Barnabas and Saul Set Apart For God's Work
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሪቫይቭ ት/ቤት አንዱ ዋነኛ ራዕይ በሁሉም 66 መፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍት የመሲሁን ሙሉ ስዕል ማመልከት ነው ፡፡ በማቴ (5፡ 17) ኢየሱስ ህግንና ነቢያትን ለመፈፀም እንጂ ለማጥፋት እንዳልመጣ ተናገረ ፤ ያንን ነዉ የምናየው -የመፅኀፍት መፈፀም ወደ ህይወት ሲመጣ ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ከጴጥሮስ ህይወት ወደ ጳዉሎስ የጉዞ አገልግሎቶች የፈጠነ ቅያሪ/መዞር እናደርጋለን ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ “ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም እንደ ተጀመረች ከዚያም ሰማሪያ፣ ደማስቆ፣ ቂሳሪያና በሶሪያ አንፆኪያን በማካተት ወደ ከተሞች እንደ ተሰራጨ ፤ ቢያንስ 40 የተለያዩ ከተሞች በሐዋሪያት ከተሞች እንደ ተጠቀሱ “ ፅፏል ፡፡ በሐዋ (1፡ 8) ኢየሱስ ሐዋሪያቱን ወንጌልን በኢየሩሳሌም ከዚያ በይሁዳና በሰማሪያ እና እስከ ምድር ዳር ድረስ እንዲሰብኩ ነግሯቸዉ ነበር ፤ አሁን ያን መስፋት በሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ እናየዋለን ፡፡ ሄነሪይ ማርትይን “ የክርስቶስ መንፈስ የሚልክ/የአገልግሎት መንፈስ ነው፣ እርሱን በደንብ ስንቀርበው በኃይል አገልጋዮች/የተላክን እንደምንሆን “ ፅፏል ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ጊዜን ማሳለፍ ስለ እርሱ ለሌሎች ለመናገር በሚገባ ይትረፈረፋል ፡፡ ሐዋሪያት ስራ (13-14) ስድስት ከተሞችን ያካተተዉን የጳዉሎስን የመጀመሪያ ጉዞ ይሸፍናል ፤ ጳዉሎስ በአንፆኪያ ጀምሮ በአንፆኪያ ጨረሰ ፡፡ ሐዋሪያት ስራ (15-18) በ50-52 AD 18 ወራት ያክል የወሰደዉን የጳዉሎስን ሁለተኛዉን የአገልግሎት ጉዞ ይሸፍናል ፡፡ ሐዋሪያት ስራ (18-21) ሁለት አመትና ሰዎስት ወር የወሰደዉን የጳዉሎስን ሰዎስተኛ ጉዞዉን ይሸፍናል ፡፡ ጳዉሎስ እነዚህን ጉዞዎች በተጠራበት የእግዚአብሄርን ስም ለአሕዛብ፣ ለነገስታትና ለእስራኤላዊያን በመሸከም አደረገ (ሐዋ 9፡ 15) ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (13፡ 1-3)፡ ሳዉል (ጳዉሎስ) እና ሌሎች አምስት ሰዎች መንፈስ ቅዱስ “ በርናባስንና ሳዉልን ለጠራኋቸው ስራ ለዩልኝ “ (ቁጥር 2) ባለ ጊዜ እየፆሙና እየፀለዩ ነበር ፡፡ በርናባስና ሳዉል በመጀመሪያዉ የአገልግሎት ጉዞ ላይ ተላኩ ፤ ፆመዉ ነበር ማለትም ምግብ መብላት አቁመዉ ነበር ማለት ነው ( በአሁኑ ጊዜ ለእኛ የተለመደዉ እንጂ ሌላ አይነት ፆም አይደለም ) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያና ማክአርቱር ሁለቱም በብሉይ ኪዳን አንድ ሰዉ ለመስዋዕት አንድ እንስሳት ሲያቀርብ ኃጢዓትን እንደ መለያ ዘዴ በእንስሳቱ ላይ በማስቀመጥ በመስዋዕቱ ላይ እጆቹን እንደ ሚያስቀምጥ ይናገራሉ ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ኢየሱስ ሰዎችን ሲፈዉስ በተለዬ ሰዎቹ ላይ እጆቹን ጭኗል ፡፡ ይህ ትንሽ የሰዎች ቡድን ለእነርሱ ሲፀልዩላቸው በበርናባስና ሳዉል ላይ እጆቻቸዉን ጫኑባቸው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (13፡ 4-5)፡ የመጀመሪያዉ የአገልግሎት ጉዞ በሴሌዉቅያ፣ በቆጵሮስ እና በስልማንም ያለዉን ያካትታል ፤ ብዙዉ የጳዉሎስ ጉዞ በዉሃ ላይ ስለ ተካሄደ ጳዉሎስ ችሎታ ያለዉ መርከበኛ የሆነ ነበር ፡፡ ቆጵሮስ የበርናባስ የትዉልድ አገሩ ነበረች ፡፡ በአገልግሎት ጉዞአቸዉ ዉስጥ ለመስበክ በአይሁዶች ምኩራብ ሄዱ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (13፡ 6-12)፡ በርናባስና ሳዉል መልካሙን ዜና በመናገር በመላዉ ደሴቲቱ ዉስጥ ሄዱ ፤ በጳፉ በደረሱ ጊዜ ሰርግዮስ ጳዉሎስ የሚባለዉ አገረ ገዢ ሰዉ ከእርሱ ጋር ወንጌልን ለመካፈል ሲሰበስባቸው የተቃወማቸዉን አንድ ጠንቋይ አገኙ/ገጠማቸው ፡፡ በቁጥር 9 ለመጀመሪያ ጊዜ ሳዉል ጳዉሎስ ተብሎ ተገለፀ/ተለዬ ፤ ሳዉል የዕብራዊ ስሙ ሲሆን ጳዉሎስ ደግሞ የሮማዊ ስሙ ነበር ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ጳዉሎስ በጠንቋዩ ላይ አትኩሮ በመመልከት በተንኮልና በማጭበርበር የተሞላ የፅድቅ ጠላት የዳቢሎስ ልጅ በማለት ጠራው ፤ ጳዉሎስም የእግዚአብሄር እጅ በእርሱ ላይ እንደሆነችና እዉርም እንደ ምታደርገው ተናገረው ፡፡ አገረ ገዢዉም ይህ ሲያይ በጌታ አመነ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (13፡ 13)፡ በጳዉሎስ የአገልግሎት ጉዞ የወንጌልን መልዕክት በፍፁም አልቀየረም ነገር ግን እንደ አካባቢዉ ሁኔታ ዘዴዉን/አቀራረቡን ቀይሯል ፡፡ ወንጌልን ለማጋራት/ለመስበክ ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ፈቃደኞች መሆን አለብን ፡፡ ጴርጌን ሲደርሱ ማርቆስ ዮሐንስ ትቷቸዉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ ፡፡ ማርቆስ ዮሐንስ ጳዉሎስና በርናባስን እንዲከዳ የሆነ ነገር ተፈጥሯል ፤ ዋይርስቤ ይሆናሉ የሚላቸዉን ምክንያቶች ገልፃል፡- ምናልባትም ናፍቆ ነበር፣ ምናልባትም አሕዛቦች ጌታን ወደ ማወቅ መምጣታቸዉን አልወደደዉም፣ ምናልባትም ጳዉሎስን አልወደደዉም ወይም ደግሞ በጴርጌን የሚገጥማቸዉን አደጋ ፈርቶ ነበር ፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ጳዉሎስ የቡድኑን አካል አጣ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (13፡ 14-15)፡ ከዚያም ጳዉሎስና በርናባስ በጲስድያ አንዮኪያ ደረሱ ፤ እዚህ ከተማ ለመድረስ በሰሜን ከ100 ማይል በላይን 600 ጫማ ከፍታ ተጉዘዉ ነበር ፡፡ በሰንበትም ወደ ምኩራብ በመሄድ ተቀመጡ (ቁጥር 14) ፤ የምኩራቡ መሪዎች ከህግና ከነቢያት ካነበቡ በኋላ ጳዉሎስንና በርናባስንእንዲናገሩ ጋበዟቸው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (13፡ 16-25)፡ እነዚህ ቁጥሮች የጳዉሎስን የመጀመሪያ ስብከት ይዘዋል ፡፡ እግዚአብሄር እንዴት እስራኤልን እንደመረጠና ሰባት አገሮችን/አሕዛቦች ወዳጠፋበት ስፍራ ወደ ከነዓን እንዴት እንዳመጣቸው ግልፅ ታሪክ ሰጣቸው ፡፡ ዘዳ (7፡ 1) እግዚአብሄር ኬጢያዊዋንን፣ ጌርጌሳዊዋዉያንን፣ አሞራዊያንን፣ ከነዓናዊያንን፣ ፌርዛዊያንን፣ ኤዊያዊያንን እና ኢያቡሳዊያንን አጠፋቸዉ ይላል ፤ ይህ ሁሉ 450 አመት ያክል ፈጅቷል (ቁጥር 20) ፡፡ ጳዉሎስ ብሉይ ኪዳንን እና የሕዝቡን