The Jews Try To Kill Paul
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንደ ሚገረፉ ነግሯቸዋል፣ ጳዉሎስም “ እሺ ይምጣ/ይሁን “ በማለት መልሷል ፤ ጳዉሎስ ሙሉ በሙሉ ምንም ቢደርስበት የትም ስፍራ ቢወስደዉም ኢየሱስን ለመከተል የተዘጋጀ ነበር ፡፡ ትናትና በሐዋሪያት ስራ 23 መጨረሻ ላይ ጳዉሎስ በሚገባ/ደህንነቱ ተጠብቆ ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ወደ ቂሳርያ ሲሄድ በወታደሮች የታጀበ ነበር (ቁጥር 31) ፡፡ የሮም አዛዥም ለአስተዳደሩ ከጳዉሎስ ጋር በጳዉሎስ ላይ ስለተደረገዉ ዛቻ/ማስፈራራት የሚናገረዉን ደብዳቤ ላከው ፡፡ ጳዉሎስ በሄርዶስ ግቢ በጠባቂዎቹ ስር ተጠበቀ (ቁጥር 35) ፤ ያም ወደ ምዕራፍ 24 መሸጋገሪያን ይሰጣል ፤ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ በዋረን ዋይርስቤ የተለዩ ሰዎስት ገፀ ባህሪያት ላይ እንመለከታለን፡ ጠበቃዉ ጠርጠሉስን፣ ተከሳሹን ጳዉሎስንና ከንቱዉ ፊልክስ ናቸው ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (24፡ 1-9)፡ጠበቃዉ ጠርጠሉስ ፡፡ ጳዉሎስ ታላቁ ካህን ሐናንያ ከጥቂት ሽማግሌዎች ጋር እና ጠርጠሉስ ከሚባለዉ አንድ ጠበቃ ጋር በአስተዳዳሪዉ ፊት ከኢየሩሳሌም እስኪወርዱ ድረስ (ቁጥር 1) ፡፡ ጠርጠሉስ በጳዉሎስ ላይ ሐሰተኛ ክስ በማምጣት (ቁጥር 2) ተቆጣጣሪዉ ፊልክስ አምጥቶላቸዉ ስለ ነበረዉ ሰላም ሁሉ አመሰገነው (ቁጥር 2-3) ፡፡ ምሳ (26፡ 28) ከሸንጋዮች ተጠንቀቁ ምክንያቱም ጥፋትን ያመጣሉ ይላል ፡፡ ከሽንገላዉ በኋላ ጠርጠሉስ ፊልክስን በቸርነቱ የሚሉትን እንዲሰማቸዉ ጠየቀዉ (ቁጥር 4) ፤ ጠርጠሉስ ጳዉሎስን በሽታ ሆነ፣ በአሸባሪነት፣ በመናፍቃን አመፅ መሪነት እና ቤተ መቅደስን አርክሷል በማለት ከሰሰዉ (ቁጥር 5-6) ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ ይህን መሰረታዊ ክስ “ እንደ ፖለቲካዊ ክህደት፣ እንደ ኃይማኖታዊ ተቃርኖ እና ቤተ መቅደስን ማርከስ “ በማለት ይገልፀዋል ፤ እንዲሁም በተጨማሪም ጳዉሎስ “ በጠቅላላ በግዛቱ ዉስጥ በሙሴ ህግ ላይ ተናግሮ ስለነበር፣ ወደ አይሁዶች ቤተ መቅደስ ዉስጥ አሕዛቦችን አምጥቶ ስለ ነበር “ ለአመፅ ምክንያት ነበር ፡፡ የፖለቲካ ክህደት ክስ ጳዉሎስ አዲስ አስተዳዳሪ አስነስቷል በማለት ተመሰረተበት ፤ ቤተ መቅደሱን አርክሷል የሚለዉ ክስ አሕዛቦችን ወደ አይሁድ ቤተ መቅደስ አምጥቷል በማለት ተመሰረተበት ፡፡ በተጨማሪም ጠርጠሉስ አይሁዶች ጳዉሎስን ራሳቸዉ ሊፈርዱበት እንደፈለጉ እና በሮማዊዉ አዛዥ ሉስዮስ በኃይል ከእጃቸዉ በመነውጠቅ/በመዉሰድ ወደ እርሱ እንዳመጣዉ ገለፀ (ቁጥር 7-8) ፡፡ ከሐናንያ እና ከጠርጠሉስ ጋር የነበሩት የአይሁድ ሽማግሌዎች በጠርጠሉስ ሪፖርት ተስማሙ (ቁጥር 9) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (24፡ 10-21)፡የተከሰሰዉ ጳዉሎስ ፡፡ ዋይርስቤ እነዚህ ቁጥሮች ለከሳሾቹ “ የጳዉሎስ እምነት የሞላበት መልሱ “ ላይ የተመለከቱ እንደሆኑ አመልክቷል ፡፡ ጳዉሎስም ምላሹን ለፊሌክስ ምስጋና ማቅረብ በመጀመር (ቁጥር 10) በኢየሩሳሌም ለመስገድ ከሄደ 12 ቀን ብቻ እንደሆነዉ ፊሌክስን አሳሰበው (ቁጥር 11) ፡፡ የቀናቱን ቁጥር በማመልከት ጳዉሎስ የፖለቲካ ክህደት ሊፈፅምበት የሚችልበት መንገድ እንዳልነበረ ገለፀ ምክንያቱም ሁሉንም ጊዜ በእስራት ዉስጥ ስለ ነበር ፤ ዋይርስቤ በዚያ የጳዉሎስን 12 ቀናቶች ዋና ነገሮችን ይሰጣል፡
ቀን 1 - ጳዉሎስ በኢየሩሳሌም ደረሰ (21፡ 17) ፡፡
ቀን 2 - ጳዉሎስ ከያዕቆብና ከሽማግሌዎቹ ጋር ተገናኘ (21፡ 18) ፡፡
ቀን 3 - ጳዉሎስ እንደ ናዝራዊ ነፅጸዉ ከነበሩት ሰዎች ጋር ቤተ መቅደስ ገባ (21፡ 26) ፡፡
- ቀን 4 - ጳዉሎስ በቤተ መቅደስ ነበር ፡፡
- ቀን 5 - ጳዉሎስ በቤተ መቅደስ ነበር ፡፡
- ቀን 6 - ጳዉሎስ በቤተ መቅደስ ታሰረ (21፡ 27) ፡፡
- ቀን 7 - ሮማዊዉ አዛዥ/ሻለቃ ከሸንጎዉ ጋር ለማገናኘት ጳዉሎስን ወሰደው (23፡ 1-10) ፡፡
- ቀን 8 - ሰዎች ጳዉሎስን ሊገድሉት በማሴራቸዉ በጥበቃ ወደ ቂሳሪያ ተወሰደ (23፡ 12, 23) ፡፡
- ቀን 9 - ጳዉሎስ በቂሳሪያ ደረሰ (23፡ 33) ፡፡
- ቀን 10 - ፊሌክስ እንዲመጡ ለአይሁድ መሪዎች ላከባቸው ፡፡
- ቀን 11 - ጳዉሎስ የአይሁድ መሪዎችን እንዲመጡ ጠበቀ ፡፡
- ቀን 12 - ጳዉሎስ የሚሰማባት ቀን እስክትመጣ ድረስ ጠበቀ ፡፡
- ቀን 13 - መስማቱ ተካሄደ ፡፡
ጳዉሎስ ሐሰተኛ ክሱን የሚያስደግፉበት ማስረጃ እንዳልነበር አመለከተ (ቁጥር 12-13) ነገር ግን በሕግና በነቢያት ተፅፏል ብለዉ ሁሉም በሚያምኑትበክርስትና መንገድ መሰረት የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሄርን እንደሚያመልክ መሰከረ (ቁጥር 14) ፡፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ በጻድቃንና በአመፀኞች ትንሳኤ ስላለዉ እምነትና በእግዚአብሄር እና በሰዉ ፊት ሁሉ ንፁህ ህሊና እንደ ነበረዉ ተናገረ (ቁጥር 15-16) ፡፡ ጳዉሎስ እነርሱን ለመባረክ ለአይሁዶች ምፅዋት ያደርግ እንደ ነበርና (1ቆሮ 16፡ 1-4, ሮሜ 15፡ 25-33) በቤተ መቅደስ ሲነፃ ያዩት በእስያ የነበሩት አይሁዶች በዚያ ስለ እርሱ እንደሚናገሩ ገለፀ ፤ ቤተ መቅደሱን አላረከሰም (ቁጥር 17-19) ፡፡ ጳዉሎስ ለሸንጎ ሲናገር አግኝተዉበት የነበረዉን የተሳሳተ ነገር ለመስማት (ቁጥር 20) ወይምስ “ ዛሬ ስለ ሙታን መነሳት በፊታችሁ በእኔ ይፈርዱብኝ ብዬ በመጮሄ “ (ቁጥር 21) በሚለዉ ንግግሩ ችግር እንደ ነበረባቸዉ ለመስማት ጠየቀ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (24፡ 22-27)፡ ከንቱዉ ፊሌክስ ፡፡ ፊሌክስ ስለ መንገዱ ስለ ሚያዉቅ የሮማዊዉ አዛዥ ሉስዮስ እስኪመጣ እንዲጠብቁ የሚሰሙትን በተናቸው (ቁጥር 22) ፤ ጳዉሎስም በጥበቃ ስር ነበር ነገር ግን ጥቂት ነፃነት በመሰጠት ጓደኞቹን እንዲያገኝ ፍቃድ አገኘ (ቁጥር 23) ፡፡ የፊሌክስ ሚስት ድሩሲላ አይሁዳዊ እና ኢየሱስን ልጅ እንዳለ ሊገድለዉ የሞከረው የታላቁ ሄሮድስ ታላቅ የልጅ ልጅ ነበረች ፤ በተጨማሪም ድሩሲላ መጥምቁ ዮሐንስን ያስገደለዉ የሄሮድስ የታላቅ እህት/ወንድም ልጅ ነበረች፣ አባቷም ሐዋሪያዉ ያዕቆብን ገድሎታል ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላምፊሌክስ ስለ ኢየሱስ ያለዉን እምነት የሚናገረዉን ጳዉሎስን በፊቱ አመጣው (ቁጥር 24) ፤ ይሁን እንጂ የጳዉሎስ ቃል ስለ እግዚአብሄር ቃል ፊሌክስን አስፈራው ጳዉሎስንም ለቀቀው (ቁጥር 25) ፡፡ ዋይርስቤ የጳዉሎስ አቀራረብን በፊሌክስ ፊት “ ስለ ትናንት ኃጢዓት “፣ “ ስለ ዛሬ ምኞት “ እና “ ስለ ሚመጣዉ ፍርድ “ በማድረግ እንዳቀረበ ይገልፃል ፡፡ ቁጥር 26 ፊልክስ ጳዉሎስ ገንዘብ ይሰጠኛል ብሎ ተስፋ አድርጎ ስለ ነበር ለጳዉሎስ ለብቻ ለማነጋገር በፊቱ እንዲመጣ ብዙ ጊዜ እንደ ላከበት ይናገራል (ቁጥር 26) ፡፡ ይህ ፊሌክስ በፊስጦስ እስኪተካ ድረስ ለሁለት አመታት ቀጠለ ፡፡ ለአይሁዶች ደስታ ፊልክስ በቂሳሪያ እስር ቤት ጳዉሎስን ተወው (ቁጥር 27) ፡፡
መደምደሚያ
ዋይርስቤ ሰይጣን ሰዎች በምድር ላይ የሚቀበሉትን ዉሸቶች ለመፈልሰፍ አራንት ጠንካራ አጋንንቶችን በገሀነም ዉስጥ ለአንድ ስብሰባ ጠራ ብሎ የተናገረዉን የዶክ.ክላረንስ ማካርትኔይ አንድ ታሪክ ያቀርባል ፤ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስቱ እያንዳንዳቸው ሰይጣን በማረጋገጫ “ እግዚአብሄር እንደ ሌለ “፣ “ መንግስተ ሰማይ እንደ ሌለ “ እና “ ሲዖል እንደ ሌለ “ መቀነስ ችሎበት በነበረዉ ዉሸት መጡ ፤ አራተኛዉ መንፈስ/አጋንንት በቀላሉ ተቀባይ ሊሆን የሚችል ዉሸት አቀረበ፡ “ ጥድፊያ የለም “ የሚል ፡፡ ዛሬ የመዳን ቀነ ነው !
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Acts (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), pp. 498–501.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1413.
Wiersbe, p. 499.
Wiersbe, pp. 499–500.
Nelson’s Commentary, p. 1413.
Nelson’s Commentary, p. 1413.
Wiersbe, p. 501.
Wiersbe, p. 502.
ጥያቄዎች
-
ሐዋሪያት ስራ 24 እንደ ዳኛ በሚያገለግለዉ በፊልክስ ፊት ህጋዊ ጉዳይን በመግለፅ ይጀምራል ፡፡ ጠርጠሉስ በንግግሩ አይነተኛ ጠበቃን ይመስላልሰ ? በሐዋ (24፡ 5-8) ለፊልክስ ባቀረበዉ ላይ ዉሸቶች ነበሩበት ? ምን ነበሩ ?
-
ጳዉሎስ ፊልክስ ጉዳዩን በሚዳኝበት እዉነት ለምን ያተኮረ/የተስማማ አልመሰለም ? ፊልክስ ምን አይነት አስተዳዳሪ እንደ ነበር ምን ተጨማሪ መፅሀፍ ቅዱሳዊ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ?
-
በሐዋ (24፡ 14-16) የጳዉሎስን ንግግር ለፊልክስ አንብቡ ፡፡ ምን ተቀብሎ አመነ ? በንፁህ ህሊና ጳዉሎስ ከመቀየሩ በፊት ስለ እስጢፋኖስ ወይም ወደ እስርቤት ስለ አስገባቸዉና ስለ አስገደላቸዉ አስቧል ብላችሁ ታስባላችሁ ? አብራሩ
-
በሐዋ (24፡ 25) ጳዉሎስ ከፊልክስ ጋር የተነጋገራቸዉ ነገሮች “ መልካም ዜና “ ይመስላሉ ? ፊልክስ ለምን ፈራ ? “ የመልካም ዜና “ መልዕክት ላጋራችኋቸዉ ሁሉ መልካም ዜና ሆኖ ይሰማቸዋል/ይመስላል ? ለምን ወይስ ለምን አይመስልም ?
-
ብዙ ጊዜ ፊልክስ ለጳዉሎስ በመላክ ለምን ከእርሱ ጋር ይነጋገራል ? ፊልክስ አማኝ እንደ ሆነ አመላካች ነገር አለ ? የጳዉሎስ ጊዜና ጥረት ባክኖ ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልባከነም ?
-
በሐዋሪያት ስራ 24 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 24:15–16
“And I have a hope in God, which these men themselves also accept, that there is going to be a resurrection, both of the righteous and the unrighteous. I always do my best to have a clear conscience toward God and men.”
ጠርጠሉስ የሚሉት ጠበቃ በገዥው ፊልክስ ፊት የውሽት ክስ እስከሚያቀርብበት ድረስ ጳውሎስ በቂሳርያ አምስት ቀን ጠበቀ ፡፡ ጠርጠሉስ ጳውሎስን በሽታ ብሎ ጠረው ፤ በሮማውያን ግዛት ሁሉ ባሉት አይሁድ መካከል ሁከትን በመቀስቀስ ፤ የመናፍቃን የናዝራውያን ወገን መሪ በመሆንና እንድሁም መቅደሱንም በማርከስ ጭምር ከሰሰው ፡፡ ጳውሎስም መከራከሪያውን ሲያቀርብ ህጉን በመከተል የሳየውን ታማኝነት ፤ በእግዚአብሔር ላይ ያለውን ተስፋ እንድሁም ደግሞ ምጽዋት ለማድረግ ስላቀረበው ስጦታ ገለጸ ፡፡ ጳውሎስ በንጹህ ህሊና ነበር የኖረው ፣ ምንም ነገር አልደበቀም ነበር ፡፡ ስለዚህም የውሽት ክስ በቀረበበት ጊዜ ጳውሎስ አልተጨነቀም ነበር ፡፡ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት መሄዱን ቀጠለ ፤ በመንገዱም ሁሉ በታማኝነት በመሄድ የእግዚአብሔር ፍቃድ እንድፈጸም አደረገ ፡፡
ለጌታ ሙሉ በሙሉ በመሰጠት ስትኖር በንጹህ ህሊና መኖርን ምረጥ ፡፡ አስተውል ከእግዚአብሔር የሚደበቅ ምንም ነገር የለም ፡፡ እርሱ ሁሉን ያያል ፡፡ በመጨረሻ እውነቱ ይገለጣል ፡፡ ክፉን ስለማድረግ መከራን ከማየት ይልቅ መልካምን በማድግ መከራን ማየት ይሻላል ፡፡ በታማኝነት ትመላለስ ዘንድ እና ሌሎችን ለማሳት ጠላት የሚያቀርበውን ፈተና ትቋቋም ዘንድ ብርታትን እንድሰጥህ ጌታን ጠይቅ ፡፡ ክስ በሚቀርብበት ጊዜ በእንደዚህ ያለ ነጻነት ውስጥ መኖር ትፈልጋለህ እንግድያውስ ራስህን መከላከል ወይም ደግሞ መጨነቅ አያስፈልግህም ፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ ምስክር በመሆን ለመመላለስ ስትወስን የጌታ ሰላም ዙሪያህን ይሸፍናል ፡፡
“እነዚህም ራሳቸው ደግሞ የሚጠብቁት፥ ጻድቃንም ዓመፀኞችም ከሙታን ይነሡ ዘንድ እንዳላቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ዘንድ አለኝ ። ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ ። “ - ሐዋርያት ሥራ 24፡15-16
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 11:3 — “ቅኖች ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፤ ወስላቶችን ግን ጠማማነታቸው ታጠፋቸዋለች ። “
- 1ኛ የጴጥሮስ 3:16–17— “በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ ። የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ቢሆን፥ ክፉ ስለ ማድረግ ሳይሆን በጎ ስለ ማድረግ መከራን ብትቀበሉ ይሻላችኋልና ። “
- 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:18–19 — “ ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ ፤ እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።