Acts Acts

Keep It Simple

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 353 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሐዋሪያት ስራ 17 የጳዉሎስን ሁለተኛ የአገልግሎት ጉዞዉን በመመዝገብሐዋሪያት ኢየሱስ በሰጣቸዉ ስልጣን እንዴት እየተጓዙ እንደ ነበረ ማሳየቱን ቀጠለ ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 15 ጳዉሎስና የጉዞ ጓደኞቹ በመላዉ አለም/ግዛት ወደ ቤተ ክርስቲያን እየተወሰዱ ከነበሩት በኢየሩሳሌም ከነበሩት አማኞች ደብዳቤ ተቀበሉ ፤ በመንገድ ሳሉም ጳዉሎስና በርናባስ ወደ አለመስማማት ተለያዩ ፡፡ ጳዉሎስና ሲላስ በልስጥራ ጢሞቴዎስን ወሰዱት ፡፡ የጢሞቴዎስ እናት አይሁድ ነበረች አባቱ ግን ግሪካዊ ስለ ነበርበአገልግሎት ጉዞ አይሁዶችንም አሕዛብንም ሁለቱንም ለማገልገል ጢሞቴዎስ ተገረዘ ፡፡ በጢሮአዳም እያሉ ከመቄዶንያ የሆነ አንድ ሰዉ መጥተዉ እንዲረዱት የሚጠይቅ አንድ ራዕይ አዩ ፤ በፊልጵስዩስ መላዉ ቤተሰቧ ክርስቶስን በመቀበል የተጠመቁት አንዲት ስሟ ሊድያ የምትባል ሴት አገኙ ፡፡ የአገልጋዮቹ ግማሽ ጉዞ ብቻ ነበር ያለቀዉ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን በመስማት በጳዉሎስና በጉዞ ጓደኞቹ ታወቀ ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 17 አገልግሎታቸዉን በሰዎስት ማህበረሰብ ዉስጥ ይሸፍናሉ፡ ተሰሎንቄ (ቁጥር 1-9), ቤርያ (ቁጥር 10-15) እና አቴና (ቁጥር 16-34) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (17፡ 1)፡ ጉዞዉ በፊልጵስዮስ ተጀመረ ፡፡ ጳዉሎስና ሲላስ በሁለት ከተማዎች ዉስጥ አለፉ፡ በአንፊጶልና በአጶሎንያም ፤ በእነዚህ ከተሞች ዉስጥ ብቻ ማለፋቸዉ መፃፉ አስፈላጊ ነው ፡፡ ጳዉሎስና ሲላስ መንፈስ ቅዱስን ሲያዳምጡ በደንብ የማያገለግሉባቸዉ ስፍራዎች ነበሩ ፡፡ ቆይቶም በዚህ ምዕራፍ ጳዉሎስ “ ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆኑ እግዚአብሄርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰዉን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው “ (ቁጥር 26) ፡፡ ጳዉሎስ ልክ አንደ አንፊጶልና አጶሎንያን በመሰሉት ጥቂት ቦታዎች ወስጥ ብቻ ማለፉ መልካም ነበር ፤ ጳዉሎስ ለአገልግሎት ባነሳሳዉ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተደገፈ ነበር፣ በተሾመበት በዚያን ጊዜ በሚቀሳቀሱበት ስፋራ ያለዉን መንፈስ በቀላሉ አልተረዳዉም ፡፡

