Job Responded
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ኢዮብ ከመፅኀፍ ቅዱስ አንዱ ትልቅ መፅኀፍ እንደሆነ የሚታሰብና እንደ ጥበብ ፅሁፍ የተከፈለ ነው ፡፡ ኢዮብ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንዴት እንደሚዳሰሱ በተግባራዊ መረጃዎች የተሞላ ነው ፡፡ የኢዮብ መፅኀፍ የመጀመሪያዉ ጥያቄ “ በችግር መካከል ላይ በእግዚአብሄር ትደገፋላችሁ ? “ ነው ፤ ነገር ግን ኢዮብም ለምን ችግሮች እንደሚገጥሙን ጥያቄዎችን አንስቷል ፤ አንዳንዶች በኃጢዓት ምክንያት ነዉ ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ ለማረም/ለማሰልጠን ሲሉ፣ አሁንም አንዳንዶች ችግርን ለእግዚአብሄር ለእኛ ፀጋዉንና መፅናናቱን እንዲያሳይ እንደ እድል ይመለከቱታል ፡፡
በትናትናዉ ትምህርታችን ኢዮብ ሁሉንም ነገሩን ማጣቱንና ጤናዉም ከሱ ተወስዶ እንደ ነበር በሰማ ጊዜ ሊጎበኘዉ የመጣዉ ከኢዮብ ወዳጆች አንድኛዉ ኤልፉዝ በምዕራፍ 3 ስለ ሁኔታው ለኢዮብ የመጀመሪያ ንግግር መመለስ ጀመረ ፡፡ በምላሹ በመጀመሪያዉ አካል ላይ ኤልፉዝ እግዚአብሄር ክፉዎችን እንደሚቀጣና ፃድቃንን እንደሚሸልም/እንደሚባርክ እንደሆነ እምነቱን ተናገረ፣ ይህም ማለት ኢዮብ መቅሰፍቱ የደረሰበት በራሱ ኃጢዓት ምክንያት ነዉ ማለት ነው ፡፡ በዛሬዉ ትምህርታችን ኤልፉዝ ለኢዮብ የመጀመሪያ ምላሹን ይቀጥላል፣ ኢዮብም ምላሹን ይጀምራል ፤ ይሁን እንጂ ኔልሰን “ ቃለምልልሱ እንደ መከራከሪያ ንግግር በወዳጁቹ መካከል በጣም ብዙ ቃለ ምልልስ እንዳልሆነ “ አመልክቷል ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (6፡ 1-7)፡ ይህ ክፍል የኢዮብን ምክንያት ለቅሬታዎቹ አጉልቶ ያሳያል ፡፡ ኢዮብ የነበረዉን ሁሉንም ነገር እንዳጣ ተናገረ፡ ቤተሰቡን እንዳጣ፣ ኃብቱን እና ጤናዉንም እንዳጣ ፤ አሁን የኢዮብ ሁኔታ ትክክለኛ የምሳሌ (27፡ 3) መልክ ነዉ፡ “ ድንጋይ ከባድ ነዉ አሸዋም ሸክሙ ጽኑ ነው ፤ ከሁለቱ ግን የሰነፍ ቁጣ ይከብዳል “ የሚለው ፡፡ ኤልፉዝ ሞኝ/ሰነፍ ነበር ፤ ኢዮብ በእርሱ ላይ ያለዉን እያወራ የነበረዉ ከኢዮብ ትክክለኛ ችግር በላይ የሚበልጥ ሸክምን ነበር ፡፡ ኤልፉዝ እና ቆይቶም ሁሉም የኢዮብ ወዳጆች የችግሩን/የመከራዉን ክብደት አልተረዱትም/አልተሰማቸው ፡፡ ኢዮብ ኢየሱስ ያበረታታዉ አይነት በችግር በእግዚአብሄር ላይ የመደገፍ ምሳሌ ሆኗል (ማቴ 11፡ 28-29) ፡፡ ይህ አመለካከት ከኤልፉዝ ተቃራኒ ነበር ፡፡
