Acts Acts

Facing The Crowd With His Testimony

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 358 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዚህ ሳምንት የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍንና በመንፈስ ቅዱስ በኩል የተሰጠዉን ስልጣን ጥናታችንን እንጨርሳለን ፡፡ ፀሎቴ በዚህ ጥናት ዉስጥ ስናልፍ በሕይወታችን ሐዋሪያት ስራን እንድንኖረዉ ነው ፡፡

ሐዋሪያት ስራ 21 መጨረሻ ላይ አይሁዶች ጳዉሎስን በመያዝ እስኪሞት ለመምታት ሞከሩ ፡፡ የሮም አዛዥ ጳዉሎስን ባሰረዉ ጊዜ ጳዉሎስ ደብድበዉት የነበሩትን ሕዝቦች መልዕክት እንዲያደርሳቸዉ እንዲፈቀድለት ጠየቀ ፤ መልዕክቱም ከሐዋ (22፡ 1) ይጀምራል ፡፡ ኮንስታብል የጳዉሎስን ንግግር እንደ “ ኢየሱስ እንደሚያደርገዉ ቃል ገብቶት እንደ ነበረው በሚያስደንቅ ክስተቶች ላይ የጌታን አገልጋዮች መንፈስ ቅዱስ የሚሉት እንደሚሰጣቸዉ በጣም ጥሩ ምሳሌ እንደ ሆነ “ ገልፆታል (ማቴ 10፡ 16-20, ማር 13፡ 9-11) ፡፡

ትምህርት

ሐዋሪያት ስራ (22፡ 1-5)፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን በዕይብራይስጥ ማድረስ ጀመረ ህዝቡም ፀጥ አለ መከላከያዉንም/መከራከሪያዉንም አቀረበ (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ ራሱን ፍርድ ላይ እንዳለ በማየት ስለ ሙሴ ሕግ በኢየሩሳሌም በገማልያ ስር የተማረ ከጠርሴስ የሆነ አይሁዳዊ እንደ ነበር አመለከተ/ተናገረ (ቁጥር 2-3) ፡፡ ምናልባትም ጳዉሎስ የሕግ አዋቂዎች መሪ ወይም የሸንጎ አባል ነበር (ገላ 1፡ 13-14) ፡፡ የኢየሱስ ተከታዮችን በቅናት ያሳድዳቸዉ እንደ ነበር ሊቀ ካህናቱና መማክርቱ/ኮሚቴዉ ማሳደዱን በዚያም እንዲቀጥል ወደ ደማስቆ ደብዳቤ ሰጥተዉት እንደ ነበርና ስለዚህም እንደሚያዉቁ አሳሰባቸው (ቁጥር 4-5) ፡፡ ጳዉሎስ የቀድሞዉን ባህሪዉን እየተናገረ/እያወጣ ነበር በዚህ ስለ መቀየሩ እግዚአብሄር ክሬዲቱን ያገኛል ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (22፡ 6-16)፡ በዚህ ክፍል ጳዉሎስ ስለ ተቀየረበት ልምድ መሰከረ ፤ ጳዉሎስ ስለ ደማስቆ መንገድ ገጠመኙና ከኢየሱስ ጋር ስለ መገናኘቱ ተናገረ (ቁጥር 6-9) ፡፡ ጳዉሎስ ኢየሱስ ወደ ደማስቆ እንዲሄድ ነገረዉ በዚያም ምን እንደሚያደርግ እንደ ነገረዉ ገለፀ (ቁጥር 10) ፤ በተጨማሪም ጳዉሎስ በኃይለኛ ብርሃን ማየት ተስኖት ስለ ነበር በዚያ በነበረ እጅ እንደ ተመራም ገለፀ (ቁጥር 11) ፡፡ ጳዉሎስ ሐናን ወደ እርሱ በመምጣት እንዴት እይታዉን እንደ መለሰለት ነገራቸው (ቁጥር 13) ፤ ከዚያም ጳዉሎስ ለሁሉም ሕዝብ ለእርሱ እንደ ምስክር ፍቃዱን አደርግ ዘንድ እግዚአብሄር መርጦት እንደ ነበር ሐናንያ እንደ ነገረዉ ገለፀ (ቁጥር 14-15) ፡፡ ሐናን ጳዉሎስን ተነስቶ እንዲጠመቅ ነገረው (ቁጥር 16) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (22፡ 17-21)፡ ጳዉሎስ በዚያ ስለ ክርስቶስ ምስክርነትን ስለማይቀበሉ ኢየሩሳሌምን እንዲለቅ ከነገረዉከኢየሱስ ጋር በራዕይ መገናኘቱን ተናገረ (ቁጥር 17-18) ፤ ጳዉሎስ ለራዕዩም ሁሉም ማን እንደ ነበርና በቤተ ክርስቲያን ላይ አድርጎት የነበረዉን ስለሚያዉቁ በኢየሩሳሌም መቀየሩን ማንም እንደ ማይቀበለዉ መለሰለት (ቁጥር 19-20) ፡፡ ኢየሱስም ጳዉሎስን ለአሕዛብ ሩቁ እንደሚልከዉ መለሰለት (ቁጥር 21) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (22፡ 22-30)፡ እዚህ ስፍራ ላይ የሚያዳምጡት ሕዝብም ጳዉሎስን ከምድር እንዲያጠፋዉ ወደ ሮማዉያንምመጮኽ ጀመሩ (ቁጥር 22) ፡፡ የሮማዉያን አዛዥም ጳዉሎስን በጠፍር ለመግረፍ እና ለምን ሕዝቡ እየጮኹበት እንደ ነበር ለመስማት መልሶ ወደ ወታደሮች ማረፊያ ወሰደው (ቁጥር 23-24) ፡፡ ጳዉሎስን ለመግረፍ እንደ ገተሩት ጳዉሎስ ያልተፈረደበት እስከሆነ ድረስ በመወለድ ሮማዊ ዜጋ በመሆኑ ይገርፉት ዘንድ ለእነርሱ የተፈቀደላቸዉ እንደሆነ ጠየቃቸው (ቁጥር 25-28) ፡፡

አለቃዉም ጳዉሎስ ሮማዊ እንደ ነበር ባስተዋለና አስሮት እንደ ነበር ባስተዋለ ጊዜ ፈራ (ቁጥር 29) ፤ በቀጣዩም ቀን አዛዡ/ሻለቃዉ ጳዉሎስን በመልቀቅ ለካህናት አለቆችና ለሸንጎዎች መለሰው (ቁጥር 30) ፡፡

መደምደሚያ

ከምዕራፍ 22 የምንወስደዉ ነገር ስለ መቀየራችንና እግዚአብሄር እንዴት ኑሮአችንን እንደ ቀየረዉ ታሪክ መኖራችን ነው ፡፡ ጳዉሎስ ታሪኩን ለመናገር ሁሉንም እድል ተጠቀመ ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Study Notes: Acts, p. 440; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/acts.pdf.

ጥያቄዎች

  1. ለዚህ መልዕክት የጳዉሎስ አድማጮቹ እነማን ነበሩ ?መናገር ከመጀመሩ በፊት ምን ለማድረግ ሞክረዉ ነበር? (ሐዋ 21፡ 30-31)
  2. ጳዉሎስ ምስክርነታችንን እንዴት መናገር/ማጋራት እንዳለብን ታላቅ ምሳሌ ሰጥቶናል ፤ ታሪኩን ለመናገር ምን አይነት ሰዎስት ሁኔታዎችን ተጠቀመ (ሐዋ 22፡ 3-5, 6-16, 17-29) ? በዚህ ሳምንንት ምስክርነታችሁን እንድትናገሩ እድል እንዲሰጣችሁ እግዚአብሄርን ጠይቁት ፡፡
  3. ጳዉሎስ ቆይቶ የአይሁዶችን ብስጭትን ያባባሰ ነገር ምን ተናገረ ? ይህ ለምን በጣም እንዲበሳጩ ምክንያት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? በህይወታችሁ የእግዚአብሄር ጥሪ ሲገለጥ ሌሎችን አበሳጭቶ ያዉቃል ?
  4. ለሮማዊዉ አዛዥ/አለቃ ጳዉሎስ ስለ ራሱ ምን ገለፀለት ? ከአዛዡ ምላሹ/መስተጋብሩ ምን ነበር ?
  5. በሐዋሪያት ስራ 22 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 22:14–15

“Then he said, ‘The God of our fathers has appointed you to know His will, to see the Righteous One, and to hear the sound of His voice. For you will be a witness for Him to all people of what you have seen and heard.’”

ጳውሎስ ሮማዊውን ሻለቃ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሰፈር ከመወሰዱ በፊት በዙሪያው ለተሰበሰበው ህዝብ ይናገር ዘንድ እንድፈቅድለት ለመነው ፡፡ ጳውሎስም ለህዝቡ በዕብራይስጥ ቋንቋ ተናገረ ፤ ከኢየሱስ ጋር እንዴት እንደተገናኘ ፣ ፍጹም የሆነ ለውጡንና በህይወቱ ያለውን አዲስ ጥሪ መሰከረ ፡፡ ህዝቡም አደመጡ እናም ግን አሁንም ጳውሎስን ነቀፉ ደግሞም እንድገደል ፈለጉ ፡፡ ሻለቃውም ጳውሎስ ከመወለዱ ጀምሮ ሮማዊ ዜጋ መሆኑን እስኪያውቅ ድረስ ሊደበድቡት ፈልገው ነበር ፡፡ ምንም እንኳ ሸንጎው የእርሱን ጉዳይ እንዴት እንደሚያደርጉ መነጋገራቸውን ቢቀጥሉም ይህ የተለየ እውነት ጳውሎስን አስፈታው ፡፡

ኢየሱስን ጌታህና አዳኝህ አድርገህ የተቀበልክበትንና እግዚአብሔር ህይወትህን የለወጠበትን ጊዜ ታስታውሳለህ ? እንደ አማኝ ምስክርነትህን ለማካፈል ተዘጋጅ ፡፡ አለም ተጨባጭ የሆነ የእግዚአብሔርን ኃይል ምስክርነት መስማት ፈልጋል ፡፡ ስለ ጌታ ፍቅር መልካምነትና በህይወትህ ስለሚሰራው ለዋጭ ኃይል ካልሰሙ በቀር ሌሎች እንዴት ስለ ኢየሱስ ሊያውቁ ማወቅስ ሊፈልጉ ይችላሉ ? ለመናገር እንዳትፈራ ፡፡ በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር ያስታጥቅሀል የምትናገረውንም ቃል ይሰጥሀል ፡፡ ክክርስቶስ በፊት በነበረው ህይወትህ የምታፍር ከሆነ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ አያይዞ ለበጎ እንደሚያደርገው መናገሩን አስታውስ ፡፡ ትላንትናህን እንደሚዋጅና ምስክርነትህን ሌሎችን ለማበርታትና ለማጽናናት እንደሚጠቀምበት እርሱን እመነው ፡፡ ድምጽህን ለማሰማትና ለሌሎች ህይወትህን ለማካፈል ሰዓቱ አሁን ነው !

“ እርሱም አለኝ፦ የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን ታውቅ ዘንድና ጻድቁን ታይ ዘንድ ከአፉም ድምፅን ትሰማ ዘንድ አስቀድሞ መርጦሃል ባየኸውና በሰማኸው በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆንለታለህና ። “

  • ሐዋርያት ሥራ 22 ፡ 14-15

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 10:18–20 — “ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና ። “

ሉቃስ 8:39 — “ በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፦ የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ ። “

2ኛ ቆሮንቶስ 1:3–4— “ የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ ። እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን ። “