Wisdom Books Job

Losing Hope

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 373 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና ለሶፋር ወደ ፀሎት የመለሰዉን የኢዮብ ምላሽ ላይ ተመልክተናል (ኢዮብ 13) ፤ በምዕራፍ 14 የኢዮብ ቃለ ምልልስ ከእግዚአብሄር ጋር ቀጠለ ፡፡ ኮንስታብል በምዕራፍ 14 የኢዮብን ቃል “ እስካሁን ሁሉም ሰዎስቱም ጓደኞቹ አድርገዉት ለነበረዉ ዋና ክርክርና የተለየ ፅሁፍ ትክክለኛ መልስ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (14፡ 1-6)፡ በኢዮ (14፡ 1) ኢዮብ የህይወትን ማጠርን መናገር በመቀጠል “ ቀኑ ያጠረና በመከራ የተሞላ ነዉ “ አለ ፡፡ ኢዮብም ህይወትን እንደ ሚወጣ አበባና እንደሚጠፋ ጥላ ገለፀው (ቁጥር 2) ፡፡ ኢዮብ ስለ ፀጋ በመጠየቅ (ቁጥር 3) ከርኩስ ነገር ንፁህን ነገር መስራት የሚችል ካለ እንደሚደነቅ ተናገረ (ቁጥር 4) ፡፡ ሁላችንም በረከሰ ሁኔታ ዉስጥ የተወለድን ስለሆንን ሁላችንም ኃጢዓተኞች ነን (1ነገ 8፡ 46, መዝ 14፡ 1, 3፣ መክ 7፡ 20፣ ኢሳ 64፡ 5፣ ሮሜ 3፡ 10, 23) ፡፡ ይህን መዉሰድ የሚችለዉ መካከለኛችን የክርስቶስ ደም ብቻ ነው ፡፡ ቀጥሎም ኢዮብ ሰዉን እንደ ተቀጠረ ሰዉ የተቆጠረ ዘመን እንዳለዉ ገለፀዉ (ቁጥር 5-6) ፡፡

ኢዮብ (14፡ 7-17)፡ ኢዮብ ከህይወት እጥረት ወደ ሞት ማብቂያነት ቀጠለ (ቁጥር 7-17) ፡፡ አንድ የተቆረጠ ዛፍ መልሶ ማቆጥቆጥ ይቻለዋል አይሞትምም (ቁጥር 7-9)(ኢሳ 6፡ 13) ፤ ለህይወት ከኢዮብ ይልቅ ዛፉ ተስፋ ነበረው ፡፡ “ ቅዱሱ ዘር “ አሁንም በዛፉ ስር ነበር ፤ ይህወደ ኢየሱስ የሚመራ ትንቢታዊ ስዕል ነው ፤ ነገር ግን ሰዉ እንዲህ አይነት ተስፋ አልነበረዉ ከአፈር ዉስጥ ከተነነ ዉሃ ጋር ተመሳሳይ ነበር ( ቁጥር 10-11) ፤ ኢዮብ እያለ የነበረዉ ሰዉ በሞት በወደቀ ጊዜ እንደ ገና ህያዉ እንደሚሆን ምንም ማረጋገጫ እንዳልነበረዉ ነው (ቁጥር 12) ፤ ይሁን እንጂ ኢዮብ እግዚአብሄርን ቁጣዉ እስኪያልፍ ድረስ በሞት እንዲደብቀው ነገረው (ቁጥር 13) ፡፡ ማክአርቱር የሚናገረዉ ኢዮብ እየጠየቀ የነበረው የእግዚአብሄር ቁጣ ከተፈጸመ በኋላ “ እግዚአብሄር ሲጠራዉ ተመልሶ እንደሚነሳ “ ነበር ፡፡ ኢዮብ ትንሳኤ ይኖር ነበር በማለት ተደነቀ (ቁጥር 14) ፤ ኢዮብ እግዚአብሄር ወደ ህይወት መልሶ ካመጣው ኃጢዓቱን ሳይመለከት የኢዮብን ቀናት መቁጠር እንደሚችልና እግዚአብሄርም ኃጢዓቱን እንደሚሸፍንለት አሰበ (ቁጥር 15-17) ፡፡

