Acts Acts

The Jerusalem Council

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 351 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ አንድ ቃላችን ስልጣን ነው ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 15 አሕዛቦች ኢየሱስን ወደ መከተል በተቀየሩ ጊዜ ወንጌልን የማጋራት/የማካፈል ስልጣን ወደ ጥያቄ መጣ ፡፡ አገልጋይ ዊልያም ኬሪይ “ እግዚአብሄር ከአረመኔነት በመቀየር በሚያስደስተዉ ጊዜ ጉልበተኛ ሰዉ ይቀመጣል ! ያለ ድጋፋችሁ ወይም ያለ አሳባችሁ ያደርገዋል “ ብሏል ፤ ነገር ግን ያ እንድናደርገዉ እግዚአብሄር ከጠራን የተለዬ ነው - በሌሎች ፊት በምስክርነታችን መሄድ ነው ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 15 እነዚህ እምነት የሌላቸዉ እንዴት ወደ ቤተ ክርስቲያን ማምጣት እንደሚቻል ለመወሰን እንደ ሐዋሪያትና ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች የኢየሩሳሌምን መማክርት መገናኘትን ይመዘግባል ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (15፡ 1-5)፡ የሰዎች ስብስብ ከይሁዳ በመምጣት (የአይሁድ እምነት ተከታዮች ተብለዉ የሚታወቁት) መገረዝ ለድነት የሚያስፈልግ ድርሻ እንዳለዉ አስተማሩ (ቁጥር 1) ፤ እነዚህ የአይሁድ እምነት ተከታዮች “ የክርስትና እምነትን የአይሁድ እምነት ወገን እንዲሆን ፈለጉ ….አሕዛብ አማኞችን የአይሁዳዊያን አዲስ አባል እንዲሆኑ ፈለጉ “ ፡፡ በክርክሩም ምክንያት ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም ከሌሎች የክርስቲያን መሪዎች ጋር እንዲገናኙ ጳዉሎስንና በርናባስን ጠራች (ቁጥር 2) ፡፡ ክርክሩ በኢየሱስ ባለዉ እምነት ላይ እንደ መስፈርት መገረዝን መጨመር ከላይ ወደ ታች ከተቀደደ በኋላ በቤተ መቅደሱ ላይ መጋረጃዉን መስፋት መሞከር ነበር (ሉቃ 23፡ 45) ፡፡ ኢየሱስ ቀድሞ ገደቦቹን/መሰናክሎቹን አስወግዷቸዋል፣ አሁን ደግሞ የአይሁድ እምነት ተከታዮች መሰናክሎቹን መልሰዉ ቦታቸዉ ላይ ማስቀመጥ ፈለጉ (ኤፌ 2፡ 14-16) ፤ በመጨረሻም የአይሁድ እምነት ተከታዮች በአሕዛብ አማኞች ላይ የሕግን ቀንበር ለመጫን እየሞከሩ ነበር (ገላ 5፡ 1) ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንለድነት/ለመዳን አማኞችን ወደ ተጨማሪ መስፈርቶች አስተሳሰብ ስር በማስቀመጥ መልሰዉ እንዲሄዱ/እንዲሳቡ ላለማድረግ መጠንቀቅ አለባት ፡፡ ጳዉሎስና በርናባስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዙ ስለ አሕዛቦች መለወጥ በመንገር በመካከላቸዉ ደስታን ፈጠሩባቸው (ቁጥር 3) ፡፡ በኢየሩሳሌም በቤተ ክርስቲያንና በመሪዎቿ መልካም አቀባበል ተደረገላቸው (ቁጥር 4) ፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ፈሪሳዊያን የነበሩ አማኞች ለአሕዛብ መቀየር/መለወጥ መገረዝና የሙሴን ህግ መጠበቅ አስፈላጊ እንደ ነበሩ እንደ ገና ተናገሩ (ቁጥር 5) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (15፡ 6-11)፡ የክርስቲያን መሪዎች (የኢየሩሳሌም መማክርት ተብለዉ የሚታወቁት) ለመወሰን ተሰበሰቡ (ቁጥር 6) ፡፡ ሁሉም ወገን ጴጥሮስ በመጨረሻ እግዚአብሄር ለአሕዛብ ወንጌል እንዲያደርስ ጠርቶት እንደ ነበርና እግዚአብሄርም ለእነዚህ አማኞች መንፈስ ቅዱስን እንደ ሰጣቸዉ በማስታወሱ ጉባኤዉን እስከሚናገር ድረስ ተከራከሩ (ቁጥር 7-8) ፡፡ ጴጥሮስ እግዚአብሄር በአይሁዶችና በአሕዛብ መካከል ልዩነት እንዳላደረገ በማብራራት/በመግለፅ እግዚአብሄር የማይፈልገዉን ተጨማሪ ቀንበር ለምን ለመጫን እየሞከሩ እንደ ነበር ጠየቃቸው (ቁጥር 9-10) ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር በመካከላቸዉ ያለዉን ልዩነት እንዳጠፋዉ “ ይገልፃል ፡፡ ቁጥር 11 በሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ የተመዘገበዉን የጴጥሮስን የመጨረሻ ቃል ይይዛል፡ “ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን “ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (15፡ 12-21)፡ የተሰበሰበዉም ሕዝብ በርናባስንና ጳዉሎስን እግዚአብሄር በአሕዛብ ዉስጥ እያደረገ የነበረዉን ሁሉንም ሲገልፁላቸው አደመጧቸው (ቁጥር 12) ፤ ከዚያም ያዕቆብ (የኢየሱስ የእናቱ ልጅ/በአንድ በኩል ወንድሙ) በሲሞን ላይ ሰምቶት የነበረዉን የእግዚአብሄርን ንቅናቄ (ቁጥር13-14) በመጨመር የተሰበሰበዉን ሕዝብ ነቢያት የእግዚአብሄር ቃል ለአሕዛብም እንደ ነበር አሳሰባቸው (ቁጥር 15-18) (አሞ 9፡ 11-12, ኢሳ 45፡ 21) ፡፡ አስታዉሉ ያዕቆብ ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ድረስ እንደ መሲህ ኢየሱስን ወደ ማመን አልመጣም ፤ ያዕቆብ ለክርክሩ መፍትሄ አቀረበ - መገረዝ ሳይሆን “ ከጣዖት ርኩሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም መራቅ “ (ቁጥር 20-21) እንደሚያስፈልግ አቀረበ እንጂ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (15፡ 22-29)፡ የተሰበሰቡትም በእነዚህ ሁኔታዎች በመስማማት ከደብዳቤዉ ጋር በመሄድ ዉሳኔአቸዉን ለመግለፅ የሚሄዱ ሰዎች ለመምረጥ ወሰኑ (ቁጥር 22-29) ፡፡ ዋይርስቤ በተሰበሰቡት ዉሳኔ መሰረት የመጡ ሰዎስት ስኬቶችን አመልክቷል፡

  1. ዉሳኔዉ ባለመስማማት የተለየች ከመሆን ቤተ ክርስቲያንን በአንድ ላይ ወደ አንድነት አመጣት ፡፡
  2. ዉሳኔዉ ቤተ ክርስቲያን ለጠፋዉ እንዴት ምስክር መሆን እንደምትችል አንድ የሆነ አቀራረብ ፈጠረ ፡፡
  3. ዉሳኔ መጋራቱ ቤተ ክርስቲያንንና ይህን የተቀበሉትን አማኞች ተቀበሉ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (15፡ 30-35)፡ መልዕክተኞቹም ደብዳቤዉን ወደ አንጾኪያ አደረሱ በዚይ የነበሩትም አማኞችም በማበረታቻዉ ተደሰቱ (ቁጥር 30-32) ፡፡ ጳዉሎስና በርናባስ ከሌሎች ጋር የክርስቶስን መልዕክት እየተናገሩ በአንፆኪያ ተቀመጡ መልዕክተኞቹን ግን መልሰዉ በኢየሩሳሌም ወደ ወንድሞቻቸዉ ተላኩ (ቁጥር 33-35) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (15፡ 36-41)፡ በጊዜዉ ጳዉሎስና በርናባስ አዲስ የተቀየሩት ምን እያደረጉ እንደ ነበር ለመጎብኘት ሰብከዉባቸዉ በነበሩት ስፍራዎች ሁሉ ጎበኙ (ቁጥር 36) ፡፡ በርናባስ ማርቆስ ዮሐንስ አብሯቸዉ እንዲሄድ ፈለገ ነገር ግን ጳዉሎስ ማርቆስ ዮሐንስ ከእነርሱ ጋር እንዲሄድ አልፈለገም ምክንያቱም ከዚህ በፊት ማርቆስ ዮሐንስ ትቷቸዉ ሄዶ ስለ ነበር (ቁጥር 37-38) ፤ ይህ በበርናባስና በጳዉሎስ መካከል የተፈጠረዉ አለመግባባት ለጓደኝነታቸዉ መለያዬት ምክንያት ሆነ ፡፡ በርናባስ ማርቆስን ከእርሱ ጋር በመዉሰድ ወደ ቆጵሮስ ሄደ (39) ፤ ጳዉሎስ ሲላስን በመዉሰድ በኪልቅያና በሶሪያ ዉስጥ ዞረ (ቁጥር 40-41) ፡፡

መደምደሚያ

ሐዋሪያት ስራ 12 መጨረሻ ላይ ከሐዋሪያት ስብከት እና ወንጌል ስርጭት ወደ ጳዉሎስ የአገልግሎት ጉዞ የሐዋሪያት ስራ ታሪክ ሽግግር ነው ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1397.

  2. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Acts (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989) p. 462.

  3. Wiersbe, p. 464.

ጥያቄዎች

  1. በሐዋ (15፡ 1) ከሙሴ ሁኔታ/ስርዓት በኋላ ስለ ግርዛት ማጣቀሻ ተደረ ፤ ይህ ማጣቀሻ/ማመሳከሪያ ምንድን ነው ? (ዘፍ 17፡ 10-14, 34፡ 21-24, ዘሌ 12፡ 3)
  2. በሐዋ (15፡ 14-17) ያዕቆብ እግዚአብሄር አሕዛቦችን ስለ መጎብኘቱ ተናገረ ፤ ቁጥር 16 ስለ መታደስ ያወራል ፡፡ ስለዚህ በትንቢት የተናረዉ ሌላ ማነው ? (ኢሳ 9፡ 6-7, ዳን 7፡ 13-14, ሆሴ 3፡ 4-5)
  3. ሐዋ (15፡ 21) በሁሉም ከተማ በምኩራብ የሙሴ ህግ ተሰብኮ እንደ ነበር ይናገራል ፤ በግል አስተያየታችሁ በአሁኑ ጊዜም ያ እዉነት ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
  4. በሐዋሪያት ስራ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 15:11

“On the contrary, we believe we are saved through the grace of the Lord Jesus in the same way they are.”

ጳውሎስና በርናባስ ከመጀመርያ የአገልግሎት ጉዞአቸው በተመለሱ ጊዜ ሁለቱ ሰዎች በዝርዝር ስለ አህዛብ መለወጥ መስክረው ነበርና ክርክር ተነሳ ፡፡ የክርክሩም ዋና ነጥብ የሚያጠነጥነው በሙሴ ህግ መሰረት ክርስትያን አህዛቦች እንደ አማኝ ለመቆጠር መገረዝ አለባቸው ወይ የሚለው ነበር ፡፡ በአማኞችም መካክል አንድነትን ለማምጣት ሐዋርያትና ሸማግሌዎች የኢየሩሳሌም ሸንጎ ተብሎ በሚጠረው በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ ፡፡ ከብዙ ውይይትም በኋላ ጴጥሮስ ፡- “ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን ፡፡ “ ከዚያም ያዕቆብ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት መጽሀፍ ጠቅሶ ፡- “ የሰው ልጅ ሁሉ ፣ አህዛብም ጭምር በእግዚአብሔር ስም ተጠርተዋል “ አለ ፡፡ ከዚያም የኢየሩሳሌሙ ምክር ቤት ወደ እግዚአብሔር በተመለሱት አህዛብ ላይ ምንም አይነት ክልከላ እንዳያደርጉባቸው ወሰኑ ፡፡

አማኞች ለአለም ሊያቀርቡት የሚችሉት ትልቁ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ምንድን ነው ? በአማኞች መካከል አንድነት ፡፡ ኢየሱስ እንድህ አለ ፡- አለም ማወቅ ያለበት እግዚአብሔር ልጁን የላከው ፣ አለም አንድነትን በሚፈልግ ጊዜ ነው ፡፡ ስለዚህ ከሌላ አማኝ ጋር አለመግባባት ካለ መስማማትን ፈልጉ ፡፡ እሱን ሳትወያዩበት ደብቃችሁ ከላይ ከላይ ብቻ ለመንካት አትሞክሩ እናም እንደሚጠፋ ተስፋ አታድርጉ ፡፡ በአለመስማማት ውስጥ እንዴት በትህትና መመላለስ እንደምትችሉ እግዚብሔርን ጠይቁ ፡፡ ተሰብሰቡና ተነጋገሩበት ፡፡ ጥበብን እንድሰጣችሁና እርቅን እንድያደርግላችሁ መንፈስ ቅዱስን ፈልጉ ፡፡ ሰላምን ለማምጣት በመጣው በኢየሱስ ላይ አትኩሩ ፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ወንድምና እህት ከሆኑት አንድነት የሚከለክልህ ነገር ካለ መንፈስ ቅዱስን ጠይቅ ? በል አሁን ሂድና በመታዘዝ አድርገው ፡፡

“ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን ።.”

—ሐዋርያት ሥራ 15:11

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዮሐንስ 17:23 — “ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል ። “
  • ሐዋርያት ሥራ 15:17–18 — “ ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ ። “
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 1:10 — “ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ ።