ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የመጨረሻዎቹ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍት ግማሹ ስለ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ እና ስለ ተቀመጡት ብዙ መልዕክቶቹ ነው ፤ ይህ የመጨረሻ ምዕራፍ 61 ወይም 62 ከክርስቶስ ሞት በኋላ የሆነ ስፍራ የተፃፈ ነበር ፡፡ ያለፈዉ ምዕራፍ ወደ ሮም ስለ ጳዉሎስ ጉዞ ይገልጻል ፤ በዛሬዉ ምዕራፍ በመጨረሻም ጳዉሎስ በሮም ደረሰ ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (28፡ 1-6)፡ ጳዉሎስና የጉዞ ጓደኞቹ የደረሱባት ደሴት መላጥያ ከኢጣሊያ ዳርቻ ከሲሲሊያ በስተደቡብ በኩል ነው ፡፡ ጳዉሎስ እና ተሳፋሪዎቹ ከዋና ወደ ዳርቻ ስለመጡ ረጥበዉ ነበር ነገር ግን “ በከፍተኛ ቸርነትም “ (ቁጥር 2) እሳትን አነደዱላቸው ፡፡ ነዋሪዎቹ እሳት ሲያነዱ ጳዉሎስ ኢየሱስ እንዳደረገዉ እንደ አገልጋይነት ስዕል ለመቀጠል እንጨት ለመሰብሰብ ሄደ “ እንዲሁም የሰዉ ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም “ (ማቴ 20፡ 28) ፡፡
ከሙቀቱም የተነሳ አንድ እፉኝነት ወጥቶ የጳዉሎስን እጅ ነደፈው ፤ ነዋሪዎቹም ጳዉሎስ እንደሚሞት አስበዉ ነበር ምክንያቱም እፉኝቱ ስለነደፈችዉ ለመኖር መፈቀዱ “ ፍትህ/ትክክል “ አይደለም ፤ ይሁን እንጂ ጳዉሎስ ምንም እንዳልተፈጠረ እፉኝቱን ከእጁ ላይ በማራገፍ በእሳት ዉስጥ ጣለው ፡፡ ነዋሪዎቹም በመርዙ ምክንያት ጳዉሎስ ያብጥ ወይም በሞት እንደሚወድቅ ቢጠብቁም ምንም ነገር አልተፈጠረም ፤ ከዚህም የተነሳ ነዋሪዎቹ/ተወላጆቹ ጳዉሎስ በእርግጥ አማልክት እንደ ነበር ወሰኑ ፡፡ ነዋሪዎቹ ያስተዋሉት ከሰዉ የበለጠዉ ነገር ስለ ጳዉሎስ የተለየዉ ነገር ነበር ፤ የእግዚአብሄርን መገኘት በእርሱ ዉስጥ አስተዋሉ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (28፡ 7-10)፡ “ የደሴቲቱ አለቃ “ ፑፕልዮስ ጳዉሎስንና የጉዞ ጓደኞቹን በመቀበል ለሰዎስት ቀን ተንከባከባቸው ፡፡ የፑፕልዮስ አባት “ በንዳድና በተቅማጥ ታሞ ነበር “ (ቁጥር 8) ፤ ጳዉሎስ ከፀለየለትም በኋላ እግዚአብሄር ፈወሰዉ ፡፡ ቃሉም በደሴቱ ዙሪያ ተሰማ/ተሰራጨ “ የቀሩትም …ደዌ የነበረባቸው እየመጡ ተፈወሱ “ (ቁጥር 9) ፡፡ ጳዉሎስ በቀላሉ ለፑፕልዮስ አባት በመፀለይ ለእግዚአብሄር በመታዘዝ ተጓዘ ፤ ጳዉሎስ እንደ ሐዋሪያ በነበረው ስልጣን በኩል እግዚአብሄር አባትዬዉን ፈወሰው ፡፡ በዚያ ድርጊት የእግዚአብሄር ክብር በታዬ ጊዜ፣ ነዋሪዎቹ በማየት የአዩት አካል ለመሆን ፈለጉ ፡፡ ለጳዉሎስና ለተሳፋሪዎቹ የሚሄዱበት ጊዜ በመጣ ጊዜ ነዋሪዎቹ ለጉዞአቸዉ የሚያስፈልጋቸዉን ሁሉንም ነገር ሰጧቸው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (28፡ 11-16)፡ ጳዉሎስ የተሳፈረባት መርከብ “ የመንታ ወንድማማቾቹ “ ጣዖት አማልዕክት ማሳያ ከመርከቢቱ ኋላ ክፍል ላይ ነበር ፤ ጳዉሎስ ከዚህ ጣዖት ማሳያ ፈርቶ አልራቀም ፤ ይልቁንም ምስጢረኛዉ እግዚአብሄር ሮም የሚደርስበትን መላ ሰጥቶት በነበረው በስልጣኑ ተጓዘ ፡፡ ከብዙ የመቆም ቀናት በኋላ በመጨረሻም ጳዉሎስ ሮም ደረሰ ፤ ሮምም በመድረሱ በከተማዋ ያሉ አማኞች ጳዉሎስን ሰላም ሊሉት መጡ ፡፡ ኃላፊዉ/ተቆጣጣሪዉ በሆነዉ በመቶ አለቃዉ ፊት ሞገስ በማግኘቱ ጳዉሎስ ከሚጠብቀዉ ወታደር ጋር በራሱ እንዲቀመጥ ተፈቀደለት ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (28፡ 17-20)፡ በሮም ከደረሰ ከሰዎስት ቀናት በኋላ ጳዉሎስ የአይሁድ መሪዎችን ቤቱ ጠራቸው ፡፡ ሲገናኙም ከኢየሩሳሌም አሁን እስካለበት ድረስ ጉዞዉን በማዉራት/በመናገር በሮም በእነርሱ ፊት ታስሮ የነበረበት ምክንያት የጳዉሎስ እምነት በኢየሱስ እንደ መሲህ “ ስለ እስራኤል ተስፋ “ እንደ ነበር ጠቅለል አድርጎ ነገራቸው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (28፡ 21-28)፡ የአይሁድ መሪዎች ከኢየሩሳሌም ከአይሁድ ስለ ጳዉሎስ ምንም ነገር አልሰሙም ነበር ነገር ግን “ ስለዚህ እምነት “ ክርስቲያን ስለመሆን “ በየስፍራዉ ሁሉ እንዲቃወሙ “ (ቁጥር 22) ስለሚያዉቁት ብቻ ለመስማት የጓጉ ነበሩ ፡፡ ለመስማት ወደ ጳዉሎስ ቤት በመጡ ጊዜ ከህግና ከነቢያት ስለ ኢየሱስ የሚያጋራቸዉን እርሱን ብቻ በመስማት ሁሉንም ቀን ተቀመጡ ፡፡ ጳዉሎስ አንዳንዶቹን እንዲያምኑ አሳመናቸዉ ነገር ግን ሌሎቹ ግን አላመኑም ፤ ጳዉሎስ ላላመኑት አይሁዶች በምላሹ በቤቱ ቀርተዉ የነበሩትን እንዲሄዱ የሚመራ ኢሳ (6፡ 9-10) ጠቀሰላቸዉ (ቁጥር 26-27) ፡፡ ጳዉሎስ ስለ አይሁዶች ኢየሱስን ስለ አለመቀበል በሮሜ መፅኀፍ ሮም ከመድረሱ አራት አመት በፊት አካባቢ ፅፏል ፤ ይህ ለእርሱ አዲስ አልነበረም፣ ይህ በጣም ለምዶት የነበረዉ ነገር ነበር ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (28፡ 28-31)፡ አይሁዶች ከቤቱ ሲሄዱ ወንጌል “ ለአሕዛቦች ተላከ፣ እነርሱም ደግሞ ይሰሙታል “ (ቁጥር 28) በማለት ጳዉሎስ ተናገረ ፡፡ በቀጣዮቹም ሁለት አመታት ጳዉሎስ በቤቱ በመቀመጥ “ ማንም ሳይከለክለዉና በሙሉ ድፍረት “ ወንጌልን ሰበከ (ቁጥር 31) ፡፡
መደምደሚያ
በአገልግሎቱ የጳዉሎስ ድፍረት ስር የተመዘገቡ/የተብራሩ አምስት ሀሳቦች አሉ፡
- መቀየሩ - በሐዋሪያት ስራ 9 ጳዉሎስ ኢየሱስን በደማስቆ መንገድ ላይ አገኘው ፤ “ ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ ፡- ሳዉል ሳዉል ስለ ምን ታሳድደኛለህ ? የሚለዉን ድምጽ ሰማ ፡፡ ጌታ ሆይ ማን ነህ ? አለው ፡፡ እርሱም ፡- አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ ፤ የመዉጊያዉን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃ አለው “ (ሐዋ 9፡ 3-5) ፤ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያንን ከማሳደድ ህይወቱን ለጌታ ወደ ማኖር ሄደ ፡፡
ጥሪዉ - “ ተነስተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገዉ ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሀል አለው “ (ሐዋ 9፡ 6) ፤ ጳዉሎስም ለኢየሱስ እሺ አለዉ ኢየሱስም የሚያደርገዉን ነገረው ፡፡ ለእርሱ የሆነ ነገር እንድናደርግ ሁላችንም በጌታ የተጠራን ነን ፡፡