ሰዉ መልሶ መኖር እንደሚችል ኢዮብ እየጠየቀ ነበር ፤ መዝሙረኛው እግዚአብሄር እርሱን በሲዖል እንደማይተወዉ (መዝ 16፡ 9-11) እና “ ሲነቃም “ የእግዚአብሄር ፊት እንደሚያይ ተናገረ (መዝ 17፡ 15, ኢሳ 26፡ 19, ዳን 12፡ 2) ፡፡ ኢዮብ ቢሞት እንኳን እንደሚነሳ ተስፋ ነበረው ፤ ኢዮ (19፡ 25-26) በሞት ላይ ተስፋ ስለሚሰጠዉ ተስፋ ስለተሰጠዉ ተቤዢ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄር በመጨረሻ ሞት ላይ ስልጣን አለው፣ሁሉም ሰዉ በፊቱ ይቆማል (ሐዋ 24፡ 15, ዕብ 9፡ 27) ፡፡ በየትኛዉ ወገን ላይ ትወድቃላችሁ ? በዉርደት በኩል ወይስ በዘላለም ህይወት በኩል ? አዲስ ኪዳንም ሰዉ ተመልሶ በህይወት የኖረ እንደሚሆን ይናገራል ፡፡ ኢየሱስም አልዓዛር በህይወት ተነስቶ እንደሚኖር ተስፋ ገባ (ዮሐ 11፡ 23-27) ፡፡ የመጨረሻ ሞትን መፍራት የለብንም ምክንያቱም ኢየሱስ ስላጠፋው (2ጢሞ 1፡ 10) ፡፡

ኢዮብ (14፡ 18-22)፡ እስከዚህ ስፍራ ድረስ ኢዮብ በእግዚአብሄር ላይ ተስፋዉን ቢጠብቅም እነዚህ የመጨረሻዎቹ ጥቅሶች የጎላ ተስፋ ማጣት ይታይበታል ፡፡ ማክአርቱር “ ኢዮብ በእግዚአብሄር ፊት ወደ ቅሬታዉ በመመለስ ስለ ሞት አይቀሬነትና መለያየት በመናገር ተስፋ ቢስ ወደ ሆነዉ ሁኔታ መልሶ ተመለሰ ፤ ስለዚህም ነገር በማሰብ በኃይለኛዉ የተበሳጨ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ኢዮብ ተስፋ ማጣቱን እንደ ሚወድቅና እንደ ሚፈራርስ ተራራ ወይም በእንቅስቃሴዉ አፈርን እንደሚጠራርግ የዉሃ ጎርፍ ገለፀው ፤ ኢዮብ እግዚአብሄርን “ እንዲሁ የሰዉን ተስፋ ታጠፋዋለህ ፡፡ ለዘላለም ታሸንፈዋለህ እርሱም ያልፋል ፤ ፊቱን ትለዉጣለህ እርሱንም ትሰድደዋለህ “ (ቁጥር 19-20) ፡፡ ተስፋ በእቸጋሪ ጊዜና በማይደግፉን ወዳጆች በኩል የሚያገኘን ብቸኛዉ ነገር ነው ፤ ተስፋ በህይወታችን ለሚገጥመን ማንኛዉም ነገር ዋና መዋጊያ መሳሪያ ነው (ዕብ 6፡ 19) ፡፡ ተስፋችን በራሱ በክርስቶስ ላይ የታሰረ መሆን አለበት ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ የኦት አማኝ ከህይወት በኃላ ትንሽ ለመባረክ ማስረጃ እንደሚያይ ይቀበላል ፤ ይህ የኢየሱስ ትንሳኤ አስፈላጊነት ነው ፤ እኔ ህያዉ ከሆኑክ እናንተም ህያዉ ትሆናላችሁ ብሎ ተስፋን ስለሰጠ “ በማለት ያብራራል ፡፡ በክርስቶስ ማመን ማለት እንደ ህያዉ ተስፋችን በእርሱ ስር መስደድ ማለት ነው (1ጴጥ 1፡ 3) ፤ ኢዮብም ያለ ተስፋ ሰዉ በራሱ ህይወት ላይ ወይም በሌሎች ኑሮ ላይ በሚሆነዉ ነገር ክብር አያገኝም (ቁጥር 21-22) ፡፡

መደምደሚያ

ቻርለስ አለን “ አንድ ሁኔታ ወይም አንድ ሰዉ ተስፋ የለዉም ስትሉ በእግዚአብሄር ፊት በሩን እየዘጋችሁት ነዉ “ በማለት ተናግሯል ፡፡ ተስፋችን ከእግዚአብሄር ይመጣል ፤ “ የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታና ሰላም ሁሉ ይሙላባችሁ “ (ሮሜ 15፡ 13) ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በየትኛዉም መልኩ እየሄዳችሁ እንደሆነ ችግር የለዉም፣ በክርስቶስ አላማ አላችሁ በእርሱም ተስፋችሁን ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes: Job, p. 62; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 626.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary: Job (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 580.