ቡድን ታሪክ - የእስራኤላዊያንን ጠቀሰ ፤ ከዚያም ጳዉሎስ እግዚአብሄር መሳፍንትን፣ ነቢዩ ሳሙኤልን ሰጣቸው፣ ንጉስ ሲፈልጉ ደግሞ እግዚአብሄር ንጉስ ሳዖልን ሰጣቸው አለ ፡፡ ከ40 አመታት በኋላ እንደ ንጉስ ሳዖል በማስወገድ “ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ “ (ቁጥር 22) ዳዊትን ሰጣቸው ፤ ከዚያም ከዳዊት ዘርም “ እግዚአብሄር ለእስራኤል አዳኙን ኢየሱስን አመጣው “ (ቁጥር 23) ፡፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ የመጥምቁ ዮሐንስን ሚና እንደ ኢየሱስ መንገድ ጠራ ገለፀዉ (ቁጥር 24-25) ፡፡ በዚህ የስብከት አካሉ ጳዉሎስ እግዚአብሄር ተስፋ ለተገባዉ መሲህ ያደረገዉን ዝግጅት ገለፀው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (13፡ 26-37)፡ ቀጥሎም ጳዉሎስ ለአድማጮቹ አዋጅ አደረገ ፤ ጳዉሎስ የእግዚአብሄር የድነት መልዕክት ተላከላችሁ (ቁጥር 26) ነገር ግን በመፍረድ (ቁጥር 27) እንዲገድለዉ ጲላጦስን ጠየቀዉ (ቁጥር 28) አላቸው ፡፡ ከዚያም በመስቀል ላይ በማዉረድም በመቃብር አኖሩት (ቁጥር 29) ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ከሞት አስነሳው (ቁጥር 30) ከዚያም በኋላ ለብዙዎች ታዬ (ቁጥር 31) ፡፡ 1ቆሮ (15፡ 6) ኢየሱስ ከ500 በላይ ለሆኑ ምስክሮች ታይቷል ይላል ፡፡ ይህን አዋጅ በማድረግ ሂደት ላይ ጳዉሎስ ከመዝ (2፡ 7)፣ ከኢሳያስ 55 እና ከመዝ (16፡ 10) ጠቀሰ ፤ ጳዉሎስ ያለማቋረጥ መልዕክቱን በመመለስ ከብሉይ ኪዳን ጋር አስተሳሰረ/አገናኘ ፡፡
3 John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1459; Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Acts (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1394.
4 Wiersbe, p. 365
ሐዋሪያት ስራ (13፡ 38-52)፡ በመጨረሻም ጳዉሎስ የግል ማመልከቻዉን አደረገ ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለእናንተ የኃጢዓት ይቅርታ የታወጀ/የመጣ ነው (ቁጥር 38) ፡፡ ጳዉሎስ ለሁሉም እምነታቸዉን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እንዲያስቀምጡ እድሎችን ሰጣቸዉ ምክንያቱም በእርሱ የሚያምን ማንኛዉም ሰዉ ስለሚፀድቅ ፡፡ ሰዎች በወንጌል ሲያምኑ አይሁዶች ብዙ ሕዝብ በማየት እርሱን በመሳደብ ጳዉሎስ የሚሰብከዉን ተቃወሙ (ቁጥር 45) ፡፡ ጳዉሎስና በርናባስ መጀመሪያ ለአይሁዶች የእግዚአብሄርን መልዕክት እየተናገሩ እንደሆነ በመናገር ምላሽ ሰጡ ነገር ግን አይሁዶች ኢየሱስን ባለመቀበላቸው ወደ አሕዛብ ይዞራሉ (ቁጥር 46) ፡፡ በግልፅ ተልዕኮአቸዉን አዉቀዋል - መልዕክቱን ለአሕዛብ ማድረስን ፤ በመጀመሪያዉ የአገልግሎት የሆነዉ ያ ነው ፡፡
መደምደሚያ
ይህ ምዕራፍ ጳዉሎስ በሐዋ (1፡ 8) እና ሐዋ (9፡ 15) እንደ ኖረ ያሳያል ፡፡ ነገ ሐዋሪያት ስራ 14 ስናጠና የአገልግሎት ጉዞ ሲቀጥል እናያለን ፡፡
6Wiersbe,p.366.
7 Wiersbe, p. 366.
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 364.
Wiersbe, p. 364.
Wiersbe, pp. 365–366.
ጥያቄዎች
-
ጳዉሎስ እና በርናባስ መንፈስ ቅዱስ ጠርቷቸዉ ለነበረዉ ስራ ለዩልኝ ባለ ጊዜ በአንፆኪያ የቤተ ክርስቲያን አካል ነበሩ ፤ ያ ስራ ምን ነበር ? ለተለየ ስራ የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ገጥሟችሁ ያዉቃል ? አዎ ከሆነ ግለፁት
-
በሐዋ (13፡ 6-12) አንድ ሐሰተኛ ነቢይ አገረ ገዢዉን ከእምነት ለማዞር ተመለከተ ፤ የዚህ ሰዉዬ ድርጊት እንዴት ወደ አገረ ገዢዉ ማመን መራ ? አንድ ሰዉን በክርስቶስ ወደ እምነት በመምራት ያበቃ ተቃዉሞ ወይም ተቃርኖ ገጥሟችሁ ያውቃል ? አዎ ከሆነ ዝርዝሩን ከምትወያዩት ቡድናችሁ ጋር ተካፈሉ/ተጋሩ
-
ሐዋ (13፡ 27) አንብቡ ፤ መሲሁን እንዴት እንዳልተረዱት ወይም ስለ እርሱ የሆኑት ትንቢቶች መፈፀማቸዉን ስለ አለመረዳታቸዉ ግለፁ
-
እግዚአብሄር ኢየሱስን ከሞት ሲያስነሳው ለማን ተገለጠ፣ እንዴትስ ምላሽ ሰጡ ? (ሐዋ 10፡ 40-42, 13፡ 30-32, 1ቆሮ 15፡ 5-7)
-
በሐዋ (13፡ 38-39) መሰረት የሙሴ ህግ ሰዎችን ነፃ መሆን ያልቻሉት ከምን ነገር ነበር ? አሁን ከሁሉም ነገር እንዴት ነፃ ወጣን ?
-
ሐዋ (13፡ 48) “ ለዘላለም ሕይወትም የተዘጋጁ የተዘጋጁ ሁሉ አመኑ “ ይላል ፤ መልሳችሁን በመፅሀፍት በማስደገፍ ምን ማለት እንደሆነ ግለፁ
-
በሐዋሪያት ስራ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 13:2–3
“As they were ministering to the Lord and fasting, the Holy Spirit said, ‘Set apart for Me Barnabas and Saul for the work I have called them to.’ Then after they had fasted, prayed, and laid hands on them, they sent them off.”
በአንጾኪያ ቤተ ክርስትያን አገልግሎት ላይ መንፈስ ቅዱስ መሪዎችን ሳውልና በርናባስን እግዚአብሔር ለጠራቸው ስራ እንድለዩ መራቸው ፡፡ ቀድሞ ጳውሎስ ኢየሱስን በደማስቆ መንገድ ላይ ባገኘ ጊዜ እግዚአብሔር ለሐናንያ ጳውሎስ የእርሱን ስም በአህዛብ ፣ በነገሥታትና በእስራኤላውያን ፊት ለመሸከም የተመረጠ እቃ እንደሆነ ነግሮት ነበረ ፡፡ አሁን ደግሞ ጊዜው ነበር ፡፡ የቤተ ክርስትያን መሪዎችም ከጾሙ ፣ ከጸለዩና እጃቸውን በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ከጫኑባቸው በኋላ ወደ መጀመሪያ የአገልግሎት ጉዞአቸው ላኩዋቸው ፡፡
ለአምልኮ መሪነት ፣ ለመጋቢነት ፣ ለሚሄድ አገልጋይነት ወይም በአገልግሎት ውስጥ በሆነ መንገድ ለማገልገል እንደተጠራህ የተሰማህ ጊዜያት በህይወትህ ይኖራሉ ፡፡ ምናልባት አሁንም ያ ጊዜ እስኪመጣ እየጠበክ ይሆናል ፡፡ አስታውስ ይህን ነገር በራስህ እንድሆን ማድረግ አትችልም ፡፡ በጸሎት ፣ እግዚአብሔርን በመፈለግ እንድሁም እግዚአብሔር እንድታልፍበት በሚመራህ በማንኛውም መንገድ በመሄድ ፣ በመንገድህ ሁሉም ጥበብን በመያዝ ቀጥል ፡፡ እግዚአብሔር በትክክለኛው ጊዜ በሩን ይከፍታል ፡፡ እግዚአብሔር ወደ አዲስ የአገልግሎት ዘመን ሲመራህ የቀድሞዋን ቤተ ክርስትያን ምሳሌ ተከተል ፡- መንፈስ ቅዱስ ለመሪዎች ተናገረ ፤ እነርሱም ጾሙ ፣ ጸለዩ እጃቸውንም ጭነው ላኩ ፡፡ በትዕግስት ሲጠብቁት ሰዎችን ለመንግስቱ ወደ አዲስ ተፅእኖ ፈጣሪ ቦታ እንደሚጠራ ስለ ሰጠው ተስፋ እግዚአብሔርን አመስግን ፡፡
“ እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ ። በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው ። “
- ሐዋርያት ሥራ 13፡2-3
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 6:8 — “ የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ ። “
ኢሳይያስ 43:1 — “ አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ ። “
ሐዋርያት 9:15 — “ ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።