Eliphaz Speaks
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በምዕራፍ 1 እግዚአብሄር የኢዮብ የሆነዉን ሁሉንም ነገር እንዲያጠቃ/እንዲያጠፋ ሰይጣንን ፍቃድ ሰጠው ፤ ቆይቶም ሰይጣን የኢዮብን ጤንነት እንዲያጠቃ ፍቃድ ተሰጠው ፡፡ የጤንነት ችግር እያለበትና ሁሉንም ነገሩን አጥቶ ኢዮብ ከእግዚአብሄር ለመመለስ እምቢ አለ ፤ የኢዮብ ሚስት ከእግዚአብሄር እንዲመለስ ልታሳምነዉ ሞከረች ፡፡ የኢዮብ ወዳጆች በመምጣት በዝምታ ለሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ተቀመጡ ምክንያቱም ምን ያክል እንደታመመ/እንደ ተቸገረ ስላዩ ፡፡ በመጨረሻም በምዕራፍ 3 ኢዮብ ተቀምጠዉ ለሚሰሙት ወዳጆቹ ተነፈሰ/ተናገረ ፡፡ ኢዮብ 4 ከኢዮብ ወዳጆች የአንዱ የመጀመሪያ ንግግር ነው ፤ እነዚህ ንግግሮች የመፅሀፉን ቀሪ ክፍሎች ይሰራሉ፣ ትንሽ መመለስ በማድረግም የኢዮብንና የወዳጆቹን ግንኙነት እናያለን ፡፡ የኢዮብ ወዳጆች እነማን ነበሩ ?
- ኤልፉዝ - እንደ ረቂቅ/የተመስጦ በሆነ ነገር አገለገለ ፡፡ በታላቅ አክብሮትና ጥንቃቄ ተናገረ ፤ የኤልፉዝ ንግግር እግዚአብሄርን “ እንደ ማይናወጥ ፍርድ ሰጪነት “ በመረዳቱ ላይ የተመሰረተ ነበር ፡፡
- በልዳዶስ - እንደ ጠበቃ ተናገረ/አደረገ ፡፡ በልዳዶስ በሚናገረዉ ቀጥተኛ የነበርና ከኤልፉዝም ያነሰ ትህትና ነበረው ፡፡
- ሶፋር - በይበልጥ በቀኖናዊ/ግትርተኝነት ተናገረ/አደረገ ፡፡ ሶፋር የማያስተዉል የነበርና በማናጨቅ “ አላዋቂ አዲስ ሰዎችን እንደሚናገር/እንደሚደርስ አንድ የትምህርት ቤት አዋቂ “ በመምሰል መጣ ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (4፡ 1-4)፡ አንድ ጠበቃ ወደ ልቡ ሊያደምጠዉና ሊያፅናናዉ ሲመለከተው በልዳዶስ የኢዮብን ልብ በእዉነት ለመፈወስ ሞከረ ፤ በልዳዶስ በፍፁም የኢዮብን ስሜት ባለመመልከቱ/ትኩረት ባለመስጠቱ ለኢዮብ ፍቅር አላሳዬም ፡፡ ከኢዮብ ጓደኞቹ ማንኞቹም ለኢዮብ ፍቅር አላሳዩም ፤ ይልቁንም ምን ያክል ያዉቁ እንደ ነበር ለኢዮብ ለማሳየት ኃይማኖታዊ ሰዎች እንደሆኑ ራሳቸዉን ያሳያሉ ፡፡ በኤፌ (4፡ 15) መሰረት ይወድቃሉ “ ነገር ግን እዉነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆነው ወደ ክርስቶስ እንደግ “ ፡፡
