Wisdom Books Job

Job and His Family

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promised Redeemer Job 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 365 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ የመፅኀፍ ቅዱስ አዲስ መፅሀፍ ኢዮብን እና አዲስ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል የጥበብ መፅሀፍትን እንጀምራለን ፤ በተጨማሪም ዛሬ ይህ 365ተኛ ክፍላችን ሲሆን የጥናታችን ግማሽ መንገድ ላይ ነን ፡፡ የመፅኀፉ ርዕስ በመፅኀፉ ዉስጥ የዋናዉን ገፀ ባህሪይ ስም ኢዮብን ተሸክሟል ፡፡ ማክአርቱር “ ይህ ስም መከራ ከሚለዉ ከዕብራዊ ቃል የመጣ ትርጉሙም የተሰቃዬ የሚል ወይም ደግሞ ከአረበኛ ቃል ንስሀ የሚል ሲሆን የተመለሰ የሚል ትርጉም የተሸከመ እንደሆነ ይናገራል “ ፡፡ በዚህ መፅሀፍ ዉስጥ የስቃይን/የመከራን ጭብጥ እና በሂደቱ የሚያስፈልገዉን ንስሀ እናያለን ፡፡ ፀሀፊዉ ኢዮብ አልነበረም “ ምክንያቱም የመፅሀፉ መልዕክት ከስቃዩ ጋር በመገናኘት በሰማይ በተከሰቱት ክስተቶች ላይ በኢዮብ እምቢተኝነት ላይ ያረፈ ስለ ነበር “ ፡፡ አንዳንድ ምሁራን ሙሴ መፅኀፉን ሊፅፈዉ እንደሚችል ይናገራሉ ምክንያቱም ኢዮብ ይኖርበት በነበረዉ በዖፅ አጠገብ በምድያም 40 አመት ስላሳለፈ ፤ ሁለተኛዉ ሊሆን የሚችለዉ ፃፊ ሰለሞን ነበር ምክንያቱም ከኢዮብ ጋር ተመሳሳይነትን የተሸከመዉን የመክብብን መፅሀፍ እና ሌሎች የጥበብ መጽሀፍት ስለፃፈ ፡፡ ሌሎች ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የሚካተቱት፡ ኢሳያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ኤርሚያስና ዕዝራ ፡፡

አንዳንድ ምሁራን ኢዮብ በመፅኀፍ ቅዱስ ዉስጥ የቀደመ መጽሀፍ እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡ ማክአርቱር መፅሀፉ በመፅሀፉ ዉስጥ ከተካሄዱት ክስተቶች በኋላ፡ 1) መፅሀፉ በተካሄደበት በኢዮብ እድሜ (ኢዮ 42፡ 16)፣ 2) በፓትሪያሪካል ጊዜ ያስቀመጠው የኢዮብ ህይወት ለ200 አመታት ቆየ (ኢዮ 42፡ 16)፣ 3) በኢዮብ ጊዜ የማህበራዊ ጓድ/አሀድ የጳጳስነት ቤተሰብ ነበር፣ 4) የኢዮብን አገልጋዮች የገደሉት (ኢዮ 1፡ 17) ከላዉዲያን መኖሪያ ከተማ እንደሌላቸዉ እንደ ዘላን ነበር የተገለፁት፣ 5) የኢዮብ ኃብት በከበረ ማዕድን ሳይሆን በከብቶች ብቻ የተቆጠረ ነበር (ኢዮ 1፡ 3, 42፡ 12)፣ 6) ኢዮብ በቤተሰቡ ዉስጥ እንደ ካህን አገለገለ (ኢዮ 1፡ 4-5) እና 7) መፅሀፉ አብርሃማዊ ኪዳን፣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ፣ የዘፀዓት ጉዞ ላይ እና ሙሴ ሕግ ላይ በሚመስሉ ነገሮች ላይ ዝም ያለ ነው፣ በሚሉት ነገሮች ላይ የተፃፈው እንደሆነ ይናገራል ፤ ማክአርቱር “ በመፅሀፉ ዉስጥ የሚገኙት ገፅታዎች የክስተቶቹ ቅደም ተከተሉን ምናልባትም ከባቢሎን ግንብ (ዘፍ 11፡ 1-9) ጊዜ በኋላ ላይ ነገር ግን ከአብርሃም በፊት ወይም በተመሳሳይ ዘመን በመከሰት እንደሚቀመጥ (ዘፍ 11፡ 27) “ ያጠቃልለዋል ፡፡

የጥበብ መጽሀፍ ኢዮብን፣ መዝሙር፣ ምሳሌ፣ መክብብንና እና መኃልይ መኃልይ ሰለሞንን ያካትታል ፡፡ እነዚህ መፅኀፍቶች በኃሳብ ሀገራዊ አይደሉም ስሪታቸዉ ግን ግላዊ ናቸዉ ፤ በአንዳንድ መፅሀፍቶች ላይ የህይወት ትርጉም ሲገለፅ በሌሎች ላይ የህይወት ተግባራዊነት በዝርዝር ተኖሯል ፡፡ ለኢዮብ መፅሀፍ ጭብጣችን ተስፋ የተገባ ተቤዢ ነው ፡፡ ኢዮብ ችግርና ስቃይ መካከል ላይ እግዚአብሄር ተስፋ አንድ ተቤዢ/ታዳጊ እንደሚሰጠዉ ነበር (ኢዮብ 19) ፡፡ ማክአርቱር እግዚአብሄር ልጆቹ በችግርና በመከራ ዉስጥ አንዳንዴ በግል ኃጢዓት ምክንያት፣ አንዳንዴ በግል በማሰልጠን ለማጠንከር፣ አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ዉስጥ የእግዚአብሄርን ምቾትና ፀጋን ለመግለጥ እና አንዳንድ ጊዜ ለማይታወቅ ነገር እንድንሄድ እንደሚፈቅድ አመልክቷል ፡፡

ትምህርት

ኢዮብ (1፡ 1-5)፡ በቁጥር አንድ ኢዮብ “ ፍፁምና ቀን እግዚአብሄርን የሚፈራ ከክፋትም የራቀ “ ከዖፅ የሆነ ሰዉ በመባል ተዋዉቋል ፤ የኢዮብ ባህሪይ እንከን የሌለበት በማለት ተገልፆአል ፡፡ ዖፅ በሰሜን አረቢያ ለምድያም የቀረበች ነበረች ፡፡ የኢዮብ ገለፃ/ማብራሪያ ፍፁም ነበር ማለት አልነበረም ምክንያቱም ማንም ሰዉ ፍፁም አይደለም (ኢዮ 6፡ 24, 7፡ 21, 9፡ 20) ፡፡ ኢዮብ ባለሀብትና በሰባት ወንድ ልጆችን በሰዎስት ሴት ልጆች፣ በትልቅ ንብረትና በሺዎች ከብቶችና እንስሳቶች በኃይል የተባረከ ነው (ቁጥር 2-3, 42፡ 13) ፡፡ “ ኢዮብ በምስራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበር “ (ቁጥር 3) ፡፡ የኢዮብ ወንድ ልጆች በቤታቸዉ ግብዣ በመስጠት የቤተሰብ ጊዜ እንዲኖራቸዉ እህቶቻቸዉን ይጠሩዓቸዋል ( ቁጥር 4) ፤ እያንዳንዱ ግብዣ ካበቃ በኋላ ኢዮብ ልጆቹ በልባቸዉ ሰርተዉት ለነበረዉ ኃጢዓት በሚቃጠል መስዋዕት ልጆቹን ያነፃቸዋል (ቁጥር 5) ፤ ይህ የኢዮብ የሁል ጊዜ ተግባሩ ይሆናል - ለቤተሰቡ እንደ ካህን በመተግበር (ቁጥር 5) ፡፡

ኢዮብ (1፡ 6-12)፡ “ የእግዚአብሄር ልጆች “ በአለም ዙሪያ ያገለገሉትን ለእግዚአብሄር ሪፖርት የሚያደርጉ የቅዱሳን መልዓክት ነበሩ (ቁጥር 6) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የእግዚአብሄር ልጆችን “ ጌታ እንደ ዋና ንጉስ የተቀመጠበት እንደ ሰማያዊ መማክርት/ኮሚቴ ይገልፃቸዋል “ ፡፡ እዚህ የፍርድ ቤት ስዕል አለ ፤ የወደቀዉ መለዓክ ሰይጣን በእነርሱ ላይ መጣ ይህ ማለት እስካሁን ከእግዚአብሄር ፍርድ የመጨረሻዉን ቅጣቱን አልተቀበለም ማለት ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሰይጣንን ከየት እንደ መጣ ጠየቀው ሰይጣንም በምድር ዉስጥ ተመላለስሁ በዉስጧም ዞርኋት አለው (ቁጥር 7) ፡፡ ማክአርቱር “ በኤደን ገነት ባልወደቀዉ አዳም በነበረዉ ስኬት ተደፋፈረ/ደፈረ፣ ሰይጣን በኢዮብ ላይ እግዚአብሄርን መፍራት እንደ ነበር እርግጠኛ ነበር፣ ራሱ ወድቆበት በነበረዉ በፈተናዉ ያልቆመ የወደቀ እንደ ነበር “ ይገልፀዋል ፡፡ በግልፅ እግዚአብሄር ሰይጣን የት እንደ ነበርና ምን አድርጎ እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ እግዚአብሄር አገልጋዩን ኢዮብን ለሰይጣን ከክፉ ነገር የራቀ እንደ ፍፁም ሰዉ አቀረበው (ቁጥር 8) ፤ ሰይጣንም “ በዉኑ ኢዮብ እግዚአብሄርን የሚፈራ በከንቱ ነዉን ? በማለት ጠየቀ (ቁጥር 9) ፤ ሰይጣን ኢዮብ የሚፈራበት መልካም ምክንያቶች እንዳሉት አመለከተ ፡፡ እግዚአብሄር በማትረፍረፍ ባርኮት ስለ ነበር እግዚአብሄርን ይፈራል (ቁጥር 10) ፤ ሰይጣን እግዚአብሄርን ከኢዮብ ሁሉንም ነገር እንዲወስድበት ከዚያም ኢዮብ እግዚአብሄርን ሲራገም እንደሚያይ ተናገረው (ቁጥር 11) ፡፡ እግዚአብሄር ኢዮብ የነበረዉን ሁሉንም ነገር በሰይጣን ኃይል ስር አስቀመጠዉ ነገር ግን ኢዮብን ራሱን እንዲነካዉ አልፈቀደለትም (ቁጥር 12) ፡፡ ሰይጣን ኢዮብን ሊፈትን ሄደ ፡፡ በዚህ በፍርድ ቤት መቀመጫ ኢዮብ ህይወቱ በእግዚአብሄር ኮሚቴ የተወያዩበት እንደሆነ እንኳን አያዉቅም ፡፡ አራት ጥፋቶች በፍጥነት በኢዮብ መንገድ ላይ የሚመጡ ነበሩ ፡፡

ኢዮብ (1፡ 13-19)፡ የሰይጣን ግብ ሁልጊዜ የሰዎችን ራዕይና ሀሳብ ከእግዚአብሄር ላይ መዉሰድ ነው ፡፡ የኢዮብ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች በሌላ ግብዣ ላይ ነበሩ፣ አንድ መልዕክተኛም ወደ ኢዮብ በመምጣት ከእርሱ በስተቀር ሁሉንም አገልጋዮች በመግደል በእርሻ ላይ ያሉትን በሮቹንና አህዮቹን የሳባ ሰዎች እንደወሰዷቸዉ ነገረው (ቁጥር 14-15) ፤ ከዚያም የመጀመሪያዉ መልዕክተኛ እየተናገረ ሁለተኛዉ መልዕክተኛ በመምጣት ከእርሱ በቀር ከሰማይ መብረቅ በመምጣት ሁሉንም በጎችና አገልጋዮች እንደ ገደላቸዉ ነገረው (ቁጥር 16) ፡፡

ከዚያም ሁለተኛዉ መልዕክተኛ እየተናገረ ሰዎስተኛዉ መልዕክተኛ በመምጣት ግመሎቹን እንደወሰዱዓቸዉና ሁሉንም አገልጋዮች እንደገደሏቸዉ ነገረው (ቁጥር 17) ፤ ከዚያም ሰዎስተኛዉ መልዕክተኛ እየተናገረ አራተኛዉ መልዕክተኛ በመምጣት የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ በታላቁ ወንድማቸዉ ቤት ኃይለኛ ንፋስ ቤቱ በላያቸዉ ላይ በመፍረሱ እንደ ሞቱና እርሱ ብቻ እንዳመለጠ ነገረው (ቁጥር 18-19) ፡፡

ኢዮብ (1፡ 20-22)፡ ኢዮብ ልብሱን በመቅደድ በማዘንም ራሱን ተላጨ ነገር ግን ወደ መሬት በመዉደቅ እግዚአብሄርን በማምለክ የነበረዉ ሁሉም ነገር እግዚአብሄር የሰጠዉ እንደ ነበር እዉቅና ሰጠ (ቁጥር 20-21) ፡፡ “ በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም ለእግዚአብሄርም ስንፍናን አልሰጠም “ (ቁጥር 22) ፡፡

መደምደሚያ

ለሙከራዎች ራሳችንን በማቅረብ አሁንም እግዚአብሄርን እናምልክ “ለምን “ እንደሆነ ምክንያቱ አናዉቅም ነገር ግን የእግዚአብሄር ፍቃድ በእነርሱ ላይ ለራሱ ምክንያት ይሆናል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 563.

  2. MacArthur, p. 563.

  3. MacArthur, p. 563.

  4. MacArthur, p. 563.

  5. MacArthur, p. 565.

  6. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 616.

  7. Nelson’s Commentary, p. 616.

  8. MacArthur, p. 569.

  9. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Acts (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), pp. 498–501.Study Notes, p. 21, available at https://planobiblechapel.org/ tcon/notes/pdf/esther.pdf.

