Changing The Boat You Didn't Want to Be On
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 27 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሐዋሪያት ስራ 26 ጳዉሎስ ወንጌልን ከንጉስ አግሪጳ እና ከፊስጦስ ጋር ተካፈለ/ተነጋገረ ፡፡ አሁን ጳዉሎስ ወደ ሮም በመንገዱ ላይ ነው ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 27 ጳዉሎስ እንዴት ወደ ሮም ብዙ መንገዶችን እንዳገኘ ታሪኩን ይናገራል ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (27፡ 1-8)፡ አንድ ዩልዮስ የሚባል መቶ አለቃ ከሮም የምትመጣዉን መርከብ/ጀልባ በመቆጣጠሩ ጳዉሎስን እንዲጠብቅ ኃላፊነት ተሰጠው ፡፡ በአገልግሎት ከጳዉሎስ አጋር ከሆኑት አንዱ ከመቄዶንያ የሆነዉ አርስጥሮኮስ እና ሉቃስ በመርከቡ/በጀልባዉ ዉስጥ ነበሩ ፡፡ ጉዞአቸዉ በቂሳሪያ ጀመረ ፤ ከዚያም የአንድ ቀን ጉዞ ያክል በጀልባ በመጓዝ ወደ ሲዶና ወደብ መጡ ፤ ከሲዶናም በቆጵሮስ ዳርቻ በመጠጋት ጉዞአቸዉን ላይ በመቀጠል ወደ ሙራ ወደብ መጡ ፡፡ ከቆጵሮስ ሰሜን መስመርተከተሉ ምክንያቱም “ ንፋሱ በእነርሱ ላይ ስለ ነበር “ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አብዛኞቹ ጀልቦቻችን በአንዳንድ አንቀሳቃሾች/ሞተር ኃይል የተሰጣቸዉ ናቸዉ ነገር ግን የመጀመሪያዉ ዘመን ጀልባዎች ጉዞአቸዉን ለማድረግ በንፋስ ላይ የተደገፉ ነበር ፡፡ በሙራ አንድ መቶ አለቃ ከእስክንድርያ ወደ ጣሊያን ይሄድ የነበረ አንድ መርከብ ላይ እስረኞቹን አስቀመጣቸው ፡፡ በባህሩ ላይ ያለዉ ሁኔታ የዚህን ጉዞ እርምጃ አዘገየው ፤ በመጨረሻም “ በብዙ አስቸጋሪነት “ (ቁጥር 8) መልካም ወደብ ተብላ ወደ ምትጠራው ወደብ ደረሱ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (27፡ 9-12)፡ ቡድኑም በመልካም ወደብ ጥቂት ጊዜ አሳለፉ ምክንያቱም ቁጥር 9 ከደረሱ ጀምሮ “ ብዙ ጊዜ አሳልፈዉ ነበር “ ይላል ፡፡ የአይሁድ ሰዎች በጦም ጊዜአቸዉ ከመጥፎ የጉዞ ጊዜ ወደ መልካም የጉዞ ጊዜ ይለያሉ ፤ የጉዞ ወቅት በበዓለ ኃምሳ ቀን ድግስ አካባቢ የሚጀምርና የዳስ በዓልን ያልፋል ፡፡ በቁጥር 9 “ ፆም “ ከፋሲካ ጋር በደንብ የሚመሳሰል ሲሆን አንዳንድ ቦታዎች ላይ መስከረም 24 አካባቢ ነው ፤ በዚህ ጊዜ በባህሩ ላይ ንፋሱ ከፍተኛ ይሆናል፣ ጉዞዉንም አስቸጋሪ ያደርገዋል ፡፡ ይህን በማወቅ ጳዉሎስ መቶ አለቃዉንናመርከበኛዉን ከሄዱ አደጋ እንደሚገጥማቸዉ መከራቸው፡ እቃቸው፣ መርከባቸዉ እና ህይወታቸዉም ሊጠፋ እንደሚችል ፤ ይሁን እንጂ “ ወደቡ በዚያ ለመቆየት ያልተመቸ ስለ ነበር “ በጉዞ አቸዉ በመቀጠል በቀርጤስ ወደ ነበረዉ ወደብ ፍንቄ በመድረስ በዚያ ለመቆየት ለመሞከር ወሰኑ ፡፡ ጳዉሎስ ከእግዚአብሄር ሰማ ነገር ግን አብሯቸዉ የነበሩት ሰዎች እንዳለዉ ምላሽ አልሰጡም ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (27፡ 13-19)፡ ሰዎች እግዚአብሄር እንደ ሰጣችሁ ለተሰማችሁ መልዕክት ምላሽ በማይሰጡ ጊዜ ወደ ጥርጣሬ/(መጀመሪያ ወዳላችኋቸዉ እንዲያዩ በማድረግ) ልትገፏቸዉ ያስፈልጋችኋል ፡፡ በዚህ የጉዞ እርምጃ መጀመሪያ ላይ መርከቧ “ የተረጋጋ/የበረደ/ልከኛ የደቡብ ንፋስ “ ስለገጠማት ሁሉንም ጳዉሎስ እንዲቆዩባት መክሯቸዉ የነበረዉን ወደብ ትተዉ መሄዳቸዉ ትክክል እንደ ነበር አሰቡ ፡፡ ከእግዚአብሄር ሰምታችሁ ይሆናል ነገር ግን ነገሮች በተለዬ አቅጣጫ መሄድ ሲጀምሩ ታያላችሁ ፤ ወደ ልባችሁ በሚስጥር አለማመን ወይም ጥርጣሬ እንዲሆን ላለመፍቀድ ጠንቃቃ ሁኑ/ተጠንቀቁ ፡፡
“ከልከኛዉ የደቡብ ንፋስ “ (ቁጥር 13)ጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላ መርከቢቱ “ አዉራ ቄስ የሚሉት አዉሎ ነፋስ “ ገጠማት ፤ ምናልባትም ይህ ማዕበል በአደገኛነቱ አዉሎ ንፋስ ነው ፡፡ በኃይልም በእነርሱ ላይ በፍጥነት የመጣ አደገኛ ንፋስ ነው ፡፡ በአንድ የጉዞ ጀልባ እየተጓዙ እንደ ነበር እና በንፋስም ላይ እንደ ተደገፈች አስታዉሱ ስለዚህም ይህ ለእነርሱ መልካም ዜና አልነበረም ፡፡ ከእግዚአብሄር ስትሰሙ ነገር ግን ሌሎች ደግሞ ምላሽ ካልሰጡ ወደ ቅሬታቸዉ እንዲመለሱ መግፋት አለባችሁ ፡፡ ጳዉሎስ ይህን እንደሚሆን ነግሬአችሁ ነበር አላቸው ነገር ግን በተከተሉት በራሳቸዉ ኃሳብ ላይ ሙጭጭ አሉ ፤ አሁን ራሳቸዉን ሙሉ ለሙሉ በንፋሱ መካከል ላይ ምህረት በመጠየቅ በአዉሎ ንፋሱ መካከል ላይ አገኙት ፡፡ ነገሮች ከባድ ሆኑ “ እንደ ምንም ታንኳይቱን መቆጣጠር ቻሉ “ (ቁጥር 16) ፤ ታንኳ ወደብ በማይኖር ጊዜ ከጀልባ ወደ ዳርቻ እቃንና ሰዎችን ለሟጓጓዝ የሚጠቅም ትንሽ ነበር ፡፡ ታንኳይቱንም ድንበር ላይ በመዉሰድ አሰሯት ከዚያም በንፋሱ ኃይል ከመሰባበር ለመጠበቅ መርከቢቱን ሽቦ/ካቦ እና ገመድ በመጠቀም አጠናከሯት ፡፡ ነገሮች ለጳዉሎስና በታንኳይቱ በር ላይ ላሉት ሁሉ በእዉነት መጥፎ ነበሩ - በጣም ከባድ ስለ ነበር ጭነታቸዉን በበሩ ላይ መወርወር ስለጀመሩ ጥልቅ ባልሆነ ዉኃም ላይ መሄድ ቻሉ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (27፡ 20-26)፡ ንፋሱም ለብዙ ቀናት ቀጠለ ፤ ከዚህም በኋላ እንደሚተርፉ ትስፋ ቆረጡ ፤ ነገር ግን ጳዉሎስ አልደነገጠም ነበር በእምነት ተጓዘ እንጂ ፡፡ ጳዉሎስ ተሳፋሪዎቹ ስላልሰሙት ተበሳጨ/ተናደደ ፤ በዚያም ፋንታ ቀድሞ ወደ ተናገረዉ መልሶ በመግፋት ከእግዚአብሄር ቃል በመስማት አበረታታቸው ፡፡ በምርጫዉ ሳይሆን ጳዉሎስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ነበር ፡፡ ጀልባዉ ዉስጥ ያሉት ሁሉም ተስፋ ተሰጣቸው ፤ ነገር ግን ጳዉሎስ በእምነት ሁኔታዉን ለመቀየር ጀመረ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (27፡ 27-32)፡ ለ14 ቀናት ከዋለሉ በኋላ መርከበኞቹ ወደ ምድር እየደረሱ እንደ ነበር ማሰብ ጀመሩ ፤ የዉሃዉን ጥልቀት ለመለየትና ዉሃዉ ጥልቅ እንዳልነበር ለማወቅ ሁለት የጥልቀት መለኪያዎችን ወሰዱ/አደረጉ ፡፡ ምሽት ስለነበር በድንጋያማዉ ዳርቻ ላይ ኃይለኛ ስብራትን ለማስወገድ መልህቅን በመጣል “ ቀንም እንዲሆን ተመኙ/ፀለዩ “ (ቁጥር 30) ፡፡ ጳዉሎስ መርከበኞቹ እንደሚድኑ ነገር ግን መርከቢቱ እንደ ምትጠፋ ካረጋገጠላቸዉ ጀምሮ ሁለት ሳምንታት አልፎ ነበር ፤ በቄሳር ፊት ትቆማለህ የሚለዉ የእግዚአብሄር ቃል መፈፀም ለጳዉሎስ ዘግይቶ ነበር ፤ ጳዉሎስ በእስራት ሁለት አመት አሳለፈ ፤ ከዚያም በመጨረሻ ወደ ሮም የሚሄድ ጀልባ አገኘ፣ ጉዞዉም አስቸጋሪና የዘገዬ ነበር ፡፡ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር ለነቢዩ ዕባቆም “ ራእዩ ገና እስከ ተወሰነዉ ጊዜ ነው ወደ ፍጻሜዉም ይቸኩላል እርሱም አይዋሽም ፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሰዉ ፤ እርሱም አይዘገይም “ ብሉ ነገረው (ዕብ 2፡ 3) ፡፡ ጳዉሎስ መጓዙን ቀጠለ በእምነትም ጠበቀ ፡፡
መልህቅ ወደ ጣሉበት የማያዉቁት ዳርቻ ላይ እንደተቀመጡ ከተጓዦቹ ዉስጥ አንዳንዶቹ ታንኳይቱን በመተዉ ወደ ዳርቻ ለመሳብ/ለመጎተት በመሞከር ለማምለጥ ወሰኑ ፤ ጳዉሎስም መቶ አለቃዉን “ እነዚህ በመርከቡ ካልቆዩ አትድንም “ አለው ፡፡ እብደት በሆነዉ ክስተት መካከል ላይ ጳዉሎስ ለመርከበኞቹ እግዚአብሄር ሰጥቶት የነበረዉን ቃል መርከበኞቹ እስካሁን ጳዉሎስን ባያዳምጡም እንኳን ነገራቸዉ/አሳሰባቸው ፤ ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ ሰሙት ፡፡ ወታደሮቹም ቀድሞ ተጠብቀዉበት የነበሩትን ገመዶች በመቁረጥ ከመርከቧ ላይ እንዲወድቅ አደረጉት ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (27፡ 33-38)፡ የመርከቢቱ መርከበኞች/ተሳፋሪዎቹ ለ14 ቀናት ምግብ አልበሉም ፡፡ ጳዉሎስ ተሳፋሪዎቹን ስለሚተርፉ የሆነ ነገር እንዲበሉ አበረታታቸው ፡፡ ጳዉሎስ ዳቦ በመዉሰድ ምስጋና በመስጠት ለ276 የተሳፋሪ አባላት ዳቦዉን አከፋፈለ ፡፡ ጉዞዉ ወደ መጨረሻ ሲመጣ የጳዉሎስ እምነት የተገኘባትን ጀልባ እየቀየረ ነበር ፤ የጳዉሎስ እምነት ራሱን እና አብረዉት የሚጓዙትን ብቻ ላይ ተፅዕኖ አላደረገም ፡፡ ሙሉዉ ጀልባዉ/ታንኳይቱ ዉስጥ ያሉት 300 ያክል ሰዎች በጳዉሎስ እምነት ተፅዕኖ ተደረገባቸው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (27፡ 39-44)፡ አንድ ዳርቻም ባዩ ጊዜ መርከቢቱን ወደ ምድር ለመግፋት ተዘጋጁ ፤ መርከቢቱም ምድሩን በመታችዉ ጊዜ የመርከቢቱ ኋለኛዉ ክፍል በማዕበሉ መሰበር ጀመረ ፡፡ ወታደሮቹም እስረኞቹን ለመግደል ወሰኑ ምክንያቱም እስረኞቹ በልምዳቸዉ አምልጠዉ የሚተርፉ ከሆነ በዚህ ምክንያት ሊገደሉ ስለሚችሉ ፤ ይሁን እንጂ መቶ አለቃዉ በኃላፊነት ጳዉሎስን ለማዳን ስለፈለገ አንድ እቅድ አመጣ ፡፡ እየዘለሉም ወደ ምድር እንዲወጡ መዋኘት የሚችሉትን ሁሉ አዘዛቸው ፤ መዋኘት የማይችሉት ጣዉላ ወይም የመርከብ ስብርባሪ በማግኘት መሬት ላይ መድረስ ይችላሉ ፡፡ እግዚአብሄር በመርከቧ በር ላይ ያሉት ሁሉም እንደሚድኑ ቃል ስለገባላቸው በስብርባሪ እና በመዋኘት መሬት ላይ ለመድረስ ለማይችሉትም ጥበቃ አደረገላቸው ፡፡
መደምደሚያ
ሁሉም ወደ ዳርቻ ደረሱ ፤ ጥቂቶች በስብርባሪ ሲንሳፈፉ ጥቂቶች በዋና ደረሱ ነገር ግን ሁሉም እግዚአብሄር ለጳዉሎስ ተስፋ ገብቶለት የነበረዉን ፍሬ አዩ ፡፡ ጳዉሎስ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ተከተለ ፤ እርሱ ብቻ አልነበረም የዳነዉ፣ የጉዞ ጓደኞቹ ብቻ አልነበሩም የዳኑት ነገር ግን ጠቅላላ የመርከቡ ሰዉ ሰዎስት መቶ ያክል ሰዉ በጳዉሎስ እምነት ምክንያት ድኗል ፡፡ ወደ ማትፈልጉበት አቅጣጫ የምትሄዱበት ስዕላዊ መርከብ (የመርከብ ምሳሌ በሚሆን ነገር ) ላይ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ ፤ እግዚአብሄርን ልታወሩት ያስፈልጋችሁኋል ምክንያቱም በዚያ አካባቢያችሁን ለመቀየር ሊጠቀምባችሁ ይሞክር ይሆናል ፡፡
አሁን ባላችሁበት ጀልባ ላይ ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው ? ፍራትን ወደኋላ በማስቀረት ከቅሬታ ርቀን በመሄድ እግዚአብሄርን እንታመን ፡፡ እግዚአብሄር በሁኔታዉ ዉስጥ እስኪመጣ ድረስ በእምነት እንጓዝ ፡፡
Charles Ellicot, Ellicot’s Bible Commentary, v. 3 (Delmarva Publications: USA, 2015) 27:9; available at: https://books.google.com/books?id=5NndCgAAQBAJ&printsec=frontcover&dq=elli- cott%27s+commentary+for+english+readers+acts&hl=en&sa=X&ved=0ahUKEwip_LCZxpjfAhVSbKwKHfr6ACgQ6AEIODAD#v=onepage&q&f=false.
ጥያቄዎች
-
በሐዋ (27፡ 1-8) ሉቃስ ጉዞአቸዉን የተጓዙባቸዉን ስፍራዎች፣ የነበሩባቸዉን መርከቦችና ገጥመዋቸዉ የነበሩትን ሰዎች በማካተት በዝርዝር ገልፆአል ፤ ይህን በሐዋሪያት ስራ መፅኀፍ ዉስጥ አደረገ ፡፡ ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ? ይህ አስፈላጊ የሖነዉ ለምን ነበር ?
-
በሐዋ (27፡ 9-10) ጳዉሎስ በመርከቢቱ ላይ ያሉትን ሰዎች ህይወታቸዉን እንደሚያጡ አስጠነቀቃቸው ፤ ይህን እንዴት አወቀ ? በተቃራኒ ምን ተፈጠረ/ሆነ ? ከጳዉሎስ ጋር ተሳፍረዉ የነበሩትን ሁሉ ህይወታቸዉን እግዚአብሄር ለምን እንዳዳናቸዉ ምን ታስባላችሁ ?
-
በሐዋ (27፡ 24) የእግዚአብሄር መለዓክ ጳዉሎስን በቄሳር ፊት ስለሚቆም እንዳይፈራ ነገረው ፤ በቄሳር ፊት መቆም ለጳዉሎስ አስፈላጊነቱ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ? (ሐዋ 26፡ 2-5)
-
ጳዉሎስ ለመቶ አለቃዉና ለወታደሮቹ “ እነዚህ በመርከቡ ካልቆዩ እናንተ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ለምን አላቸው “ ? (ሐዋ 27፡ 31)
-
ጳዉሎስን ወደ ደህንነት ማምጣት ለመቶ አለቃዉ አስፈላጊነቱ ምን ነበር (ሐዋ 27፡ 43) ? ይህን ሀሳብ የት ሊያገኘዉ ቻለዉ ?
-
በሐዋሪያት ስራ 27 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 27:20, 22
“For many days neither sun nor stars appeared, and the severe storm kept raging. Finally, all hope that we would be saved was disappearing. Now I urge you to take courage, because there will be no loss of any of your lives, but only of the ship.”
ልክ ጌታ እንደተናገረው ለቄሳር ይግባኝ ማለት ይችል ዘንድ ጳውሎስ ወደ ሮም እንድሄድ ንጉሥ አግሪጳ አዘዘ ፡፡ ጳውሎስ ፣ ሉቃስና ሌሎች እስረኞችም በተጨማሪም ዩልየስ የተባለ መቶ አለቃ ሆነው ከቂሳርያ ወደ ሮም ጉዞ ጀመሩ ፡፡ መርከቧም ነፋሱ ወደ ኋላና ወደ ፊት በውኃው ላይ በገለበጣት ጊዜ ያልታሰበ ችግርን አስተናገደች ፡፡ አንዱ ነፋስ ቀላል ነበረ ነገር ግን ሌላው አውሎ ነፋስ ነበረ በመጨረሻም መርከቧ በማልታ ደሴት አካባቢ አደጋ ገጠማት ፡፡ ተጓዦቹም ተስፋ ቆረጡ አዘኑም ፡፡ ሆኖም ግን በድቅድቁ ጨለማ ሌሊት በዚያ የአውሎ ነፋስ መአት ጌታ ለጳውሎስ ተገልጦ በመርከቡ ላይ ያሉት ሁሉም እንደሚተርፉ ተናገረው ፡፡ ጌታ ለተጓዞቹ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነውና እንድበረቱ ደግሞም እንዳይፈሩ ጳውሎስን ተጠቅሞ ተናገራቸው ፡፡
ለቀናት እንደሰጠምክ ወይም በጨለማ እንደተከበበክ ፣ እንዳለቀልህ ተሰምቶህ ያውቃል ? ልክ እንደዛሉት ተጓዦች ምንም ተስፋ እንደሌለ ይሰማሀል ? ዛሬ ይህን ቃል ከጌታ መስማት የስፈልግህ ይሆናል ፡- ጌታ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ በርታ ጓደኛዬ ፤ በክርስቶስ ተስፋ አለህ ፡፡ ጌታ ይወድሀል እናም ሊያድንህ ይችላል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በህይወት ውስጥ ከባዱ ነገር በእምነት መራመድ አይደለም በእምነት መጠበቅ እንጅ ፡፡ በህይወትህ ቀጥሎ ምን እንደምታደርግ ግራ ሲገባህ ወይም ጨለማ ሲከብህ የጌታን ስም ጥራ ፡፡ በጨለማው ላይ ስልጥን ፡፡ ኢየሱስ በእርሱ ድል እንደምታደርግ ተናግሯል ፡፡ እርሱ ቃሉ ለእግርህ መብራት ለመንገድህም ብርሀን እንደሚሆን ተናግሯል ፡፡ ዛሬ ቀጣይ የምትወስደውን እርምጃ ካላወክ የእግዚአብሔርን ቃል ግለጥ ፡፡ እርሱ አቅጣጫን እንድሰጥህ ቃል ገብቷል ፡፡ ተረጋጋና እርሱን እመነው ፡፡
“ ብዙ ቀንም ፀሐይን ከዋክብትንም ሳናይ ትልቅ ነፋስም ሲበረታብን ጊዜ፥ ወደ ፊት እንድናለን የማለት ተስፋ ሁሉ ተቈረጠ ። አሁንም፦ አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና ። “ - ሐዋርያት ሥራ 27፡20 ፤ 27፡22
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኢሳይያስ 41:10 — “ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ ። “
- ዕንባቆም 3:17–19 — “ ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል ። “
- ሶፎንያስ 3:17 — “ አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።