Wisdom Books Job

"You Deserve Worse."

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 371 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሙሉ የችግር፣ የቅሬታና የወዳጁቹ ሳምንት ነው ፡፡ ዛሬ ምን እንደሚሆን ገምቱ ? ሌለኛዉ ወዳጁ ኢዮብን እንዳልወደደዉ ይነግረዋል ፡፡ የተነጋገርንበት የመጀመሪያዉ ሰዉ ስለ ኤልፉዝ ነበር ከዚያም ከኢዮብ ወዳጅ ከበልዳዶስ መስማታችንን አስታዉሱ ፡፡ በመፅሀፍ እዚህ ስፍራ ላይ ኢዮብ በቁስል፣ በህመም የተሸፈነ እንደ ነበር እና ከወዳጆቹም ጋር ስሜቱን እየተጋራ እንደ ነበር በደንብ አስታዉሉ ፡፡ በሚከተሉት ፅሁፎች እንዴት ሶፋር ምላሽ እንደ ሰጠ እናያለን ፡፡

ሶፋር በኢዮብ መፅሀፍት ላይ ሁለት ንግግሮችን አድርጓል/ሰጥቷል ፡፡ ማክአርቱር “ የመጀመሪያዉ ንግግር ኢዮብን በእግዚአብሄር ልክ እንዲሆን መናገር (ኢዮብ 11፡ 1-20) ፤ ሁለተኛዉ ንግግር ፍትሁን በመጠየቅ እግዚአብሄርን በመተዉ ኢዮብን መክሰስ (ኢዮ 20፡ 1-29) “ እንደ ሆነ ፅፏል ፤ በተጨማሪም “ አሁን ነዕማታዊዉ ሶፋር ኢዮብን በመመርመር ላይ መቀጠሉን ፤ ጓደኛዉን በመቅረብ በተመሳሳይ የበቀል ህግ ኢዮብንለመጉዳት በመምረጥ በጣም የቀረበ እንደ ነበር ፤ ሰማያዊዉን እዉነት ስለማትረዳዊ ኢዮብ ንስሃ መግባት አለ እንዳለ “ ፅፏል ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (11፡ 1-6)፡ ኢዮብ ለማጥናት ጠንካራ መፅሀፍ ነው ፡፡ በሰዉ ስቃይ ላይ እና የኢዮብ ወዳጆች ደግመዉ ደግመዉ ስህተት ሰርቶ እንደ ነበር ሲነግሩት እየተመለከትን ነው ፡፡ የሆነ ስፍራ ላይ አንድ ሰዉ ኢዮብን ያፅናናዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ፤ ነገር ግን ማንም የለም ! ኮንስታብል “ ሶፋርን ያስጨነቁትን ስለ ኢዮብ አራት ነገሮች ፅፋል፡ ቃል ማብዛቱ/ለፍላፊነቱ (ቁጥር 2)፣ ፉከራዉ (ቁጥር 3)፣ የራሱ ፅድቅ (ቁጥር 4) እና ቸልተኝነቱ (ቁጥር 5) “ ፡፡

ኢዮብ በጠቅላላ በመፅኀፉ ዉስጥ ንፁህ ሆኖ መቆየቱን ማስተዋል አስፈላጊ ነገር ነው ፤ ፍፁም ነበር ማለት አይደለም (ኢዮ 7፡ 21፣ 13፡ 26) ፡፡ ኢዮብ ያን ካርድ አልተጫወተም ፤ ሶፋር ኢዮብን እንደጥፋተኛ በማድረግ የዳኝና የአስተዳዳሪ ተግባርን እየተጫወተ ነበር ፡፡

