Acts Acts

Baptized in Jesus' Name

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 355 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሐዋሪያት ስራ 18 መጨረሻ ከጳዉሎስ የሁለተኛ ጉዞ አገልግሎት መጨረሻ ወደ ሰዎስተኛዉ ጉዞ ሽግግር ያመለክታል ፡፡ ጳዉሎስ በኤስያ በምትገኘዉ ወደ ኤፌሶን ተጓዘ/ደረሰ ፡፡ በሁለተኛዉ የአገልግሎት ጉዞ መንፈስ ቅዱስ ጳዉሎስን ወደ ኤስያ እንዳይገባ ከለከለው ፤ በዚያም ፋንታ ጳዉሎስ አንድ መቄዶናዊ ሰዉ በዚያ ስፍራ ያሉትን ሰዎች መጥቶ እንዲረዳቸዉ ሲጠይቀዉ ከጌታ ራዕይን ተቀበለ ፡፡ አሁን በሰዎስተኛ የአገልግሎት ጉዞዉ ጳዉሎስ ጉዞዉን ወደ ኤስያ አደረገ ፡፡

ትምህርት

ሐዋሪያት ስራ (19፡ 1-6)፡ በምዕራፍ 18 አጵሎስ በኤፌሶን ማገልገል ጀምሮ ነበር (ቁጥር 23) ፤ አሁን ጳዉሎስ ኤፌሶን ሲገባ አጵሎስ ወደ ቆሮንቶስ ተጉዞ ነበር ፡፡ ጵርስቅላና አቂላም በቀድሞዉ አለም ከሰባቱ አንዱ አስገራሚ በአርቴምስ በቤተ መቅደሱ በጣም ታዋቂ በነበረው ወደ ኤፌሶን መጀመሪያዉኑ ወንጌልን አምጥተዋል ፡፡ ኤፌሶን በፖለቲካ፣ በንግድና በትምህርት ጠቃሚ ማዕከል ነበረች ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 18 ጵርስቅላና አቂላም በዚያ መጀመሪያ ወንጌልን ቢሰብኩም በኤፌሶን እስከዚህ የአገልግሎት ጉዞ ድረስ ቤተ ክርስቲያን አልተመሰረተም ነበር ፤ በመጨረሻም ጳዉሎስ በኤፌሶን ለሰዎስት አመት ይቆያል ፡፡ ጳዉሎስ በሄደም ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ላይ በኃላፊነት አስቀመጠው ፤ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን “ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደ ሌለው ወደ ትዉልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመነሁህ “ (1ጢሞ 1፡ 3) ፡፡ ኮንስታብል “ ኤፌሶን የአጉል አምልኮ ማደጊያና የአስማት ድርጊት የሚደረግበት እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡

ጳዉሎስ ደቀ መዛሙርቱን መንፈስ ቅዱስን ተቀብለዉ እንደ ሆን ጠየቃቸው ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ስለ መኖሩ እንኳን ሰምተዉ አያዉቁም ነበር ፡፡ ከኃጢዓት የንስኃ ጥምቀት በሆነዉ በዉሃ በዮሐንስ ጥምቀት ብቻ ተጠምቀዉ ነበር ፤ ጳዉሎስ በዮሐንስ ጥምቀትና በኢየሱስ ጥምቀት መካከል ያለዉን ልዩነት ገለፀላቸዉ በኢየሱስም ስም ተጠመቁ ፡፡ በዮሐንስና በኢየሱስ ጥምቀት መካከል የነበረዉ ልዩነት ምን ነበር ? መጥምቁ ዮሐንስ ራሱን “ እኔ ለንስሐ በዉኃ አጠምቃችኋለሁ ፤ ጫማዉን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል “ (ማቴ 3፡ 11) በማለት ገልፃል ፡፡ የምታምኑት ኢየሱስ የማዕዘን መለኪያዉ መሲህ ነው፣ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ተጠምቃችኋል ፡፡

ይህን ከተማሩ በኋላ ጳዉሎስ እጆቹን በእነርሱ ላይ ጫነ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ ፤ መንፈስ ቅዱስም ሲወርድ አማኞቹ በሌላ ቋንቋና ትንቢት ተናገሩ ፤ ተመሳሳይ ክስተት በሐዋሪያት ስራ ዉስጥ ተከስቷል፡

