The Leading Of The Holy Spirit
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህን ሳምንት የጳዉሎስን የአገልግሎት ጉዞ እየተከተልን ነው ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 20 ጳዉሎስ በግሪክና በመቄዶንያ ያሉትን አማኞች ቻዉ አላቸው/ተሰናበታቸው ፡፡
በሐዋሪያት ስራ 21 ጳዉሎስ ከሰዎስተኛዉ የአገልግሎት ጉዞዉ ተመልሶ በመሄድ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳትመለስ የሚል ቃል ከመንፈስ ቅዱስ ተቀበለ ፤ በዚያም ፋንታ ጳዉሎስ አገልግሎቱን/ተልዕኮዉን ቀጠለ ፡፡ ይህ ምዕራፍ ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዝ ስንብቱ ይቀጥላል ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (21፡ 1-5)፡ በኤፌሶን የቤተ ክርስቲያንን መሪዎች ትቶ መሄድ ለጳዉሎስና ለጓደኞቹ አስቸጋሪ ነበር - ከእነርሱ ተለይተዉ ሄዱ ፡፡ 400 ማይል ያክል ጉዞ የሚሆን ወደ ፊንቄም የሚሄድ አንድ የጭነት መርከብ አገኙ ፤ ይህ ወደ መሽቀዳደሚያ ማረፊያ የጉዞ እቅድን እና በምዕራብ የወጣዉን የመጀመሪያዉን አዉጦብስ ከመያዝ ጋር ይመሳሰላል - የማያቆም አዉቶብስ ሳይሆን ወደ ተወሰነ መዳረሻ የሚሄድ ነው (ቁጥር 1-2) ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ ጳዉሎስ በፊልጵስዮስ ከሰዎስት ሳምንታት ቀድሞ ፋሲካን ስላከበረ ለበዓለ ኃምሳ ቀን ጊዜ በዚያ ለመሆን ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ለማድረግ ከ30 ቀን በታች እንደ ነበረው ይገልፃል ፤ ይሁን እንጂ በአጋን ባህር ላይ ለመጓ የራሱ ጊዜ ነበረው ፡፡ በአመቱ በዚህ ጊዜ የበጋ ነፋስ በጥዋት ይነፍሳል ነገር ግን ዘግይቶ ከስዓት ይጠፋል ፤ መርከቦች ጉዞን ለመቀጠል ተመልሰዉ በቀጣዩ ቀን ማለዳ ለመምጣት ለደህንነታቸዉ እያንዳንዱን ምሽት ንፋሱ እንዲያልፍ ይጠብቃሉ ፡፡ መርከቡ እቃዉን/የጫነዉን ለማራገፍ ወደ ሶሪያ ወደብ ጢሮስ ሄደ (ቁጥር 3) ፡፡
በዚያ እያሉ ጳዉሎስና ጓደኞቹ አንዳንድ ደቀ መዛሙርቶችን አገኙ ለአንድ ሳምንትም ከእነርሱ ጋር አሳለፉ ፤ ደቀ መዛሙርቱም ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ የሚለዉን የመንፈስ ቅዱስን ቃል ነገሩት (ቁጥር 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በዚህ ጉዞ የጳዉሎስን እድገት/የጉዞ ሂደት፡ ከመንፈስ ቅዱስ ምሪት ጋር የተገናኘ እንደ ነበር ( ሐዋ 16፡ 6), ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከመንፈሱ ጋር የተሳሳረ እንደ ነበር (ሐዋ 20፡ 22) ኪዚያም ቆይቶ ለመቀጠል የኢየሱስን እገዛን እንደ ተቀበለ (ሐዋ 23፡ 11) ያመለክታል ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ማስጠንቀቂያ ስለ ኢየሩሳሌም እንዳይቀጥል በዚያ የሚገጥመዉ ችግር ስለ መኖሩ ነበር ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ፣ ሚስቶቻቸዉና ልጆቻቸው ከጳዉሎስ ጋር ተመልሰዉ ወደ መርከቡ በመሄድ ከመለያየታቸዉ በፊት ከእርሱና ከጓደኞቹ ጋር ፀለዩ (ቁጥር 5-6) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (21፡ 7-17)፡ ወደ ጢሮስ በመርከብ ተጓዝን ከዚያም ከክርስቲያን ወንድሞቻቸዉ ጋር እንደ ገና ወደ ተገናኙበት አካ ደረሱ ፡፡ ከእነርሱ ጋር አንድ ቀን በማሳለፍ ወደ ቂሳርያ በመሄድበወንጌላዊዉ ፊልጶስ ቤት ተቀመጡ (ከሐዋሪያት ስራ 8 ከሰባቱ አንዱ ወደ በሆነው) (ቁጥር 7-8) ፡፡ ፊልጶስ ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴት ልጆች ነበሩት (ቁጥር 9) ፡፡ ከኢዩኤል (2፡ 28) ይህ የጴጥሮስ ትንቢት መፈፀም ነው፡ “ ስጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ “ (ሐዋ 2፡ 17) ፡፡
ከብዙ ቀናት በኋላ በሐዋ (11፡ 27-30) የተጠቀሰዉ ከይሁዳ የሆነዉ አንድ አጋቦስ የሚባለዉ ነቢይ ወደ ጳዉሎስና ወደ ጓደኞቹ መጣ ፤ የጳዉሎስን ቀበቶም በመዉሰድ በኢየሩሳሌም እንደ ሚሆን እንደ ሚታይ ትንቢት በጳዉሎስ ፊት እግሩንና እጁን ለማሰረን ተጠቀመበት (ቁጥር 10-11) ፡፡ እንደ ገና በቂሳሪያ ያሉት አማኞችና ጓደኞቹ “ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ ለመኑት “ (ቁጥር 12) ፤ ይህ ጳዉሎስ ከእግዚአብሄር ተቀብሎ እንደ ነበር የጳዉሎስ ጥሪ ሌላ ማረጋገጫ ነበር ፡፡ ጳዉሎስም እንዲሰራዉ ኢየሱስ ሰጥቶት የነበረዉን ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ አለ - በጌታ በኢየሱስ ስም ለመሞት (ቁጥር 13) ፡፡ የጳዉሎስ ዝግጁነት በሂደት/በለዉጥ ላይ የነበረና ወደ መሰቀለ/መከራ/ስቃይ በሙሉነት በመጓዙ ምክንያት ነበር ፡፡ በትንሽ ነገር መንፈስ ቅዱስን ስናደምጥ ለሚመጣዉ ለትልቅ ነገር ዝግጁ እንደ ሚያደርገን አምናለሁ ፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ የዚህን ሂደት ዝግጁነት ተመልከቱ፡
ማቴዎስ 5:10 | ዮሐንስ 15:18 | 2 ጢሞቴዎስ 3:12 |
2 ቆሮንቶስ 12:10 | ሉቃስ 6:22 | ሮሜ 12:19 |
ሮሜ 8:35 | ማቴዎስ 5:44 | 1 ጴጥሮስ 5:8 |
መዝ 23:4 | መዝ 31:5 | ማርቆስ 10:29–30 |
ቁጥር 14 “ ምክርም ሊቀበል እምቢ ባለ ጊዜ (ጳዉሎስ) የጌታ ፈቃድ ይሁን ! ብለን ዝም አልን “ ይላል ፤ ጳዉሎስና የጉዞ ጓደኞቹ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ ከቂሳሪያም በአንዳንድ ደቀ መዛሙርቶች ተሸኙ (ቁጥር 15-16) ፡፡ ቂሳሪያዊያን ጳዉሎስን ምናልባት የጴጥሮስን ስብከት ከሰሙት ከ120 ዉስጥ ወደሆነዉ (ሐዋ 1፡ 15) “ ወደ ደቁሞዉ ደቀ መዝሙር “ ወደ ምናሶን ወሰዱት ፡፡ በመጨረሻም በኢየሩሳሌም ሲደርሱ ወንድሞቻቸዉ ጳዉሎስን በደስታ ተቀበሉት (ቁጥር 17) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (21፡ 18-25)፡ በቀጣዩ ቀንም ጳዉሎስ በያዕቆብ እና በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ፊት በመሄድ እግዚአብሄር በአሕዛብ መካከል እያደረገ የነበረዉን ነገር ነገራቸዉ (ቁጥር 18-19) ፡፡ ይህ በሐዋሪያት ስራ 15 የኢየሩሳሌም መማክርት/ኮሚቴ ከተገናኙ ከሰባት አመት በኋላ ነበር፣ ሁሉም ነገር ተቀይሯል ፡፡ ማንኛዉም ሌላ ሐዋሪያ ከሐዋሪያት ስራ 15 በኋላ አልተጠቀሰም በዚህም የሚገመተዉ የማቴ (28፡ 19) እና ሐዋሪ (1፡ 15) ታላቅ ተልዕኮ ለመፈፀም ወጥተዉ/ተበትነዉ እንደ ነበር ነው ፡፡ አንዳንድ ጥቂት ጠንካራ ማስረጃዎች ጳዉሎስ የነበረዉ የእግዚአብሄር ስራ ከእርሱ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ሄደዉ የነበሩት የአሕዛብ አማኞች ቡድን እንደ ነበር ነው ፡፡
ሽማግሌዎቹ የጳዉሎስን ሪፖርት በሰሙ ጊዜ እግዚአብሄርን በማመስገን በሺ የሚቆጠሩ አማኞች የሆኑትን አይሁዶችንም አመለከቱ ፡፡ እነዚህ የአይሁድ አማኞች አሁንም በሙሴ ህግ የቀኑ እና ጳዉሎስ ስለ ማይገረዙት ወይም የአይሁድን ልምድ ስለ ማይከተሉት አሕዛቦች እየነገራቸዉ እንደ ነበር የተጨነቁ/የሚያስቡ ነበሩ (ቁጥር 20-21) ፡፡ ሽማግሌዎቹ ጳዉሎስን ስለት የነበረባቸዉን አራት ሚስኪን ሰዎች በመዉሰድ ራሳቸዉን እንዲላጩ በመክፈል ጳዉሎስ የአይሁድን ሕግ መከተል እንዳልተወ እንደሚታይ ምሳሌ ከእነርሱ ጋር ራሱን እንዲያነፃ ጠየቁት (ቁጥር 24) ፡፡ ጆሴፍስ አግሪጳ ሄሮድስ መጀመሪያ ንጉስ ሲሆን ለእግዚአብሄር አክብሮት እንዳለዉ ለምልክት የናዝራዊነትን ስለት ለመዉሰድ ብዙ ሰዎችን እከፍላለሁ እንዳለ መዝግቦታል ፡፡ በቁጥር 25 ሽማግሌዎቹ ጳዉሎስን ለአሕዛቦች መስፈርቱን ቀድመዉ ሰባት አመት ወስነዉ እንደ ነበር አሳሰቡት ፤ እንደ ተጠየቀዉም ጳዉሎስ አደረገ (ቁጥር 26) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (21፡ 26-40)፡ ከሰባት ቀን መንፃት በኋላ አይሁዶች ሕዝቡን በእርሱ ላይ ባስነሱበት ጊዜ ጳዉሎስ በቤተ መቅደስ ነበር ፤ ያዙትም ከመቅደስም ጎትተዉ በማዉጣት የሮም የጭፍራ አለቃ ሲሰማ ሊገድሉት እየሞከሩ ነበር (ቁጥር 27-31) ፡፡ የጭፍራ አለቃዉም ጳዉሎስን እየመቱ የነበሩትን አይሁዶች ያስቆሙት ወታደሮቹ በሰንሰለት በማሰር ጥበቃ ወደሚደረግለት ወሰዱት (ቁጥር 32-33) ፡፡ አዛዡምተፈጥሮ የነበረዉ ትርጉም አልሰጥ ሲለዉ/ሳይገባዉ ሲቀር ጳዉሎስን ወደ ወታደሮቹ ሰፈር ወሰደው (ቁጥር 34) ፤ ጳዉሎስ በኃይለኛዉ ተመቶ ስለነበር በወታደሮቹ እንዲሸከሙት ተደረገ (ቁጥር 35-36) ፡፡ አዛዡም ጳዉሎስን አመፅ መርቶ የነበረዉ ግብጻዊ መሪ እንደ ነበር ጠየቀዉ ጳዉሎስም ከጠርሴስ የሆነ አይሁዳዊ ሰዉ እንደ ነበር መለሰለት (ቁጥር 38-39) ፡፡ ከዚያም ጳዉሎስ ለአይሁድ ሰዎች እንዲናገር ጠየቀ በምዕራፍ 22 የተሸፈነዉ እድልም ተሰጠው (ቁጥር 40) ፡፡
መደምደሚያ
ጳዉሎስ ከመንፈስ ቅዱስ በማዳመጥ በእርሱ መታመን ተማረ ፤ ከዚያም የሚገጥመዉን አደጋ በተነገረዉ ጊዜም በመንፈስ ቅዱስ በመታመን በአገልግሎቱ/ተልዕኮዉ ላይ ቆዬ/ቀጠለ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1409
Nelson’s Commentary, p. 1409.
Nelson’s Commentary, p. 1409.
ጥያቄዎች
-
በሐዋ (21፡ 4) ጳዉሎስ በመንፈስ በአንዳንድ ደቀ መዛሙርቶች ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይጓዝ አስጠነቀቁት ፤ ጳዉሎስ ማስጠንቀቂያቸዉን ያልተገበረዉ ለምን ነበር ? በእርሱ ዉሳኔ ትስማማላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አትስማሙም ?
-
ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርስ ያዕቆብንና ሽማግሌዎቹን በማየት በአገልግሎቱ እግዚአብሄር በአሕዛብ መካከል አድርጎት የነበረዉን ሊነግራቸዉ ሄደ ፤ በጳዉሎስ ላይ ሀሳባቸዉ ምን ነበር ? “ መፍትሄአቸው ” አሁንም ጳዉሎስ በሕግ ስር እየኖረ እንደ ነበር ማመናቸዉን ይገልፃል ? መልሳችሁን በጥቅስ አስደግፉ ፡፡
-
በሐዋ (21፡ 24) በእቅዳቸዉ መሰረት ለመጓዝ/ለመሄድ የጳዉሎስ ፍቃደኝነት ጳዉሎስ በዚህ ጉዳይ ላይ ሕግን በመጠበቅ የቆመ እንደ ነበር ይገልፃል ? ለምን ወይስ ለምን አይገልጥም ? (1ቆሮ 9፡ 20)
-
በሐዋ (21፡ 28) ከእስያ የመጡት አይሁዶች ስለ ጳዉሎስ ምን ተናገሩ/ገመቱ ? ከሌሎች ቤተ ክርስቲያን በመጡ በሌሎች ላይ ፍርድን ወይም ግምትን በማድረግ ራሳችሁን ስህተት ዉስጥ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ኃጢዓታችሁን ስታዉቁት ሁኔታዉን እንዴት አስተካከላችሁት ?
-
በጳዉሎስ ላይ አመፅና ድብደባ ሲደረግ በማግኘታቸዉ የሮም ወታደሮች እንዴት አደረጉ ? ከሐዋ (21፡ 10-11) ያለዉ ትንቢት ጳዉሎስ በሁለት ሰንሰለት ሲታሰር የተፈፀመ ነው ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ሁኔታ ማስወገድ መምረጥ ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ ለምን አላደረገዉም ? ታደርጉት ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አታደርጉትም ነበር ?
-
በሐዋሪያት ስራ 21 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 21:13–14
“Then Paul replied, ‘What are you doing, weeping and breaking my heart? For I am ready not only to be bound but also to die in Jerusalem for the name of the Lord Jesus.’ Since he would not be persuaded, we stopped talking and simply said, ‘The Lord’s will be done.’”
ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ እየሄደ ሳለ በጢሮስ አረፈ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ቆየ ፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ በመንፈስ አሳሰቡት ፡፡ ቢሆንም ግን ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱን ቀጠለ ፡፡ ከዚያም በአካ አረፈ ፡፡ ምሽቱንም ከአማኞች ጋር እያሳለፈ ሳለ ጳውሎስ አይሁድ በኢየሩሳሌም እንደሚያስሩት መልዕክት የነገረውን አጋቦስ የተባለውን ነብይ አገኘ ፡፡ ይህንም ከሰሙ በኋላ በዙሪያው ያሉት ጳውሎስ ከዚያ በኋላ እንዳይጓዝ ለመኑት ፡፡ በዚህ ሁሉ ግን ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም የመመለስ ጥሪው እናም ህይወቱን ስለ ክርስቶስ አሳልፎ መስጠት ላይ ጽኑ ነበር ፤ እንድህ ብሎ መለሰላቸው “እኔ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ተሰናድቼአለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም ። “ ይህንም ከሰሙ በኋላ ዝም አሉ እናም በቃ “ የጌታ ፈቃድ ይሁን “ አሉ ፡፡
“ የጌታ ፍቃድ ይሁን “ ብለህ ጸልየህ ታውቃለህ ? ይህ የትህትና ፣ ራስን አሳልፎ የመስጠትና በእግዚአብሔር የመታመን ጸሎት ነው ፡፡ ይህ ጌታን ማመን ነው ማዳኑ ባይመጣ እንኳ ፣ ስራህን ብታጣ እንኳ ፣ መከራ ብታሳልፍም ፤ የኢየሱስን ስም ለማክበር ሀይማኖትን ትጠብቃለህ ! ጳውሎስ ራስን ሙሉ ለሙሉ አሳልፎ ወደ መስጠት መጥቷል ፣ ህይወቱን እንኳ ሊያሳጣው ቢችል ፡፡ ኢየሱስ በመከራ ውስጥ ሲያልፍና በስቃይ ወደ ህይወቱ ማብቂያ ሲደርስ “ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ “ ብሎ ወደ አብ ጸለየ ፡፡ የጌታ ፍቃድ እንድሆን ስትለምን እንድሁም ህይወትህን በዚህ መንገድ አሳልፈህ ስትሰጥ ፤ በዚህ ስቃይና መከራ ውስጥ እግዚአብሔር እንደሚያበረታህ አስታውስ ፡፡ የእርሱ ተስፋ ለዘላለም ነው ፡፡
“ጳውሎስ ግን መልሶ፦ እያለቀሳችሁ ልቤንም እየሰበራችሁ ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ተሰናድቼአለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም አለ ። ጳውሎስ ግን መልሶ፦ እያለቀሳችሁ ልቤንም እየሰበራችሁ ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ተሰናድቼአለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም አለ ። “
- ሐዋርያት ሥራ 21፡13-14
ተጨማሪ ጥቅስ
ሉቃስ 22:42 — “ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር ። “
2ኛ ቆሮንቶስ 12:10 — “ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና ። “
ፊልጵስዩስ 3:7–8 — “ ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ ። አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።