Acts Acts

The Beginning of Paul's Journey To Rome

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 23 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 359 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ እንደ ክርስቲያን ለእኛ መሰረት ነው ፡፡ ዛሬ ከዚህ ብዙ ተግባራዊ ነገሮችን እንዳገኘ በጳዉሎስ ህይወት ላይ እንድንመለከት እፈልጋለሁ ፡፡ ጳዉሎስ በጥሩ ሁኔታ የጨረሰ ሰዉ ነበር ፡፡ በዚህ ሳምንት በዕብራዊ 11 በኩል እያጠናሁና እየፀለይኩ እግዚአብሄር ባልተጠበቁ መንገዶች የተጠቀመባቸዉን ሁሉንም ሰዎች እየተመለከትኩ ነው ፡፡

ትምህርት

ሐዋሪያት ስራ (22፡ 30)፡ ትናትና እንዳየነው ጳዉሎስ ጥሪዉንና አላማዉን ተረድቷል እንዲሁም ከመንገዱም እንዲያስቀረዉ/እንዲያሰናክለዉ ምንም ነገርን አልፈቀደም ፡፡ እስራት፣ ስቃይ እና መከራ እንደሚገጥመዉ እያወቀ በፍቃደኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ ሙሉ በሙሉ ተላልፎ የተሰጠ ነበር ፡፡ ምስክርነቱን ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር የአይሁድ ሰዎች በጳዉሎስ ላይ ከተመለሱ በኋላ ጳዉሎስ በሮማዊዉ አዛዥ ምሽቱን ሙሉ ወደ ወታደሮች ሰፈር ተመልሶ ተወሰደ ከዚያም በማግስቱ ጥዋት ተመልሶ በሸንጎዎች ፊት ተወሰደ ፡፡ አዛዡም በአይሁዶችና በጳዉሎስ መካከል እየሆነ የነበረዉን ለመስማት ፈለገ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (23፡ 1-5)፡ ጳዉሎስ በሸንጎዉ ፊት በመምጣት ህይወቱን በእግዚአብሄር ፊት እንደ ኖረ ገለፀ (ቁጥር 1) ፤ ነገር ግን ሊቀ ካህናቱም ሐናንያ ጳዉሎስን በአፉ ላይ እንዲመቱት ሰዎችን አዘዘ (ቁጥር 2) ፡፡ ጳዉሎስ ሐናንያን በሕግ መሰረት ለፍርድ እግዚአብሄር እንደሚቀጣዉ እናም በዚህ ሕግ ተላላፊ እንደሚሆን ነገረው (ቁጥር 3) ፤ በጳዉሎስ አጠገብ የነበሩት ሊቀ ካህናቱን እንዴት በዚህ መልኩ ሊያናግራቸዉ እንደ ቻለ ጠየቁት (ቁጥር 4-5) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (23፡ 6-10)፡ ጳዉሎስ ፈሪሳዊና የፈሪሳዊ ልጅ እንደ ነበር ነገር ግን ስለ ትንሳኤ ተስፋ የተፈረደብኝ በመሆን የተገደልኩኝ ነበር በማለት አሳሰባቸው/ነገራቸው (ቁጥር 6) ፡፡ ንግግሩም በፈሪሳዊያንና በሰዱቃዉያን መካከል ስለ ጳዉሎስ የጥል ክክርክር መንስኤ ሆነ (ቁጥር 7-8) ፡፡ የሮማዊዉ አዛዥም ጳዉሎስን እንዳይገነጣጥሉት ወደ ወታደሮቹ ሰፈር ገለል አደረገው (ቁጥር 9-10) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (23፡ 11-21)፡ ኢየሱስ ከሐዋሪያቱ አንዱ እንዲሆን በጠራዉ ጊዜ ጳዉሎስ በደማስቆ መንገድ ላይ ኢየሱስን አግኝቶታል ፤ በቁጥር 11 ኢየሱስ እንደ ገና ወደ ጳዉሎስ በመምጣት በሮም ስለ እርሱ ምስክር እንደሚሆን ስለ ቀጣዩ ስራዉ ነገረው ፡፡ በመሰረቱ ኢየሱስ ጳዉሎስን አገልግሎቱን እንዴት እንደ ሚጨርስ ነግሮታል፡፡

ከሐዋ (20፡ 22-24) እና ከሐዋሪያት ስራ 23 ለእኛ መኖር የምንችልባቸዉን አራት መርሆች ማዉጣት እፈልጋለሁ፡

የመጀመሪያዉ መርህ

ሙሉ ለሙሉ ለመንፈስ ቅዱስ የተሰጠን/የተማረክን መሆን አለብን ፡፡ (ሐዋ 19፡ 21, 20፡ 22-24, 21፡ 10-14, 22፡ 30-23፡ 1) የጳዉሎስ ታሪክ በኢየሩሳሌም አልጀመረም ፡፡ በሐዋ (20፡ 22-24) ጳዉሎስ በኤፌሶን ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች ያላቸው፡ “ አሁንም እነሆ እኔ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ በዚያም የሚያገኘን ምን እንደሆነ አላዉቅም ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ፡-እስራትና መከራ ይቆይሀል ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል ፡፡ ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበለሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሄርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈፅም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ “ ፡፡ ጳዉሎስ ለእግዚአብሄር እቅድ ሙሉ ለሙሉ ራሱን ያስገዛ/የሰጠ ነበር ፡፡ በኢየሩሳሌም ምን እንደሚጠብቀዉ ያዉቃል ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ “ እስራትና ግርፋት እንደሚገጥመው “ ስለመሰከረለት ፤ ነገር ግን ጳዉሎስ አልተንቀሳቀሰም ነበር ምክንያቱም በጥበቃዉ በመታመን ለእግዚአብሄር ባለዉ መታዘዝ እየተጓዘ ስለ ነበር (ሐዋ 20፡ 23-24) ፡፡ ለመንፈስ ቅዱስ ሙሉ ለሙሉ የተሰጠ ለመሆን ብቸኛዉ መንገድ ከመንገዳችን መዉጣት ነው ፡፡ ማቴ (16፡ 24) “ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፡- እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ “ ይላል ፡፡

ሁለተኛዉ መርህ

ሙሉ በሙሉ የተሰጠን ስንሆን ሊገድል የሚችል በቀልን እንዴት መያዝ እንዳለብን እንማራለን ፡፡ (ሐዋ 23፡ 2-5, ዮሐ 15፡ 26 – 16፡ 4) ጳዉሎስ በጥርጣሬ ወይም በአለመስማማት ፊት እንዴት አለመደናቀፍ እንደሚቻል አሳይቷል ፡፡ ጳዉሎስ በእርሱ ላይ ለሐናንያ ጥቃት በእዉነታና በማስረጃ ምላሽ ሰጠ ምክንያቱም ሐናንያ ሊቀ ካህን እንደ ነበር አላስተዋለም ፡፡ ባደረገም ጊዜ ጳዉሎስ ምላሹ በእግዚአብሄር ህግ መሰረት ያልሆነ እንደ ነበር በትህትና አሳወቀ ፤ የበቀል/የሚገድል ሁኔታ ሲመጣ ዝንባሌዉ መሆን ያለበት ቆሞ መጣላት ሳይሆን ቆርጦ ማምለጥ ነው ፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተገናኘን የምንሆንበት ብቸኛዉ መንገድ ክፉ/የሚገድ/በቀል ያለበት ሁኔታን መያዝ ስንችል ነው ፤ ኢየሱስ ይህን በመስቀሉ ላይ አድርጎታል ፡፡

ሰዎስተኛዉ መርህ

በታላቅ ተቃዉሞ/ተቃርኖ መካከል መለኮታዊ አላማችሁን ማወቅ አለባችሁ ፡፡ (ሐዋ 23፡ 6-10, ዮሐ 18፡ 37) ጳዉሎስ ለምን ተልኮ እንደ ነበር ያዉቃል ፤ በምንም ሁኔታ ዉስጥ ራሱን ያግኘው በዚያ እሳቤ ለመቀጠል ችግር የሌዉም ፡፡ እግዚአብሄር ማንም እንሁን ምንም እያደረግን እንሁን ለእኛ መለኮታዊ አላማ አለው ፤ መለኮታዊ አላማችን ኢየሱስ ማን እንደሆነ እዉነተኛ ምስክር እንድንሰጥ ነው ፤ የምንመሰክር ስለሆንን ለመናገር የተዘጋጀን እንሁን ፡፡

አራተኛዉ መርህ

በእግዚአብሄር ስጦታን ተስፋ ልንታመን ያስፈልገናል ፡፡ (ሐዋ 23፡ 16, 23, ኢያ 21፡ 45, 1ሳሙ 3፡ 19) በእምነት ስንጓዝ እግዚአብሄር እንደሚያገኘንና ምናልባትም የምናስበዉን እንደ ማንመስል ሙሉ ለሙሉ ያመንን መሆን አለብን ፡፡ እግዚአብሄር ለሰጠዉ ተስፋ የታመነ ስለሆነ በመታመኑም ላይ መደገፍ እንችላለን (ኢያ 21፡ 45) ፤ በሐዋ (23፡ 12-15) ከ40 የሚበልጡ አይሁዶች ጳዉሎስን እስኪገድሉት ድረስ ምንም ላይበሉና ላይጠጡ በአንድ ላይ ተደጋገፉ/ተማማሉ ፡፡ የጳዉሎስ የእህቱ ልጅ ስለ ሴራዊ ሰማ ጳዉሎስንም ነገረው፣ ጳዉሎስም የእህቱን ልጅ ከዜናዉ ጋር ወደ አዛዡ ላከው (ቁጥር 16-22) ፡፡ አዛዡም ጳዉሎስን በጠባቂዎች ስር ወደ ቂሳርያ ላከው፣ ጳዉሎስ ቀጣዩን የጉዞዉን እርምጃ ወደ ሮም አደረገ (ቁጥር 23-35) ፡፡ ጳዉሎስ እንዴት ሮም እንደ ደረሰ ይደነቃል ነገር ግን በመንገድ ላይ ወታደራዊ አጃቢ ይኖራል ብሎ በፍፁም አላሰበም ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ ታዛዥ ባይሆን ኖሮ ወንጌል ሮም እንዴት ይደርስ ነበር ? ታዛዦች ካልሆንን እግዚአብሄር መልዕክቱን ለማሰራጨት እንዴት ሊጠቀምብን ይችላል ?

ጥያቄዎች

  1. በሐዋ (23፡ 6-10) ጳዉሎስ በፈሪሳዊያንና በሰዱቃዊያን መካከል ሆን ብሎ መከፋፈልን አድርጓል ? ስትራቴጁ ራሱን የመከላከል ነበር ወይስ የሚበልጥ ነገር እየተካሄደ ነበር ?
  2. በሐዋ (23፡ 11) እግዚአብሄርን ጳዉሎስን በሮም ምስክሩ እንደሚሆን ነገረው ፤ ጳዉሎስ እንዴት የእግዚአብሄር ምስክር እንደሚሆን ግለፁ ፤ ይህን ለምን እንደ ጥሩ ነገር ይሆናል ?
  3. ሴራዉ በጳዉሎስ የእህት ልጅ በመገለጥ ለአዛዡ ተነገረዉ ፡፡ ሐዋ (23፡ 16) በጳዉሎስ ላይ ስለ ተሴረዉ ሴራ ጎበዙ ሰዉዬ መስማትን ወደ ምን አይነት ባህሪይ ታዩታላችሁ ? በእግዚአብሄር ጣልቃ ገብነት ከማመን ዉጪ በምንም ልትገልጡት የማትችሉት “ አጋጣሚ “ በህይወታችሁ ሆኖ አይታችሁ ታውቃላችሁ ?
  4. ስለ ሴራዉ አዘዡ እንዴት ምላሽ ሰጠ ( ሐዋ 23፡ 22-30) ? የተገለጠዉን ዝምን እንዲል ወዲያዉኑ ያሰናበተዉን ጎበዝ የጳዉሎስ ዘመድን አዛዡ በቀላሉ ለምን እንዳመነዉ ምን ታስባላችሁ ?
  5. በሐዋሪያት ስራ 23 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 23:11

“The following night, the Lord stood by him and said, ‘Have courage! For as you have testified about Me in Jerusalem, so you must also testify in Rome.’”

ጳውሎስ ሸንጎው በእርሱ ላይ ምን እንደሚያደርግ እስከሚወስን በመጠበቅ ላይ ሳለ በኢየሩሳሌም ጉዳት ማስተናገዱን ቀጠለ ፤ ጌታም በአንድ ሌሊት ተገልጦ ፡- “በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባሃልና አይዞህ “ አለው ፡፡ ጳውሎስ በፊቱ ሞት በተጋረጠበት ጊዜ ጌታ ግን ለእርሱ ህይወትን ተናገረው ፤ በሮምም ይመሰክርለት ዘንድ ተልዕኮን ሰጠው ፡፡ ከጳውሎስ ምልከታ አንጻር ያለበትን ሁኔታ መቋቋምና ወደ ሮም መሄድ የሚችል አልመሰለውም ነበር ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የልተጠበቀ እቅድን አዘጋጀለት ፤ በኢየሩሳልም ካሉ ጠላቶቹም አስመለጠው ወደ ቂሳርያም በሰላም አደረሰው ፡፡

እግዚአብሔር ህይወትን ሙሉ በሙሉ አሳልፈህ ለጌታ በመስጠት እንድትኖር ፣ ራስህን እንድትክድና ኢየሱስን እንድትከተል ያዝሀል ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር ያከተመ በሚመስልበት ጊዜ እንዴት ነው መጽናት የሚቻልህ ? በሮቹ ተዘግተዋል ፣ በአካውንትህ ውስጥ ምንም ገንዘብ የለህም ፤ በቃ እግዚአብሔር ጠርቶኛል ብለህ ወደ ምታስበው ቦታ ለመድረስ ምንም አይነት መንገድ የሌለ ይመስላል ፡፡ ጓደኛዬ በንጹህ ህሊና ቀጥል ፡፡ በጥሪህ እመን ፡፡ በውስጥህ የሚነሳውን ማንኛውንም ትምክህት ከልክል እናም በትህትና ተመላለስ ፡፡ ሁሉንም ነገር ፈጽመህ ለጌታ አሳልፈህ ስጥ ፡፡ እግዚአብሔር እንደሚያደርገው በነገረህ ስጦታና ጥበቃ ላይ በፍጹም ታመን ፡፡ ለእግዚአብሔር ሁሉም ይቻላል ሁሉም ፡፡ ስለዚህ ጉዞህን ቀጥል ፤ ተስፋ እንዳትቆርጥ ፡፡ እግዚአብሔር ለህይወትህ የሰጠውን ተስፋ ይፈጽም ዘንድ ያልተጠበቀ ነገር ሊያደርግ ነው ፡፡ አይዞህ በርታ !

“በሁለተኛውም ሌሊት ጌታ በአጠገቡ ቆሞ፦ ጳውሎስ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባሃልና አይዞህ አለው ። “

- ሐዋርያት ሥራ 23፡11

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኢያሱ 21:45 — “ እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም ። “
  • ኢሳይያስ 43:16–19 — “ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል ፤ እግዚአብሔር ሰረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል፤ እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፥ አይነሡም፤ ቀርተዋል፥ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ ። እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ ። “
  • ማቴዎስ 16:24 — “ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ። “