ጥሪዉ የተረጋገጠ ነበር(ጥሪዉ ተረጋገጠ) – “ በደማስቆ ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበር ጌታም በራዕይ ሐናንያ ሆይ አለዉ ፡፡ እርሱም ጌታ ሆይ እነሆኝ አለ ፡፡ ጌታም ተነስተህ ቅን ወደ ሚባለዉ መንገድ ሂድ በይሁዳ ቤትም ሳዉል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰዉ ፈልግ ፤ እነሆ እርሱ ይጸልያልና ፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰዉ ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቶአል አለው ፡፡ ሐናንያም መልሶ፡- ጌታ ሆይ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰዉ ከብዙዎች ሰምቼአለሁ ፤ በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ስልጣን አለዉ አለ ፡፡ ጌታም፡- ይህ በአሕዛብም በነገስታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነዉና ሂድ ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና አለው ! “ (ሐዋ 9፡ 10-16) ፡፡ ሐናንያ ጳዉሎስ ከእግዚአብሄር እንደሰማ ጥሪዉን አረጋገጠ ፡፡
ተልዕኮዉ (አገልግሎቱ) – “ ከዚያም እኔን ሩቅ ለአሕዛቦች ስለምልክህ ሂድ አለኝ “ (ሐዋ 20፡ 21) ፤ እግዚአብሄር ጳዉሎስን ለአሕዛቦች ላከው ፤ ጳዉሎስ እግዚአብሄር “ ሂድ “ ሲለዉ ሰማ ሄደም ፡፡
ንግግሩ/ግንኙነቱ - “ ነገር ግን በእናቴ ማህፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋዉም የጠራኝ እግዚአብሄር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ ወዲያዉ ከስጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም “ (ገላ 1፡ 15-16) ፡፡ እግዚአብሄር ምን እንድታደርግለት እንደጠራችሁ ለሌሎች ሰዎች የምትናገሩት የሆነ ነገር አለ - የሰማችሁት እዉነት እንደሆነ እንደገና የሚያረጋግጥ ፡፡ ጳዉሎስ ደግሞ ደግሞ እንደ ገና ከሌሎች ሰዎች ጋር ምን እንዲያደርግ እግዚአብሄር እንደ ጠራዉ ተነጋገረ ፤ ይህን በትዕቢት አላደረገም ነገር ግን በዚህ ሌሎች እንደ ራሱ ማስታወሻነት እና ለተጠያቂነት እያደረገ የነበረዉን ይረዱታል (ኤፌ 3፡ 1-2, 8፣ 1ጢሞ 2፡ 7) ፡፡
ልክ እንደ ጳዉሎስ ሁላችሁም ጥሪ አላችሁ ፡፡ በተጠራችሁ ጊዜ እግዚአብሄር እንድታደርጉት የጠየቃችሁን ለማድረግ ስልጥን ተቀብላችኋል ፡፡
ጥያቄዎች
-
በሐዋ (28፡ 3) በነደፈዉ እፉኝት ለምን አልተጎዳም ነበር (ማር 16፡ 17-18) ? የተወላጆቹ/የነዋሪዎቹ ምላሽ/ሁኔታ እንዴት ነበር ?
-
ጳዉሎስ እየጠበቀ በነበረዉ ጠባቂ ወታደር ስፍራ ራሳችሁን አስቀምጡ (ሐዋ 28፡ 16) ፤ ከሁሉም ፈዉሶችና ተዓምራቶች ምስክርነት በኋላ ምን ታስባላችሁ ? የጳዉሎስን ትምህርት ከሰሙት ዉስጥ ብዙዎቹ ወደ ክርስቶስ አለመምጣታቸዉ አላስገረማችሁም ? ይህ ኢየሱስ ከነበረበት እንዴት ይለይ ነበር ? ይህ ስለ ሕዝቡ ልብ ሁኔታ ምን ይላል ?