ኢዮብ (11፡ 7-12)፡ ሶፋር ለእግዚአብሄር ጥበብ ምስጋና ሰጠ ፤ በዚህ መፅሀፍት ጥቅሶች ዉስጥ የጠየቃቸዉ ጥያቄዎች አስደንጋጭ ነበሩ ምክንያቱም ማንም ሊረዳቸዉ የማይችሉ ነገሮች ስለ ነበሩ ፡፡ ሶፋር የእግዚአብሄርን እቅድ እንደተረዳ፣ ምክንያቱን እና እዉነቱን እንደተረዳ የሚያስብ በግሉ በጣም የፀደቀ ነበር ፤ ሶፋር ጠንካራ አስተምሮና መንፈሳዊ ትምህርት ነበረዉ ነገር ግን ለኢዮብ ፍቅርን ባለማሳየቱ የተሳሳተ አተገባበር ነበረው ፡፡ የሚያደርገዉ ሁሉም ነገር ለኢዮብ እግዚአብሄርን ምንያክል ያዉቀዉ እንደ ነበር ለማሳየት ፈልጎ ነበር ፤ በተዘዋዋሪያ ሶፋር ኢዮብን የማታዉቅ ብሎ እየተናገረዉ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የኢዮብ ባዶ/ትርጉም የለዉ ንግግር ባዶ ጭንቅላት እንደ ሆነ የሚያመለክቱ ነዉ እያለ እንደሆነ (ቁጥር 2-21) “ ይገልፃል ፡፡ ምንም ይሁን ምንም ይህ ሰዉ ማን ነበር ? እስካሁን ለኢዮብ ክፉዉ ነበር ፡፡

ኢዮብ (11፡ 13-20)፡ ሶፋር ለኢዮብ ለመነ ፡፡ በሌላ ቋንቋ ኢዮብ መቀየር ከፈለገ ወደ ሙሉ ለዉጥና ንስሀ የሚመሩ አራት ነገሮችን ማድረግ ያስፈልገዋል ፤ በእነዚህ ነገሮች ላይ ስንመለከት እንደ እዉነትና መርህ ለመዉሰድ አስቸጋሪ ነዉ ምክንያቱም ከአንድ ሰዉ/ከሆነ ሰዉ ክብር የመጣ ስለሆነ ፡፡ በተሳሳተ አስተሳሰብ የመጡ ቢሆኑም ስለ እነዚህ ነገሮች ትክክል ነበር ፤ ኢዮብ ለንስሀ የሚያስፈልጉት አራት ነገሮች እነዚህ ናቸው፡

  1. “ ልብን ወደ እግዚአብሄር በመመለስ “ ፤ ይህን የማስቀመጥ ሌላዉ መንገድ ለእግዚአብሄር ልብን በሙሉ መስጠት ነው ፡፡ ለእግዚአብሄር እንዴት ልባችሁን የተሰጠ ታደርጉታላችሁ ? ህይወታችሁን በእግዚአብሄር ቁጥጥር ስር መተው (ምሳ 3፡ 5-6) ፡፡ በእግዚአብሄር ስትታመኑ በራሳችሁ ማስተዋል አትደገፉም፣ ነገሮችን በራሳችሁ ለመሳል አትሞክሩም ፤ ይህ ፍርድን በመጫወት ሙሉ ጊዜዉን የእግዚአብሄርን እቅድ ለመሳል ሲሞክር ለነበረው ለሶፋር ይህን ሀሳብ ለማድረግ ቀልድ እንደ ሆነ ነዉ የማስበው ፡፡
  2. “ በፀሎትና በይቅርታ ወደ እርሱ እጆቻችሁን ማንሳት “ ፤ እጆቻችሁን በማንሳት ፀሎት የምታደርጉት መቼ ነው ? እሞክረዋለሁ ! ሶፋር እንደ ነበረዉ እንደ እብድና ራስን እንደ ማፅደቅበእግዚአብሄር ላይ አይንን ስለመጠበቂያ መንገዶች እዉነት ተናገረ ፡፡ እጆችን ማንሳት የመለቀቅና የመታዘዝ ምልክት ነው ፡፡
  3. “ ኃጢዓታችሁን አርቁ “ ፤ በህይወታችሁ ኃጢዓት ካለ አስወግዱት ! በኃጢዓት ለመያዝ ወይም ላለመያዝ የምንፈልግ ከሆነ መወሰን እንችላለን ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ባህል በአንዳንድ ምክንያቶች ኃጢዓታችንን መደበቅ እንደምንችል እናስባለን ፡፡
  4. “ በድንኳናችሁ ኃጢዓትን አትፍቀዱ “ ፤ በቤታችሁ የሚጓዘዉን የእግዚአብሄር እንዳልሆነ ነገሩን ጠይቁ ፤ ወደ መንፈስ ቅዱስ አዳምጣችኋል ?

