሁ ። “ - ኢዮብ 15፡19

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሮሜ 2:4 — “ ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን ?
  • 1ኛ የጴጥሮስ 1:6–7 — “በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል ። “
  • 2ኛ የጴጥሮስ 3:9 — “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል ። “