Acts Acts

Founding the Corinthian Church

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 354 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሐዋሪያት ስራ 17 ጳዉሎስና ሲላስ ከፊልጵስዮስ ወደ ተሰሎንቄ ሄዱ ፤ በስደት/በመከራም ምክንያትም ወደ ቤርያ ሄዱ ከዚያም ወደ አቴና ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 18 አቴናን በመተዉ ወደ ቆሮንቶስ ሄዱ ፤ ይህ የጳዉሎስ የአገልግሎት ሁለተኛ ጉዞዉ ነበር ፡፡ በቆሮንቶስ ጳዉሎስ የተጋ አጋዥ አገኘ ፡፡

ትምህርት

ሐዋሪያት ስራ (18፡ 1-3)፡ ቆሮንቶስ የአካይያ የፖለቲካ ዋና ከተማና የመራባት የወሲባዉ አማልዕክት ማምለኪያ ማዕከል ነበረች ፤ በተጨማሪም ከተማዋ የአፖሎ ዋና ቤተ መቅደስ መገኛ ነበረች ፤ የስነ ምግባር ብልሹነት ከተማ ነበረች ፡፡ አንድ ቆሮንቶሳዊ ተብሎ መጠራት ወሲባዊ ስነ ምግባር ብልሹ የሆነ ነዉ ተብሎ ከመጠራት ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ ጳዉሎስ ወደዚህ ማህበረሰብ በመጣ ጊዜ ቀላዉዴዎስ ሁሉም አይሁዶች ከሮም እንዲወጡ ባዘዘዉ ምክንያት ከጣሊያን መጥተዉ የነበሩትን አቂላን እና ሚስቱን ጵርስቅላን አገኘ ፡፡ ወደ እነዚህ ጥንዶች ጳዉሎስን በአንድ ላይ ለማምጣት በጊዜዉ እግዚአብሄር በፖለቲካ ድርጊት በኩል ሰራ (ሐዋ 17፡ 26) ፤ በብዙ በሚመስል መልኩ አቂላና ጵርስቅላ በሮም የቤተ ክርስቲያንን አባላት እያገኙ ነበር ፤ ምክንያቱም ጳዉሎስ ከእነርሱ ጋር በመቀመጥ እንደ ድንኳን ሰራተኛ ከእነርሱ ጋር በመስራት ተመሳሳይ ስፍራ ተጋርተዉ ነበር ፡፡ ለጳዉሎስ እና ለአገልግሎቱ ኑሮአቸዉን አደጋ ዉስጥ አስገቡ (ሮሜ 16፡ 3-4) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በልስጥራና ልድያን በተሰሎንቄ እንዳገኘ እናስታዉሳለን ፡፡ የእግዚአብሄርን መንግስት ስታገለግሉ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸዉ ቡድኖች ከእናንተ ጋር የሚያገለግሉ ቅሪቶችን ያስነሳላችኋል ፡፡ እግዚአብሄር አንድን ቡድን ለማሳደግ በትክክለኛዉ ስፍራ በትክክለኛዉ ጊዜ ሰዎችን ያስቀምጣል ፤ አቂላና ጵርስቅላ በተጨማሪም በኤፌሶን አገዙት (ሐዋ 18፡ 18) ፡፡ በ 1ቆሮ (16፡ 19) በቤታቸዉ ቤተ ክርስቲያንን አዘጋጁ ብሏል ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (18፡ 4-5)፡ የራሱን ስርዓት በመከተል በሁሉም ሰንበት አይሁዶችንና ግሪኮችን ሁለቱንም ለማሳመን በመሞከር ጳዉሎስ በምኩራብ አስተማረ ፡፡ ሲላስና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ ሲመጡ ጳዉሎስን መልዕክቱን ሲናገርና ኢየሱስ መሲህ እንደሆነ ሲመሰክር አገኙት ፡፡ ጳዉሎስ ወንጌልን በማካፈል ከከተማ ወደ ከተማ ሲጓዝ ይረዱት የነበሩ የሰዎች ቡድን ነበረው ፤ “ እነዚህ ጓደኞቹ ….ለጳዉሎስ ጌታን በሚገባ እንዲያገለግል ቀላል አደረጉለት “ ፡፡ ራልፍ ዋልዶ ኢመርሰን “ እግዚአብሄር ሁላችንም ኃብታሞች ወይም ኃያላኖች ወይም ታላቅ እንድንሆን አይፈልግም ሁላችንም ጓደኛሞች እንድንሆን እንጂ “ በማለት ፅፏል ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (18፡ 6)፡ እንደ ገና ጳዉሎስ በወንጌል ተቃዉሞ ገጠመው ፤ ከዚያም ጳዉሎስ አይሁዶችን ከማገልገል በአሕዛቦች ላይ ወደ ማትኮር ዞረ ፡፡ ልክ እንደ ጳዉሎስ ስራችን ቀላል ነዉ መልካሙን ዜና ማድረስ ብቻ ፤ እንደ ጳዉሎስ ተቃዉሞ እንደሚገጥመን መጠበቅ አለብን ፡፡ ነህ (5፡ 13) እና ሐዋ (13፡ 51) ሁለቱም የእግዚአብሄር ሰዎች መልዕክታቸዉን ካልተቀበሏቸዉ ሰዎች ሲመለሱ ልብሳቸዉን በማራገፍ ወይም ከእግራቸዉ ላይ ትንቢያን ሲያራግፉ ያሳያል ፤ በማቴ ( 10፡ 14) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ “ ብሎ ነገራቸዉ ፡፡

“ ነገር ግን በተቃወሙትና በተሳደቡ ጊዜ ልብሱን እያራገፈ ደማችሁ በራሳችሁ ነው እኔ ንጹሕ ነኝ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ አላቸው “ (ቁጥር 6) ፡፡ በኢያ (2፡ 19) ሰላዮቹ ረዓብን ቤቷን ትቶ የሚሄድ (በከተማዋ ላይ ዉጊያ/ጦርነት ሲመጣ) ማንኛዉም ደማቸዉ በራሳቸዉ ላይ እንደሚሆን፣ ሰላዮቹም ከደሙ ንፁህ እንደሚሆኑ ነገሯት ፡፡ በእሷ ቤት በመቀመጥ ለሚቀሩት ብቻ ተጠያቂ ይሆናሉ ፡፡ ለእነዚህ ፅሁፎች ትርጉሙ መታዘዝ የሚል ነው፡፡ በሕዝ (3፡ 17-21) እግዚአብሄር ሕዝቅኤልን በእስራኤል ላይ እንደ ጠባቂ ሰዉ ጠራው ፤ መቼም ቢሆን ሕዝቅኤል ከእግዚአብሄር አንድ ቃል ሲሰማ እነርሱን የማስጠንቀቅ ኃላፊነት ነበረበት ፡፡ ሕዝቅኤል የእግዚአብሄርን ቃል ካላደረሰ ለመሞታቸዉ ተጠያቂ ይሆናል ፤ ነገር ግን ሕዝቅኤል የእግዚአብሄርን ቃል ሲያደርስ ቃሉን በመቀበላቸዉ ወይም በመታዘዛቸዉ ተጠያቂነቱን ራሳቸዉ ይወስዳሉ ፤ ይህ በቆሮንቶስ ከጳዉሎስ ጋር የሚነፃፀር ነው ፤ የሚጠበቅበትን ወንጌልን እየሰበከ ነበር ፤ ቆሮንቶሳዊያንም ለምላሻቸዉ ተጠያቂ ነበሩ ፡፡ ይህ በወንጌል ብታፍሩ አፍርባችኋለሁ የሚለዉን የኢየሱስን ንግግር ያስታዉሰናል ፡፡ ይህ አሁንም ለቤተ ክርስቲያን እዉነት ነው ፤ ምን እንደ ምናደርግና እንደ ምንል ተነግሮናል፡ ጥያቄዉ በትክክል እያደረግነዉ ነው ?

ሐዋሪያት ስራ (18፡ 7-11)፡ ጳዉሎስም የቤቱም በር ከምኩራብ አጠገብ በሆነዉ የእግዚአብሄር አምላኪ በነበረዉ ወደ ኢዮስጦስ ቤት ወጥቶ ሄደ (ቁጥር 7) ፤ በ1ቆሮ (1፡ 14) ጳዉሎስ ቀርስጶስና ጋይዮስና አጥምቋለሁ አለ ፡፡ በቆሮንቶስ እንደ ጌታ በኢየሱስ በሚያምንም ቀርስጶስ የምኩራብ መሪ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ጳዉሎስ በምሽት በቆሮንቶስ ለመናገር እንዳይፈራ ነገረዉ ምክንያቱም እግዚአብሄር ከጳዉሎስ ጋር ስለሚሆንና ስለሚጠብቀዉ ፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ የእግዚአብሄርን ቃል እያስተማረ አንድ አመት እና ከግማሽ ተቀመጠ ፡፡ በዘፍ (15፡ 1) እግዚአብሄር አብርሃምን እንዳይፈራ ነገረዉ ምክንያቱም እግዚአብሄር ጋሻዉ ስለሚሆን ፤ በዘፍ (26፡ 24) እግዚአብሄር ይስሐቅን እንዳይፈራ ነገረዉ ምክንያቱም እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ነበር ፤ በዘፍ (46፡ 3) እግዚአብሄር ያዕቆብን ተመሳሳይ ነገር አለው ፡፡ እግዚአብሄር ለሆነ ነገር ሲጠራን በስልጣንና በራስ መተማመን መጓዝ እንችላለን ፤ በዕብ (13፡ 5) እግዚአብሄር በፍፁም እንደ ማይተወንና እንደ ማይጥለን ተስፋ ገብቶልናል ፤ ይህ የእምነትን ሙሉ ዝላይ/ከፍታ እንድንወስድ ይረዳናል ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (18፡ 12-17)፡ አይሁዶች በጳዉሎስ ላይ “ የተቀናጀ ጥቃት “ በማድረግ ጋልዮስ በአካይያ በአገረ ገዢ በነበር ጊዜ ወደ ፍርድ ወንበር አመጡት ፡፡ ጋልዮስ በሮም ምክር ቤት የአካይያን አዉራጃ (ቆሮንቶስ በዚህ አዉራጃ ነበር ) እንዲያስተዳድር የተሾመ ነበር ፤ አይሁዶች “ ይህ ሕግን ተቃዉሞ እግዚአብሄርን ያመልኩት ዘንድ ሰዎችን ያባብላል “ (ቁጥር 13) ባሉ ጊዜ ጋልዮስ ጉዳያቸዉን ለመስማት እምቢ አለ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እግዚአብሄር የታመኑ የአገልጋዮቹን ሕይወት እንደሚጠብቅ “ ተናግሯል ፡፡ አይሁዶች በምኩራቡ መሪ በሶስቴንስ ላይ ቁጣቸዉን ገለፁ (ቁጥር 17) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (18፡ 18-23)፡ ከእነዚህ ክስተቶች በኋላ ጳዉሎስ በመርከብ ወደ ሶሪያ ሄደ ፡፡ በክርክራኦስ ላይ ራሱን ተላጨ ምክንያቱም ስለት ተስሎ ነበርና ፤ ይህ ድርጊት የናዝራዊነትን ስለት በሚያደርጉት የተወሰደ ነበር ፡፡ ኤፌሶን በደረሰ ጊዜ ጳዉሎስ በዚያ ጵርስቅላንና አቂላምን ተዋቸው ፡፡ በምኩራቡም ከአይሁዶች ጋር ተነጋገረ፣ እንዲቆይ ቢጠይቁትም እሺ አላለም ፤ ከዚያም በዚያ ያሉትን ቤተ ክርስቲያን ሰላም ለማለት ከኤፌሶን ወደ ቂሳርያ በመርከብ ሄደ ቀጥሎም ወደ አንጾኪያ ወረደ ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ ሁለተኛዉን የአገልግሎት ጉዞ ወደ አንጾኪያ በመመለስ ጨረሰ ፡፡ ቀድሞ ከዮሐንስ ማርቆስና በርናባስ ጋር ቢለያዩም ጳዉሎስና ሲላስ ደቀ መዛሙርቱን ለማጠንክር በዚህ ጉዞ ላይ ሄዱ ፡፡ የእግዚአብሄርን መንግስት የማሻሻል ጠቅላላ ግቡና ደቀ መዛሙርቱን በማጠናከር ተፈፅሟል ምክንያቱም ጳዉሎስ እግዚአብሄር በመንፈስ ቅዱስ በኩል ሰጥቶት በነበረው ስልጣን እየተጓዘ ስለ ነበር ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Acts (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1402.

  2. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Acts (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 475.

  3. Quoted in Wiersbe, p. 475.

  4. Nelson’s Commentary, p. 1403.

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ በቆሮንቶስ በደረሰ ጊዜ ማን አገኘ ? እነዚህ ሁለት ሰዎች በቆሮንቶስ ለመድረስ እንዴት መጡ ንግዳቸዉስ ምን ነበር ?
  2. በስነ ምግባር በመላዉ ሮም ግዛት የቆረንቶስ ዝና ምን ነበር ? (ሮሜ 1፡ 18-32)
  3. በቁጥር 5 ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ መልሶ ያመጣዉ የሚያበረታታና መልካም ዜናዉ ምን ነበር ? (2ቆሮ 11፡ 9, 1ተሰ 3፡ 6-10)
  4. ሁል ጊዜ እግዚአብሄር በስራ ላይ እንዳለ ለማረጋገጥ ጳዉሎስ ወንጌልን በድፍረቱ በመናገር ምን ለመደ/ምን አደረገ ? (ሐዋ 17፡ 5-13, 1ቆሮ 16፡ 9, 1ተሰ 2፡ 14-16)
  5. መፅኀፍትን አጵሎስ በሚገባ ካወቀ፣ የእግዚአብሄር መንገድ ያስተምር ነበር እንዲሁም ሌሎችንም ስለ ኢየሱስ እያስተማረ ከነበር ጵርስቅላና አቂላም ለእርሱ ስለ እግዚአብሄር በደንብ ለምን ገለፁለት (ሮሜ 10፡ 1-4) ? ለሰዎች ሙሉ ወንጌልን መስበክ አስፈላጊነቱን/ጥቅሙን ታዩታላችሁ ?
  6. በሐዋሪያት ስራ 18 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 18:9–11

“Then the Lord said to Paul in a night vision, ‘Don’t be afraid, but keep on speaking and don’t be silent. For I am with you, and no one will lay a hand on you to hurt you, because I have many people in this city.’ And he stayed there a year and six months, teaching the word of God among them.”

ጳውሎስ ሁለተኛውን የአገልግሎት ጉዞ ሲጓዝ አቴናን ለቆ ወደ ቆሮንቶስ ሄደ ፡፡ ጳውሎስ ኢየሱስ እርሱ መሲህ እንደሆነ የሚመሰክረውን መልዕክት በምኩራብ ለአይሁድና ለአህዛብ ያስረዳና ይሰብክ ነበር ፡፡ ከአይሁድም ተቃውሞን ማስተናገድ ጀመረ ፡፡ ስለዚህም ጳውሎስ መስበኩን ቀጠለ ነገር ግን ትኩረቱን ፍሬን ወደ አገኘባቸው ወደ አህዛብ ላይ አደረገ ፡፡ በዚህ ጊዜም ጌታ የሚያጸና ቃልን ለጳውሎስ በአንድ ምሽት በራዕይ ተናገረው ፡፡ ጳውሎስን የነገረውን ተስፋ አስታወሰው ፡- “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል ፡፡ “ ጳውሎስም ቀጠለ ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በቆሮንቶስ ለአንድ አመት ከስድስት ወር አስተማረ ፡፡

ልክ እንደ ጳውሎስ በስራህ ውስጥ ስታሳልፍ ፣ በዕለት ተዕለት ተግባርህ ደግሞም እንድሁ በሀላፊነቶችህ የትም ቢሆን ጌታ አለህ ፡፡ እንድሁም ደግሞ ምናልባት ተቃውሞ ሊያጋጥምህ ይችላል ወይም ደግሞ በዚያ ሰዓት ሞገስ ታገኝ ይሆናል ፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ ከጌታ የሚያጸናን ቃል መስማት በጣም አበረታች ነው ፡፡ ጌታ በህልምና በራዕይ ፣ በመጽሀፍ ቅዱስ ቃል እንድሁም ደግሞ በጸሎት ጊዜ በጓደኛ ቃል ጭምር ይናገራል ፡፡ ምናልባት ዛሬ ይህ ከጌታ የሆነው ተስፋ ለአንተ ይሆናል ፡- ““እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል ፡፡ “ በጌታ ስልጣን ተራመድ እንድሁም ልትፈራ እንደማይገባህ በሙሉ ልብህ እመን ፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው !

“ ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን፦ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና አለው ። በመካከላቸውም የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማረ ዓመት ከስድስት ወር ተቀመጠ ። “

  • ሐዋርያት ሥራ 18፡9-11

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 90:17 — “ የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን፡፡ የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና ። “

መዝሙር 138:7 — “ በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች ። “

ኢሳይያስ 41:10 — “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ ። “