እጃችሁን ወደ እግዚአብሄር አንሱ ! ሞኝነት አይሰማችሁ ፡፡ ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በልጦ በመገኘት እግዚአብሄርን ማመስገን ያስፈልገናል ፡፡ እነዚህ ታላቅ ቀላል መርህ ቢሆኑም ሶፋር ስራን መሰረት ያደረገ እምነት መጠቀሙን አልወደድኩትም ፤ ይህ ማለት 1, 2 እና 3 ካደረጋችሁ 1, 2 እና 3 ታገኛላችሁ ማለት ነው ፤ ነገር ግን በእነዚህ መርሆች ላይ ጥቅሙን እንመልከት ፡፡ ኮንስታብል “ እነዚህ ጥቅሞች ንፁህ ህሊና፣ ታማኝነትና አለመፍራት (ቁጥር 15)፣ ችግሮቹን መርሳቱ (ቁጥር 16)፣ ደስታ (ቁጥር 17)፣ ተስፋና እረፍት (ቁጥር 18)፣ ሰላም፣ እዉቅና፣ መሪነትና ደህንነት (ቁጥር 19) “ እንደ ነበሩ ፅፏል ፡፡ የሁሉን ቻይ አምላክ ነፀብራቅ የሆኑትን እነዚህን ጥቅሞች ሰዎች ለምን እንደማይፈልጉ አላዉቅም ፡፡ እነዚህን ጥቅሶች መጥኖ ያጠቃለለበትን ታላቅ ንግግር ከማክአርቱር ማንበብ እፈልጋለሁ ፡፡

“ ኢዮብ ንስሀ ባይገባ ይሞታል ፤ ሶፋር የእምነት ህይወት በእግዚአብሄር ላይ በኃጢዓት ላይ በትክክለኛ ንስሀና መታዘዝ ላይ የተመሰረተ ነዉ በማለቱ ትክክል ነበር ፤ እግዚአብሄር ሰዎችን በተስፋ፣ በሰላምና በደህንነት ይባርካል ማለቱም ትክክል ነበር ፤ ነገር ግን እንደ ወዳጆቹ እግዚአብሄር የማይጠበቅና ፍትሀዊ/ተገቢ የማይመስል መከራን በማይታወቅ ምክንያት በምድር ላይ ማምጣቱን ባለመረዳቱ ስህተት ነበር ፤ ለኢዮብ መልሱ ንስኃ ብቻ ነበር ብሎ መገመቱ ስህተት ነበር “ ፡፡

ሶፋር ክርክሩን በተዘዋዋሪያ ኢዮብን ክፉ/የተረገመ ብሎ በመጥራት ዘጋ ፡፡ ኮንስታብል “ የኤልፉዝ ስልጣን ግላዊ ልምድ ሲሆን፣ የበልዳዶስ ደግሞ ልምድ/ወግ ላይ የተመሰረተ ሲሆን የሶፋር ደግሞ ተቋማዊ እንደሚመስል (20፡ 1-5) “ ፅፏል ፡፡ ያቋቋመዉ ተቋም/ስርዓት ስህተት ነበር ፡፡

መደምደሚያ

የኢዮብ ታሪክ የእብደት/ግራ የሚያጋባ ታሪክ ነው ! እነዚህ ሰዎስት ወዳጆቹ መልካምና መጥፎ አሳብ ነበራቸዉ ለማለት እፈልጋለሁ ነገር ግን ጥረታቸዉ በእርግጠኝነት ከመጥፎ የተነሳ ነው ፤ ሁሉም ማረጋገጫዎቻቸዉና ምክሮቻቸዉ በእዉነት ላይ የተመሰረቱ እንጂ በፍቅር አይደሉም ፡፡ ኤፌ (4፡ 15) “ ነገር ግን እዉነትን በፍቅር እየያዘን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ “ ይላል ፡፡ እንደ ክርስቶስ ለመሆን የምናድግበት ያ ነው ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 578.

  2. MacArthur, p. 577.

  3. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Study Notes: Job (Sonic Light, http://planobiblechapel.org/soniclight/, 2017), p. 55.

  4. Constable, p. 56.

  5. Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 624.

