Paul's Defense Before King Agrippa
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሐዋሪያት ስራ መፅኀፍት ዉስጥ በወንጌል ዉስጥ ደቀ መዛሙርቱን ኢየሱስ ሞደል እንደሆናቸዉ ሲጓዙ አይተናል ፡፡ ሐዋሪያቱ በአገልግሎታቸዉ በመንፈስ ቅዱስ ስልጣን ተጓዙ ፡፡ በዛሬዉ ምዕራፍ ጳዉሎስ እንደ ገና በደማስቆ መንገድ ላይ የገጠመዉን ይናገራል ፤ ጳዉሎስ “ በአሕዛብም በነገስታትም በእስራኤል ልጆችም ፊት ስሙን ይሸከም ዘንድ የተመረጠ የኢየሱስ እቃ “ ነበር (ሐዋ 9፡ 15) ፡፡ በምዕራፍ 26 ጳዉሎስ በንጉስ አግሪጳ ፊት ቆመ ፤ ሐዋሪያት ስራ 26 የሐዋ (9፡ 15) መፈፀም ነው ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (26፡ 1-11)፡ አግሪጳ ለጳዉሎስ ስለራሱ እንዲናገር ፍቃድ ሰጠው ፡፡ የአክብሮትና የጨዋነት ምልክት ካሳዬ በኋላ ጳዉሎስ መከራከሪያዉን ማቅረብ ጀመረ ፤ ጳዉሎስ አግሪጳን “ በአይሁዶች ስርዓትና ክርክር “ (ቁጥር 3) በአግሪጳ ማወቅ አመሰገነው ፤ ይህ ለጳዉሎስ ለአግሪጳ የተወደደ እንደሆነ የገለፀበት መንገድ ምናልባትምእዉነት ነበር ፡፡ በኃይለኛዉ በቀላሉ ሁኔታ ጳዉሎስ በጥሩ/በመልካም ንግግር ተመራ ፤ በተጨማሪም አግሪጳን ሲጠይቅ “ ንጉስ አግሪጳን ሆይ ነቢያትን ታምናለህን ? እንድታምናቸው አዉቃለሁ “ (ቁጥር 27) በማለት በመልካም ንግግር ዘጋ ፡፡
ዋይርስቤ ጳዉሎስ ለአግሪጳ በመከላከያዉ አምስት ቁልፍ ንግግሮች ተመልክቷል ፡፡ መጀመሪያ ጳዉሎስ አግሪጳ እንደ ፈሪሳዊ እንደ ኖረ እንዲያዉቅ ፈለገ (ቁጥር 4-11) ፤ በሐዋ (23፡ 6) ጳዉሎስ ራሱን “ እንደ አንድ ፈሪሳዊ፣ እንደ አንድ ፈሪሳዊ ልጅ “ ገለፀ ፡፡ ጳዉሎስ ለፊልጵስዮስ ሰዎች ራሱን “ በስምንተኛዉ ቀን የተገረዘሁ ከእስራኤል ትዉልድ ከብንያም ወገን ከዕብራዊያን ዕብራዊ ነኝ ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ ፈሪሳዊ ነበርሁ ፤ ስለ ቅንዓት ብትጠይቁ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ ፤ በሕግ ስለሚገኝ ፅድቅ ብትጠይቁ ያለ ነቀፋ ነበርሁ “ በማለት ገለፀ (ፊል 3፡ 5-8) ፡፡ ጳዉሎስ እንደ ማንኛዉም ፈሪሳዊ አልነበረም ፤ ጳዉሎስ በኃይል የተሰጠ/የሚሰራ ፈሪሳዊ ነበር ፡፡ በኢየሱስ የአሁኑን እምነቱን ለማሳየት ጳዉሎስ አግሪጳን ከየት እንደ መጣ እንዲያዉቅ ፈለገ ፡፡
ጳዉሎስ አሁን “ ከእግዚአብሄር ዘንድ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠዉ ተስፋ ቃል ለመፋረድ “ (ቁጥር 6) ቆሜአለሁ በማለት ጠቀሰ ፤ ይህ በሁለት ነገሮች ላይ ያማከለ ነበር፡ ትንሳኤዉንና የእስራኤልን ተስፋ ፡፡ ጳዉሎስ በኢየሱስ አካል መነሳት ያመነና እንዲሁም ደግሞ ይህ ማለት አሁንም እስራኤል የወደፊት ተስፋ እንደ ነበረዉ አምኗል ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄር ለእስራኤል ባደረጋቸዉ ሁለት ተስፋዎች ላይ አምኗል፡ በመጣዉ መሲህ እና የእግዚአብሄር መንግስት መልሶ ስለ መቋቋሙ/ስለመመስረቱ ፤ ጳዉሎስ እነዚህ ተስፋዎች በኢየሱስ ትንሳኤ የተፈፀሙ እንደሆኑ ተረድቷል ፤ ይህን ሀሳብ ለማጠናከር ጳዉሎስ “ 12 ነገዶቻችንን “ እና በመሲሁ ላይ ያልተጨበጠ ተስፋቸዉን ጠቀሰ ፡፡ የዚህ ተስፋ የኢየሱስ ሀሳብ ለእስራኤል በማቴ (19፡ 28)፡ “ እዉነት እላችኋለሁ እናንተስ የተከላችሁኝ በዳግመኛ ልደት የሰዉ ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአስራ ሁለቱ ዙፋን ጥቀመጣላችሁ “ የሚል ነው ፡፡
ከዚያም ጳዉሎስ በተጨማሪ ከቤተ ክርስቲያን አንፃር እንደ ፈሪሳዊ ህይወቱን አጉልቶ አሳዬ/ገለፀ ፤ ኢየሱስን በሚከተሉት ላይ የነበረዉን ተቃዉሞ እንደ ገና ተናገረ፣ ስለ ክርስቲያኖች መታሰር የእርሱን ሚና አሳዬ፣ ለክርስቲያኖች መገደል/ፍርድ የተመረጠ እንደ ነበር አመለከተ በተጨማሪም የኢየሱስን ስም በማጥፋት ክርስቲያኖች በሌሎች ከተሞች እንዲሆኑ /እንዲሰደዱ ለማድረግ እንደሞከረ አመነ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (26፡ 12-13)፡ ለአግሪጳ የጳዉሎስ ሁለተኛዉ ቁልፍ ንግግር ብርሃን አይቶ እንደነበር ነበር ፡፡ እንደ አንድ ፈሪሳዊ ጳዉሎስ በተመሳሳይ መንገድ በኃይማኖት መሪነት ስልጣን በስርሩ ወደ ነበሩት ተመሳሳይ ሰዎች ኋላ ይሄዳል ፤ የጳዉሎስ ጉዞ “ ከፅሀይ በሚበልጥ ብርሃን “ ተቋረጠ ፤ ይህ በእግዚአብሄር ስራ በኩል ብቻ ሊሆን የሚችል ነው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (26፡ 14-18)፡ ለአግሪጳ የጳዉሎስ ሰዎስተኛዉ ቁልፍ ንግግር አንድ ድምፅ መስማቱ ነበር ፡፡ ብርኃኑን ካዩ በኋላ ጳዉሎስና የጉዞ ጓደኞቹ መሬት ላይ ወደቁ ፤ አንድም ድምፅ በዕብራይስጥ “ ሳዉል ሳዉል ስለ ምን ታሳድደኛለህ ? የመዉጊያዉን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል “ (ቁጥር 14) አላቸው ፡፡ ይህ ቋንቋ ከዚህ በፊት ቀንበር አርፎበት ያልነበረን አንድ በሬን ይጠቅሳል ፡፡ መጀመሪያ ሲጠመድ አንድ በሬ መልሶ በመገረፍ ይገራል ፤ ይህን ለመዋጋት/ለመታገል ከበሬዎ የኋለኛዉ እግር መጨረሻ ላይ የሚያልቅ ምልክት አንድ ብትር አንድ ሰዉ ይይዛል ፡፡ በሬዉ ሲመታ ምልክቷን ይመታዋል በስፍራዉም ላይ ይቆማል ፤ በሬ ለቀንበሩ/ለጠመደዉ ሰው መታዘዝ ይማራል ፡፡ በዳማስቆ መንገድ ላይ ከገጠመዉ ነገር በፊት ጳዉሎስ ኢየሱስን ያለማቋረጥ ተቃዉሟል ፤ ከዚያም በኋላ ህይወቱን ለኢየሱስ አላማ ማስገዛት ተማረ ፤ ያ አላማም አሕዛቦች “ ከጨለማ ወደ ብርኃን ከሰይጣንም ስልጣን ወደ እግዚአብሄር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸዉን ትከፍት ዘንድ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ “ (ቁጥር 18) በማለት ወደ አሕዛብ የተላከ ነበር ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (26፡ 19-21)፡ ለአግሪጳ የጳዉሎስ አራተኛዉ ቁልፍ ንግግር