  4. MacArthur, p. 580.

  5. Nelson’s Commentary, p. 627.

ጥያቄዎች

  1. በግል አስተያየታችሁ እግዚአብሄር ለእያንዳንዱ ሰዉ ህይወት የተወሰነ ወራትን መወሰኑን ኢዮብ እንዴት ሊያዉቅ ቻለ (ኢዮ 14፡ 5, መዝ 139፡ 16)
  2. በኢዮ (14፡ 12) ትንሳኤ እንደሚሆን የሚያዉቀዉን ኢዮብ ተናገረ ፤ ኢዮብ እንዴት ይህን ሊያዉቅ ቻለ ? ብበሉይ ኪዳን ዉስጥ ስለ ትንሳኤ የሚናገሩ ሌሎች ምሳሌዎች የት ላይ ናቸው ? (ኢዮ 19፡ 26, ኢሳ 25፡ 8-9, 26፡ 19፣ ዳን 12፡ 2)
  3. በኢዮብ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 14:14–15

“When a man dies, will he come back to life? If so, I would wait all the days of my struggle until my relief comes. You would call, and I would answer You. You would long for the work of Your hands.”

ኢዮብ ለጓደኞቹ ምክር ምላሽ መስጠቱን ቀጠለ ፡፡ በምላሹም ተስፋ መቁረጡ ይታይ ነበር ፡፡ በመከራም ዝሎ ነበር ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔርን ሁሉንም አይነት ጥያቄዎች መጠየቅ ጀመረ ፡፡ ህመሙም በተባባሰ ጊዜ ኢዮብ ከሞት በኋላ ስላለው ህይወት ሳይቀር ጠየቀ ፡፡

በተስፋህ መጨረሻ ላይ በምትሆንበት ጊዜ ምንድን ነው የምታደርገው ? ስለ ህይወት ከምታስበው በበለጠ ስለ ሞት ታስባለህ ? ራስህንም ትጠይቅ ይሆናል ፡- በውኑ ተስፋ ለማድረግ የቀረ ነገር አለን ? በዚህ በምድር ላይ ምንድን ነው የኔ ስራ ? መልሱ ይሄው ፡፡ ተስፋ አላለቀም ፤ ተስፋ አለ ፡፡ የተነገረው ቤዛ የዚህ አለም ተስፋ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ አለህ ፡፡ እርሱ ለህይወትህ የደህንነት ምንጭ ነው ፡፡ እርሱ ምቹና አስተማማኝ ነው ፡፡ በክርስቶስ በሚገኘው ተስፋ ይሞላህ ዘንድ ለመንፈስ ቅዱስ ፍቀድ ፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ስታምን እርሱ በደስታና በሰላም ይሞላሀል ፡፡ ከዚያም በኢየሱስ በማመን የዘላለም ሕይወት ይኖርሀል ፡፡ በአሁኑ ሰአት ስለ ህይወት እየጠየክ ከሆነ እነዚህን ንግግሮች ለራስህ አዳምጥ ፡- ስራ አለህ ፤ አንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ ሲል ወደ ምድር መምጣት የተገባህ ሰው ነህ ፡፡ ተወደሀል ፤ ብቻህንም አይደለህም ፤ ተስፋ አለህ ፡፡ በኢየሱስ ውስጥ በሚገኝ ስራ ላይ ጽና እንድሁም መንፈስ ቅዱስ እንድሞላህ ለምን ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር እንደሚሰማህና እንደሚመልስልህ በማመን በየቀኑ መጸለይ ያስፈልግሀል ፡፡

“በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን? መለወጤ እስኪመጣ ድረስ፥ የሰልፌን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር ። በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር ፤ የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር ። “

  • ኢዮብ 14፡14-15

ተጨማሪ ጨዋታ

ሮሜ 15:13 — “ የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ ። “

2ኛ ጢሞቴዎስ 1:10 — “ አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና ፡፡ በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል ። “

ዕብራውያን 6:19 — “ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው ፡፡ “