Wisdom Books Job

The Threat of Traditions

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 369 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እስካሁን በኢዮብ ችግር ላይ እና በኢዮብ ችግር ጥሩ ስሜት ተሰምቷቸዉ ባልነበሩት ብዙ ሰዎች ላይ ተመልክተናል ፡፡ ኢዮብ አንድኛዉንም መከራ/ችግር አልወደደዉም ነገር ግን ሁሉም ችግሩ ኃጢዓት በመስራቱ ምክንያት እንዳልነበር እንዲረዱት ፈለገ ፡፡ የኢዮብ ወዳጆች ለምን በነበረበት ሁኔታ እንደ ነበር ስለሚያስቡት በብዙ በቃል ብቻ የነበሩ ጥቂቶች ነበሩ ፡፡ እስካሁን በኤልፉዝ ምላሽ ላይ ተመልክተናል ፤ ከዚያም ኢዮብ ለኤልፉዝ በምዕራፍ 6-7 ምላሽ ሰጠው ፤ ቀጥሎም የኢዮብ ሁለተኛዉ ወዳጁ በልዳዶስ ኢዮብን ተናገረው ፡፡ ለኢዮብ መፅኀፍ ሐረጋችን ተስፋ የተገባ ተቤዢ ነው፣ ያም ተስፋ ኢዮብ ወድቆበት/ገብቶበት ከነበረዉ ሁኔታ መዉጣት የሚያገኝበት ነው ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (8፡ 1-7)፡ የአብርሃም ዘመድ በልዳዶስ ኢዮብን እንደ “ ዉሸታም/ወሬኛ “ እንደ ሆነ ሰዉ ከሰሰዉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የበልዳዶስን አስተያዬት ኢዮብን “ ወሬ የሚያሞቅ “ እንደ ነበር ብሎ እንደ ተናገረው ይገልፃል ፡፡ በልዳዶስ ኢዮብ ከእግዚአብሄር የማይገባዉን ምንም ነገር እያልተቀበለ እንደ ነበር ሊቀበለዉ አልቻለም (ቁጥር 1-3) ፤ በልዳዶስ የኢዮብ ልጆች ተቀጡ ምክንያቱም በእግዚአብሄር ላይ አምፀዉ ስለ ነበር አለ (ቁጥር 4) ፡፡ እነዚህ ቃላቶች በእግዚአብሄር እንዲጓዙ ልጆቹን ለመጠበቅ ሁሉንም ነገር አድርጎ ለነበረው ለኢዮብ ያስደነግጣሉ ፡፡ ቡልሎክ “ በግልፅ የወዳጆቹ አስተምሮ ከኢዮብ ይበልጥ በብዙ የሚያስፈልግ እንደ ነበር “ ጠቁሟል ፡፡ በልዳዶስም ሁለት ነገሮችን እንዲያደርግ ነገረው - በቅንነት እግዚአብሄርን በመፈለግ ስለ ምህረቱ በመጠየቅ ንፁህ እና ቋሚ መሆን ይህ ከሆነም እግዚአብሄር ብልጥግናዉን ይመልሳል (ቁጥር 5-7) ፡፡ ይህ እንደ ገና ኢዮብ የሆነ ነገር ቢያደርግ ባደረገዉ ነገር ምክንያት እግዚአብሄር ወዲያዉኑ ይባርከዋል ብሎ የሚያምንበት የበልዳዶስ መጥፎ እምነት ነበር ፡፡

ኢዮብ (8፡ 8-10)፡ በልዳዶስም ንግግሩን በታሪክ ማስረጃ ለማስደገፍ ቀጠለ ፤ በልዳዶስ ወደ ቀደሙት ትዉልዶች እና አባቶቻቸዉ ስለ መረመሩት ነገር ጠቆመ (ቁጥር 8) ፤ ይሁን እንጂ በልዳዶስ ምንም ነገር እንደማያዉቅ አሳወቀ/አረጋገጠ (ቁጥር 9) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በእዉነት ትንሹ በልዳዶስ እንዴት በማወቅ “ የኢዮብ መፅሀፍ አንዱ አላማው የቀድሞዉን የተለመደ ስርዓት መሟገት እንደሆነ - በተለይም ቅጣት ስለሚገባዉ ቅኖና/ስርዓት/ህግ “ ይናገራል ፡፡

መፅሀፍ ስለ ልምድ ምን ይላል ? በክርስቶስ ላይ እስከተመሰረቱ ድረስ ልምዶች መጥፎ አይደሉም ፡፡

  • ጸንቶ በመቆም ልምዶችን መያዝ (2ተሰ 2፡ 15) ፡፡
  • ማንም በፍልስፍና እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ/ተመልከቱት (ቆላ 2፡ 8) ፡፡
  • ስለ ልምድ ለምን ትዕዛዞችን ለምን ትጥሳላችሁ (ማቴ 15፡ 3) ?
  • በሁሉም ነገር ክርስቶስ በማስታወስ ባህልን/ወግን መጠበቅ (1ቆሮ 11፡ 2) ፡፡
  • ስለወጋችሁ የእግዚአብሄርን ቃል የተሻረ አደረጋችሁት (ማቴ 15፡ 6) ፡፡
  • የሽማግሌዎችን ወግ ጠበቁ (ማር 7፡ 3-9) ፡፡

ከወግ አንፃር “ የበልዳዶስ ስፍራ/አቋቋም እዉነት የሆነዉ አዲስ አይደለም አዲስ የሆነዉ ደግሞ እዉነት አይደለም ነው “ ፡፡ ታሪክ ፀሀፊዉ ጀሮስላቭ ፔሊካን “ ወግ የሞቱት ህያዉ እምነት እንደ ሆነ ወግ አጥባቂነት ደግሞ የሞተ የህያዉ እምነት እንደ ሆነ ይገልፃል “ ፡፡ በወግ ላይ እዉነት መኖር ን ይመስላል ? የእግዚአብሄር እዉነት የሰዉን ወግ ይፈጥራል/ይጣራል ፡፡

የኢየሱስ ንግግር የሰዉን ስልጣን በለጠ (ዮሐ 7፡ 48-49) ፤ ኢየሱስ ማን እንደ ነበር ፈሪሳዊያን አላመኑበትም ፡፡

የኢየሱስ ተግባራት (አጋንንትን እንደ ማስወጣት አይነቶቹ) የኃይማኖት መሪዎቹን አበሳጯቸው (ማቴ 12፡ 23-24) ፡፡

ኢየሱስ ለኃይማኖት ስርዓታቸዉ ስጋት ነበር (ዮሐ 2፡ 13-17) ፤ በቤተ መቅደስ ማገልገያ/ገበታ ላይ በወረወራቸዉ ጊዜ ያን ስጋት አሳይቷቸዋል ፡፡

ኢየሱስ ለኃይማኖታዊ ስርዓት መንገድ ህይወት የሚያስፈራ ነበር ፡፡

የኃይማኖት መሪዎችን በማበሳጨት ኢየሱስ ህዝቡን ተግባባ/አገኛቸው (ማቴ 11፡ 19, ሉቃ 7፡ 39) ፡፡

ለወግ/ለልማዳቸዉ ኢየሱስ አክብሮት አልነበረዉም (ማር 3፡ 4-5) ፡፡

ኢዮብ የመጣዉ ክርስቶስ አስገራሚ መልክ ነው ፡፡

ኢዮብ (8፡ 11-18)፡ በልዳዶስ እግዚአብሄር እንዴት ክፉዎችን እንደሚቀጣና ፃድቃንን እንዴት እንደሚባርክ መረዳቱን ለመደገፍ ከተፈጥሮ ብዙ ማሳያዎችን ተጠቀመ (ቁጥር 11-12) ፡፡ እያንዳንዱን ለማዳበር በዉጫዉ ምንጭ ላይ የተደገፈ ነበር ፡፡ በልዳዶስ እግዚአብሄር የሌላቸዉ ይጠፋሉ ምክንያቱም የሚያስፈልጋቸዉን እግዚአብሄርን ስለረሱ በማለት ጠቆመ/አመለከተ (ቁጥር 13) ፤ እግዚአብሄርን የረሱ ለመደገፍ በቂ ባልሆነ በሸረሪት ድር ቤት ላይ ለመታመን ይሞክራል (ቁጥር 14-15) ፡፡ በልዳዶስም ኢዮብን በሚገባ ስር ለመስደድ ሁሉም ነገር ተትረፍርፎለት ከነበረው በሚገባ ዉኃ ከጠጣ አንድ ዛፍ ጋር በማወዳደር አሁን እግዚአብሄርን አያዉቅም (ቁጥር 16-18) ፡፡ በእነዚህ ቁጥሮች እያለ ያለዉ ኢዮብ ከእግዚአብሄር ይልቅ በኃብቱ ተደግፎ ነበር ነው ፡፡

