Acts Acts

Paul's Defense Before Governor Festus

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 25 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 361 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ሐዋሪያት ስራ 25 እንመለከታለን ፡፡ ስለዚህ ምዕራፍ የወደድኩት ነገር የምትፈልጉትን የፍርድ ቤት ድራማ የፍርድ ጉዳይ ማስቀመጡ ነው ፡፡ ጳዉሎስ የእምነቱን መከላከያ ሰጠ ፤ ጳዉሎስ በሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ አምስት መከላክያዎችን ሰጥቷል ፤ ምዕራፍ 25 አምስተኛዉ መከላከያ ነው ፤ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስቱ በሐዋሪያት ስራ 22፣ በሐዋሪያት ስራ 23 እና በሐዋሪያት ስራ 24 ላይ ይገኛሉ ፡፡ አምስተኛዉ መከላከያ ደግሞ ምዕራፍ 26 ላይ ይገኛል ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ቁልፍ ተዋናዮቹ/ገፀ ባህሪያቱ ፊስጦስ፣ የካህናቱ አለቃና የአይሁድ መሪዎች፣ ጳዉሎስ እና ንጉስ አግሪጳ ፡፡ በምዕራፉ ዉስጥ ስንጓዝ እነዚህን እያንዳንዳቸዉን እናያቸዋለን ፡፡

ትምህርት

ሐዋሪያት ስራ (25፡ 1-12)፡ “ ፊስጦም “ የሚለዉ ስም የደስታ ወይም ደስተኛ ማለት ነው ፡፡ ፊስጦም እንደ አስተዳዳሪ ይሁዳን ከፊልክስ በመዉሰድ ከፊልክስ በተሸለ የአስተዳደረ ነበር ፡፡ ፊስጦም በግዛቱ/በአዉራጃዉ ከደረሰ ከሰዎስት ቀናት በኋላ በዚያ ካሉት አይሁዶች ጋር ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ትስስር ለመገንባት ኢየሩሳሌም ሄደ (ቁጥር 1) ፡፡ ሊቀ ካህናቱና የአይሁድ ሽማግሌዎች በጳዉሎስ ላይ ጉዳያቸዉን በመናገር ጳዉሎስን ሊገድሉት ፈልገዉ ስለነበር ፊስጦምን ጳዉሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲጠራዉ ጠየቁት (ቁጥር 2-3) ፡፡ ይህ ጳዉሎስን በሁሉም ሰዉ ይጠላበት በነበረዉ በኢየሩሳሌም ለማግኘት ይሞከር የነበረ ህጋዊ ስልት/ሽግግር ነበር ፤ ፊስጦምም እምቢ በማለት በጳዉሎስ ላይ ክሳቸዉን እንዲያቀርቡ ከእርሱ ጋር ወደ ቂሳሪያ እንዲሄዱ ሽማግሌዎቹን ጋበዛቸው (ቁጥር 4-5) ፡፡ ፊስጦም በሂደቱ ድርሻዉን እያስታወቀ በከፍተኛ መልካምነት ጠንቃቃ መሪ እንደ ነበር እየተናገረ ነበር ፡፡ ፊስጦም በአይሁድ ሽማግሌዎች መካከል ከስምንት እስከ አስር ቀን በመቆየት ከጳዉሎስ ለመስማት ወደ ቂሳሪያ ተመለሰ (ቁጥር 6) ፡፡