ጥያቄዎች

  1. እንደ ቤተሰበ በኢዮ (1፡ 5) ኢዮብ ምን አደረገ ? ቤተሰብ ከሆናችሁ ስለ ልጆቻችሁ እንዴት ትማልዳላችሁ/ትፀልያላችሁ ?
  2. መለዓክቶች ወይም “ የእግዚአብሄር ልጆች “ ራሳቸዉን በእግዚአብሄር ፊት ለማቅረብ በመጡ ጊዜ እግዚአብሄር ሰይጣንን ከወዴት መጣህ ብሎ ጠየቀው ፤ እግዚአብሄር ሁሉን አዋቂ ሲሆን ለምን ጠየቀዉ ?
  3. ሰይጣን እግዚአብሄርን በምድር ላይ ሲዞርና ሲመላለስ ቆይቶ እንደ መጣ ነገረው ፤ በ1ጴጥ (5፡ 8) መሰረት ሰይጣን ሲዞር ምን ያደርጋል?
  4. ኢዮብን አንዲመለከተዉ ለሰይጣን መስጠት የእግዚአብሄር ባህሪይ እንደሆን ግለፁ ፡፡
  5. በጥቂት ስዓታት ዉስጥ ንብረቱንና ልጆቹን ሲያጣ የኢዮብ ምላሽ ምን ነበር ? ይህ የኢዮብን ባህሪይ እንዴት ይገልፃል ? ነገሮች በመጥፎ ሲሄዱባችሁ እንዴት ምላሽ ትሰጣላችሁ ምላሻችሁስ ምን አይነት ባህሪያችሁን ይገልጣል ?
  6. በኢዮብ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Job 1:21–22

“‘Naked I came from my mother’s womb, and naked I will leave this life. The LORD gives, and the LORD takes away. Praise the name of Yahweh.’ Throughout all this Job did not sin or blame God for anything.”

ኢዮብ በዖፅ አገር ይኖር ነበር ፡፡ እርሱም በምስራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ታላቅ ነበር ፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ፣ ከክፉም የራቀ ፍጹምና ቅን ነበር ፡፡ ሰይጣንም ምድርን ሲዞር ኢዮብን ያጠቃው ዘንድ እግዚአብሔር እንድፈቅድለት ጠየቀው ፡፡ እግዚአብሔርም ፈቀደለት ነገር ግን በኢዮብ በራሱ ላይ እጁን እንዳይዘረጋ ከለከለው ፡፡ ስለዚህም ሰይጣን የኢዮብን እንሰሳት ፣ አገልጋዮቹንና ልጆቹን ጭምር የሚያጠፋባቸውን አራት የተለያዩ አደጋዎች አዘገጀ ፡፡ በዚህ ሁሉ መከራ መሀል ኢዮብ በመሬት ላይ ወድቆ ለእግዚአብሔር ሰገደ “ እግዚአብሔር ሰጠ ፥ እግዚአብሔርም ነሣ ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን ። “ በዚህ ፈተና ውስጥ ኢዮብ በቅንነት ፣ ያለምንም መተላለፍ እንድሁም እግዚአብሔርን ስለምንም ሳያማርር ቀጠለ ፡፡

እንደ አማኝ መከራ ይገጥምህ ይሆናል ፡፡ አሁን እንኳ ሰይጣን ሊሰርቅ ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ያደባል ፡፡ በመሬት ላይ በፊትህ ስትሰግድና ፤ በህመምና ስቃይ ወደ እግዚአብሔር ስታለቅስ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንደሚሆን ተናግሯል ፡፡ በአደጋ ውስጥ ተስፋ ታደርግ ዘንድ እግዚአብሔር ምክንያትን ይሰጥሀል ፡፡ አይኖችህን በተነገረለት ቤዛ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አድርግ ፡፡ እግዚአብሔር ይሰጣል ደግሞ ይነሳል ፡፡ ይህ ቢሆንም ግን “ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን “ ማለትህን ትቀጥላለህን ? በመከራ መሀል እንኳ ሁነህ ሳለ እግዚአብሔርን ማመሰገን ምረጥ ፡፡ አወ መራራ ነው ነገር ግን ተስፋ ማድረግን ምረጥ ፡፡ እግዚአብሔር እንደገና እንደሚያነሳህ ፣ እንደሚያጸናህ ፣ እንሚያበረታህና ከመከራ ዘመንህ በኋላ እንደሚያግዝህ ተናግሯል ፡፡ የሰጠህን ተስፋ ጠብቅ ፡፡

“እንዲህም አለ፦ ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን ። በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም፥ ለእግዚአብሔርም ስንፍናን አልሰጠም ። “ - ኢዮብ 1፡21-22

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 1ኛ ሳሙኤል 2:6–7 — “እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል ። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል ። “
  • 1ኛ የጴጥሮስ 1:6–7 — “በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል ። “
  • 1ኛ የጴጥሮስ 5:10 — “ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል ። “