ኢዮብ (8፡ 19-22)፡ ኢዮብ ላይ የደረሰበት ያሁሉ ነገር እያለ በልዳዶስ የእግዚአብሄር በረከት ተስፋ እንደ ነበር ጠቆመ (ቁጥር 19) ፤ ነገር ግን በልዳዶስ እግዚአብሄር በፍፁም ፍፁምን ሰዉ እንደማይተው በመናገር በኢዮብ ላይ ፍርድን አስቀመጠ (ቁጥር 20) ፡፡ በገጠመዉ ዉስጥ ሁሉ ኢዮብ ፍፁም ሰዉ እንደ ነበር ወደ እዉነቱ የተሰቀለ ነበር ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ወደ ኢዮብ ህይወት ደስታን በማምጣት (ቁጥር 21) የኢዮብን ጠላቶች የእፍረት ልብስ ያለብሳቸዋል (ቁጥር 22) ፡፡

መደምደሚያ

ኮንስታብል “ ሰዎች በችግሮች ከፅኑ አቋማቸዉ ትንሽ እርዳታ ያገኛሉ፣ በአዲስ ማስረጃ ብርሃን ቴዎሪያቸዉን እንደ ገና ለመመዘን እምቢ በማለት በቀላሉ እንደ ገና ወግን በመመለስ ሀሳብ የማይቀበሉት በልዳዶሶዎች እንደሆኑ ፅፏል ፤ በራሳችን ብቻ ሳይሆን የምንከተላቸዉምእዉነቶችን በትክክል ላንተረጉም ስለምንችል ሁሉ ጊዜ ለአዲስ ማስረጃ፣ ለአዲስ እይታ እና ዝንባሌዎች ክፍት መሆን እንዳለብን “ ይፅፋል ፡፡ አንደርሰን “ የበልዳዶስ ማረጋገጫ በተመሳሳይ እዉነት ኢየሱስን የዘለፉትን ግንባር ቀደም የሚያደርጉትን እንከን የሌሽ ሰዎች እግዚአብሄር እንደማያስወግዳቸዉ፡ በእግዚአብሄር እንደሚታመን፣ እግዚአብሄር ነፃ እንዲያወጣው እንደሚፈቅድ (ማቴ 27፡ 43) ፤ ኢዮብ ከጌታ ያነሰ ችግር/ስቃይ አለዉ፣ እያንዳንዱም ሰዉ የራሱ አለው ፤ ነገር ግን ኢየሱስን ስለ እግዚአብሄር መተዉ ስናዉቅ ግዴታችን እንደ ገና የኢዮብን ያክል በፍፁም ጨለማ ሊሆን እንደማይችል “ ፅፏል ፡፡ ከበልዳዶሶች ተጠንቀቁ ፡፡ p. 47; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

5 S. R. Driver and G. B. Gray, International Critical Commentary Series: A Critical and Exegetical Commentary on the Book of Job (Edinburgh: T. & T. Clark, 1921), p. 78; quoted in Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes: Job, p. 47; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

8 Francis I. Andersen, Tyndale Old Testament Commentaries: Job (Leicester, Eng. And Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1976), pp. 142-143; quoted in Thomas Constable, Dr. Con- stables Bible Study Notes: Job, p. 48; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  1. Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes: Job, p. 46; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 622.

  3. C. Hassell Bullock, An Introduction to the Poetic Books of the Old Testament (Chicago: Moody Press, 1979), p. 34; quoted in Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes: Job,

  4. Nelson’s Commentary, p. 623.

  5. Quoted in Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Job (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2004), p. 22.

  6. Constable, p. 49.

ጥያቄዎች

  1. በምዕራፍ 7 ኢዮብ ለመሞት በመጠየቅ አሁን ምንም ጥቅም እንዳልነበረው ተሰማው ፤ ኢዮብ እንደተፈተነዉ ማንም አልተፈተነም ነበር ፡፡ መከራዉና ፈተናዉ ለእኛ ጥቅም ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይም ለምን አይጠቅምም ?
  2. ሙሉ ለሙሉ ተስፋ ቢሰ መሆን ዝቅ አለ ስፍራ ላይ እንደሆናችሁ እና እግዚአብሄር እንደተዋችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? ዉጤቱ ምን ነበር ? በዚያን ጊዜ ዉስጥ ምን አገኛችሁ ?
  3. በኢዮ (7፡ 17) ኢዮብ “ ታከብረዉ ዘንድ ሰዉ ምንድን ነዉ ? “ በማለት ጠየቅ ይህ ተመሳሳይ ጥያቄ ሲጠየቅ ሌላ የት ላይ ትሰሙታላችሁ (መዝሙር 8፡ 4) ? ለዚያ ጥያቄ መልሱ ምን ይሆናላ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  4. በኢዮብ 8 በልዳዶስ ለኢዮብ ተናገረ ፤ ለኢዮብ ጥሩ ወዳጅ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አልሆነም ?
  5. በኤፌ (4፡ 29) የሚጠግን እንጂ የማያስለቅስ ነገር እንድንናገር ተነግሮናል ፤ ኢዮብ 8 ካነበባችሁ በኋላ በልዳዶስ የዚያ ጥቅስ ጥሩ ምሳሌ እንደሆነ ይሰማችኋል ? ለበልዳዶስና ለወዳጆቹ ጉዳዩ ምን ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ኢሳ 55፡ 8-9) ? እንደ በልዳዶስ አይነት ወዳጆች አሏችሁ ? በአሁኑ ጊዜ ማን ሊያበረታታችሁ ይችላል ?
  6. በኢዮብ 7-8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 8:8–9

“For ask the previous generation, and pay attention to what their fathers discovered, since we were born only yesterday and know nothing. Our days on earth are but a shadow.”

በልዳዶስ የኢዮብን ጊዜ በልማድ መነፅር መረመረው ፡፡ ኢዮብን ለህመምና ለስቃይ የዳረገውን ምክንያት በደንብ ሳያውቅ በልዳዶስ በልማዳዊ አስተሳሰብ መለሰ ፡- እግዚአብሔርን በቀናነት ከፈለከው ስለዚህ ምህረትን እንድያደርግልህ ጠይቀው ፡፡ እናም ንጹህ እና ትክክል ከሆንክ እግዚአብሔር ይመልስልሀል ፡፡ በልዳዶስ ማለት የፈለገው እግዚአብሔር ኢዮብን ከህመሙ ስላልፈወሰው ኢዮብ የሰራው የሆነ ኃጢአት አለ ነው ፡፡ ኢዮብ ለበልዳዶስ አመክንዮ የመለሰው እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ሉዓላዊ አምላክ እንደሆነ በመናገር ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንከን የሌለባቸው ንጹሀን እንድሁም ደግሞ ክፉዎች ህመምና ጥፋት ይደርስባቸዋል ፡፡ ምንም እንኳ ሁሉም ነገር መልሶ ወደ እግዚአብሔር ቢጠቁምም እርሱ ብቻውን አምላክ ነው ፤ እርሱ ብቻውን ሉዓላዊ ነው ፡፡

የበልዳዶስ ምላሽ ሁሉንም አጋጣሚዎች በተመሳሳይ መንገድ በማየት ልማድ ውስጥ ላለመግባት እንደ ማንቂያ ሆኖ ያገለግላል ፡፡ እያንዳንዱ መጥፎ አጋጣሚ ሁልጊዜ የተለየ ትርጉም አይኖረውም ፡፡ ሁልጊዜም በሆነ መደብ ላይፈረጅ ይችላል ፡፡ ነገር ግን አሁንም እግዚአብሔር ያያል ፤ እርሱ ልብን ያያል ፣ እርሱ አሳብን ያያል ፡፡ ሁሉንም እውቀት እርሱ ይዟል ፡፡ በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን እንድመራህ ፣ እንድመክርህና እውቀትን ሁሉ እንድሰጥህ ልኮታል ፡፡ ስለዚህም እውነት እንድሆን በምትፈልገው የተስፋ ቃል ውስጥ ስትመላለስ በእያንዳንዱ ሁኔታ እንድረዳህ መንፈስ ቅዱስን ፈልግ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በህይወትህ ሲሰራ እርሱ ስለ ክብሩና ነፍሳት ወደ መንግስቱ እንድፈልሱ ትእግስትንና ጥበብን ይሰጥሀል ፡፡ በእያንዳንዱ አድስ አጋጣሚ እግዚአብሔር እንድረዳህና እንድመራህ ጸልይ እንድሁም ደግሞ በመንገድህ ሁሉ እርሱ እንደሚመራህ እመን ፡፡

“ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውና እኛ የትናንት ብቻ ነን፤ ምንም አናውቅም፤ ስለዚህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥ አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትጋ ፡፡ “

  • ኢዮብ 8፡8-9

ተጨማሪ ጥቅስ

ማርቆስ7:5 — “ፈሪሳውያንም ጻፎችም፦ ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ ብለው ጠየቁት ። “

ዮሐንስ 16:13 — “ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል ። “

ቆላስይስ 2:8 — “እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ ። “