Wisdom Books Job

Job's Initial Response to Zophar

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 372 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በኢዮብ ጥናታችን አንድ ሙሉ ሳምንት ብቻ ነበረን ነገር ግን ቢያንስ ለአንድ ወር እንደቆየን እንዲሰማን ያደርጋል ፤ ሳጠናዉ ድግግሞች እንዲሰማኝ ያደርገኛል ፡፡ ከእርሱ እስኪመለሱ ድረስ አይናቸዉን በእግዚአብሄር ላይ ከሚያደርጉት ከእስራኤላዊያን ታሪክ ጋር በደንብ ይመሳሰላል ፤ ይህም በአመለካከት በትንሽ ልዩነት ደግመዉ ደግመዉ ተመሳሳይ ነገር በሚሉት በሰዎስት ወዳጆቹ መሰረት በኢዮብ ላይ እየተካሄደ ካለዉ ኡደት ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ የኢዮብ የቀጠለዉ ቃለ ምልልስ ከወዳጆቹ ጋር በምዕራፍ 3-31 ላይ የተመዘገበ ነው ፤ የኢዮብ ወዳጆች ኤልፋዝ፣ በልዳዶስ እና ሶፋር ነበሩ ፡፡ ዋይርስቤ በምዕራፍ 13 “ ኢዮብ መጀመሪያ በሰዎስት ወዳጆቹ መበሳጨቱን (ቁጥር 1-13)፣ ከዚያም በእግዚአብሄር ላይ ያለዉን እምነት ማወጁን (ቁጥር 13-17 )፣በመጨረሻም እግዚአብሄር መጥቶ አንዴ ሁሉንም ነገሩን እንደሚያስተካክለዉ መፈለጉን (ቁጥር 18-28) “ ጠቁሟል ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (13፡ 1-12)፡ ኢዮብ በወዳጆቹ መበሳጨቱን ነገራቸዉ ምክንያቱም የተረዳዉን ነገር እንዲገልፁለት ስላልፈለጋቸው ፡፡ ማክአርቱር ኢዮብ “ ጉዳዩን በእግዚአብሄር ፊት መዉሰድ እንደ ፈለገ “ አመልክቷል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ምፀትን ኢዮብም ሆነ ወዳጆቹ በደንብ አያዉቁትም ምክንያቱም የቅጣትን የማይቀየር ዶግማ/ስርዓት ስለሚያስቡ “ ይናገራል ፡፡ ቴዎሪያቸው መልካም ሰዉ ሁል ጊዜ ይባረካል ክፉ ሰዉ ደግሞ ሁል ጊዜ በራሱ ላይ እርግማንን ያመጣል በሚለዉ ሀሳብ ላይ የተመሰረተ ነበር ፡፡ ሰዎስቱ ወዳጆቹ ኢዮብን እንደተመለከቱት ከዚህ በኋላ እንደማይባረክና በረከት እንደማይኖረዉ አጠቃለዉ ስለ ነበር ርጉም ይሆናል ፡፡ ኢዮብ ለእግዚአብሄር ቀጥታ ለመናገር ፈለገ (ቁጥር 3) ፤ በቁጥር 4 ወዳጆቹ ልማዳዊ አመለካከታቸዉን ለመጠበቅ የቅጣት ዉሸታቸዉን ኖራ እየቀቡና እያሰራጩ ነበር (መዝ 119፡ 69) ፤ በኢዮብ ህይወት ላይ እየሆነ ስለ ነበረዉ ነገር ጥሩ የሆነ መረዳት ስላልነበራቸው ዝም እንዲሉና ምንም እንዳይናገሩ ነገራቸው (ቁጥር 5) ፡፡

በቁጥር 6 ኢዮብ ክርክሩን በመጀመር ወዳጆቹን ስለ እግዚአብሄር ሀሰት ነገር እንደሚመሰክሩ ጠየቃቸው (ቁጥር 7) ፤ ማክአርቱር የኢዮብን ጥያቄ በቁጥር 8 “ በእግዚአብሄር መከላከያ ላይ ለመከራከር በማስተዋል በቂ ናችሁ ? “ ብሎ እንደ ጠየቃቸዉ ተርጉሞታል ፡፡ ኢዮብ ወዳጆቹ እግዚአብሄርን ማታለል እንደማይችሉና ለማታለል ከሞከሩ ራሱ እግዚአብሄር ድርጊታቸዉን እንደሚገስፅ አመለከተ (ቁጥር 9-10) ፡፡ ኢዮብ ወዳጆቹን ቃላቸዉ እግዚአብሄር የሚያዉክ ብቻ ሳይሆን አጥጋቢ ያልሆነና ዋጋ የሌለዉ እንደ ነበር ነገራቸው (ቁጥር 11-12) ፡፡ በወዳጆቹ የተሰማዉ ሁሉም የኢዮብ ብስጭት በኢዮ (42፡ 7-8) በእነርሱ ላይ በእግዚአብሄር ብስጭት የተረጋገጠ ይሆናል ፡፡

