Satan's Second Test
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 2-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለኢዮብ መፅኀፍ ሀረጋችን/ቃላችን ተስፋ የተገባ ተቤዢ ነው ፡፡ አንዳንዶች በመፅኀፍ ቅዱስ ዉስጥ የኢዮብ መፅኀፍ በዘፍጥረት 11 ከባቢሎን ግንብ በኋላ በመከናወን እና በዘፍጥረት 12 ከአብርኃም በፊት ወይም በዚያን ጊዜ በመከናወን ትልቁ ነዉ ይላሉ ፡፡ በምዕራፍ 1 ኢዮብ በአራት ኃይለኛ አስደንጋጭ ጥፋቶች ተመቶ ነበር ፤ ሁለቱ ጥፋቶች መንጋዉን ከነዱበት/ከወሰዱበትና አገልጋዮቹን ከገደሉበት ከምድር ጠላቶቹ መጡ ፤ ሁለቱ ደግሞ በመብረቅና በኃይለኛ ንፋስ መልክ እንስሳቶቹን፣ አገልጋዮቹንና ልጆቹን የገደሉት ከሰማይ መጡ ፡፡ በአራቱ ጥፋቶች ምክንያት ያለዉን -ከብቶቹን፣ አገልጋዮቹን እና ሰባት ወንድ ልጆቹንና ሰዎስት ልጆቹን እንኳን ሳይቀር ሁሉንም ነገር አጣ ፡፡ ኢዮብ 1 መጨረሻ ላይ ኢዮብ ለእነዚህ ጥፋቶች “ እግዚአብሄር ሰጠ ፤ እግዚአብሄርም ነሳ ፤ የእግዚአብሄር ስም የተባረከ ይሁን “ (ቁጥር 21) በማለት ምላሽ ሰጠ ፡፡ በህመምና በችግር ቢሆንም እንኳን ኢዮብ አሁንም በእግዚአብሄር እንደሆነ እዉቅና ሰጠ፤ ማክአርቱር እግዚአብሄር ልጆቹ አንዳንድ ጊዜ በግል ኃጢዓት ምክንያት፣ አንዳንድ ጊዜ በግል በመቅጣት ሂደት ዉስጥ ለማሰልጠን፣ አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ዉስጥ የእግዚአብሄርን ምቾትና ፀጋ ለመግለጥ እንደ እድል እና አንዳንድ ጊዜ በማይታወቅ ነገር በህመምና በችግር ዉስጥ እንዲሄዱ እንደሚፈቅድ ያመለክታል ፡፡ በኢዮብ 1 በተቀመጠው በፍርድ ቤት ሰይጣን ኢዮብ የነበረዉን ኃብት እንዲወስድ ፍቃድ ተሰጥቶታል ነገር ግን በምንም መንገድ ኢዮብን እንዲነካና እንዲጎዳ አልተፈቀደለትም ፡፡ ምዕራፍ 1 “ በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም ለእግዚአብሄርም ስንፍና አልሰጠም “ (ቁጥር 22) በሚሉት ቃላቶች ተጠቃለለ ፤ ያም በሰይጣንና በእግዚአብሄር መካከል ስለ ኢዮብ ቃለ ምልልስ ወደ ሚቀጥልበት ወደ ምዕራፍ 2 መሸጋገሪያን ይሰጠናል፣ ኢዮብም በእርሱ ላይ ለሆነዉ ዉጊያ ሳያስተዉል ይቆያል ፡፡
ትምህርት
ኢዮብ (2፡ 1-10)፡ እንደ ገና የእግዚአብሄር ልጆች በጌታ ፊት መጡ ሰይጣንም በመካከላቸዉ መጣ (ቁጥር 1) ፡፡ እግዚአብሄርም ሰይጣንን ከየት እንደ መጣ ጠየቀዉ ሰይጣንም በምዕራፍ 1 እንደ ነበረው - በምድር ላይ እንደ ዞረና እንደ ተመላለሰ (ቁጥር 2) ምላሽ ሰጠ ፡፡ እግዚአብሄር እንደ ገና የሰይጣንን ሀሳብ ወደ አገልጋዩ ኢዮብ በማምጣት “ ያለምንም ምክንያት “ (ቁጥር 3) በሰይጣን የተጠቃ ቢሆንም እንኳን ኢዮብ ፍፁምነቱን እንዳለቀቀ አመለከተው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ያለምንም ምክንያት ሰይጣን ኢዮብ እግዚአብሄርን በከንቱ እንደ ማያመልከዉ በተጫነ ስሜት ከተጠቀመዉ ከዕብራዊ ቃል ጋር ተመሳሳይ ትርጉም እንደ ሆነ ይገልፃል “ ፡፡
በዚህ ወቅት በህይወቱ ምንም ነገር የሆነበት ቢሆንም ኢዮብ እንደ ነበረው ተመሳሳይ ሰዉ ነበረው ፤ ይህ በትክክል ለሁላችንም ጥያቄ ነው - ነገሮች መልካም በሚሆኑ ወይም በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ በሚሆኑ ጊዜ የጥፋት ወቅት እንኳን በሚመጣ ጊዜ ሁል ጊዜ እንደ ምንሆነዉ ተመሳሳይ ሰዉ እንሆናለን ? ሌሎች ማወቅ የማይፈልጉበትን የተኮረጀ ዘዴ ማግኘት እንፈልጋለን ? ወይስ በሁሉም ነገር ወደ እግዚአብሄር በመመለስ እናመልከዋለን ? ሰይጣን ያለማቋረጥ “ ለመስረቅ፣ ለማጥፋትና ለመግደል “ በእኛ ላይ ይመጣል (ዮሐ 10፡ 10) እንዲሁም አይናችንን ከእግዚአብሄር ላይ ለማንሳት ይመጣል ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ የሰይጣንን እነዚህን ባህሪያት ያቀርባል ፡፡ ሰይጣን ለእግዚአብሄር ተጠያቂ በመሆን የቀረና በሙሉ ኃይለኛ አይደለም ፤ ፍጥሩ ስለሆነ በአንድ ጊዜ ከአንድ ስፍራ በላይ የመሆን ችሎታ ስለሌለዉ በምድር ላይ ስራዉን እንዲሰራ በሚረዱት በተጣሉ መለዓክት ላይ የተደገፈ ነው ፤ በተጨማሪም ሀሳባችንን ማንበብና ወዲፊታችንን ማወቅ አይችልም ፡፡ በእርግጥ “ ሰይጣን ከእግዚአብሄር ፍቃድ ዉጪ አንድም ነገር ማድረግ አይችልም “፣ እግዚአብሄርም “ መሸከም ከምንችለዉ በላይ እንድንፈተን “ አይፈቅድም (1ቆሮ 10፡ 13) ፡፡ በኢዮብ 42 እግዚአብሄር ኢዮብን ነፃ አወጣው/ታደገው ምክንያቱም ሁልጊዜ እግዚአብሄር የምንወጣበትን መንገድ ስለሚመለከት - ተስፋ በተሰጠዉ ተቤዢ/አዳኝ በኩል ማለት ነው ፡፡
ሰይጣን እንደ ገና “ ቁርበት ስለ ቁርበት ! “ በማለት በመናገር ተጫነ ፤ ሰይጣንም ኢዮብ አካሉ ቢመታ/ቢጎሳቆል ፍፁምነቱ አይቀጥልም አለው (ቁጥር 4-5) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ቁርበት ስለ ቁርበት “ የሚለዉን ሀረግ “ የእንስሳት ቆዳዎች ከመለወጥ ተግባር ….ወይም “ ህይወትን ስለ ህይወት፣ አይንን ስለ አይን እና ጥርስን ስለ ጥርስ ከሚለዉ ምሳሌ ተመሳሳይ ሀረግ “ የመጣ እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር እንደ ገና ፍቃዱን ሰጠዉ ነገር ግን ሰይጣንን የኢዮብን ህይወት መዉሰድ እንደ ማይችል ነገረው (ቁጥር 6) ፡፡ ሰይጣንም ከእግዚአብሄር ወጥቶ በመሄድ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ ኢዮብን በኃይለኛ ቁስል መታው (ቁጥር 7) ፡፡ ኢዮብ በአመድ መካከል በመቀመጥ ቁስሉን ለማከክ ገልን ተጠቀመ (ቁጥር 8) ፡፡ ዋይርስቤ ምልክቶቹ ኃይለኞች እንደ ነበሩ አመልክቷል፡ “ በኃይል ያሳክካል (2፡ 8)፣ የእንቅልፍ ማጣት (7፡ 4)፣ ቁስልና ቅርፊት የበዛበት (7፡ 5)፣ ቅዠት (7፡ 13-14)፣ መጥፎ ትንፋሽ (19፡ 17)፣ ክብደት መቀነስ ( 19፡ 20)፣ ብርድና ትኩሳት (21፡ 6)፣ ተቅማጥ (30፡ 27) እና የቆዳ መጥቆር (30፡ 30) “ ፡፡
ዋይርስቤ በኢዮብ 2-3 አራት የተለያዩ ድምፆች ተሰምተዉ እንደ ነበር አመልክቷል ፡፡ የመጀመሪያዉ በሚያናድድ ሁኔታ ብዙ ዋጋን ስልጣን በመስጠት ራሳችንን እንደ ተጠቂ የምናይላቸዉ “ የከሳሾቹ ድምፅ ነበር “ (2፡ 1-8) ፡፡ ሁለተኛዉ ድምፅ እግዚአብሄርን ሰድቦት እንዲሞት የነገረችዉ የኢዮብ ሚስት የሆነው “ የተስፋ ቆራጭ ድምፅ “ ነበር (2፡ 9) ፡፡ ኢዮብም ከንቱ ነገር ተናገርሽ አላት ምክንያቱም መልካሙን ነገር ከእግዚአብሄር መቀበል እንዳልቻለዉ ጥፋትም ሊቀበል ስለ ማይችል (2፡ 10) ፤ እንደ ገና ኢዮብ በተናገረዉ ስንፍናን አላደረገም (2፡ 10) ፡፡
ኢዮብ (2፡ 11-13)፡ ሰዎስተኛዉ ድምፅ የኢዮብ የሰዎስቱ ወዳጆቹ የነበረዉ “ የሀዘንተኞች ድምፅ ነበር “ (2፡ 11-13) ፤ ወዳጆቹም በኢዮብ ላይ የሆነዉን ሰሙ ሊያዩትና ሊያፅናኑትም መጡ (ቁጥር 11) ፡፡ ከሩቅም በትንሹ ኢዮብን ለዩት ፤ ወዳጆቹም በምላሹ ጮኸዉ በማልቀስ ልብሳቸዉን በመቅደድ አቧራ ወደ ሰማይ እየረጩ በራሳቸዉም ላይ ትቢያን ረጩ (ቁጥር 12) ፡፡ ወዳጆቹም ከእርሱ ጋር ለሰባት ቀንና ሌሊት ምንም ነገር ሳይናገሩ ተቀመጡ ምክንያቱም የኢዮብ ሕመም እጅግ የበዛ/የጠነከረ ስለ ነበር (ቁጥር 13) ፡፡
ሰዎስቱ ወዳጆቹ ኤልፉዝ፣ በልዳዶስ እና ሶፋር ነበሩ ፡፡ ኤልፉዝ ጥልቁ ነበር፣ በመፅሀፉ ንግግሩም ረጅምና በጣም የበሰለ እና ቀጥታ ከእግዚአብሄር የሰማ ነበርም ፤ ኤልፉዝ ከኤዶም ወይም ከአረብ ወገን ነበር ፡፡ በልዳዶስ ሁለተኛዉ ትልቅ ምናልባትም ከአብርሃም የመጨረሻ ልጅ ስዌሕን ጋር የተዛመደ ነበር (ዘፍ 25፡ 2) ፡፡ ከሰዎስቱ ትንሹ ሶፋር ከይሁዳ ከተማ ከነዕማታዊ ነበር ፡፡ ኮንስታብል “ በህመማችሁ ለመጎብኘት ከሩቅ በመምጣት ህመማችሁን በማክበር ለሰባት ቀን ምንም ሳይናገሩ አብረዋችሁ የሚቀመጡ ስንት ወዳጆች አሏችሁ ? “ በማለት ይጠይቃል ፡፡
መደምደሚያ
በታሪኩ ላይ እዚህ ስፍራ ላይ የከሳሾቹና የተስፋ ቆራጭ ድምፅ ጥሩ አልነበረም ፤ ነገር ግን የኢዮብ ወዳጆች የነበሩት የሀዘንተኞቹ ድምፅ መልካም ነበር ፡፡ ለኢዮብ በመጨነቅ ሊያፅናኑትና ሊንከባከቡት መጡ ፤ ይህ የክርስቶስ አካል አስተሳሰብ መሆን አለበት - የሰዎቹ ፍላጎት በመገናኘት እነዚያም ሰዎች ለምንከባከብ መሆን ማለት ነው ፡፡ ለእርሱ እዚያ በመሆን ብቻ በዝምታም ለሰባት ቀን ተቀመጡ ፡፡ በኢዮብ 3 አራተኛዉ ድምፅ “ የህመምተኛዉ/የችግረኛዉ ድምፅ “ ተሰማ ፡፡ ስንቸገር የተሰማንን መናገር ችግር የለዉም ፤ እንዲሁም ምልክቶቹ እያሉ እግዚአብሄር በጉዞዉ ጊዜ ወደ እኛ የሚያዳምጡና በእነዚህ ጊዜያት አብረዉን የሚጓዙ ሰዎች ይሰጠናል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 563.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 618.
Nelson’s Commentary, p. 617.
Nelson’s Commentary, p. 618.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Acts (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2004), p. 12.
Wiersbe, p. 12.
Wiersbe, p. 13.
Wiersbe, p. 14.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Study Notes: Job, p. 28; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/job.pdf.
Constable, p. 29.
Wiersbe, pp. 14.
ጥያቄዎች
-
በኢዮ (2፡ 9) ለመከራዉ የኢዮብ ሚስት እንዴት አፀፋ ሰጠች ? ለምን በዚህ መንገድ አፀፋ እንደሰጠች ምን ታስባላችሁ ?
-
በኢዮ (3፡ 13, 17-18) ኢዮብ ሞትን፡ በዝምታ፣ በእረፍትና በምቾት በእነዚህ መግለጫዎች ገለፀው ፤ ኢዮ (3፡ 26)(NASB) ይህን ከአሁኑ ሁኔታዉ ጋር ያወዳድረዋል፡ “ በምቾት አይደለሁም በእረፍትም አይደለሁም በፀጥታም አይደለሁም ነገር ግን ብጥብጥ መጣብኝ “ ከሚለዉ ሁኔታ ጋር ፡፡ ኢዮብ ስለሞት ትክክል ያልሆነ አመለካከት ነበረዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ይህ መከራ ቢደርሳችሁ ልክ እንደ ኢዮብ ይሰማችኋል ? ወይስ ነገሮችን እንዴት በተለዬ አመለካከት ታዩታላችሁ ?