ኢዮብ ስሜቱን “ ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላፃ በስጋዬ ዉስጥ ነዉ “ በማለት ገለፀ (ቁጥር 4) ፡፡ ፍላፃዎች የፍርድ ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ ፤ የኢዮብ ይህን ስዕል አጠቃቀም እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ክፉዎችን ይቀጣል ፃድቃንን ደግሞ ይሸልማል በሚለዉ በኤልፉዝ እምነት በያንስ ለጊዜ ተፅዕኖ እንደ ደረሰበት ያመለክታል ፡፡ የኢዮብ ችግር ከባድነት ወደ መማረር ቀይሮት ነበር ፡፡ “ ሰዉነቴ ትነካዉ ዘንድ እምቢ አለች፤ እንደሚያፀይፍ መብል ሆነብኝ “ (ቁጥር 7) ብሎ ከማናገሩ በፊት ጣዕም ያልነበራቸዉን ብዙ አይነት ምግቦች ዘርዝሯል ፤ ኔልሰን ይህን ንግግር “ ትርጉም የሌለዉን “ የኤልፉዝን ምክር አለመቀበል እንደ ነበር ፅፏል ፡፡
ኢዮብ (6፡ 8-13)፡ ይህ ክፍል የኢዮብን ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ አጉልቶ ያሳያል ፤ ዋይርስቤ የኢዮብ ቋንቋ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እንደሚያሳይ ፅፈዋል ፡፡ ኢዮብ እግዚአብሄር “ ሊያደቀዉና “ ሊያጠፋዉ “ (ቁጥር 9) እንደ ፈለገ ገለፀ ፤ በኢዮብ መከራ እዚህ ስፍራ ላይ ይህ “ መጽናናት ይሆንልኛል/ያመጣልኛል “ (ቁጥር 10) ፤ ኢዮብ እግዚአብሄርን አልካደም ነገር ግን የችግሩን ደረጃም ሊክድ አልቻለም ፡፡ ኔልሰን ኢዮብ “ ለእግዚአብሄር ህመሙን በሞት እንዲያስወግድለት በመጠየቅ ከቅዱሱ ጋር ያለዉን ግንኙነት ለመጠበቅ በጣም ያተኮረ እንደ ነበር “ ተመልክቷል ፡፡ በቁጥር 11 መጀመሪያ ላይ በኢዮብ ንግግር ላይ ለዉጥ ጀመረ ፤ ኢዮብለኤልፉዝ ከመመለስ በጸሎት ወደ መናገር ዞረ ፡፡
ኢዮብ (6፡ 14-23)፡ ኢዮብ በጓደኞቹ ብስጭቱን ገለፀ ፤ ኢዮብ ወዳጆቹን በክረምት ወቅት እንደሚሞላና ነገር ግን በበጋ እንደሞደርቅ ከአንድ ወንዝ ጋር አነፃፀራቸው ፡፡ በክረምት በዚህ ወንዝ አጠገብ እንደሚጓዙ ተጓዦች ሙሉ ለሙሉ ደረቅ ለማግኘት እንደፈሩት/እንደሚፈሩት የኢዮብ ወዳጆች በቃላቸዉና በድርጊታቸው ከችግሩ መፅናናትን ለማቅረብ በመዉደቅ አስፈራሩት ፡፡ ሊዎናርድ ራቬንሂል “ ሁሉም አስተምሮቶቻችሁ ትክክል ሊሆኑ ይችላል - የእግዚአብሄር መገኘት ባይኖርበትም “ በማለት ተናግሯል ፡፡ በመንገዱ ላይ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የኢዮብ ወዳጆች ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነታቸዉ ከራሱ ከእግዚአብሄር ይልቅ በይበልጥ ስለ ህግ፣ ስለ ስርዓት እና ስለ መተዳደሪያ እንዲሆን ፈቀዱ ፡፡ ልባቸዉ ከእርሱ ርቆ በማደግ ደረቀ ፡፡ የኢዮብ ወዳጆች ወደ እግዚአብሄር መመለስና እንዲሞላቸዉ መፍቀድ ያስፈልጋቸዋል (ኤር 24፡ 7, ዘካ 1፡ 3, ያዕ 4፡ 8) ፤ ይሁን እንጂ እዚህ ስፍራ ላይ እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር እንዳልነበር አያዉቁም ልክ እንደ ሳምሶን እግዚአብሄር ትቷቸዉ እንደ ነበር አላስተዋሉም (መሳ 16፡ 20)፡፡
ኢዮብ (6፡ 24-30)፡ ኢዮብ ያደረገዉን ስህተት እንዲረዳ እንዲረዱትና እንዲያስተምሩት ጠየቃቸው ፤ ዘልፈዉት/ሰድበዉት ለነበሩት ለወዳጆቹ የሚያስደንቅ ትህትና አሳያቸው፣ ነገር ግን “ ፅድቄ በዚሁ ነገር ነዉን “ በማለት አሳሰባቸው (ቁጥር 29) ፡፡ ኢዮብ በእርሱ ላይ የመጣዉ ጥፋት በኃጢዓቱ ምክንያት እንደ ሆነ መለየት እንደሚችል በተመሳሳይ መንገድምበምላሱ ላይ የተለያዩ ጣዕሞችን መለየት እንደሚችል እየተነገረ ነበር (ቁጥር 30)፡፡
መደምደሚያ
ኢዮብ በወዳጆቹ ብስጭት እንደ ተገለፀዉ የማይታገል ተጋፍ አልነበረም ፤ በችግሩ ጊዜ ኢዮብ ወዳጆቹን በበርሃ መካከል የሚያፅናና ምንጭ ከመሆን ይልቅ ለእርሱ የሚያቀርቡት ምንም የሌላቸዉ ደረቆች ሆነዉ አገኛቸው ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ራሳችሁን ደረቅ ሆናችሁ ካገኛችሁት ወደ እርሱ ተመለሱ ፤ እንዲሞላችሁም ፍቀዱለት ከዚያም ለሌሎች የምታቀርቡት የሆነ ነገር ይኖራችኋል ፡፡
5 Nelson, 6:5–7.
7 Nelson, 6:8–10.
8Constable, p. 42.
9Constable, p. 43.
TThomas Nelson, Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999) 6:1. Accessed electronically https://books.google.com/books?id=rVkt20rhM- 9wC&printsec=frontcover&dq=nelson%27s+illustrated+commentary&hl=en&sa=X&ved=0ahUKEwihkdLawazfAhUBKK0KHSdrBpcQ6AEIKDAA#v=onepage&q=job%205&f=false on 12/19/18.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Study Notes: Job, p. 42; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.
Warren Wiersbe, Be Patient (Job): Waiting on God in Difficult Times (Colorado Springs: David Cook, 1991), p. 39.
Wiersbe, p. 39.
Wiersbe, p. 39.
ጥያቄዎች
-
በኢዮብ 5 ስለ እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር እንደሚያዉቅ በግልፍተኝነት እንደ ተናገረዉ ኤልፉዝ ይሰማችኋል ? (1ቆሮ 13፡ 12)
-
ኤልፉዝ “ ይህችን መረመርን የሰማነዉም ይህ ነው “ አለ (ኢዮ 5፡ 27) ፤ “ እኛ “ በመላት ሲጠቅስ ማን እያመለከተ እንደ ነበር ታስባላችሁ ?