  • ሐዋሪያት ስራ 2፡ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን ተቀበለች፣ የእግዚአብሄርም እሳት በመዉረዱ በሌሎች ቋንቋ ተናገሩ ፡፡
  • ሐዋሪያት ስራ 10፡ አሕዛቦች ወንጌልን ሰሙ፣ የእግዚአብሄርም እሳት ወረደ፣ መንፈስ ቅዱስንም በመቀበል በሌሎች ቋንቋ ተናገሩ ፡፡

በቁጥር 5 ካመኑ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ህይወት መጣ ፡፡ ቁጥር 6 በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቁ ተፈጥሮ የነበረዉን ይገልፃል ፡፡ ለእኛ በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቅን መሆን ለአንዳንዶች በድንገት የሚሆን ሊሆን ይችላል ለሌሎች ደግሞ ምናልባት በጊዜ ቆይታ ለመንፈስ ቅዱስ መሪነት ራሳችንን ማቅረብን የምንማርበት ሂደት ነው ፡፡ በአንዱ መንገድ የህይወታችንን ቆሻሻ መንፈስ ቅዱስ ባቃጠለዉ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀናል ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (19፡ 7-10)፡ በጳዉሎስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በመጀመሪያ ቃለ ምልልስ ሁሉም አስራ ሁለቱም በመንፈስ ቅዱስ ተጠመቁ ፤ በቀጣዮቹ ከሰዎስት ወር በላይ - ከቆሮንቶስ በተለዬ ጳዉሎስ ለረጅም ጊዜ በአንድ ምኩራብ ለረጅም ጊዜ ተቀመጠ - ጳዉሎስ ያለማቋረጥ “ ስለ እግዚአብሄር መንግስትእየተነጋገረና እያስረዳቸዉ “ (ቁጥር 8) ይናገርበት ወደ ነበረዉ ምኩራብ ሄደ ፡፡ ምናልባትም ጳዉሎስ በሌሎች ቦታዎች እንዳገለገለዉ በጊዜዉ በምኩራቡ በተመሳሳይ ቀረበ ፡፡ የብሉይ ኪዳንን መፅሀፍት በተለይም ስለ ኢየሱስ ትንቢት የሚናገሩትን በመዉሰድ ወደ ኢየሱስ እንዴት እንደ መሲህ እንዳመለከቱ አሳያቸዉ ፡፡ ከሰዎስት ወር በኋላ የማያምኑት ስለ ጳዉሎስና ስለ ደቀ መዛሙርቱ ስም ማጥፋት ማሰራጨት ጀመሩ ስለሆነም ጳዉሎስ ከምኩራብ በመዉጣት “ ከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ ጢራኖስም በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር “ (ቁጥር 9) ፡፡ ጢራኖስ (ትርጉሙም “ ጨካኛችን “ ማለት ሲሆን) የትምህርት ቤቱ አዳራሽ ባለቤት ሊሆን ወይም በትምህርት ቤቱ አዳራሽ ላይ ትምህርት ያደረገ ፈላስፋ ሊሆን ይችላል ፡፡ የጢራኖስ ትምህርት በማይኖር ጊዜ ምናልባትም ጳዉሎስ በትምህርት ቤቱ አዳራሽ ላይ ከምሽቱ 5ሰዓት እስከ ምሽቱ 10 ሰዓት አስተማረ ፡፡

ይህ ለሁለት አመታት ከቀጠለ በኋላ “ በእስያም የኖሩት ሁሉ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም የጌታን ቃል ሰሙ “ (ቁጥር 10) ፤ በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቁት እነዚህ የመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ሰዎች በእግዚአብሄር ቃል በደንብ በመጠጣት መላዉ አህጉር መልዕክቱን እንዲሰሙት ለእንደዚህ አይነት ፈጣን ለዉጥ ምክንያት ሆኑ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (19፡ 11-12)፡ ድንኳኖች ሲሰራ ጳዉሎስ ለብሷቸዉ የነበሩትን ነገሮች ወደ ታመሙት እና በመንፈስ ተይዘዉ ወደ ነበሩት ወሰዱት ሰዎቹም ተፈወሱም ነፃ ወጡም ፡፡ ጳዉሎስ ያደረጋቸዉ ተዓምራቶች ሰብኮት የነበረዉ መልዕክት ትክክል እንደ ነበር ማስረጃ/ማረጋገጫ ሰጡ ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር ትልቅ አምላክ ነው ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ በኩል እያንዳንዳችንንና ሁላችንንም ሊጠቀምብን ይፈልጋል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ ልንማር ይገባናል ፤ ስናደርገ ህይወታችን የተቀየረ ይሆናል ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1401.

  2. Tom Constable, Dr. Constable’s Study Notes on Acts, p. 385; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/acts.pdf.

  3. John MacArthur, The MacArthur New Testament Commentary: Acts (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1474.

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ ደቀ መዛሙርቱን በኤፌሶን “ ስታምን መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችኋል “ ብሎ ጠየቃቸው ? አማኞች እንደ ነበሩ በመመልከት ይህን ለምን እንደ ጠየቃችዉ ምን ታስባላችሁ ? በእናንተ ላይ በቀላሉ መንፈስ ቅዱስ ያድራል ወይስ እንደ ህይወት ዉሃ ጎርፍ በህይወታችሁ የሚፈስ ነው ?
  2. በኤፌሶን ደቀ መዛሙርቱ ምን ስጦታዎችን ተቀበሉ (ሐዋ 19፡ 6) ? በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ የተጠቀሱት አንዳንድ ስጦታዎች ምንድን ናቸዉ ? (1ቆሮ 12፡ 4-11, ሮሜ 12፡ 6-8)
  3. በግል አስተያየታችሁ የአይሁድ ተከታዮች በዉስጣቸዉ በነበሩት ክፉ መንፈሶች ላይ ለምን ስልጣን አልነበራቸዉም ክፉዉ መንፈስ ለምን እዉቅና አልሰጧቸዉም ?
  4. ድሜጥሮስ በጳዉሎስ ላይ ለምን ነበር የተበሳጨው ? የሚሆነዉን ነገር በመፍራት የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማትባለመፈለግ/በመዉደቅ እንደ ክርስቲያን ብዙ ጊዜ እንዴት እናደርጋለን ? ፍርሃት ወይም ልመና ከኢየሱስ ጋር በጥልቅ ግንኙነት መንገድ መፈለግ ላይ እንዲኮን ወይም በህይወታችሁ በተለዬ ጥሪ ለመጓዝ እንዴት ያደርጋል ?
  5. በሐዋሪያት ስራ 19 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 19:2b

“‘No,’ they told him, ‘we haven’t even heard that there is a Holy Spirit.’”

ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሄደ በዚያም አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን አገኘ ፡፡ ኢየሱስን ቢያምኑም ነገር ግን ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ በጠየቃቸው ጊዜ እነርሱ ፡- “አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት ። “ ጳውሎስም ስለ መንፈስ ቅዱስ ነገራቸው ፤ እጁንም ጫነባቸው ጸለየላቸውም ፡፡

ኢየሱስን ጌታህና አዳኝህ አድርገህ ተቀብለህ ይሆናል ፡፡ እንዲህም ጸልየሀል ፡- “ አዎ ! ጌታ ሆይ አንተ መንገድ ፣ እውነትና ህይወት እንደሆንክ አምናለሁ ! ኢየሱስ አንተን ወደ ህይወቴ እቀበላለሁ ፡፡ “ ሆኖም ግን ኢየሱስን ስትቀበል እርሱ በአንተ ውስጥ ይኖር ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ለመለክ ቃል እንደገባ ታውቃለህ ? በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ አለ ! ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን በነገር ሁሉ ወደ እውነት የሚመራ መሪ አድርጎ ይጠቁማል ፡፡ በመንፈስ ስትመላለስ የመንፈስን ፍሬ ታንጸባርቃለህ ፡፡ መንፈስም እንድሁ በስጦታ ያሳድግሀል ፡፡ ማለትም ለአገልግሎቱ ስራ ቅዱሳኑን በመለኮታዊ ኃይል ያስታጥቃል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መመላለስ ከኢየሱስ ጋር ከምታስበው በላይ ወደ ሆነ ድል ይመራል ! በዚህ የክርስትና ጉዞ ብቻህን እንደሆንክ አታስብ ፡፡ በውስጥህ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አለህ ፡፡ እባክህ እንድህ በማለት አትጨርስ “ መንፈስ ቅዱስ እንዳለ አልሰማሁም ፡፡ “ ህይወትህን ኃይል ወደ ሚያስታጥቀው ወደ መንፈስ ቅዱስ ንቃ !

“ እነርሱም፦ አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት ። “

- ሐዋርያት ሥራ 19፡2

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዮሐንስ 14:16–17 — “ እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል ፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ ። “
  • ዮሐንስ 16:13 — “ ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው ። “
  • ሮሜ 8:9 — “ እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም ። “