The Conclusion of Paul's First Missionary Journey
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሐዋሪያት ስራ የመጀመሪያዎቹ 12 ምዕራፎች በቀደመችዉ ቤተ ክርስቲያን የጴጥሮስን ስራ ይሸፍናል ፤ በሐዋሪያት ስራ 13 ትኩረቱ ወደ ጳዉሎስ ዞረ ፡፡ ሐዋ (28፡ 30-31) ጳዉሎስ ወደ ሮም መወሰዱን፣ በተከራየበት በራሱ ቤት ሁለት አመትን እንዳሳለፈ፣ የጎበኙት ሁሉ በደህና እንደተቀበሉትና በድፍረት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማራቸው ይነግረናል ፤ ይህ ጳዉሎስ በአገልግሎት አመታቱ ዉስጥ እንዴት እንደ ኖረ ነበር ፡፡ የሐዋሪያት ስራ 13 ፈጣን ዳሰሳ ለመጀመሪያ የአገልግሎት ጉዞ ጳዉሎስና በርናባስ ተሾመዉበት በነበሩበት በሶሪያ አንፆኪያ ጳዉሎስ መስበኩን ይገልጣልሰ ፡፡ በቆጵሮስ ደሴት ላይ ጳፉን ጎበኙ ፤ ጳዉሎስና በርናባስ ማርቆስ ዮሐንስ ትቷቸዉ ወደ ሄደባት ጴርጌን ቀጠሉ ፤ ጳዉሎስ የመጀመሪያዉን ስብከት ወደ ሰጠበት በጲስድያ ወደ አንፆኪያ ተጓዙ ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 14 የጳዉሎስን የመጀመሪያ አገልግሎት ጉዞ ማጠቃለያ ይሸፍናል ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (14፡ 1)፡ ጳዉሎስና በርናባስ መከፋፈል ወደ ገጠማቸዉ ወደ ኢቆንዮንም ተንቀሳቀሱ/ተጓዙ ፡፡ ማክአርቱር ለኢቆንዮንምን የነዋሪዎች/የተወላጆች ማህበረሰብ “ ባህል እንደ የጋራ መኖሪያ “ ጠቅሷታል፡ የግሪክ፣ የአይሁድና የሮማዉያን ግዛቶችን ፡፡ ብዙ አይሁዶችና ግሪኮች አመኑበት ስፍራ ላይ መጀመሪያ በምኩራብ በመናገር ስርዓቱን/ሂደቱን ተከተሉ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (14፡ 2-3)፡ ለማመን እምቢ ያሉት አይሁዶች አሕዛቦችን በጳዉሎስ እና በበርናባስ ላይ አዞሩባቸው/አስነሱባቸው ፡፡ የሆኑ ሰዎች እየሰራችሁ ያላችሁትን ወይም ደግሞ እናንተን ካልወደዱ ሴራ ማሰር ይጀምራሉ ፡፡ ጳዉሎስና በርናባስ ግን በእነርሱ ድንቅና ታዓምራትን ስለ አደረገዉ ሰለ ክርስቶስ በድፍረት ተናገሩ (ቁጥር 3) ፡፡ የሆነን ሰዉ ስለ ጌታ በድፍረት እንዲናገር የፈቀደላቸዉ ምንድን ነው ? በዉስጣቸዉ ያለዉ መንፈስ ቅዱስ ፤ ነገር ግን በዚያ ዉስጥ አንጠለፍ/አናልፍም ምክንያቱም ሌሎች የሚመልሱትን ስለምንፈራ ፡፡ በአሜሪካ በማንኛዉም ሰዉ መወቀስ/መከሰስ ስለማንፈልግ ወደ ኋላ በመሳብ ስለ ክርስቶስ በድፍረት አንናገረም ፡፡ በዮሐንስማክአርቱር ገለፃ መሰረት ምልክቶች ከተዓምራቱ ኋላ የእግዚአብሄርን ኃይል ያመለክታሉ ፤ ድንቆች/አስደናቂ ነገሮች ሰዎች ለመለኮታዊ ስራዎች ወይም ድንቆች ምስክር በመሆን ሲለምዱት የሚደነቁባቸዉ ናቸው ፡፡ እነዚህ ምልክቶችና ድንቆች እንደ እግዚአብሄር የእዉነት መልዕክተኞች እነዚህን ሰዎች ያረጋግጣሉ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (14፡ 4)፡ በከተማዋ ያሉ ሰዎች ተከፋፈሉ፣ አንዳንዶች ከአይሁድ ወገን ሌሎች ደግሞ ከሐዋሪያት ወገን ፡፡ ሐዋሪያ የሚለዉ ቃል “ የተላከ “ ማለት ነው ፤ በይበልጥ ብዙዎች ቃሉን በማር (3፡ 17-19) ክርስቶስ እርሱን እንዲከተሉት መርጣቸዉ የነበሩት 12 እንደሚያመለክት ይስማማሉ ፤ ከዚያም ይሁዳ ሲወጣ ማቲያስን ጨመሩ ፡፡ ማክአርቱር ክርስቶስ ሐዋሪያቱን ሐዋሪያነታቸዉን እንዲያረጋግጡና እንዲያጠናክሩ ኃይል እንደ ሰጣቸዉ አመልክቷል ፡፡ ከብዙ በላይ/ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሁሉም አዲስ ኪዳን መፅሀፍት በአንድ ሐዋሪያ የተፃፈ ነበር ፡፡ ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን መሰረት ነው ፡፡ የጳዉሎስን የደማስቆ መንገድ ልምምድ እንዳየነዉ (ሐዋሪያት ስራ 9) ኢየሱስ ጳዉሎስን መርጦታል ይህ ማለትጳዉሎስ ክርስቶስን በማየቱ/በመቅመሱ ምክንያት ምስክር ወይም ሐዋሪያ መሆን ይችላል ፡፡ ብዙ ወግ አጥባቂ አስተሳሰቦች ሐዋሪያት ክርስቶስ ሕያዉ እንደ ነበር ያገኙትና የተለማመዱት ነበሩ ይላሉ ፤ ስለሆነም ለጌታ እንደ መልዕክተኛ ማገልገል ችለዋል ፡፡ በ 2ቆሮ (8፡ 23) ጳዉሎስ ቲቶን እንደ ባልንጀራና እንደ አብሮ ሰራተኛ እና ወንድሞችን ደግሞ እንደ ቤተ ክርስቲያን መልዕክተኞች ገልፆአቸዋል ፤ በ 2ቆሮ (11፡ 13) ጳዉሎስ ሐሰተኛ ሐዋሪያቶች እንደ ነበሩ ተናግሯል - ይህ ማለትም እዉነተኛ ሐዋሪያቶች አሉ ፤ ምናልባትም ክርስቶስን በፍፁም በአካል ያላገኙት በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛ ሐዋሪያት ነበሩ ፡፡ በኤፌ (4፡ 11-13) ጳዉሎስ ኢየሱስ “ አንዳንዶች ሐዋሪያት እንዲሆኑ፣ አንዳንዶች ነቢያቶች፣ አንዳንዶች ወንጌል ሰባኪዎች እና አንዳንዶችን አስተማሪዎችና ሰባኪዎች አድርጎ እንደ ሰጠ “ ተናግሯል ፡፡ አንዳንዶች በቤተ ክርስቲያን “ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመስራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ “ (ኤፌ 4፡ 12)አምስት የአገልግሎት ዘርፎች አሉ የሚል ሀሳብ ይይዛሉ ፡፡ በኢቆንዮን እንደ ነበረዉ መከፋፈል በአሁኑ ጊዜም በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን መከፋፈል አለ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ለሐዋሪያት እና ለነቢያት እዉቅና ስለማንሰጥ ፤ ይሁን እንጂ ጳዉሎስ ለአገልግሎት ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት/ለማሳደግ አስፈላጊ እንደ ነበሩ ተናግሯል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (14፡ 5-7)፡ መከፋፈሉ በጣም መጥፎ በመሆኑ ምክንያት ሰዎች ጳዉሎስንና በርናባስን መዉገር ፈለጉ ፤ ነገር ግን ጳዉሎስና ጓደኞቹ/አብረዉት የነበሩት ሰሙ ወንጌል መስበካቸዉን ወደ ቀጠሉበትም ወደ ልስጥራና ደርቤ ሸሹ ፡፡ ለምን ጳዉሎስ ሸሸ ? በማቴ (10፡ 23) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች በሚያሳድዷቸዉ ጊዜ “ ወደ ሌላ ከተማ እንዲያመልጡ “ እንዳዘዛቸው እናስታዉሳለን ፤ በኢቆንዮን ስደት ሲገጥማቸዉ ጳዉሎስ መልስ መስጠት እንደማይችል ህፃን ልጅ ሳይሰማዉ ወደ ልስጥራና ደርቤ ለመሸሽ ፍቃድ ነበረው ፡፡ ብዙ ጊዜ ጳዉሎስ ከመከራ/ከስቃይ ሸሽቷል ነገር ግንበተልዕኮዉ/በአገልግሎቱ ቀጠለ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (14፡ 8-20)፡ በልስጥራ ወንጌልን ሲሰብኩ ከንቱ ኃሳብ ገጠማቸው ፤ ጳዉሎስ ሲሰብክ ለመፈወስ እምነት የነበረዉን ከመወለዱ ጀምሮ ሽባ የሆነን አንድ ሰዉ አዬ (ቁጥር 9) ፡፡ በድፍረት ያለምንም እንቅፋት ጳዉሎስ ሰዉዬዉን እንዲነሳ ነገረው ፤ ሰዉዬዉም እየዘለለ ተመላለሰ (ቁጥር 10) ፡፡ ሕዝቡም ጳዉሎስንና በርናባስን እንደ አማልዕክት ሄርሜን እና ድያ ብለዉ በመጥቀስ ምላሽ ሰጡ (ቁጥር 11-12) ፤ ከዚያም የድያ ካህን ለጳዉሎስና ለበርናባስ መስዋዕት በሚቀርብባቸዉ በሮች ላይ ኮርማዎችን አመጣ (ቁጥር 13) ፡፡ ማክአርቱር በቀድሞዉ ተረትና ምሳሌዎች መሰረት ድያና ሄርሜን ለምግብና ለመኖሪያ ለመጠየቅ ልስጥራን ጎበኙ ነገር ግን እምቢ እንደ ተባሉ ይገልፃል ፤ በእርግጥ ፊልሞን ብቻ (የመፅኀፍ ቅዱሱ ፊልሞን ሳይሆን) እንዲበሉት ምግብና እንዲቀመጡበት ስፍራን ድያን እና ሄርሜን ሰጣቸው ፡፡ በምላሹም ድያንና ሄርሜን እነርሱን ለመርዳት ፍቃደኞች ያልነበሩትን ሁሉንም ጎርፍ እንዲወስዳቸዉ ምክንያት ሆኑ ፤በመጨረሻም ካህንና የሴት ካህን ወደ ሚኮንበት ቤተ መቅደሱ ዉስጥ የፊልሞንና የሚስቱ ንብረት በሆነዉ አንድ ትንሽ ጎጆ ዉስጥ ተመለሱ ፡፡ የልስጥራ ሕዝብ ጳዉሎስንና በርናባስን ባዬ ጊዜ ድያ እና ሄርሜን ማንነታቸዉን ሳያሳዉቁ ወደ ከተማ እየመጡ እንደ ነበር አሰቡ ድያና ሄርሜን እንደ ገና ከተማቸዉን እንዲያጠፉ አልፈለጉም ፡፡
ነገር ግን ሐዋሪያት፣ በርናባስና ጳዉሎስ ልብሳቸዉን በመቅደድ ለልስጥራ ሰዎች ማን እንደ ነበሩ እና ለምን በዚያ እንዳሉ ለመናገር ፈጠኖ/ሮጡ (ቁጥር 14-18) ፡፡ በርናባስና ጳዉሎስ “ ከእነዚህ ከንቱ ነገሮች ወደ ህያዉ እግዚአብሄር” (ቁጥር 15) እንዲዞሩ አሳሰቧቸው ፡፡ ለሐዋሪያት ስራ ቃላችን ስልጣን እንደ ሆነ እናስታዉሳለን ፤ በድፍረት ለመናገር በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በምንጓዝ ጊዜ ስልጣን አለን ፡፡ ጳዉሎስ በዚህ የአገልግሎት ጉዞ ድፍረትን አሳዬ ፡፡ እነዚህን ነገሮችም በመናገር ጳዉሎስና በርናባስ ብቻቸዉን ለእነርሱ እንዳይሰዉላቸዉ ሕዝቡን አስቆሙት (ቁጥር 18) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (14፡ 19-20)፡ ከዚያም በልስጥራ የነበሩትን ሰዎች ተከትለዉ እና ተባብረው የነበሩት ከኢቆንዮን የመጡት አይሁዶች ጳዉሎስን በድንጋይ በመዉገር ከከተማዋ ዉጪ ጣሉት ምክንያቱም ገድለዉት እንደ ነበር ስላሰቡ (ቁጥር 19) ፤ ጳዉሎስ በዉሸት የሞተ ሆኗል ወይም መንቀሳቀስ ወይም መናገር አልቻልቻለም ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ጳዉሎስን በከበቡት ጊዜ በመነሳት ወደ ከተማዋ ሄደ ፡፡ በማግስቱም ወደ ደርቤ ሄዱ (ቁጥር 20) ፤ መከራዉ/ስደቱ እያለ ጳዉሎስ ስራዉን ቀጠለ ምክንያቱም ለአሕዛብ፣ ለነገስታትና ለእስራኤላዊያን የብርሃን አገልጋይ እንዲሆን እንደተሸመ ስለሚያዉቅ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (14፡ 21-28)፡ በደርቤ ወንጌልን ከሰበኩ በኋላ ወደ ልስጥራ፣ ኢቆንዮን እና አንፆኪያ ተመለሱ (ቁጥር 21) ፤ ጳዉሎስና በርናባስ ተመልሰዉ ወደ አንጾኪያ በመምጣት ሆኖ የነበረዉን ሁሉንም ነገር በመስጠትና እግዚአብሄር “ ለአሕዛብ የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ “ (ቁጥር 27) ፡፡ ብዙ ስነ መለኮታዊያን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲያስተምሩና ሲያሰለጠኑ ለአንድ አመት ያክል አሳልፈዋል ይላሉ ፤ ጳዉሎስ ሌሎችን ለማሰልጠን በዚህ አለፈ ፡፡
መደምደሚያ
ሐዋሪያት ለመሆን፣ ነቢያት ለመሆን፣ ወንጌል ሰባኪ ለመሆን፣ አስተማሪ ለመሆን ወይም ደግሞ ሰባኪ ለመሆን በአገልግሎት ህይወታችሁን መስራት አለባችሁ ፡፡ እዉነተኛ ህይወትን በማድረጋችን ሌሎችን ለማሰልጠንና ለማዘጋጀት መንፈስ ቅዱስ በእኛ በኩል ሊናገር ይችላል በዚህም ብዙ ሊሰሩ ይችላሉ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 366.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1461.
MacArthur, p. 1461.
MacArthur, p. 4651.
Wiersbe, p. 367.
MacArthur, p. 1462.
ጥያቄዎች
-
ለመከፋፈል ምክንያት ስለ ሆኑትና ብጥብጥን ስለ ዘሩት (ሐዋ 14፡ 2) መፅኀፍ ምን ይላል ? (ምሳ 6፡ 14, 16-19, ሮሜ 16፡ 17-18, ቲቶ 3፡ 9-11) ልክ እንደዚህ ከሆነ ሰዉ ጋር ገጥሟችሁ ያዉቃል ? አዎ ከሆነ ግለፁ
-
በሐዋ (14፡ 3) መሰረት ጳዉሎስና በርናባስ በድፍረት የሚናገሩትን የፀጋዉን መልዕክት እንዴት አፀናላቸዉ/አረጋገጠላቸው ? በድንቅና በምልክት ያላችሁን ማንኛዉንም ምስክርነት ግለፁ
-
ጳዉሎስ አንካሳዉ ሰዉዬ የዳነ ለመሆን እምነት እንደ ነበረዉ አስተዋለው (ሐዋ 14፡ 9) ፤ የተፈወሰ ለመሆን ይህ መስፈርቱ ነው ? መልሳችሁን በሌሎች መፅኀፍት አስደግፉ
-
ሕዝቡም ለጳዉሎስና በርናባስ መስዋዕት ለማቅረብ ሲሞክሩ ጳዉሎስ በሐዋ (14፡ 16-17) ምላሽ ሰጣቸው ፤ እነዚህ ጥቅሶች በእርሱ ህያዉ ምስክሮች ላይ የእግዚአብሄርን መልካምነት እንድትረዱ እንዴት ይረዷችኋል ?
-
ሐዋ (14፡ 21) “ በዚያችም ከተማ ወንጌልን ከሰበኩ በኋላ ብዙዎችን ደቀ መዛሙርት አደረጉ “ ይላል ፤ ብዙዎች ተቀየሩ አይልም ፡፡ ወንጌልን ስትሰብኩ የሆነ ሰዉ ኢየሱስ የእርሱ/የእርሷ ጌታ ሲያደርጉት ኃላፊነታችሁን እንዴት ታዩታላችሁ ?
-
ጳዉሎስና በርናባስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት “ በብዙ ችግር ዉስጥ ማለፍ አስፈላጊ እንደ ነበር “ በመግለፅ በእምነታቸዉ እንዲቀጥሉ አበረታቷቸው ፤ ሌሎች ጥቅሶች ይህን በምን ይረዳሉ ሰዎችንስ እንዲረዱት ያስችላሉ ?
-
በሐዋሪያት ስራ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 14:21–22
“After they had evangelized that town and made many disciples, they returned to Lystra, to Iconium, and to Antioch strengthening the disciples by encouraging them to continue in the faith and by telling them, ‘It is necessary to pass through many troubles on our way into the kingdom of God.’”
ጳውሎስና በርናባስ እግዚአብሔር ለመጀመርያ የአገልግሎት ጉዞአቸው ከመራቸው በኋላ ከከተማ ወደ ከተማ ተዘዋወሩ ፡፡ በእምነታቸው እንድጸኑ በመንገር ደቀ መዛሙርቱን ለማበርታት ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ ። ጳውሎስና በርናባስ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንደ አማኝ በብዙ መከራ ውስጥ ሊያልፉ እንደሚገባ ነገሩዋቸው ፡፡ ጳውሎስና በርናባስ ራሳቸው መከራና ስደት ደርሶባቸዋል ከዚህ ሁሉ ጋር ግን ወንጌልን ሲመሰክሩ በደስታና በመንፈሳዊ እድገት ነበር ፡፡ እግዚአብሔር ጸጋን ሰጣቸው በመንገዳቸውም አበረታቸው ፡፡
የእግዚአብሔርን መንግስት ስትሻ ለአንተም እንድሁ ተመሳሳይ ነው ፡፡ መከራና ስደትን ትቀበላለህ ? አዎ ፡፡ ነገር ግን በርታ በተስፋም ጽና ፡፡ እግዚአብሔር አለምን አሸንፏል ፡፡ እምነት ይኑርህ ፡፡ ከምትቀበለው ከማንኛውም መከራ እግዚአብሔር ይበልጣል ፡፡ ወንጌልን ስትመሰክር ፣ ኢየሱስን ላይ አትኩር በተትረፈረፈ ጸጋውም ትበረታለህ ፡፡ ከእግዚአብሔር የሆነው ተልዕኮ በእርሱ ኃይልና ስልጣን እንድትወጣና ስሙን እንድታውጅ ፡፡ ይህን በማድረግ ራስህን በፊት መስመር ላይ ታስቀምጣለህ ምናልባት በኮርፖሬት መስሪያ ቤት ፤ በተልዕኮ ቦታ ፣ በጉርብትናህ ወይም በቤተስብህ ውስጥ ሊሆን ይችላል ፡፡ ለኢየሱስ ድምጽ ሁን ፤ በመከራም እንደሚያጸናህ እመን ፡፡
“ በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ ። “
- ሐዋርያት ሥራ 14፡21-22
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ16:33 — “ በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ ። “
ሐዋርያት ሥራ 14:26–27 — “ ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ ። በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ ። “
2ኛ ቆሮንቶስ11:28–31 — “ የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው ። የሚደክም ማን ነው፥ እኔም አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፥ እኔም አልናደድምን ? ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ፥ ከድካሜ በሚሆነው ነገር እመካለሁ ። ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።