ጳዉሎስ በፊስጦም ፊት በመጣ ጊዜ ከኢየሩሳሌም የመጡ በዚያ የነበሩ አይሁዶች በጳዉሎስ ላይ ኃይለኛ/ከባድ የሆነ ክስ አመጡ (ቁጥር 7) ፤ ነገር ግን ጳዉሎስ ስልጣኑ በክርስቶስ እንደ ነበርና የአይሁዶች ህግ፣ የቤተ መቅደስ ህግ ወይም ደግሞ ራሱም ቄሳርም በእርሱ ላይ ጥፋት ሊያገኙበት እንደ ማይችሉ መከላከያዎን በማሳየት ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 8) ፡፡ በአማራጭ አይሁዶችን ደስተኛ ለማድረግ ፊስጦም ጳዉሎስን ፊስጦም በሚሆንበት በእርሱ ፊት ክሱን ለመጋፈጥ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ ይፈልግ እንደሆን ጠየቀው (ቁጥር 9) ፤ ፊስጦም በነበረዉ ነገር ፖለቲካሊ እየተጫወተ ነበር ፡፡ የጳዉሎስን ንፁህነት ያዉቅ ስለ ነበርና በቂሳሪያ ለመጠበቅ ፈለገ ነገር ግን አይሁዶች ከእነርሱ ነገር እንደ ነበር እንዲያስቡ እየሞከ ነበር ፤ በባህሪዉ መፍረክረክ ነበር ፡፡ ጳዉሎስም በአይሁዶች ፊት ንፁህ በመሆኑ በቄሳር እንዲፈረድበት ጠየቀ (ቁጥር 10-11) ፡፡ ጳዉሎስ በክርስቶስ ስልጣኑን እና እንደ ሮማዊ ዜጋ በቄሳር ፊት ይግባኝ የመጠየቅ መብት እንደ ነበረዉ አሳዬ ፡፡ በክርስቶስ ስልጣን ስንጓዝ ለእኛ ያደረገዉን እና ምን እንድናደርግ እንደጠራን እናዉቃለን ፤ ፊስጦም እንደ ሮማዊ ዜጋ ጳዉሎስ ለፍርድ ለቄሳር ይግባኝ በመጠየቁ ተስማማ (ቁጥር 12) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (25፡ 13-22)፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ንጉስ አግሪጳና ሚስቱ በርኒቄም ፊስጦስን ለማለት ወደ ቂሳሪያ መጡ (ቁጥር 13) ፡፡ የአግሪጳ አባት የዘብድዮስን ልጅ እና የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን ገድሎት ነበር ፤ ቅድም ወንድ አያቱም ህፃኑን ኢየሱስን ሊገድል ሞክሮ የነበረዉ ታላቁ ሄሮድስ ነበር፣ ታላቁም አጎቱ የሮም ወታደር/አንቲጳስ መጥምቁ ዮሐንስን አንገቱን ቀላው/ቆረጠው ፡፡ ከክፉ ቤተሰብ የመጣ ክፉ ሰዉ ነበር ፤ በርኒቄም እህቱና ሚስቱ ነበረች ፡፡ በቂሳሪያም እያሉ ፊስጦስ የጳዉሎስን ጉዳይ ከሁሉም ዝርዝር ድርጊቱ ጋር ለንጉሱ አቀረበው (ቁጥር 14-18) ፤ በጣም በአስፈላጊነት ፊስጦም ጳዉሎስ ከአይሁዶች ጋር ስለ እምነታቸዉና ጳዉሎስ ከሞት ተነስቷል ስለ ሚለዉ ኢየሱስ ክርክር እንደነበራቸዉ ገለፀ (ቁጥር 19) ፡፡ ከዚያም ፊስጦስ ጳዉሎስ ጉዳዩ በቄሳር እንዲታይለት እንደ መረጠ ገለፀ/ተናገረ (ቁጥር 20-21) ፤ ንጉስ አግሪጳ የጳዉሎስን ጉዳይ እርሱም ለመስማት ጠየቀ (ቁጥር 22) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (25፡ 23-27)፡ በቀጣዩም ቀን ንጉስ አግሪጳ እና በርኒቄም ሁሉንም በማስቆም ከወታደሮቻቸዉ ጋር እና ከከተማዋ ታዊቂ ሰዎች ጋር በፍርድ ቤት ተገኙ ፤ ከዚያም ጳዉሎስን በንጉሱ ፊት አመጡት (ቁጥር 23) ፡፡ ፊስጦስም ጳዉሎስን ለንጉስ አግሪጳ በማቅረብ አይሁዶች ጳዉሎስ ከዚህ በኋላ እንዳይኖር እየጮኹ እንደ ነበር አብራራለት (ቁጥር 24) ፤ ፊስጦስ በጳዉሎስ ላይ ሞት የሚገባዉ ጥፋት እንዳላገኘበት ስላወቀ/ስለተቀበለ ወደ ቂሳሪያ ሊልከዉ ፈለገ ነገር ግን ወደ ቄሳር ለመላክ ለመርዳት የሚፅፈዉን ለማወቅ ፈለገ (ቁጥር 25-27) ፡፡

መደምደሚያ

ምንም መጥፎ ነገር አድርጎ እንዳልነበር የጳዉሎስን ቀለል ያለ ንግግር እናስታዉስ (ቁጥር 10) ፤ ጳዉሎስ የሚጓዝበትን ስልጣን ስለሚያዉቅ ወደ ፊትም በልበ ሙሉነት ተጓዘ ፡፡ ፊስጦስ የጳዉሎስን ጉዳይ በትክክል/ በፍትህ በመያዝ መልካም ስራ አደረገ ነገር ግን መነሳሳቱ/ፍላገቱ የጠራ/ፍፁም የሆነ አልነበረም ፡፡ በሮሜ (8፡ 5-8) ይህን ሀሳብ ንፁህ መሆን ወይም መልካም የመሆን ፍላጎት መኖር በሚል አድርሷል፡

“ እንደ ስጋ ፈቃድ የሚኖሩ የስጋን ነገር ያስባሉና እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ ፡፡ ስለ ስጋ ማሰብ ሞት ነዉና ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው ፡፡ ስለ ስጋ ማሰብ በእግዚአብሄር ዘንድ ጥል ነዉና ፤ ለእግዚአብሄር ሕግ አይገዛምና መገዛትም ተስኖታልና ፤ በስጋ ያሉትም እግዚአብሄርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም “ ፡፡

ጳዉሎስ እና ፊስጦስ ላይ ስንመለከት በሁለት ክፍል እናያለን፡

በእዉነቱ መልካም/ትክክል (ጳዉሎስ) የመልካም ነገር ከፍተኛ ተስፋ (ፊስጦስ)

ሀሳቡ - በመንፈስ ሀሳቡ - በስጋ

  • ሕይወትና ሰላም ሞት
  • እግዚአብሄርን ይፈልጋል እግዚአብሄርን ይጠላል

ጳዉሎስ በነገሮች ላይ በመንፈስ የሆነ አስተሳሰብ ነበረው ፤ ለዚያ ነዉ በስልጣን የሄደዉ ፡፡ ፊስጦስ በነገሮች ላይ በስጋ የሆነ አስተሳሰብ ነበረው - ብልጠት ነበር፣ ሞከረ ነገር ግን በስጋ ነበር ፡፡ በስጋ የሆኑት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይችሉም ፤ ፊስጦስ እግዚአብሄርን አላስደሰተም ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በሐዋ (25፡ 3) አንዳንድ ሰዎች ጳዉሎስን ለመጠበቅ በመዋሸት ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ ሊገድሉት ፈለጉ ፤ ጳዉሎስን በጉዞዉ ላይ ለመግደል ይህ የመጀመሪያ ጊዜ እቅዳቸዉ ነው ? አይደለም ከሆነ የመጀመሪያ ጊዜ ሁኔታዎቹ ምን ነበሩ ? (ሐዋ 23፡ 16)
  2. በሐዋ (25፡ 11) ወደ ቄሳር የጳዉሎስ ይግባኝ ማለት አላማዉ ምን ነበር (ሐዋ 28፡ 18-19) ? ጳዉሎስ ከዚህ በፊት በቄሳር ፊት ቆሟል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  3. ፊስጦስ ንጉስ አግሪጳ ጳዉሎስን እንዲሰማዉ ለምን ፈለገ (ሐዋ 25፡ 26) ? በግል አሰተያየታችሁ ፊስጦስ ንጉስ አግሪጳ አይሁዳዊ በመሆኑ ምክንያት ብዙ ያዉቃል ብሎ ማሰቡ ነበርን ? ለምን ወይስ ለምን አልነበረም ?
  4. በሐዋሪያት ስራ 25 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 25:25

“Now I realized that he had not done anything deserving of death, but when he himself appealed to the Emperor, I decided to send him.”

ገዥው ፊልክስ ጳውሎስን ለሁለት አመት በእስር ቤት ተወው ፡፡ ከዚያም ጶርቅዮስ ፊስጦስ ፊልክስን ተካ ፡፡ ወድያውኑ ፊስጦስ ገዥ ሆኖ ስልጣኑን ከተረከበ ከሶስት ቀን በኋላ የጳውሎስን ጉዳይ እንደሚቋጨው ተስፋ በማድረግ ሊቀ ካህናቱ ጉዳዩን እንደገና አቀረቡለት ፡፡ ሆኖም ግን እቅዳቸው ፈረሰ ፡፡ ጳውሎስ በፊስጦስ ፊት በተቀመጠ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ በሆነ ስልጣንና በበጎ ህሊና ተናገረ ፤ “ ምንም ጥፋት አላጠፋሁም “ አለ ፡፡ በመጨረሻም የጳውሎስ ክስ በቂሳርያ በንጉሥ አግሪጳ ፊት ቀረበ ፡፡ ገዥው ፊስጦስ ለንጉሡ ጳውሎስ ምንም ጥፋት እንዳላጠፋና ሞትም ይገባዋል ብሎ እንደማያምን ገለጸለት ፡፡

በገዥዎች ፊት ቀርበህ “ ምንም ጥፋት አላጠፋሁም “ ብለህ የምትናርበትን ህይወት እንዴት ይሆን የምትኖረው ? በትዕቢት አይደለም ነገር ግን ይልቁንም በኢየሱስ ስልጣን በመታመን እንጅ ፡፡ በክርስቶስ እንተ ፍጹም ጻድቅ ነህ ፡፡ አዲስ ፍጥረት ነህ አሮጌው ደግሞ አልፏል ፡፡ ይህ እውነት ነጻ ያወጣሀል ፤ በክርስቶስ አዲስ ተደርገሀል ፡፡ በስጋህ በትዕቢት ፣ በዕብሪት ፣ በቁጣ ፣ በፍትወት ወይም በራስ ወዳድነት ወደ ኃጢአትም ወደ ሚመሩ ነገሮችና መንገድህን በሚያስቱ ነገሮች እንዳትመላለስ ፡፡ ይልቁንም በመንፈስህ በሰላም ፣ በየዋህነት ፣ በደግነት ፣ በትዕግስት ፣ ራስን በመግዛት እና በፍቅር ተመላለስ ፡፡ ኢየሱስን ስትቀበልና በእርሱ መንፈስ ስትመላለስ ለውሸት ክስ ቦታ አይኖርህም ምክንያቱም በክርስቶስ ፍጹም ነጻነት ስላለህ !

“እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፥ እርሱም ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቈረጥሁ ። “ - ሐዋርያት ስራ 25፡25

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሐዋርያት ስራ 25:10— “ ጳውሎስ ግን፦ እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልሁም ። “
  • ሮሜ 8:5–9 — “ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው ። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል ፤ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም ። እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም ። “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 5:21 — “ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው ። “