ታዛዥ እንዳልነበር ነበር ፡፡ አላማዉን ከኢየሱስ ከተቀበለ በኋላ ጳዉሎስ አሁን የሚሰብከዉን ያምኑት የነበሩትን ለማሰር ሄዶበት ከነበረዉ በጣም ቅርብ በደማስቆና በኢየሩሳሌም ለእርሱ የተሰየመዉን ስራ በመስበክ ሄደ ፡፡ በአይምሮ መለወጡ በባህሪ መለወጡ የተደገፈ/የተረጋገጠ ነበር ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (26፡ 22-32)፡ ለአግሪጳ የጳዉሎስ አምስተኛዉ ቁልፍ ንግግር እስከዚህ ቀን ድረስ እንደቀጠለ ነበር ፡፡ ኢየሱስ እንዲሰራዉ ጠርቶት ከነበረዉ ነገር ጳዉሎስን ምንም አላስቆመዉም ፡፡ በሉቃ (9፡ 62) “ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሄር መንግስት የተገባ አይደለም “ ባለ ጊዜ በኢየሱስ ሀሳብ ዉስጥ ከነበረዉ ጳዉሎስ ተመሳሳይ ነበር ፡፡ አንዴ ከእግዚአብሄር ሰምታችሁ ወደ ቀድሞዉ ህይወት መንገዳችሁ ከተመለሳችሁ ለእግዚአብሄር የታዘዛችሁ አትሆኑም ፡፡ ይህን ጳዉሎስ “ ነቢያትና ሙሴ ይሆን ዘንድ ያለዉን ክርስቶስ መከራን እንዲቀበል በሙታን ትንሳኤ ለሕዝብና ለአሕዛብ ብርሃንን በመጀመሪያ ሊሰብክ እንዳለዉ ከተናገሩት በቀር አንድ ስንኳ የተናገረሁት የለም በማለት “ (ቁጥር 22-23) ድርጊት አደረገ ፡፡
የጳዉሎስ መከራከሪያ ጡዘት ላይ ፊስጦስ ጳዉሎስን አብድኃል በማለት ከሰሰው (ቁጥር 24) ፤ ፊስጦስ ጳዉሎስ በእምነቱ ስልጣን መጓዙን በማየት ጳዉሎስን ለእርሱ እንዳበደ ተመለከተው ፡፡ ጳዉሎስ ለቆሮንቶስ “ እብዶች ብንሆን ለእግዚአብሄር ነው ፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን ለእናንተ ነው “ (2ቆሮ 5፡ 13) ብሎ ፃፈላቸዉ ፡፡ ጳዉሎስ እንደ እብድ ታይቶ ከነበር፣ ከአይምሮ ዉጪ የሆነ መልዕክት ይዞ ስለነበር ነበር ፤ የኢየሱስ የራሱ ቤተሰቦች “ ከአይምሮ ዉጪ እንደ ነበር “ አስበዋል (ማር 3፡ 21) ፡፡
ጳዉሎስ በድፍረት የፊስጦስን ክስ በመቃወም ለንጉስ አግሪጳ ይግባኝ በማለት በግልፅ “ ንጉስ አግሪጳ ሆይ ነቢያትን ታምናለህን ? እንድታምናቸዉ አዉቃለሁ “ (ቁጥር 27) በማለት ጠየቀው ፡፡ ንጉስ አግሪጳ ክርስቲያን እንዲሆን ለማሳመን የጳዉሎስን ሙከራ እንዳላወቅ ለመምሰል ሞከረ ነገር ግን ጳዉሎስ የሚሰሙት ሁሉ ክርስቲያን እንዲሆኑ ለሁሉም ፍላጎቱን እንደገና ተናገረ ፡፡ ባለስልጣኖቹም ጳዉሎስን ትተዉ ዞር ካሉ በኋላ እርስ በእርሳቸዉ ጳዉሎስ ምንም ጥፋት አድርጎ እንደ ነበር ምንም ማስረጃ ሊያገኙ እንዳልቻሉና ለቄሳር ይግባኝ ብሎ ባይሆን መልቀቅ እንደሚቻል አወሩ ፡፡
መደምደሚያ
ጳዉሎስ በድፍረት ለንጉሱና ፍርድ ለሚሰጡት ከኢየሱስ ጋር ስለ መገናኘቱና እንዴት እንደ ቀየረው ተናገረ ፤ ጳዉሎስ ከእግዚአብሄር ተሰጥቶት በነበረዉ ስልጣን ተጓዘ ፤ ታስሮ እና በፍርድ ፊት ቆሞም እንኳን የጳዉሎስ ግብ ከነበሩበት አስፈላጊነት ዉጪ ከኃጢዓታቸዉ ንስሀ በመግባት ከሞት የተነሳዉን መሲሁን እንዲከተሉ የሚያደምጡትን ማሳመን ነበር ፡፡
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 403.
Wiersbe, p. 403.
Wiersbe, p. 403.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1415.
Wiersbe, p. 404.
Wiersbe, p. 404.
ጥያቄዎች
-
በንጉስ አግሪጳ ፊት ለፊት ለመናገር ለምን ጳዉሎስ ደስተኛ ነበር ?
-
ጳዉሎስ ንጉስ አግሪጳን በደማስቆ መንገድ ላይ ስለ ነበረዉ ቃለ ምልልስ በነገረዉ ጊዜ ከታሪኩ ምን አስወጣ/ተወ (ሐዋሪያት ስራ 9) ? ሙሉ ታሪኩ ተነግሮ ቢሆን ልዩነት ያደርግ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አያደርግም ?
-
በሐዋ (26፡ 23) ጳዉሎስ ኢየሱስ ከሞት የተነሳ የመጀመሪያዉ እንደ ሆነ ተናገረ ፡፡ መልሰዉ ይህን የሚጠቅሱ ጥቂት መፅሀፍቶች እነማን ናቸው ? (ማቴ 27፡ 51-53, 1ቆሮ 15፡ 20-21, ራዕ 1፡ 5)
-
በሐዋሪያት ስራ 26 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 26:29
“‘I wish before God,’ replied Paul, ‘that whether easily or with difficulty, not only you but all who listen to me today might become as I am—except for these chains.’”
ጳውሎስ አሁንም እንደገና በደማስቆ መንገድ ላይ ጌታ በእርሱ ላይ ታላቅ ብርሀን ከማብራቱ ጀምሮ ፤ ጌታ ከእርሱ ጋር እንዳወራ እናም ደግሞ የህይወት ጥሪ እንደሰጠው የህይወት ምስክርነቱን በንጉሥ አግሪጳ ፊት ቀርቦ አካፈለ ፡፡ ንጉሡ ጳውሎስ አብዷል ብሎ እስከሚያስብ ድረስ ጳውሎስ በንጉሥ አግሪጳ ፊት የወንጌል መልዕክትን ማካፈሉን ቀጠለ ፡፡ ጳውሎስ ከጌታ በሆነ ስልጣን በድፍረት መሰከረ ፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ምስክርነት አጥብቆ ያምን ስለነበር ጳውሎስ በድፍረት ንጉሡ በኢየሱስ እንድያምን ጠየቀው ፡፡
የልብህን አሳብ ፣ ምስክርነትህን ፣ እናም የመጣህበትን መንገድ ለሆነ ሰው አካፍለህ እናም ከዚያ “ በቃ በእርሱ እንድታምን እመኛለሁ ? “ ብለህ ታውቃልሀ ምክንያቱም ኢየሱስ የአንተን ህይወት ለውጧልና የምትወዳቸውንም ሰዎች ሕይወት እንድለውጥ ትፈልጋለህ ፡፡ ብዙውን ጊዜ ወንጌልን የምታካፍላቸው ፣ የምትወዳቸውና መልካምነትን የምታደርግላቸው ሰዎች በህይወትህ ይኖራሉ ፡፡ እስከአሁንም ግን እነርሱ አለማመንን መርጠዋል ፡፡ በተጨማሪም እንድያምኑ ልትገፋፋቸው ትፈልግ ይሆናል ነገር ግን ማስገደድ አትችልም ፡፡ ያ የአንተ ድርሻ አይደለም ፡፡ ንጹህ የሆነ ንስሀ ለመግባት እና በኢየሱስ ለማመን መንፈስ ቅዱስ ብቻ ልብን መንካት ይችላል ፡፡ እንደ አማኝ መጸለይህን ቀጥል ፣ እርሱም ወደ ሚመራህ መሄድህንና የክርስቶስን ፍቅር ማካፈልህን ቀጥል ፡፡ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ ፡፡ ዘርን እየዘራህ ነው ፡፡ ስለ ስሙ እና ስለ ክብሩ በፍቅር ስትመላለስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ይንቀሳቀሳል ፡፡
“ ጳውሎስም፦ በጥቂት ቢሆን ወይም በብዙ አንተ ብቻ አይደለህም ነገር ግን ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህ እስራቴ በቀር እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እለምናለሁ አለው ። “
- ሐዋርያት ሥራ 26፡29
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘካርያስ 4:6 — “ መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፡፡ “
ሐዋርያት ሥራ 26:17–18 — “ የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ ። “
1ኛ ቆሮንቶስ 3:6 — “ እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።