ኢዮብ (13፡ 13-17)፡ ኢዮብ የእምነት መግለጫዉን/አዋጁን ጀመረ ፤ ኢዮብ ቃሉን እንዲያደምጡ እርሱም ስለ ቃሉና ስለ ህይወቱ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ነገራቸው (ቁጥር 13-14) ፡፡ የድርጊቱ ዉጤት ምንም ቢሆን የኢዮብ ተስፋ በእግዚአብሄር ነበር (ቁጥር 15) (ዳኒ 3፡ 16-18) ፤ ኢዮብ እንደ እግዚአብሄር ሰዉ ነጻ መዉጣትን/መዳንን ጠበቀ (ቁጥር 16) ፡፡ በዚህም ምክንያት ወዳጆቹ ለቃሉና ለእምነቱ ትኩረት ይሰጡታል (ቁጥር 17) ፡፡

ኢዮብ (13፡ 18-28)፡ ኢዮብ እግዚአብሄር በእርሱ ህይወት ላይ እንዲሆን በመፈለግ ቀጠለ ፡፡ ኢዮብ ጉዳዉን በማዘጋጀት እግዚአብሄር እንደሚፈታለት ያውቃል (ቁጥር 18-19) ፡፡ ማክአርቱር ኢዮብን “ በእግዚአብሄር ፊት ንፁህ መሆኑን እንደሚከላከልና በትክክል የዳነ እንደ ነበርና ግብዝ እንዳልነበር እርግጠኛ እንደ ነበር “ ይገልፀዋል ፡፡ በቁጥር 20 ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር ክርክሩን ወደ እግዚአብሄር በመፀለይ ዘጋ ፡፡ ኢዮብ ሁለት ነገሮችን ጠየቀ ፤ መጀመሪያዉ እግዚአብሄር እጁን ከእርሱ ላይ እንዲያነሳ ጠየቀ - ኢዮብን ገጥሞት የነበረዉን ስቃይ ፤ ሁለተኛዉ ማስፈራቱ እንዲያስፈራዉ በእርሱ ላይ እንዳይፈቅድ እግዚአብሄርን ጠየቀው (ቁጥር 20-21) ፡፡ ይህ ሁለተኛው ጥያቄ ከእግዚአብሄር ጋር ስለ ነበረዉ ግንኙነት ነበር ፤ ከእርሱ የራቀዉን እግዚአብሄርን በጣም መፍራት አልፈለገም፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄር እንዲጠራዉና እንዲናገረዉ ፈለገ (ቁጥር 22)(ኤር 33፡ 3, ማቴ 7፡ 7, 21፡ 22, ሉቃ 18፡ 1, ዮሐ 14፡ 13, ፊል 4፡ 6, ዕብ 4፡ 16, ያዕ 4፡ 3) ፤ ኢዮብም እግዚአብሄርን ሁሉንም ኃጢዓቱን እንዲገልጥለት ጠየቀው (ቁጥር 23) ፡፡ ማክአርቱር ኢዮብ የኃጢዓቱን ዝርዝር ለመስማት በመፈለግ “ ከኃጢዓቱ አደገኝነት አንፃር የመከራዉ መጠን እንደሚመጣጠን መወሰን ለመቻል እና ከዚያም ስለማያዉቃቸዉ ኃጢዓቶች ንስሀ ለመግባት እንዲችል እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ኢዮብም እግዚአብሄር ለምን እንደጠላት እንደተመለከተዉና ለምን የቀድሞ ኃጢዓቱን በእርሱ ላይ እንደመለሰበት ጠየቀ (ቁጥር 24-25) ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄርን በተረዳዉ መንገድ እየሰራ እንዳልነበር እየተናገረ ነበር (ቁጥር 27) ፤ ቁጥር 28 በኢዮብ (14፡ 1) ምርጥ መረዳት ነው “ ከሴት የተወለደ ሰዉ…….የህይወት ዘመኑ ጥቂትና መከራም ይሞላዋል “ ፡፡ የሰዉ ልጅ ሁኔታ አስቸጋሪ ነው ፤ ኢዮብ ኃይለኛ ስቃይ ደርሶበት የነበርና እነዚያ ምልክቶችና ስቃዮች በራሱ ኃጢዓቱ ምክንያት እንደሆነበት መቀበል አልቻለም ፡፡

መደምደሚያ

በዚህ መፅኀፍ ስለ ኢዮብ የምወደዉ ነገር እግዚአብሄርን መዉደድ አለማቆሙን ነው ፡፡ ስለ መከራዉ እግዚአብሄርን አልወቀሰም ፤ ሁል ጊዜ ኢዮብ ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነቱን ለማደስ ፈለገ ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Job (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 28.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary: Job (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 579.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 625.

  4. MacArthur, p. 579.

  5. MacArthur, p. 579.

  6. MacArthur, p. 579.

ጥያቄዎች

  1. በኢዮ (13፡ 4) ኢዮብ ወዳጆቹን የማትጠቅሙ ባለመዳኒቶች ናችሁ ብሎ ጠራቸው ፤ በዚያ መጥራቱ ምን ማለቱ እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  2. በኢዮ (13፡ 8)(NASB) ኢዮብ ወዳጆቹን “ ለእግዚአብሄር ትከራከራላችሁን ? “ በማለት ጠየቃቸው ፤ እግዚአብሄር ለእርሱ እንዲከራከርለት የሆነን ሰዉ ያስፈልገዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ይህን ስታደርጉ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ?
  3. በኢዮ (13፡ 15) ኢዮብ “ ቢገድለኝ እንኳን እርሱን በትዕግስት እጠባበቃለሁ “ ባለ ጊዜ ኃይለኛ ንግግር አረገ ፤ ይህ ስለ ኢዮብ እምነት ምን ይላል ? ይህ ንግግር ከኃላ በኢዮ (2፡ 5) ላይ ሰይጣን “ ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ስጋዉን ዳብስ ፤ በእዉነት በፊትህ ይሰድብሃል አለዉ “ ብሎ በኢዮብ ላይ ያመጣዉ ክስ ስህተት እንደ ነበር አረጋግጧል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  4. ኢዮ (13፡ 24) በመጥቀስ እግዚአብሄር ዝም ያለ ሲመስል ሁኔታዉን እንዴት ትይዙታላችሁ ? ለመልስ ወደ እርሱ መቼ ትጮኋላችሁ ? ኢዮብ እንዳደረገዉ እግዚአብሄር እንደ ጠላት እንደተመለከታችሁ ይሰማችኋል ?
  5. በኢዮብ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 13:5

“If only you would shut up and let that be your wisdom!”

ኢዮብ ለሶስት ጓደኞቹ በሚመልስበት ጊዜ ከጭንቅላቱ እስከ እግር ጥፍሩ በቁስል ተሸፍኖ ነበር ፡፡ የእነርሱንም ምርምር እና እውነት ሲያደምጥ ቆየ ፤ እነርሱንም ተረዳቸው ነገር ግን ከእነርሱ እንደሚያንስ አላመነም ነበር ፡፡ ኢዮብም ወደ ልባቸውና ወደ አሳባቸው ሲመለከት እርሱን በሚመክሩበት ጊዜ የሆነ ነገር እንደተሳሳቱ ተገነዘበ ፡፡ አንድ ጊዜ ኢዮብ ሶፋርን ፡- “ ምነው ዝም ብትልና ይህ ጥበብ በሆነልህ ! “

ብዙ ቤተሰቦችና ትምህርት ቤቶች “ ዝም በል “ ከሚለው ሀረግ ጋር የሚቃረን ህግ አላቸው ፡፡ በአብዛኛው ባህል ውስጥ ይህ ንግግር የሚሰማው ትህትና በሌለው እናም ደግሞ ብልግና በሞላበት ንግግር ውስጥ ተደርጎ ነው ፤ ይህም ንግግር በቃጥታ ሲታይ የሆነን ሰው ማውራት እንድያቆም መንገር ነው ፡፡ ሆኖም ግን ኢዮብ ይህን ሀረግ በሶስት ጓደኞቹ ላይ ሰነዘረው ፤ በጥበብም ዝም እንድሉ መከራቸው ፡፡ አዎው አንዳንድ ጊዜ አፍህን መዝጋት እና ምክርን ከመለገስ መቆጠብ በእርግጥም ምርጡ ጥበብ ነው ፡፡ ዛሬ አስተውል በተጨማሪም የምታስበውን ሁሉ አትናገር በማህበራዊ ሚድያ አስተያየቶችህ ፣ ዜናዎችህ ወይም መልእክቶችህም ጭምር ፡፡ የሆነ ነገር ከማለትህ በፊት ቆም በል ፣ ዝም በል እናም ሌላ ጊዜ ከምታደርገው በተለየ መልኩ ለረጅም ጊዜ አድምጥ ፡፡ አሳብህን የመናገር ግዴታ እንደሌለብህ አውቀህ ፣ በዚህ እውነት እረፍ ፡፡ እግዚአብሔር ሉአላዊ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ያያል ፡፡ ከምትናገረው ራስህን መቆጣጠርን ካስለመድክ በሁኔታው ላይ እግዚአብሔርን እንድሰራ ታስችለዋለህ ፡፡ ስለዚህ ኢዮብ እንዳለው “ ዝም በልና ዝምታው ጥበብህ ይሁን ፡፡ “

“ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ! ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር ። “

  • ኢዮብ 13፡5

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ17:28 — “ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቈጠራል፥ ከንፈሩንም የሚቈልፍ፦ ባለ አእምሮ ነው ይባላል ። “

ምሳሌ 18:2 — “ሰነፍ የጥበብን ነገር አይወድድም፤ በልቡ ያለውን ሁሉ መግለጥ ብቻ ይወድዳል እንጂ ። “

ያዕቆብ 1:19 — “ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን ፡፡ “