  6. Constable, p. 56.

  7. MacArthur, p. 578.

  8. MacArthur, p. 578.

  9. MacArthur, p. 578.

  10. MacArthur, p. 578.

  11. MacArthur, p. 578.

  12. Constable, p. 56.

  13. MacArthur, p. 578.

  14. Constable, p. 56.

ጥያቄዎች

  1. የሶፋር አስተምሮት ትክክል የነበረዉና አተገባበሩ ስህተት የነበረዉ እንዴት ነበር (ኢዮ 42፡ 7) ? በኢዮ (2፡ 1) መሰረት በመጀመሪያ ሌሎቹ ሁለቱ ለማድረግ አቀዱ ? ሶፋር ምን ሊል ቻለ ወይም በተለዬ ለምን በተለዬ ጨረሰ ?
  2. ሶፋር ለኢዮብ የገለፀዉ ተስፋ ምን ነበር ? ሶፋር ኢዮብን በኢዮ (11፡ 13-20) የተገለፀዉን በረከት ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለበት ነገረው ? እንደ ኢዮብ ሁኔታ ምክሩ ስህተት ወይስ ትክክል ነበር ?
  3. የንፁሁ ኢዮብ መዘለፍ ወደ ንፁሁ ኢየሱስ መዘለፍ እንዴት ያመለክታል ? (ማቴ 27፡ 29, 41, ማር 15፡ 27-31)
  4. ከሕዝቦችና ከነገስታት ጋር እንዳለዉ ግንኙነት ስለ እግዚአብሄር እና ስለ ሉዓላዊነቱ ኢዮብ የነበረዉ መረዳት ምን ነበር (ዳን 2፡ 20-22, ሐዋ 17፡ 24-28) ? በመፅኀፍት ዉስጥ ሰዎች ከእግዚአብሄር ዉጪ የሆነ ነገር ለመስራት የሞከሩበት ሌላ ጊዜ አለ ? (ዘፍ 4፡ 16-18, 11፡ 1-9, መዝ 127፡ 1) ዉጤቱ ምን ነበር ?
  5. በኢዮብ (11-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 11:13–15

“As for you, if you redirect your heart and lift up your hands to Him in prayer—if there is iniquity in your hand, remove it, and don’t allow injustice to dwell in your tents—then you will hold your head high, free from fault. You will be firmly established and unafraid.”

የኢዮብ ሶስተኛው ጓደኛ ሶፋር ለኢዮብ ህመምና ስቃይ በጥበብ የመጽሀፍ ቅዱስን እውነት ተናገረ ፡፡ ሆኖም ግን ሶፋር ኢዮብ ንስሀ መግባት እንደማያስፈልገው አላወቀም ነበር ፡፡ ሶፋር የኢዮብን ልብ አላወቀም ነበር ፡፡ እግዚአብሔር ብቻ ነበር የኢዮብን ልብ እንድሁም ደግሞ የመከራውን ምክንያት የሚያውቀው ፡፡

እግዚአብሔር ብቻ ልብህን ያውቃል ፡፡ ስቃይህን ያያል ደግሞም የልብህን አሳብ ያውቃል ፡፡ ሆኖም ግን በመከራ ውስጥ ከሆንክ ልታስተውላቸው የሚገቡ ተግባራዊ ምክሮችን ሶፋር አስቀምጧል ፡፡ ጌታን ጠይቅ ምናልባት እነዚህ ተግባራዊ እርምጃዎች ለአንተ ከሆኑ ፡፡ ልብህን ወደ ጌታ መልስ ፡፡ በቃ ለጌታ መማረክህንና ለእርሱ ተገዥ መሆንህን ለማግለጽ እጆችህን ወደ ላይ አንሳ ፡፡ ከህይወትህ የትኛውንም ኃጢአት አስወግድ ከአንተም አርቀው ፡፡ በቤትህ ውስጥ ለየትኛውም አይነት የኃጢአት ፈተና አትፍቀድ ፡፡ ዛሬ ጌታ እንደመራህ እነዚህን ነገሮች ለማስተካከልና እንድሁም እርምጃ ለመውሰድ ጊዜን ውሰድ ፡፡ ይህን ስታደርግ ጌታ ከአንተ ጋር ይሆናል ፡፡ ምንም እንኳ አሁንም መከራ እያሳለፍክ ቢሆን ፤ በእነዚህ ከባድ ቀናት ሳይቀር እግዚአብሔርን በንጹህ ልብ ስትሻ ተስፋ ፣ ደስታ ፣ ድፍረትና ነጻነትን ታገኛለህ ፡፡

“በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው ፤ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፤ አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ ፥ በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፤ ትበረታለህ ፥ አትፈራምም ። “

  • ኢዮብ 11፡13-15

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 28:2 — “ወደ መቅደስህ ማደሪያ እጄን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ ። “

2ኛ ጢሞቴዎስ 2:21 — “እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል ። “

2ኛ ጢሞቴዎስ 4:5 — “አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም ። “