Acts Acts

Paul's Final Journey Toward Jerusalem

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 356 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ አንዱ/ዋናዉ ቃል ስልጣን ነው ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 20 በኢየሱስ ክርስቶስ በተሰጠዉ ስልጣን በጥሪዉ ላይ የጳዉሎስን ሰዎስተኛዉን የአገልግሎት ጉዞ ላይ በመመልከት ይቀጥላል ፡፡ ዋይርስቤ ምዕራፍ 20 የጳዉሎስ የመሸኛ ጉዞ በማድረግ ይገልፀዋል ፡፡ ትናትና በሐዋሪያት ስራ 19 ጳዉሎስ በኤፌሶን ለሰዎስት አመትም በዚያ ነበር ፤ ሐዋሪያት ስራ 19 መጨረሻ ላይ አንድ አመፅ ተካሄደ/ሆነ ፤ ሐዋሪያት ስራ 20 የሚያነሳዉ ያን ሀሰባ ነው ፡፡

ትምህርት

ሐዋሪያት ስራ (20፡ 1-6)፡ አመፁ ካበቃ በኋላ ጳዉሎስ በኤፌሶን ለደቀ መዛሙርቱ በመላክ ከሰሜን ወደ መቄዶንያን ከመሄዱ በፊት ሰላም/ቻዉ አላቸዉ (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ ሰዎስት ወር ወደ ተቀመጠባት ግሪክ ከመሄዱ በፊት በሁለተኛዉ የአገልግሎት ጉዞዉ ጎብኝቷቸዉ በነበሩት ስፍራዎች ዉስጥ አለፈ (ቁጥር 2) ፡፡ ከግሪክ ወደ ሶሪያ በመርከብ ለመሄድ አቀደ ነገር ግን አይሁዶች በእርሱ ላይ ማሴራቸዉን ሲሰማ ተመልሶ በመቄዶንያን በኩል ሄደ (ቁጥር 3) ፤ በተጨማሪም ከጳዉሎስ ተመሳሳይ የአገሩ ሰዎችም ተቃርኖ ነበር (2ቆሮ 11፡ 26, ሐዋ 18፡ 12) ይህን ሴራ ወደጎን መተዉ ማለት ጳዉሎስ አስቸጋሪ ነገር አይገጥመዉም ማለት አይደለም ፡፡ አብረዉት የሚሰሩትም ከመቄዶንያንና ከእስያ ጳዉሎስን ሸኙት (ቁጥር 4) ፤ እነዚህ አብረዉ ሰራተኞቹ ከጳዉሎስና ከሉቃስ ፊት በመሄድ በጢሮአዳ ቆዩአቸው (ቁጥር 5) ፡፡ ጳዉሎስና ሉቃስከፋሲካ በኋላ ከፊልጵስዮስ በመዉጣት/በመሄድ በአምስት ቀን ጢሮአዳ ደረሱ (በመጨረሻ ጊዜ ከፊልጵስዮስ በመርከብ ሁለት ቀን የሚወስደዉን) ፡፡ ከመሄዳቸዉም በፊት በጢሮአዳም ሰባት ቀን ቆዩ (ቁጥር 6) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (20፡ 7-12)፡ በሳምንቱ በመጀመሪያዉ ቀን ላይ (እሁድ) ጳዉሎስና የጉዞ ጓደኞቹ እንጀራ በአንድ ላይ ለመቁረስና ጳዉሎስ የሚናገረዉን ለመስማት ተሰበሰቡ ፤ በቀጣዩ ቀን ይሄድ ስለ ነበር ጳዉሎስ ንግግሩን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ቀጠለ (ቁጥር 7) ፤ አይሁዶች እንደ ሙሴ ህግ አካል ሰንበትን(ከአርብ ማታ አመሻሻ እስከ ቅዳሜ አመሻሽ ድረስ) ይጠብቁ ነበር ( ዘጸ 31፡ 16-17, ነህ 9፡ 14, ሕዝ 20፡ 12) ፡፡ በኢየሩሳሌም መማክርቶች/ኮሚቴዎች በአዲስ ኪዳን ስር ከሆነ ክርስቲያን የቅዳሜን ሰንበት መጠበቅ አያስፈልገዉ በማለት ስምምነት አድርገዋል፣ ጳዉሎስ ወደ ክርስቶስ የመራቸዉን በአንዱም ሰንበትን መጠበቅ በፍፁም አላስተማራቸዉም ፤ ቤተ ክርስቲያን መቼ ማምለክ እንዳለባት በአዲስ ኪዳን ትዕዛዝ የለም (ሮሜ 14፡ 5, ገላ 4፡ 10-11, ቆላ 2፡ 16-17) ፡፡

አንድ ጎበዝ ሰዉዬ በመስኮቱ ላይ በመቀመጥ እያዳመጠ ነበር ምናልባትም በዘይት ከሚበራዉ ኩራዝ ጭስ ምክንያት ከባድም እንቅልፍ ወደቀበት ፡፡ ጎበዙ ሰዉዬ አዉጤኪስ ከሰዎስተኛዉ ፎቅ መስኮትም ላይ በመዉደቅ በምድር ላይ ሞቶ ተገኘ (ቁጥር 8-9) ፡፡ ጳዉሎስ ወደ ታች በመዉረድ የአዉጤኪስን ሰዉነት በማቀፍ አሁንም ነፍሱ አላች አላቸዉ (ቁጥር 10) ፡፡ ጳዉሎስ ተመልሶም በመዉጣት በላ፣ እስኪነጋ ድረስም ማስተማሩን ቀጠለ ከዚያም ሄደ (ቁጥር 11) ፡፡ ብላቴናዉም በህይወት ቤት ተወሰደ (ቁጥር 12) ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የታመሙትን እንዲፈዉሱና የሞቱትን እንዲያስነሱ ትዕዛዝ ሰጥቷቸዋል (ማቴ 10፡ 8) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (20፡ 13-16)፡ ከጳዉሎስ ቡድን ዉስጥ አንዳንዶቹ ጳዉሎስ በየብስ ሲጓዝ ጳዉሎስን ለመገናኘት ቀድመዉ ወደ አሶን በመርከብ ሄዱ (ቁጥር 13) ፤ ከዚያም ጳዉሎስ ከእነርሱ ጋር በመርከብ ከአሶን ወደ ሚጢሊን ከዚያም ወደ ኪዩ ከዚያም ወደ ሳሞን በቀጣዩም ቀን ወደ ሚጢሊን ሄደ (ቁጥር 14-15) ፡፡ ጉዞዉ ፍጥነትን ለመያዝ የተጀመረ እንደ ነበር ይመስላል ፤ ጳዉሎስ በኤፌሶንና በእስያ አጠገብ ለማለፍ ወሰነ ምክንያቱም ከበዓለ ኃምሳ ቀን በፊት በኢየሩሳሌም ለመድረስ ስለ ቸኮለ (ቁጥር 16) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (20፡ 17-38)፡ በሚጢሊን ጳዉሎስ በኤፌሶን ያሉትን ሽማግሌዎችን ወደ እርሱ እንዲመጡ ጠየቃቸው (ቁጥር 17) ፤ ሲደርሱም ከእነርሱ ጋር አሳልፎት የነበረዉን ጊዜና ከእነርሱ ጋር ተካፍሎት የነበረዉን የወንጌልን አገልግሎትአሳሰባቸው (ቁጥር 18-21) ፡፡ ከዚያም ጳዉሎስ በኢየሩሳሌም የሚጠብቀዉ ነገር እንደሚሆን ያም መንፈስ ቅዱስ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀዉ እንደ ነገረዉ ነገራቸው (ቁጥር 22-23) ፡፡ ጳዉሎስ ይህን የክርስቶስ ወንጌል በምስክርነት ለመስራት ተጠርቶ እንደ ነበር እንደ ማረጋገጫነት ወሰደው ( ቁጥር 24) (ማቴ 10፡ 38, 16፡ 24, ማር 8፡ 34, ሉቃ 9፡ 24) ፡፡ ጳዉሎስ መሪዎቹን በፍፁም ደግመዉ እንደ ማያዩት ነገር ግን በህይወቱ ላይ ለእግዚአብሄር ጥሪ ታዛዥ እንደሚሆን ነገራቸው (ቁጥር 25-26) ፡፡ ጳዉሎስ ታዛዥነቱን “ ለእግዚአብሄር ሙሉ እቅድ “ (ቁጥር 27) በማለት ገልፆታል ፤ ማክአርቱር ይህን ሙሉ እቅድ፡ “ የፍጥረት መለኮታዊ እዉነትን፣ ምርጫን፣ መስተካከልን፣ መቀበልን፣ መቀየርን፣ መቀደስን፣ ቅዱስ ኑሮን እና ክብርን “ በማካተት እንደ ድነት ሙሉነት ይገልፀዋል ፡፡ ጳዉሎስ ወደ ሞቱ እየሄደ እንደ ነበር በማወቁ ሽማግሌዎቹን ለራሳቸዉ የተጠነቀቁ እንዲሆኑ አስጠነቀቃቸዉ ፤ ቤተ ክርስቲያንንም ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ካሉ ሐሰተኛ አስተማሪዎችና ከዉጪ ከሚመጣዉ ተቃዉሞ እንዲጠነቀቁ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 28-31) ፡፡ ጳዉሎስ ከእነርሱ ምንም አይነት እርዳታ ጠይቆ እንዳልነበር በማስታወስ ለእግዚአብሄር የተሰጡ እንዲሆኑ መከራቸው (ቁጥር 34-35) ፤ ከዚያም ጳዉሎስ ለእነርሱ ፀለየላቸዉ፣ ጳዉሎስንም በማቀፍ በዚህ የመጨረሻ መለያያ ላይ ሁሉም አለቀሱ (ቁጥር 36-38) ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ አገልግሎት ፈላጊ ነበር ነገር ግን ያገለገላቸዉንም ሰዎች ይወዳል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs, Co: David C. Cook, 1989), p. 483.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1477–1478..

  3. JMacArthur, p. 1479.

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ ወደ ተለያዩ ከተሞች ሲጓዝ ሰዎችን ከእርሱ ጋር ለምን ይወስዳል ? ጳዉሎስ የመጀመሪያዉ ለአገልግሎት የተላከ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  2. በበዓለ ኃምሳ ቀን ላይ ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም መመለሱ ለምን ነበር አስፈላጊነቱ ? (ዘጸ 23፡ 14-17)
  3. ህይወታችሁ በማንኛዉም መንገድ የጳዉሎስን ያሳያል ? ለእግዚአብሄር ከጳዉሎስ መታዘዛ የትኛዉ ክፍል ሊያስተምረን ይችላል ?
  4. በሐዋ (20፡ 20-23) ጳዉሎስ መከራ በሁሉም ከተማ እንደሚገጥመዉ እያወቀ ለአይሁዶችና ለግሪኮች ለሁለቱም በትምህርቱ የሚጠቅማቸዉን ነገር አላስቀረሁባችሁም አላቸዉ ፤ ስለ እምነታችሁ መከራ፣ ስቃይ እና መገደል/መሰደድ እንደሚገጥማችሁ እያወቃችሁ ስለ ኢየሱስ እዉነቱን ማካፈልን ትቀጥላላችሁ? ለምን ወይስ ለምን አትቀጥሉም ?
  5. ጳዉሎስ በሐዋ (20፡ 26) “ ስለዚህ እኔ ከሰዉ ሁሉ ደም ንፁኅ እንደ ሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ “ ሲል ምን ማለቱ ነበር ? (ዘጸ 3፡ 20-21)
  6. በሐዋሪያት ስራ 20 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 20:31–32

“Therefore, be on the alert, remembering that night and day for three years I did not stop warning each one of you with tears. And now I commit you to God and to the message of His grace, which is able to build you up and to give you an inheritance among all who are sanctified.”

በኤፌሶን ሶስት አመታትን ካሳለፈ በኋላ ጳውሎስ እግዚአብሔር ያስቀመጠው አዲስ ጊዜ በኢየሩሳሌም እየጠበቀው እንደሆነ ተረዳ ፣ ይህም የእስራትና የመከራ ጊዜ ነበር ፡፡ ሆኖም ግን ከመሄዱ በፊት የሚያበረታን ቃል ፣ ለአይሁድም ለግሪኮችም እውነትን እንድሁም የኢየሱሰ ደቀ መዛሙርት ሆነው ይጸኑ ዘንድ ማስጠንቀቂያን ነገራቸው ፡፡ የሚወዳቸውንም አማኞች ለመሰናበት ልቡ አዘነ ፡፡ ቢሆንም ግን እነርሱን ለጌታ አደራ ይሰጣቸው ዘንድና እርሱ ወደ አዲስ የአገልግሎት ጊዜ ይሄድ ዘንድ መረጠ ፡፡

ከምትወዳቸው ሰዎች የመለየት እናም ደግሞ እነዚህን የምቀርባቸውን ሰዎች እንድሁም በክርስቶስ ጠንካራ ይሆኑ ዘንድ የሚያስፈልጋቸውን እነዚህን ምን ልበላቸው ብለህ አስበህ ታውቃለህ ? ምናልባት ትሄድ ይሆናል ፤ ከአገልግሎቱ ቦታ ትርቅ ወይም በተጨማሪ ልጅህን ከኮሌጅ ታስወጣ ይሆናል ፡፡ እንዴት የምትወዳቸውን ሰዎች በመጨረሻ ደቂቃ የጥበብ ፤ የፍቅርና የጸጋ ቃላትን በማካፈል እንደምትለይ ጳውሎስ ጥሩ ምሳሌ ነው ፡፡ በመጀመርያም ሊያበረታቸውና ተስፋን ሊሰጣቸው የሚችለውን የኢየሱስን ፍቅርና የእርሱን የጸጋ ቃል አስታውሳቸው ፡፡ ቀጥሎም ጠላት እምነታቸውን የጠፋና ተስፋን ያስቆርጣቸው ዘንድ በዙሪያቸው ይዞራልና ራሳቸውን እንድጠብቁ አስጠንቅቃቸው ፡፡ በመጨረሻም እንድነቁ ምከራቸው ፡፡ ከእነርሱ ስትለይም መንፈስ ቅዱስ እነርሱን እንደሚሸከማቸው አመን ፡፡ ለመሰናበት ቀላል አይደለም ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ አዲስ አገልግሎት ሲጠራህ ፣ እርሱ ታማኝ እንደሆነ አስተውል ፡፡

“ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ ። አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ ። “

- ሐዋርያት ሥራ 20፡31-32

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 1ኛ ቆሮንቶስ 16:13 — “ ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ ። “
  • ዕብራውያን 10:38–39 — “ ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም ። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም ። “
  • 1ኛ የጴጥሮስ 5:8 — “ በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና “