ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሐዋሪያት ስራ መፅኀፍ እየተከናወኑ ያሉ ብዙ አሉ - በእዉነት ለመልካም ነገር ምክንያቶች የሆነ ፡፡ እየሆነ የነበረዉ ሁሉም ነገር ለሐዋሪያቱ አዲስ ነበር ! ከኢየሱስ በመማር ሰዎስት አመታትን አሳልፈዉ ነበር ፤ መሰቀሉን ተመልክተዉ ስለ ነበር ትንሳኤዉን እና ወደ ሰማይ ማረጉን መስክረዋል ፡፡ መንፈስ ቅዱስን በመቀበል በዚህ ነገር መጓዝን ጀመሩ ፡፡ ከዚያም ሳዉል ኢየሱስን በደማስቆ መንገድ ላይ አገኘዉ እንደ ኢየሱስ ተከታይ እና ሐዋሪያት በሙሉ የተቀየረ ህይወት ነበረው ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 15 እምነት በሌላቸዉ በአዲሶች ቤተ ክርስቲያን እንዴት ወደ ፊት እንደምትቀጥል ለመወሰን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ ፡፡ በምዕራፉ መጨረሻ ላይ እንደ ወዳጅ በበርናባስና በጳዉሎስ መካከል መለያዬት ነበር ፤ በርናባስ ማርቆስ ዮሐንስን ሲወስድ ጳዉሎስ ከሲላስ ጋር ለመጓዝ ሄደ (ሐዋ 15፡ 36-41) ፤ ይህ ፀብ ወይም መከፋፈል አልነበረም ነገር ግን የአገልግሎት ቡድንን ቁጥር እጥፍ ለማድረግ በግል አስተያዬት መለያዬት ነበር ፤ በዚህ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ጠንካራ ነበረች ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (16፡ 1-5)፡ ከኢየሩሳሌም በሰሜን በመሄድ ጳዉሎስ ወደ ደርቤንና ልስጥራ ደረሰ ጢሞቴዎስን አገኘው ፡፡ ከግሪክ አባቱና ከአይሁድ እናቱ በሀያዎቹ ያነሰ ወይም በልጅነቱ ያነሰ/ልጅ በመሆን ጢሞቴዎስ ወጣት ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን “ በእምነት እንደ እዉነተኛ ልጁ “ (1ጢሞ 1፡ 2) ገልፆታል ፤ ጢሞቴዎስ የጳዉሎስ ተማሪ በመሆን በመጨረሻም የጳዉሎስ የታመነ የስራ ጓድ ሆነ (1ቆሮ 4፡ 17, 1ተሰ 3፡ 2, ፊል 2፡ 19) ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጢሞቴዎስ ከተሸመ በኋላ (1ጢሞ 4፡ 14) ጳዉሎስንና ሲላስን ተቀላቀለ (2ጢሞ 1፡ 6) ፤ በመጨረሻም ጢሞቴዎስ እንደ የጳዉሎስ አገልግሎት አጋር የሲላስን ስፍራ ወሰደ ፡፡ የግሪክና የአይሁድ የሁለቱም ቤተሰብ እንደ መሆኑ ጢሞቴዎስ የሁለቱንም አለም ያገኝ/የመድረስ መብት ነበረው ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን የአይሁድን ተቀባይነት እንዲያሟላ ካስገረዘዉ በኋላ ከእርሱ ጋር ወሰደው (ቁጥር 2-3) ፤ የጢሞቴዎስ መገረዝ “ ከጳዉሎስና ከሲላስ ጋር ወደ ምኩራብ ገብቶ ለመጎብኘት ሙሉ “ እድል ሰጠው ፤ ያለመገረዝ አይሁድ ጢሞቴዎስ የአይሁድነት ዘሩን አጥቶት እንደ ነበር ሊያመለክቱ ይችላሉ ፡፡ ጳዉሎስ፣ ሲላስ እና ጢሞቴዎስ እንደ ተጓዙ የኢየሩሳሌም መማክርት ዉሳኔን በማድረስ ቤተ ክርስቲያንን በእምነትና በአዲስ ለዉጥ በሁለቱም አጠነከሩ (ቁጥር 4-5) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (16፡ 6-10)፡ የጳዉሎስ እቅድ በእስያ መስበክ ነበር ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በዚያ እንዳይሄድ ከለከለው (ቁጥር 6)፣ መንፈስም ወደ ቢታኒያ እንዳይሄዱ ከለከላቸው (ቁጥር 7) ፡፡ በአጌን ባህር (በቀድሞዉ ዘመን በግሪክና በቱርክ መካከል የነበረ ከፍተኛ የንግድ መስመር) የባህር ወደብ በነበረችዉ በጢሮአዳ ጳዉሎስ አዲስ ራዕይ ተሰጠው - በመቄዶንያ እንዲያስተምር መጠራቱን አየ (ቁጥር 8-9) ፤ ይህ ከጳዉሎስ ስድስት ራዕዮች ዉስጥ ሁለተኛዉ ነበር (ሐዋ 4፡ 36, 18፡ 9-10, 22፡ 17-18, 23፡ 11, 27፡ 23-24) ፡፡ መቄዶንያ የግሪክ ግዛት በየብስ ላይ የምትገኝ ነበረች ፤ “ ወንጌልን ከኤስያ ወደ አዉሮፓ ለመዉሰድ “ ቀጣያ እርምጃ ሆነች ፡፡ ጳዉሎስ, ሲላስና ጢሞቴዎስ ወዲያዉኑ ስለ መቄዶንያ ወሰኑ (ቁጥር 10) ፤ ይህ ሉቃስን እንደ አንድ ተጓዥ በማካተት የመጀመሪያዉ “ እኛ “ የሚል የጉዞ ክፍል መጀመሪያ ነው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (16፡ 11-15)፡ ጉዞአቸዉ በጣም ቀጥተኛዉን/ቀላሉን መንገድ ተጠቀሙ - ከጢሮአዳም ወደ ሳሞትሬቄ ደሴት ሄድን ፤ ቀጥሎም በሁለተኛዉ ቀን ወደ መቄዶንያ ዋና ወደብ ናጱሌ ከዚያም ከናጱሌ በምድር ላይ ወደ ምትገኘው የመቄዶንያ መሪ/ትልቅ ከተማ ወደ ሆነችዉ ፊልጵስዩስ በቀጥታ ሄዱ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ጳዉሎስና ጓደኞቹ ስለ መቄዶንያ ወይም ስለ ፊልጵስዩስ ከተማ ምንም ነገር አያዉቁም ! በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ስር ተጓዙ ፡፡ በዚያ ለብዙ ቀናት ቆዩ፣ በሰንበትም ለመፀለያ ስፍራ ለማግኘት ከከተማዋ ዉጪ ወደ ወንዝ ሄዱ (ቁጥር 13) ፤ ለእነርሱ ለአምልኮ የሚሆን ምኩራብ በፍልጵስዩስ አልነበረም ምክንያቱም በከተማዋ ከአስር የሚያንሱ አይሁዶች ስለ ነበሩ ፡፡ በዚያ ወንዙ ላይ ከተሰበሰቡት ሴቶች ጋር ሲነጋገሩ በኤስያ ትገኝ ከነበረች ከትያጥሮስ የነበረች እግዚአብሄርን የምታመልክና የሚናገሩትን ትሰማ የነበረች ልድያ የምትባል አንዲት አሕዛብ አገኙ (ቁጥር 13) ፡፡ ልድያ የዉድ ቀይ ልብስ ሻጭ ባለፀጋ ነበረች ፡፡ እግዚአብሄርም ልቧን ጳዉሎስ እየተናገረ ለነበረዉ ነገር ከፈተው (ቁጥር 14) ፤ ልድያና ቤተሰቧ ወዲያዉኑ ወንጌልን በመቀበል ተጠመቁ ፡፡ ልድያም ጳዉሎስንና ጓደኞቹን በቤቷ እንዲቆዩ ለመነቻቸው (ቁጥር 15) ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር አንዲት ሴትን በተለዬ መልኩ ስለ ተጠቀመባት ጠቅላላ ቤተሰቧ ወደ እዉነት መጣ ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 16 በእግዚአብሄር ጊዜ ምክንያት ሁሉም ነገር ሆነ/ተፈጠረ - ጳዉሎስ ኤስያ ከመግባት የተከለከለ ሆነ፣ ጳዉሎስ ወደ አዲስ ሰራተኛ ወደ ጢሞቴዎስ ተመራ በተጨማሪም ጳዉሎስ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ለመሆን ዝግጁ ወደ ነበረችና ጠቅላላ ቤተሰቧ ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርግ ወደ መራችዉ ከኤስያ ወደ ሆነች አንዲት ሴት ተመራ ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ልድያ ለጳዉሎስ፣ ለሲላስና ለጢሞቴዎስ ቤቷን ብቻ አልነበረም የከፈተችላቸዉ በፊልጵስዩስ ለቤተ ክርስቲያንም በር ከፈተች እንጂ (ቁጥር 40) ፡፡ ጳዉሎስና ልድያ የእግዚአብሄርን መንፈስ በመስማት ታዘዙ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1466.
MacArthur, p. 1467.
MacArthur, p. 1467.
MacArthur, p. 146.
ጥያቄዎች
-
በሐዋ (16፡ 3) ከመዉጣታቸዉ/ከመሄዳቸዉ በፊት ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ገረዘው ፤ ያን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ?
-
በግል አስተያየታችሁ መንፈስ ቅዱስ ወደ እስያ፣ ወደ ሚስያ እና ወደ ቢታንያ እንዳይሄዱ ለምን ከለከላቸዉ?
-
በሐዋ (16፡ 16-18) ጳዉሎስ ከአገልጋይቱ/ከባሪያይቱ ሴት የጥንቆላን መንፈስ ለምን እንዳስወጣዉ ተደንቃችሁ ታዉቃላችሁ ? እዉነት እየተናገረች ስለ ነበር ለምን አስወጣው ?
-
ጳዉሎስ በእርሱ ከተሰቃየም በኋላም እንኳን ለእስር ቤት ጠባቂዉ ምህረትንና ቸርነትን አሳዬ ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ ሌላ የት ላይበኢየሱስ ሰዎች አጠገብ እንዲህ አይነቱ ምህረት ሲታይ እናያለን (ሐዋ 7፡ 60) ? በራሳችሁ ህይወት እንዲህ አይነቱን ምህረትና ቸርነት እናሳያለን ብላችሁ ይሰማችኋል ? ስለ አለምስ ? ለምን ወይም ለምን አይሰማችሁም ?
-
በሐዋሪያት ስራ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 16:6–7
“They went through the region of Phrygia and Galatia and were prevented by the Holy Spirit from speaking the message in Asia. When they came to Mysia, they tried to go into Bithynia, but the Spirit of Jesus did not allow them.”
ጳውሎስ ፣ ሲላስ እና ጢሞቴዎስ የተባለው ወጣቱ ደቀ መዝሙር ሁለተኛውን የአገልግሎት ጉዞ ጀመሩ ፤ መንፈስ ቅዱስ በእስያ የወንጌል መልዕክትን እንዳይናገሩ ከለከላቸው እንድሁም ወደ ቢታንያ እንድሄዱም አልፈቀደላቸውም ፡፡ በጢሮአዳም ምሽቱን ሲያሳልፉ ወደ መቄዶንያ እንድሄድ የሚመራ ራዕይ ለጳውሎስ መጣለት ፡፡ ጳውሎስ ራዕዩን ካየ በኋላ ወንጌልን ለመስበክ ወደ መቄዶንያ ተነሱ ፡፡ ከተዘጉ ሁለት በሮች በኋላ ፣ በእርግጠኝነት በመጨረሻ እግዚአብሔር ልድያ ለተባለች ነጋዴ ሴት ሰጣቸው ፡፡ እሷና መላ ቤተሰብዋም ዳኑ ! እግዚብሔር ከሁሉም የተሸላ እቅድ ነበረው !
በቃ ቀጥታ ወደ ሌላ የተዘጋ በር ለመሮጥ አንድ የተዘጋ በር እንዳንኳኳህ ተሰምቶህ ያውቃል ? መሸማቀቅ ፣ ግራ መጋባት ደግሞም ተስፋ መቁረጥ ሊሰማህ ይችላል ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት እግዚአብሔርን ማመንህን ቀጥል ፡፡ በሩ መዘጋቱን እርሱ እንደሚያውቅ እመን ፡፡ መሸማቀቅህን እርሱ እንደሚያውቅ እመን ፡፡ አስታውስ እግዚአብሔር ለአንተ እቅድ እንዳለው እንደተናገረ ፡፡ ጽና ፡፡ እርሱን ስትጠብቅ እግዚአብሔር ያበረታሃል ፡፡ የሚመራህን መንፈስ ቅዱስን አድምጥ ፡፡ የእግዚአብሔር እቅድ አሁንም ለአንተ ምርጡ እቅድ ነው ደግሞም ለጉዞህ ወጋ አለው ፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔር እርምጃ ልክ ወደ እግዚአብሔር ቦታ መራመድህን ቀጥል እናም በእርሱ ዘንድ ብቻ የሚገኘውን ሰላምና ደስታ ትቀበላለህ ! ተስፋ አትቁረጥ !
“ በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ ፤ በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም ፡፡ “
- ሐዋርያት ሥራ 16፡6-7
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ3:5–6 — “ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን ፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል ። “
ኤርምያስ 29:11 — “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም ። “
ሐዋርያት ሥራ 16:9–10 — “ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር ። ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።