ተሰሎንቄ በደረሱ ጊዜ አንድ የአይሁድ ምኩራብ ፈለጉ ፤ አንድ ምኩራብ ለመፍጠር ቢያንስ አስር አይሁዶችን ይጠይቃል/ይፈልጋል ማለትም አስር ቤተሰብ ይሆናሉ ማለት ነው ፡፡ በፊልጵስዮስ ምኩራብ አልነበረም ፡፡ በፊልጵስዮስ ጳዉሎስና ቤተሰቦቹ በወንዙ አጠገብ ወደ እግዚአብሄር የሚፀለዩ እና ከእነርሱ ጋር ወንጌልን የሚካፈሉትን አገኙ ፤ ነገር ግን የምኩራብ መኖር የአገልግሎታቸዉ ስኬት ዋስትና አይሰጥም ፡፡ በእርግጥ ዋይርስቤ ተሰሎንቄ “ ቃሉን በመቃወም “ የተሰየሙ ነበር ፅፏል ፤ ተሰሎንቄ በሮማዉያን ስር የነበረች አንድ የግሪክ ከተማ ነበረች ፤ እንደ ነፃነት እንዳለበት ከተማ ትታወቅ ነበር ማለትም የራሳቸዉን መሪ መርጠዋል የመቄዶኒያም ዋና ከተማ በመሆን አገልግላለች ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (17፡ 2-4)፡ ጳዉሎስ በሰንበት ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ ፤ እነርሱ በብዛት አይሁዶችን ወይም እግዚአብሄርን የሚፈሩ አይሁዶችን የሚመስሉ ናቸው ፡፡ ይህ ቢያንስ ለሰዎስት ሳምንት ተካሄደ/ሆነ ፡፡ ከመፅኀፍት “ ሲጠቅስ/ሲተረጉምም “ ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሳ ይገባዋል “ እያለ እያስረዳ ነበር (ቁጥር 3) ፡፡ እነዚያ ሰዎስት ቃላቶች ( ተረጎመ, አስረዳ እና አሳያቸዉ) የሚሉት ቃላቶች ጳዉሎስ ለተለያ ሰዎች በተለያዩ አገልግሎት አቀራረቦች እንዳገለገለ ያመለክታል ፡፡ የጳዉሎስ ጠቅላላ አገልግሎቱ የተለያዩ አቀራረቦችን በተለያዩ ሁኔታዎችና በተለያዩ ሰዎች በመጠቀም አስፈላጊነቱን አሳይቷል ፤ ጳዉሎስ ሁል ጊዜ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ተመሳሳይ መጠን ጊዜ አልቆየምም ሁልጊዜም ተመሳሳይ አቀራረብና ዘዴም አልነበረዉም ፡፡ ጳዉሎስ ለነበረበት ስፍራ አገባብና ሲያገለግል ስለ ሚመራዉ መንፈስ ቅዱስ ያተኮረ/የተጠነቀቀ ነበር ፤ ይሁን እንጂ ጳዉሎስ የተጠቀመዉ ዘዴ ምንም ይሁን የጳዉሎስ አላማ በግልፅ በቁጥር 4 ላይ ተጠቅሷል፡ ወንጌልን እንዲያምኑ ለማሳመን ተመለከተ ፡፡ አገልግሎታቸዉ ዉጤታማ ነበር ምክንያቱም “ እግዚአብሄርን የሚፈሩ ብዙ ግሪካዉያን እንዲሁም ደግሞ ብዙ የሴቶች ቁጥር አመኑ “ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (17፡ 5-9)፡ የኢያሶን ቤት ምናልባትም ጳዉሎስና ጓደኞቹ የተቀመጡበት ነበር ፤ ሕዝቡም ጳዉሎስን፣ ሲላስንና ጢሞቴዎስን ባላገኟቸዉ ጊዜ ኢያሶን ጳዉሎስና ጓደኞቹ አድርገዉት በነበረዉ ነገር አለመደሰታቸዉንና ኢያሶን ከእርሱ ጋር እንዲቀመጡ ፈቅዶ እንደ ነበር በመግለፅ በህዝቡ ፊት ጎትተዉ አወጡት ፡፡ ሕዝቡም መልዕክታቸዉን በግልፅ ባለመረዳት ኢየሱስን ትክክለኛዉ ንጉስ ነዉ በማለት የቄሳሪያን ስልጣን ዝቅ አድርገዋል በማለት ጳዉሎስና ጓደኞቹን ከሰሷቸው ፡፡ የከተማዋም አለቆች “ ከኢያሶንና ከሌሎቹም ዋስ በመቀበል “ (ቁጥር 9) ለቀቋቸው ፤ ለመለቀቅ ጉቦ ከፈሉ ፡፡ አንዱ “ የዋስትና “ ጉዳይ/መስፈርት ጳዉሎስ ወደ ተሰሎንቄ አይመለስም ፤ ከዚህ በኋላ ጳዉሎስ ወደ ቤርያ ተጓዘ ፡፡ ጳዉሎስ ለሰዎስት ሳምንታት በተሰሎንቄ እንደ ነበረ እናዉቃለን - በዚያ አገልግሎቱ በሐዋሪያት ስራ 9 ቁጥሮችን ብቻ ይሸፍናል - ነገር ግን እነርሱን ለመጎብኘት ለቤተ ክርስቲያን ሁለት ደብዳቤዎች ፅፏል ፡፡

ጳዉሎስ “ በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለዉን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን እግዚአብሄርን ሁልጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን “ በማለት ፅፏል (1ተሰ 1፡ 2-4) ፡፡ የተሰሎንቄ አማኞች በጳዉሎስ ላይ መነሳሳትን አድርገዋል ፡፡

1ተሰ (1፡ 5) በሐዋሪያት ስራ 17 ለተሰሎንቄ የጳዉሎስን ዘጠኙን ቁጥሮች አገልግሎት ይገልፃል ፤ ጳዉሎስ “ ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና ፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታዉቃላችሁ “ በማለት ፅፏል ፡፡ ጳዉሎስ በተሰሎንቄ በቃል ወንጌልን ሰበከ ፤ መሰከረላቸዉ፣ ገለፀላቸው፣ ስላሳያቸዉና ስላሳመናቸዉ ያምናሉ ፤ ነገር ግን የጳዉሎስ አገልግሎት በቃል ብቻ የተወሰነ አልነበረም ፤ ጳዉሎስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ እነርሱ እንደ መጣ አገናኘዉ ፡፡ እነርሱን ለማግኘት በሌሎች ስፍራዎች ላይ እየዘለለ ነበር ፤ በተጨማሪም ጳዉሎስ ወደ ተሰሎንቄ “ በእምነት “ ወይም “ በመነቃቃት “ ማለት ሊሆን በሚችለዉ “ በማረጋገጫ “ መጣ ፡፡ ኢየሱስን መከተል ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ለሌሎች ወንጌልን ለመስበክ ምሳሌ ሆናቸዉ ፡፡ በሰዎስት አጭር ሳምንታት እንኳን አዲስ አማኞች ስደት/መከራ ገጠማቸዉ ነገር ግን አዲስ እምነታቸዉን እንዲተዉ እንዲያሳምናቸዉ ለመከራቸዉ አልፈቀዱለትም ፡፡ ከጳዉሎስ በኋላ ተግቶ መስራታቸዉና ሞደል መሆናቸዉ በአካባቢዉ ለሌሎች ምሳሌ ሆኑ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (17፡ 10)፡ ጳዉሎስ ከተሰሎንቄ ወደ ቤርያ ተጓዞ ነገር ግን በተሰሎንቄ የነበረዉ አጭር ጊዜ በከተማዋ ላይ፣ በራሱ ላይና በታሪኩ ዉስጥ ባሉት ክርስቲያኖች ላይ በጣም ልቅ ተፅዕኖ ነበረው ፡፡

መደምደሚያ

ወንጌልን መስበክን በጣም የተወሳሰበ ማድረግ እንችላለን ነገር ግን ጳዉሎስ በተሰሎንቄ ቀጥተኛ በሆነ ዘዴ/ስልት ወደ ፊት ቀጠለ ፡፡ በሲሞን ቤት በመቀመጥ ኢየሱስ መሲሁ እንደ ነበር ተረጎመ፣ ገለፀም አሳያም፣ በመንፈስ ቅዱስ መሪነትና አጋዥነት ስር አደረገዉ እንዲሁም በመነሳሳት አደረገው ፡፡ ብዙ ጊዜ እነዚህን ሁሉንም አካላቶች/ይዘቶች በአንድ አናስቀምጥም ፡፡ አገልግሎታችሁን ቀለል አደርጉት ፤ እነዚህን ቁልፍ አካላቶችን በማብራራት ጌታ እንዴት እንደሚቀሳቀስ /እንደሚጓዝ እዩ ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Acts (Colorado Springs, CO: David C Cook, 1989), p. 469.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1401.

ጥያቄዎች

  1. ተሰሎንቄ፣ ቤሪያ እና አቴና ለወንጌል እንዴት በተለያየ መልኩ ምላሽ ሰጡ ?
  2. በጊዜዉ አዲስ ኪዳን ባለመኖሩ በምን መፅሀፍት ጳዉሎስ ለሕዝቡ ምክንያት ለማቅረብ እንደተጠቀመ ታስባላችሁ ? (መዝሙር 22፣ ኢሳያስ 53፣ ዘካሪያስ 12)
  3. ጳዉሎስን ለማበረታታት በርናባስ ምን አደረገ ? በሚነግራችሁ በሌላ ሰዉ ላይ ከመደገፍ ይልቅ ለራሳችሁ መፅሀፍን ማንበብና ማጥናት ለምን አስፈላጊ/ጠቃሚ ነው ?
  4. ጳዉሎስ ቤሪያን እንዲለቅ የተገደደዉ ለምን ነበር ? እንዴትስ ምላሽ ሰጠ ?
  5. “ ለማይታወቅ አማልዕክት “ የተባለ አንድ መሰዊያ አቴና ለምን ነበር ያላት ? በመልዕክቱ ጳዉሎስ ስለ እግዚአብሄር የተናገረዉ ጥቂት እዉነቶች ምንድን ናቸው ? (ሐዋ 17፡ 24-34)
  6. በሐዋሪያት ስራ 17 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 17:13–14

“But when the Jews from Thessalonica found out that God’s message had been proclaimed by Paul at Berea, they came there too, agitating and disturbing the crowds. Then the brothers immediately sent Paul away to go to the sea, but Silas and Timothy stayed on there.”

ጳውሎስ በሁለተኛ የአገልግሎት ጉዞው ኢየሱስ እርሱ መሲህ እንደሆነ እየመሰከረ ፤ ከመጽሀፍም እየገለጠ የኢየሱስን ወንጌል ያስረዳ ፣ ይተረጉምና ያሳይ ነበር ፡፡ አንዳንዶች ተቀብለው አመኑ ፡፡ ነገር ግን ብዙዎች ፣ በተለይም አይሁዶች ቀኑ እንድሁም ጳውሎስን ያስፈራሩ ዘንድ መንጋን ሰበሰቡ ከዚህም አልፎ ጳውሎስን ያበሳጩና አገልግሎቱን ይረብሹ ዘንድ ከተሰሎንቄ እስከ ቤርያ ተከተሉት ፡፡ ነገር ግን ጳውሎስ በጉዞው ብቻውን አልነበረም ፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በጢሞቲዎስና በሲላስ ላይ ተደግፎ ነበር እነርሱም ከእርሱ ኋላ በመሆን በቤርያ የተነሳውን ተቃውሞ ይጋፈጡ ነበር ይህም ጳውሎስን ወንጌልን ወደፊት እንድያራምድና ወደ አቴና እንድጓዝ አስቻለው ፡፡

ጓደኝነትን መመስረትና ከሌሎች ጋር በህብረት መቆየት በተለይም የመከራና የስደት ጊዜያትን በምታሳልፍበት ጊዜ በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ከጎንህ የሚቆምና ውጊያውን እንድትዋጋ የሚረዳህ ሰው ያስፈልግህ ይሆናል ይህም በጸሎት ወይም ደግሞ ለአንተ በመናገር መርዳት ሊሆን ይችላል ፡፡ ራስህን ከህብረት አታርቅ ፡፡ ብቸኛ እንደሆንክ ማንም እንደሌለህ ከተሰማህ በጸሎት እግዚአብሔርን ጠይቅ ሸክምህን የምታካፍለው ሰው እንድሰጥህ ፡፡ አስታውስ እንደ እግዚአብሔር ልጅ አንተ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል ነህ ፡፡ ብቻህን አይደለህም ፡፡

“በተሰሎንቄ ያሉት አይሁድ ግን ጳውሎስ በቤርያ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ሰበከ ባወቁ ጊዜ፥ ወደዚያው ደግሞ መጡና ሕዝቡን አወኩ ። በዚያን ጊዜም ወንድሞቹ ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ ። “

  • ሐዋርያት ሥራ 17፡13-14

ተጨማሪ ጥቅስ

1ኛ ቆሮንቶስ 12:26 — “ አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል ። “

ገላትያ 6:2 — “ ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ ። “

2ኛ ጢሞቴዎስ 3:12 — “ በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ ። “