እነዚህ ቁጥሮች የኤልፉዝ አቀራረብን ለኢዮብ ሁኔታ ያሳዬናል፡፡ ኤልፉዝ “ ልክ እንደ ግሰፃና ወቀሳ “ ተገበረ ፤ በማመስገን በመጀመር፣ ትችቱን አመጣ ከዚያም በመጨረሻ ላይ አቀዘቀዘዉ ፡፡ ኤልፉዝ ኢዮብ ለሌሎች አድርጎት በነበረዉ ነገር የሚያበረታታን የተረጋጋ ለመሆን ሞከረ ፤ ለኢዮብ አንዱ የኤልፉዝ ምስጋና ተቸግረዉ የነበሩትን ሰዎች ማበረታቻ አቅርቦላቸዉ ለነበረዉ ነገር ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ በትክክለኛዉ ጊዜ በትክክለኛ መነሳሳት/ፍላጎት የተነገረ ትክክለኛ ቃል በሌሎች ላይ ልዩነት ማምጣት እንደሚችል “ ኢዮብም ያን እንዳደረገ ተናገረ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (4፡ 5-11)፡ ስለ ቀድሞ ድርጊቱ ኢዮብን ካመሰገነ በኋላ አሁን ኤልፉዝ በኢዮብ ላይ ክስ አመጣ ፤ በቁጥር 5-6 የኤልፉዝ የመጀመሪያዉ ጥያቄ ለኢዮብ ህይወቱ በእግዚአብሄር መንገድ የሄደበት ቢሆን ኖሮ ከእግዚአብሄር ምን የሚያስፈራዉ ነገር እንደማይኖር ገለፀለት ፡፡ በኤልፉዝ ሀሳብ ኢዮብ እነዚህ ሁሉንም መቅሰፍቶቹን የደረሱበት በራሱ ኃጢዓት በራሱላይ እንዳመጣቸዉ ነው ፤ እያንዳንዳቸዉ የኢዮብ ወዳጆች ተመሳሳይ ክርክርን ያደርጋሉ ፡፡ ለኢዮብ ሁኔታ ለእነርሱ ማንኛዉም ገለፃ ኃጢዓትን በማድጉ በራሱ ላይ ከማምጣጡ በስተቀር የሚታሰብ አልነበረም ፡፡
የብሉይ ኪዳን ምሁር ኬንት ሁግሄስ የኤልፉዝ መጥፎ አስተምሮ አራት ምልክቶችንዘርዝሯል/አስቀምጧል፡
ኤልፉዝ “ ሁሉም ነገር በፍፁም በቁጥጥር ስሩ እንደሆነ “ ያምናል ፤ በመርህ በዚህ ሀሳብ እንስማማለን ፤ ነገር ግን ኤልፉዝ ይህን ያደረገበት መንገድ ችግር ያመጣል ፡፡
ኤልፉዝ “ እግዚአብሄር በሙሉ ፍታዊ/ትክክለኛ እንደ ነበር “ ያምናል ፤ በኤልፉዝ በሁለተኛዉ እምነቱ ላይ ችግሩ የእግዚአብሄር የፍትሀዊነት ሀሳብ ከእኛ ጋር የሚመሳሰል አለመሆኑ ነበር ፡፡
ኤልፉዝ “ ሁል ጊዜ ክፉዎችን እንደሚቀጣና ፃድቆችን እንደሚባርክ “ ያምናል ፡፡ በኤልፉዝ አስተምሮ መሰረት እግዚአብሄር ክፉዎችን ካልቀጣና ፃድቆችን ካልባረከ ትክክል/ፍትኃዊ አይሆንም ማለት ነው ፤ የኤልፉዝ አስተምሮ መጥፎ የሚሆንበት ስፍራ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ክፉዎችን አይቀጣም ፃድቆችንም አይባርክም
ኤልፉዝ አንድ ሰዉ ከታመመ/ችግር ከደረሰበት ያሰው ኃጢዓት አድርጓል በኃጢዓቱም ምክንያት እየተቀጣ እንደሆነ ያምናል ፡፡
ለአንድ ሰዉ ኃጢዓት የሚመጣዉ ፍርድ ኤልፉዝ የሚጠብቀዉ በኃጢዓታኛዉ ላይ ልክ ተተክሎ በነበር እህል ላይ በቀስታ ወይም በፍጥነት እንደ ጎርፍ/ንፋስ ወይም እንደሚያጠቃ አንበሳ ሊመጣ እንደሚችል ነበር (ቁጥር 9-11) ፤ ነገር ግን ለኃጢዓት ፍርድ በእርግጥ ይመጣል ፤ አዎ እነዚህ ነገሮች እዉነት ናቸው ፡፡ እግዚአብሄርአንድን ሰዉ ስለ ኃጢዓት ሊቀጣ ይችላል ቅጣቱም ቀስ ብሎ ወይም በፍጥነት ሊመጣ ይችላል፡፡ አንበሳ እንደሚያጠቃዉ በፍጥነት ሊያጠቃን ስለማይችል ጥበቃ እንዲያደርግልን ጌታን ያለማቋረጥ መጠየቅ አለብን (መዝሙር 91) ፡፡
ኢዮብ (4፡ 12-21)፡ አሁን ኤልፉዝ ኢዮብን ክርክሩ ላይ አመጣው ፤ “ ለእኔም በምስጢር ቃል መጣልኝ……” የሆነ ራዕይ የሚመስል ነገር ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን መልዕክቱ ከየት እንደመጣ አናዉቅም ፡፡ ኤልፉዝ በቁጥር (13-15) ለኃሳቡ ዋጋ እንዲኖረዉ ለማድረግ በመሞከር በዚህ ራዕይ ዙሪያ የነበሩትን ሁኔታዎች ገለፀ ፤ ከዚያም ኤልፉዝ በምሽት በእርሱ ፊት ቆሞ ከነበረው “ ከአንድ መልክ/ምስል “ የሆነዉን መልዕክት ገለፀ (ቁጥር 16-21) ፡፡ ይህ ምስል/መልክ ለኤልፉዝ እግዚአብሄር በመለዓክቱ ላይ “ እምነት እንዳላስቀመጠ “ እና በጣም ደካማ በሆነዉ በሰዉ ላይ እንዴት ሊያስቀምጥ ይችላል ብሎ በመጠየቅ ያመለከተዉን አንድ መልዕክት ነገረው ፡፡
ኤልፉዝ ስለ እግዚአብሄርና ስለ ሰዉ ሁሉንም ታሪክ አልተናገረም ፤ አዎ የሰዉ ልጅ ሁሉ የደከመና የተወሰነ ነዉ በተለይ ደግሞ ከእግዚአብሄርና ከመለዓክት አንፃር ፤ ነገር ግን ኤልፉዝ በመጨረሻ ወቀሳና ግሰፃዉ መካከል ላይ የመጨረሻ ምስጋናዉን ተወው ፡፡ በማበረታታት ጀመረ፣ ትችቱን አመጣ ከዚያ የሰዉ ልጅ በእግዚአብሄር መልክ እንደ ተሰራ በማመልከት ወደቀ ፤ ራሱን በሰራዉ እግዚአብሄርን እና ኢዮብን እንደ እግዚአብሄር ፀጋና ፍትህ በማመልከት ወደቀ ፡፡ ኤልፉዝ ለመዉጣትና ትክክል እንደ ሆነ በማረጋገጥ ኢዮብን እንደ በለጠ ለማሳየት እንደፈለገ ይመስላል ፡፡
መደምደሚያ
ኤልፉዝ የታመመ/የተቸገረ ወዳጁን በኃይለኛዉ በኃይማኖታዊ መንፈስ ቀረበው ፤ በኢዮብ ችግር መካከል ላይ ኤልፉዝ በሁኔታዉ ላይ በእዉነተኛዉ መንገድ ብቻ ተነጋገረ/አወራ ፡፡ ለታመመ/ለተቸገረ ወዳጁን ፍቅር ከማሳየት ይልቅ ኤልፉዝ ራሱ ልክ እንደ ነበር ማረጋገጥ እና የራሱን አስተምሮ እመግለፅ ላይ በይበልጥ ያተኮረ ነበር ፡፡ ልብን በእዉነት መፈወስ/ማዳን አንችልም በፍቅር እንጂ ፤ “ እዉነትን በፍቅር “ እንናገራለን (ኤፌ 4፡ 15) ፡፡ ሁል ጊዜ ይህ አቀራረብ ሌሎችን በብዙ እግዚአብሄር እንደሚወዳቸው በመርዳት በማሰብ እንጂ ራሳችን ልክ እንደሆንን በማረጋገጥ አይደለም ፡፡ ኤልፉዝ ሁል ጊዜ ትክክል ሲሆን እግዚአብሄርም ሁል ጊዜ እንደሚባርከዉ ነበር ያሰበዉ ፤ ነገር ግን ይህ በቀላሉ እዉነት አይደለም ፡፡
Warren Wiersbe, Be Patient (Job): Waiting on God in Difficult Times (Colorado Springs: David C Cook, 1991), pp. 31–32.