-
በምዕራፍ 6 ኢዮብ ምን የተሳሳተ ነገር እንዳደረገ ሳይጠቅስ በኃጢዓት በመክሰሱ በኤልፉዝ በግልፅ የተበሳጨ ነበር ፤ ኢየሱስ ስለዚህ ምን አለ ? (ማቴ 7፡ 3, ሮሜ 12፡ 15)
-
በኢዮብ ላይ የሆነዉ በራሱ ህይወት ላይ በተደበቀ ኃጢዓቱ ምክንያት በእርሱ ላይ እንደሚሆን ኤልፉዝ እንዲፈራ ያደረገዉ ነበር (ሮሜ 6፡ 21) ? የኢዮብ አጣብቂኝ ዉስጥ መግባት ወዳጆቹ እንዳሰቡት በራሱ ኃጢዓት ዉጤት ነበር ? በራሳችሁ የምታዩትን ኃጢዓት በሌላ ላይ ጥፋት ሆኖ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ?
-
በኢዮብ 5-6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 6:2–3
“If only my grief could be weighed and my devastation placed with it in the scales. For then it would outweigh the sand of the seas! That is why my words are rash.”
ኢዮብ ለጓደኛው ለኤልፋዝ በታማኝነት መለሰ ፡፡ እርሱ በእውነትም በመከራ ውስጥ መሆኑን አመነ ፡፡ ኢዮብም መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ ! ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበር አለ ፡፡ እርሱ በአካሉ ላይ ያለው ቁስል ለስቃይ እንደዳረገው አመነ ፡፡ አሁንም ግን ኢዮብ ምንም እንኳ የመከራውን መራራነት ቢቀምስም ፤ ምንም እንኳ በጓደኞቹ ምላሽ ባይስማማም ወደ እግዚአብሔር ለጸሎት ተመለሰ ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ከባድ ሀላፊነት አንደተሸከምክ ለማመን ከባድ ይሆናል ፡፡ ለቤተሰብና ለጓደኞች ግልጽ በመሆን “ ደክሞኛል እናም ደግሞ ፈርቻለሁ “ ብሎ ለማመን አስቸጋሪ ነው ፡፡ ይህንን ለመቀበል ታማኝነት እና ትህትና ያስፈልጋል ፡፡ ሆኖም ግን እንደ አማኝ የምትራመደው ከአዳኝ ፣ ከንጉሥ እንድሁም ደግሞ ስሙ ኢየሱስ ከተባለ እናም ደግሞ እጁን ዘርግቶ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ። “ ከሚል ጓደኛ ጋር ነው :: ኢየሱስ “ እኔ እረፍታችሁ ነኝ “ ይላል ፡፡ ጓደኛዬ በኢየሱስ እረፍ ፡፡ መጀመሪያ ሸክምህን እመን ፡፡ በረጅሙ ወደ ውስጥና ወደ ውጭ ተንፍስ ፡፡ ወደ ውጭም ስትተነፍስ “ እግዚአብሔር ሆይ ይህን ሸክም ከእኔ ውሰድ ፡፡ ይህንን በመሸከም ዝያለሁ ፡፡ ይህንን ሸክም ለእኔ እንደምትሸከምልኝ አምናለሁ “ በል ፡፡ አሁን እጆችህን ወደ ላይ አንሳ ማለት ሸክሙ ከመዳፍህ እየወጣ እንደሆነ እንዲያሳይ አድርገህ ፡፡ እርሱ ወስዶታል ፡፡ እርሱ ሊሸከመው ይችላል እናም ይህን ጊዜ መሸገር እንድትችል ጸጋንና ኃይል ሊያስታጥቅህ ይችላል ፡፡ በእርሱ እረፍ ፡፡
“ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ ! ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና ስለዚህ ቃሌ ደፋር ሆኖአል ።
- ኢዮብ 6፡2-3
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 62:5–8 — “ ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና ። እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም ። መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው ። የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው ። “
መዝሙር 91:1–2 — “በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል ። እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ ። “
ማቴዎስ 11:28–30 — “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።