-
በሮም የነበሩት አይሁዶች ስለ ጳዉሎስ መጥፎ ነገር ለምን እንዳልሰሙ ምን ትላላችሁ (ሐዋ 28፡ 21) ?
-
በአሁኑ ጊዜ ክርስቲያኖች የኢየሱስ ወንጌልን ለመስበክ አዲስ ኪዳንን ይጠቀማሉ ፤ ጳዉሎስ የኢየሱስን ወንጌል በአይሁዶች ላይ እንዴት ሰበከ ? (ሐዋ 28፡ 23)
-
አይሁዶች አልቀበልም ባይሉት ኖሮ ወንጌል ለአሕዛቦች ይመጣል ብላችሁ ታስባላችሁ/አይሰማችሁም ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም/አይሰማችሁም ?
-
በሐዋሪያት ስራ 28 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 28:5–6
“However, he shook the creature off into the fire and suffered no harm. They expected that he would swell up or suddenly drop dead. But after they waited a long time and saw nothing unusual happen to him, they changed their minds and said he was a god.”
ጌታ እንደተናገረው ጳውሎስና ሁሉም የመርከቢቱ ተሳፋሪዎች በደኅና መላጥያ ወደ ምትባል ደሴት ዳርቻ ደረሱ ፡፡ የደሴቲቱም ነዋሪዎች በቸርነት ተቀበሏቸው ፡፡ ጳውሎስ እሳት ለማንደድ ጭራሮ ሲጨምር እፉኝት ነደፈችው ፡፡ ሰዎቹም እጁ አብጦ ይሞታል እያሉ ሲጠብቁ ነገር ግን ጳውሎስ እባቧን ወደ እሳቱ አራገፋት ፤ ምንም ጉዳትም አላስተናገደም ነበር ፡፡ ጥንካሬውና መልካም ጤንነቱ ሰዎቹን አስደነገጠ ስለዚህም አከበሩት ፡፡
በትንሷ የመላጥያ ደሴት ሳይቀር ጳውሎስ ተፈትኖ ነበር ፡፡ የምትሄደው የትም ይሁን በጌታ ስልጣን ፣ በእርሱ ብርታት ለእርሱ ክብር ስትራመድ ጠላት በዙሪያህ ይዞራል ፡፡ ፈተናው ይመጣል ፡፡ ነገር ግን ጌታ በውጊያው ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ አለትህ ነው ፤ እርሱ መሸሸጊያህ ነው ፡፡ እርሱ ለአንተ ይወጋል ፡፡ እንዳትፈራ ነገር ግን ንቃ ፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ለጌታ ታዘዝ ፤ ሰይጣንን ግን ተቃወመው እርሱም ከአንተ ይሸሻል ፡፡ የጦር ዕቃህን ልበስ ስለዚህም ጠላት ሲመጣ ፣ የእርሱን ሽንገላ መቃወም ትችላለህ ፡፡ ጓደኛዬ በአንተ ላይ የተሰራ ማንኛውም መሳሪያ አይከናወንም ፡፡ ስለዚህ ከኢየሱስ ጋር መራመድህን ቀጥል ፡፡ እርሱ በውስጥህ ብርቱ ነው ! አንተ ጸንተህ ስትቆም ሰዎች ኢየሱስን በአንተ ውስጥ ያያሉ ፡፡
“ እርሱ ግን እባቢቱን ወደ እሳት አራገፋት አንዳችም አልጐዳችውም ፤ እነርሱም፦ ሊያብጥ ወይም ወዲያው ሞቶ ሊወድቅ ነው ብለው ይጠባበቁት ነበር ብዙ ጊዜ ግን ሲጠባበቁ በእርሱ ላይ የሚያስገርም ነገር ምንም ባላዩ ጊዜ፦ ይህስ አምላክ ነው ብለው አሳባቸውን ለወጡ ። “
- ሐዋርያት ሥራ 28፡5-6
ተጨማሪ ጥቅስ
ሉቃስ 10:19 — “እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም ። “
1ኛ የጴጥሮስ 5:8 — “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና “
ኤፌሶን 6:11–12 — “ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።