Wiersbe, p. 35.
Wiersbe, p. 36.
Wiersbe, p. 36.
Christopher Ash, Preaching the Word: Job: The Wisdom of the Cross, ed. R. Kent Hughes (Wheaton, IL: Crossway, 2014), p. 90.
Ash, p. 90.
Ash, p. 90.
Ash, p. 90.
Wiersbe, p. 36.
Wiersbe, p. 36.
ጥያቄዎች
-
ኢዮ (4፡ 12-14) ኤልፉዝ ራዕይ እንደ ነበረዉ እንደሚጠቅስ ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ ከእግዚአብሄር ነበር ?
-
በኢዮ (4፡ 15) ኤልፉዝ በፊቱ አልፎ ከነበረዉ መንፈስ ጋር ተነጋገረ ፤ ይህ መንፈስ ከየት መጣ ብላችሁ ታምናላችሁ ? ከእግዚአብሄር፣ ከሰይጣን ወይስ ከስጋ ነበር ?
-
በኢዮ (4፡ 7) ኤልፉዝ መልካምና ንፁኅ ሰዎች በፍፁም መከራ አይደርስባቸዉም እያለ ነበር ? (መዝሙር 73, ሉቃ 16፡ 19-31)
-
ሰዎች ስለ ኃጢዓታቸዉ ይቀጣሉ ብላችሁ ታስባላችሁ (ዘኁ 27፡ 12-14, 2ሳሙ 12፡ 11-14) ? አዎ ከሆነ ስላደረጋችሁት ስህተት ነገር እግዚአብሄር ቀጥቷችሁ ያዉቃል ?
-
በኢዮብ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 4:8
“In my experience, those who plow injustice and those who sow trouble reap the same.”
ከኢዮብ ጋር ለሰባት ቀን በስቃዩ አብረው ከተቀመጡ በኋላ ከሶስቱ የኢዮብ ጓደኞች አንዱ ተናገረ ፡፡ ኤልፋዝ በኢዮብ ላይ በደረሰው ነገር ምክንያት በእርሱ ላይ ክስ እና ሙግት አቀረበ ፡፡ የመጀመሪያው ተናጋሪ እንደመሆኑ መጠን ኤልፋዝ አጀንዳ ነበረው ፡፡ ኤላፋዝ የወንድም ፍቅሩን ከማሳየት ይልቅ የራሱን ጥበብ ተናገረ ፡፡
የመከራ ጊዜን እያሳለፈ ያለን ጓደኛህን ስታይ ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ልታይ ትችላለህ ፡፡ ሆኖም ግን እንደ ጓደኛ ስለ ጉዳዩ የምታስበውን ከመናገርህ በፊት የእግዚአብሔርን ልብ ስለ ጥበብ ፈልግ ፡፡ ለመናገር ቀስ በል ፡፡ ከዚያም የሆነ ነገር ስትናገር ከተደበቀ ፍላጎት ሳይሆን በንጹህ ልብ ተናገር ፡፡ በትክክለኛው ጊዜ እውነትን በፍቅር ትናገር ዘንድ እንድረዳህ እግዚአብሔርን ለምን ፡፡ ምናልባት ጓደኛህ ከእግዚአብሔር ያገኘኸውን መገለጥ ለመስማት ዝግጁ ላይሆን ስለሚችል ጸልይ ፡፡ በመከራ ውስጥ ስላለው ጓደኛህ ጸልይ ፡፡ የእውነት ንግግርህን በእርሱ ፍቅር እንድሸፍንልህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ ፡፡ ጸልይ እግዚአብሔር ንግግርህን ለጓደኛህ በቃሉ እንድያጸናለት ፡፡ ከሁሉም በላይ ይህንን በመታዘዝ አድርገው እንድሁም ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ከሰው ንግግር በላይ በሆነ መንገዱ እንደሚሰራ እመን ፡፡
“እኔ እንዳየሁ ፥ ኃጢአትን የሚያርሱ፥ መከራንም የሚዘሩ ይህንኑ ያጭዳሉ። “
- ኢዮብ 4፡8
ተጨማሪ ጥቅስ
ኤፌሶን 4:15 — “ ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ “
ኤፌሶን 4:29 — “ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ ። “
1ኛ የጴጥሮስ 1:22 — “ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።