-
ኢዮብ በእርሱ ላይ መጥተዉ የነበሩትን የፈራቸዉን ነገሮችና ስጋት በእርሱ ላይ ወድቆ እንደ ነበር ጠቀሰ ፤ ኢዮብ የሚያስፈራዉን ሰይጣን በማወቅ በዚያ መንገድ እንዳጠቃዉ ወይም ደግሞ የኢዮብ ንግግር ማጠቃለያ እንደ ነበር ካሰባችሁ ግለፁ ፡፡
-
በኢዮብ 2-3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Job 2:13
“Then they sat on the ground with him seven days and nights, but no one spoke a word to him because they saw that his suffering was very intense.”
እግዚአብሔርም እንደገና ለሰይጣን ኢዮብን ይጎዳው ዘንድ ፈቀደለት ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ሰይጣን የኢዮብን ህይወት አይንካ እንጅ በአካሉ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችል ነበር ፡፡ ሰይጣን ኢዮብ ከራስ ጸጉሩ ጀምሮ እስከ እግሩ ጥፍሩ ሲቆስል በእርግጠኝነት እግዚአብሔርን እንደሚሳደብ አስቦ ነበር ፡፡ ሆኖም ግን ኢዮብ ሰይጣን መሳሳቱን አረጋገጠ ፡፡ በዚህ ስቃይ ውስጥ ኢዮብ ጸና ፤ በቅንነትም ቀጠለ ፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን እንድሰድብ ለምትፈልገው ለሚስቱ እንድህ አላት ፡- “ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን ? “ በሌላ በኩል ከኢዮብ ጋር ጊዜን ለማሳለፍ የኢዮብ ሶስት ጓደኞቹ ሄዱ ፡፡ መልካሙን ጓደኛቸውንም በታላቅ ስቃይ ውስጥ ሆኖ በማየታቸው ጓደኞቹ አብረው አለቀሱ ፤ ከኢዮብ ጋርም በዝምታ ለሰባት ቀን ተቀመጡ ፡፡
የሆነን ሰው ስቃይ ስትመለከቱ እና ምን እንደምታደርጉና ምን እንደምትሉ በማታውቁበት ጊዜ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ፡፡ የከሳሽ ድምጽም መሆን ትችላላችሁ እንድህ በማለት ፡- “ ዝም ብለህ ወደ ፊት ቀጥል ፤ ተስፋ ለመቁረጥም ብዙ ምክንያት አለህ ፡፡ “ ወይም ደግሞ አጽናኝ ድምጽ መሆን ትችላላችሁ ማለት ፡- በሆነ ሰው የስቃይ ወቅት አብሮ የሚቀመጥ ጓደኛ በመሆን ፡፡ በካንሰር ህመም ፣ በስራ ማጣት ወይም በድብርት ውስጥ ላለ ጓደኛችሁ ምን እንደምታደርጉ ላታውቁ ትችላላችሁ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትጨናነቁና ምንም አታደርጉም ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር ጥበብ እንድሰጣችሁ ጠይቁ ፡፡ ምናልባት እርሱ ከቤታቸው ውጭ በመኪናችሁ ውስጥ ሆናችሁ እንድትጸልዩላቸው ወይም ደግሞ ምናልባት አቅፋችኋቸው በሆስፒታል መጠበቂያ ክፍል ውስጥ እንድትቀመጡም ሊመራችሁ ይችላል ፡፡ ማንኛውም የደግነት ተግባር የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫ ነው ፡፡ አሁን ሂዱና እግዚአብሔር በልባችሁ ላስቀመጠው ለሆነ ሰው ደግነትን አድርጉ ፡፡
“ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም ከእርሱ ጋር በምድር ላይ ተቀመጡ፤ ሕመሙም እጅግ እንደ በዛ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም ። - ኢዮብ 2፡13
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኢዮብ 2፡11 — “ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ ። “
- ምሳሌ 17:17 — “ ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል፤ ወንድምም ለመከራ ይወለዳል ። “
- ቆላስይስ 3:12 — “እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።