Needing a Mediator
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለኢዮብ መፅሀፍ የሜንዲ ስዕል ከሌሎቹ አንዳንድ መፅኀፍት የጨለመ ነው ፡፡ ኢዮብ ገጥሞት ወደ ነበረዉ ችግር/ስቃኝ እና እንዴት ችግሮች እኛላይ እንደሚሆኑብን ለምን ብለን እንድንጠይቅ በትክክል ያሳያል ፤ በተጨማሪም ወደ መፅሀፉ ሀረግ/ቃል - ተስፋ የተገባ ተቤዢ ወደ ሚለዉ ይጠቁመናል ፡፡ መካከል ላይ ማዕበል እያለ ሁል ጊዜ ተስፋ አለ ፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩት የኢዮብን ወዳጆች አይተናል ፡፡ ዛሬ በምዕራፍ (9-10) ኢዮብ ላይ እየሆነ ስለ ነበረዉ ነገር በበልዳዶስ ገለፃ ላይ እና ለበልዳዶስ የኢዮብ መልስ ላይ እናተኩራለን ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (9፡ 1-13)፡ ኢዮብ በልዳዶስ አንዳንድ ጥሩ ነጥቦች እንዳደረገ አረጋገጠ (ቁጥር 1-2) ፤ ይሁን እንጂ ኢዮብ ማንኛዉም ለፍርድ በእግዚአብሄር ፊት የተወሰደ ከአንድ ሺዉ አንድ እንኳን የእግዚአብሄርን ክስ መመለስ አይችሉም (ቁጥር 3) ምክንያቱም እግዚአብሄር አስተዋይና ኃያል ስለሆነ (ቁጥር 4) በማለት ጠቆመ ፡፡ ኢዮብ ማንም እግዚአብሄርን እንዳልተቃወመና ከጉዳት እንዳልወጣ/እንዳላመለጠ ተናገረ ፡፡ ዙክ ኢዮብ እግዚአብሄርን ወደ ፍርድ መዉሰድ ጥቅም እንዳልነበረዉ ለምን እንደተረዳ አራት ምክንያቶችን ይሰጣል፡ 1) እግዚአብሄር ኃያል ነው (ኢዮ 9፡ 3-14)፣ 2) እግዚአብሄር ለቅሶዉን ማስወገድ ስለሚችል እና ከእርሱ ተቃራኒም መሆን ስለ ሚችል (ኢዮ 9፡ 15-19)፣ 3) እግዚአብሄር ንፁሀንንና ክፉዎችን ሁለቱንም የማጥፋት ስልጣን ስላለዉ (ኢዮ 9፡ 20-24) እና 4) ኢዮብ ችግሩን ለመርሳት ወይም ኃጢዓቱን ለመናዘዝ ቢሞክርም እግዚአብሄር አሁንም ጥፋኝነት ስለሚያገኝበት (ኢዮ 9፡ 25-32) ፡፡ ኢዮብ የእግዚአብሄርን ኃይል ሳያዉቁት ተራሮች መነቃነቃቸዉንና መሬት በራሷ ምሰሶዎች እንደምትናወጥ በመግለፅ ቀጠለ (ቁጥር 5-6) ፡፡ እግዚአብሄር በፀሀይና በከዋክብቶች ላይ፣ በሰማያትና በባህር ሞገዶች ላይ እና በሰማይ ባሉት ህብረ ከዋክብት ላይ ስልጣን አለው (ቁጥር 7-9) ፡፡ እግዚአብሄር በመደነቅ የሚሞሉንን የማይታመኑ ነገሮችን ያደርጋል (ቁጥር 10) ፤ እግዚአብሄር በአጠገባችን ያልፋል ነገር ግን አንለየዉም ምንም ነገር ከማድረግም ልናስቆመዉ አንችልም (ቁጥር 11-12) ፤ እንዲሁም እግዚአብሄር ከቁጣዉ አይመለስም በፍራትም ሰዎች እንዲያለቅሱ ምክንያት ሊሆን ይችላል (ቁጥር 13) ፡፡
ኢዮብ (9፡ 14-24)፡ በብርሃን በእግዚአብሄር ታላቅነት ኢዮብ ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት ክርክር ሊኖረዉ እንደሚችል ጠየቀ (ቁጥር 14) ፤ ምንም እንኳን ኢዮብ ፃድቅ ቢሆንም እግዚአብሄርን ሊመልስበት እንደማይችል ያዉቃል (ቁጥር 15) ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄርን ቢጠራዉ ያለዉን እግዚአብሄር እንደሚሰማዉ አያምንም በአዉሎ ንፋስ እንደሚገረፍ እንጂ (ቁጥር 16-17) ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄርን መጋፈጥ ቢሞክር ነገሮች በደህና አይሄዱም - እግዚአብሄር በመራራ ነገር ያጠግበዋል እንጂ (ቁጥር 18) ፤ ኢዮብ እንደ ገና የእግዚአብሄርን ጥንካሬና ፍትሀዊነት በመጠቆም በራሱ አንደበት በሁሉን ቻዩ እግዚአብሄር ፊት ጥፋተኝነቱን እንዳመነ ተናገረ (ቁጥር 19-20) ፡፡ ኢዮብ እንከን የሌለበት እንደነበር ነገር ግን እንከን የሌለበትንና ክፉዉን ሁለቱንም ከሚያጠፋዉ (ቁጥር 22) ከእግዚአብሄር ኃይል ጋር በተጋፈጠ ጊዜ ህይወቱ መቀጠሏ ችግሩ እንዳልሆነ ገለፀ (ቁጥር 21) ፡፡ ኢዮብ ጥፋት ፈጣን ሞት ሲያመጣ እግዚአብሄር በንፁሀን ይሳለቃል (ቁጥር 23) ፡፡ ምድር ለክፉዎች ትሰጣለች እግዚአብሄርም ፈራጆቿን ይሸፍናል (ቁጥር 24) ፡፡
ኢዮብ (9፡ 25-35)፡ ኢዮብ ህይወቱ ምንም መልካም ነገር ሳታይ እየበረረች እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 25-26) ፤ አልፎበት የነበረዉን ሁሉንም ነገር ለመርሳት ቢሞክር እግዚአብሄር ሊተወዉ እንደማይችል ስለሚያዉቅ በህመሙ ፍርኃት እንደሚኖርና (ቁጥር 27-28) ጥፋት እንደሚያገኝበት ተናገረ (ቁጥር 29) ፡፡ ኢዮብ በእግዚአብሄር ፊት ቆሻሻነቱ በጣም መጥፎ ነበር ልብሱም እንደሚፀየፈዉ ተናገረ (ቁጥር 30-31) ፤ ኢዮብ እግዚአብሄር እርሱ እንደ ነበረዉ አይነት ሰዉ ስላልነበር በመካከላቸዉ ሊዳኛቸዉ የሚችል ሰዉ እንደሌለ ተረዳ (ቁጥር 32-33) ፤ በእግዚአብሄርና በኢዮብ መካከል ድልድይ አልነበረም ፡፡ ኢዮብ የእግዚአብሄርን በትር ከእርሱ ላይ እንዲወሰድ ፈለገ ስለዚህም የእግዚአብሄር ማስፈራት ብዙ አያስፈራዉም ፤ ኢዮብን ጉዳዉን ከሚያግዘዉ መካከለኛ ዉጪ ብቻዉን ነበር (ቁጥር 34-35) ፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን ተስፋ መቁረጣችን መካከል ላይ ኢየሱስን መካከለኛ/አስታራቂ ሰጠን (1ጢሞ 2፡ 5) ፡፡
መደምደሚያ
አስታራቂ ለምን አስፈለገን የእግዚአብሄር አስታራቂስ በመፅሀፍት እንዴት ተገልጧል ?
1ጢሞ (2፡ 5-6)፡ ሰዉ በመሆን ራሱን እንደ ቤዛ የሰጠን ክርስቶስ የእግዚአብሄር አስታራቂ/መካከለኛ ነበር ፤ ሁላችንም የፍርድ ቦታ ላይ ይገጥመናል በመካከለኛችን በኢየሱስም እንወከላለን ፡፡
ኢሳ (64፡ 6)፡ ሁላችንም እንደረከሰና እንደቆሸሸ ነገር በመሆን ኃጢዓታችን ልክ እንደ ንፋስ ከቦታ ወደ ቦታ ይወስደናል ፡፡
ዕብ (9፡ 15)፡ ኢየሱስ ሞት በቤዛነት በመተካቱ ምክንያት ተስፋ ለተሰጠዉ የዘላለም ርስት የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ሆነ ፡፡
1ጴጥ (3፡ 18)፡ ወደ እግዚአብሄር ሊያመጣን ኢየሱስ ስለሁላችን ኃጢዓት መከራን ተቀበለ ፡፡
ጉዳያችንን ስለ ድነታችን ለማድረግ በፍርድ ፊት ከሄድን ልንከተለዉ የምንችለዉ መንገድ አለን፡
- ሮሜ (3፡ 23)፡ ሁሉም ኃጢዓተኞች ናቸዉ የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሏቸዋል ፤ የእግዚአብሄርን ክብር በፍፁም አናሟላም ፡፡
- ሮሜ (6፡ 23)፡ የኃጢዓት ደሞዝ ሞት ነው ፤ የእግዚአብሄር ስጦታ ግን የዘላለም ህይወት ነው ፡፡
- ሮሜ (5፡ 8)፡ ነገር ግን ገና ኃጢዓተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሄር ለእኛ ያለዉን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ፡፡
- ኤፌ (2፡ 8-9)፡ በእግዚአብሄር ፀጋ ድነናል እንጂ በማንኛዉም ስራችን አይደለም ፡፡
- ሮሜ (10፡ 9-10)፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ በልባችን ስንናገርና በልባችን ስናምንእንድናለን ወደ እግዚአብሄርም ሙሉ መደረስ ይኖረናል ፡፡
- 2ቆሮ (5፡ 21)፡ ያለኃጢዓት የነበረዉ ኢየሱስ የእኛን ኃጢዓት በመዉሰድ በእርሱ የእግዚአብሄር ፅድቅ መሆን ቻልን ፡፡
በመካከለኛዉ በኩል እግዚአብሄር እንዴት ህይወታችሁን ቀየረው ? ዕብ (8፡ 6) ኢየሱስ የተሸለ ኪዳን የላቀ መካከለኛና የተሸለ ተስፋ የመሰረተ ነው ይላል ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 623.
Roy B. Zuck, Everyman’s Bible Commentary: Job (Chicago: Moody Press, 1978), p. 47; quoted by Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Study Notes: Job, p. 50; available at https:// planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.
ጥያቄዎች
-
በአንፃራዊ ሁኔታ እና በትክክለኛ ሁኔታ ስለፅድቅ መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይናገራል ? (ዘፍ 7፡ 1, ኢዮ 1፡ 1, ሮሜ 5፡ 19)
-
እንደ ፈጣሪ እየተረዳችሁት እያለ በኢዮ (9፡ 9-11) ስለ እግዚአብሄር እንዴት ተሰማችሁ ? በህይወታችሁ እግዚአብሄር የራቃችሁ የሚመስላችሁ ጊዜ መቼ ነው ?
-
በምዕራፍ 9 ኢየሱስን የናፈቀ ሲመስል የት ላይ ታዩታላችሁ ? እንደ መካከለኛ በእግዚአብሄርና በሰዉ መካከል ኢየሱስ ምን አደረገ ? (ዮሐ 14፡ 7-11, 1ጢሞ 2፡ 5, 1ጴጥ 3፡ 18)
-
ኢዮብ 10 እግዚአብሄር እንደ ፈጠረን እንዴት ግልፅ ያደርገዋል ? መፅሀፍ ቅዱስ ይህን ሌላ የት ላይ ግልፅ ያደርገዋል (መዝ 119፡ 73, 139፡ 13) ? ይህን እዉነት ማወቅ እንዴት ይታገላችኋል ?
-
በኢዮ (10፡ 15-22) ኢዮብ እንዳደረገዉ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በእነዚህ ጊዜያት ጊዜ አጥብቃችሁ ልትይዙት የምትችሉት ነገር ከእግዚአብሄር ምን ተስፋ ተሰጥቷችኋል ? (ዕብ 13፡ 5)
-
በኢዮብ (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 9:2
“Yes, I know what you’ve said is true, but how can a person be justified before God?”
ኢዮብ በመከራ ታግሶ ለበልዳዶስ መለሰ ፡፡ ኢዮብ ይህን ጥያቄ ጠየቀ ፡- “ እንዴት ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን ይችላል ? “ እናም ከዚያ በስቃዩ መሀል ሁኖ ሳለ እንኳ ኢዮብ ለእግዚአብሔር ባህርይ እውቅና መስጠቱን ቀጠለ ፡- እግዚአብሔር ጠቢብ ነው ደግሞም ኃያል ነው ፡፡ ተራሮችን ይነቅላል፤ አያውቁትምም ፡፡ ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል ። የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥
የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል ። በስቃይ ውስጥ ሳለ እንኳ ፣ ኢዮብ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ይናገር ጀመር ፡፡
እግዚአብሔር እንደዚህ ያለ ድንቅ አምላክ ከሆነ እና አንተ እንዴት ነው በፊቱ ልትጸድቅ የምትችለው ? እንዴት ነው በእግዚብሔር ፊት የምትቀርበው ? መልሱ የምንጠብቀው ቤዛችን ኢየሱስ ነው ፡፡ ኢየሱስ አስታራቂህ ነው ፡፡ እርሱ ወደ ምድር መጥቷል ስለዚህም ራስህን በእግዚአብሔር ፊት መከላከል አይጠበቅብህም ፡፡ ኢየሱስ ከኃጢአት ነጻ ሊያወጣህ መጥቷል ፡፡ እርሱ ከእግዚአብሔር ለአንተ እንድትቀበለው ስጦታ ሁኖ መጥቷል ፡፡ ኢየሱስን ወደ ህይወትህ ስትቀበል ከእርሱ ጋር ተመላለስ ፤ አይኖችህንም በእርሱ ላይ አድርግ እናም እርሱ ህይወትህን ይለውጣል ፡፡ ኢየሱስን የግል አዳኝህና ጌታህ አድርገህ ካልተቀበልክ እና ነገር ግን ኃጢአተኛ እንደሆንክ ካመንክ እና ያለምንም ዋጋ በክርስቶስ መጽደቅ ከፈለክ እርሱን ዛሬ ተቀበል ፡፡ ለጌታ “ ኢየሱስ ከሞት የተነሳኸው መሲህ በአንተ አምናለሁ ፤ ህይወቴን ለአንተ እሰጥሀለሁ ፡፡ አንተን አዳኜ እና አማላጄ አድርጌ እቀበላለሁኝ ፡፡ “ ኢየሱስ ህይወትህን እንድቆጣጠር ስትለምነው በመከራ ውስጥ ሆነህ እንኳ በውስጥህ ባለው በእርሱ ተስፋ መቆም ትችላለህ ፡፡ እግዚአብሔርን ስለ ድንቅ በረከቱ አመስግነው ፡፡
“በእውነት እንዲህ እንደ ሆነ አወቅሁ ፤ ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል ? “
- ኢዮብ 9፡2
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ3:23-24 — “ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል ፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ ። “
1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5-6 — “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ፤ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ ፡፡ “
ዕብራውያን 9:15 — “ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።