The Result of Earnest Prayer
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ሁሉም ሐዋሪያቱ በሉቃስ ወንጌል ተመርዉት የነበረዉን በእዉነት ሲጓዙበት ያሳያል ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 12 አንዱ የህይወት አንዱ የሞት ሁኔታ ነው ፤ ዋይርስቤ ሐዋሪያት ስራ 12 መዝ (34፡ 15-16) ወደ ህይወት እንደሚመጣ እንደ ማንቂያ ጥሪ ይገልፀዋል ፡፡ የጌታ አይኖች እየተመለከቱ ነው (1ጴጥ 3፡ 12) ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (12፡ 1-5)፡ ምዕራፉ ሄሮድስ በጭካኔ አንዳንዶችን በቤተ ክርስቲያን በማጥቃቱና የዮሐንስ ወንድም ያዕቆብን እንደገደለዉ በሚለዉ ሪፖርት ይጀምራል (ቁጥር 1-2) ፡፡ ያዕቆብ ከሐዋሪያት የተሰዋ የመጀመሪያዉ ነበር ፡፡ ንጉስ ሄሮድስ በኢየሱስ መወለድ ጊዜ ሁሉንም ህፃናት ገድሏቸዉ የነበረዉና ከ37-44 AD አስተዳድሮ የነበረዉ ታላቁ ሄሮድስ የልጅ ልጅ ሄርድስ አግሪጳ የመጀመሪያዉ በመባልም ይታወቅ ነበር ፡፡ ሄሮድስ መጥምቁ ዮሐንስን ገሎት የነበረዉ ሄሮድስ የእህት ልጅ ነበር ፡፡ ሄሮድስ በሮም እዳዎችን አጠፋ ለማስተዳደር በተመረጠበት በሰሜን ፍልስጤም ወደ ፍልስጤም አመለጠ ፤ በጊዜው ሄሮድስ ከአይሁዶች ጋር ግንኙነቱን በማሳደግ ኃይሉን በሮም አጠበቀ ፡፡
ሄሮድስ ድርጊቱ አይሁዶችን እንዳስደሰታቸዉ ባዬ ጊዜ ጴጥሮስንም በማሰር በብዙ ጠባቂዎች ስር አስቀመጠው (ቁጥር 3-4) ፤ ይህ የጴጥሮስ ሰዎስተኛዉ እስራት ነበር (ሐዋ 4፡ 3፣ 5፡ 18) ፡፡ ሁኔታዉ ለሐዋሪያቱ በጣም ኃይለኛ ስለሆነ ሁሉም ስለ ወንጌል ለመሞት ፍቃደኞች እንደ ነበሩ ይወስናሉ/መወሰን ይጠበቅባቸዋል ፤ ጴጥሮስ እስርቤት እያለ እንዲለቀቅ ቤተ ክርስቲያን በኃይል ፀለየች (በመቀጣጠልና በእምባ) (ቁጥር 5) ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር መከራችንን ሲያይ “ እና “ ፀሎታችንን ሲሰማ “ እግዚአብሄር ሄሮድስ ምን እያደረገ እንደ ነበር በሙሉ እንደሚያዉቅ አመልክቷል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (12፡ 6-10)፡ ጠባቂዎቹ ሁል ጊዜ በጴጥሮስ ዙሪያ ነበሩ ፡፡ የጴጥሮስ መገደል ለቀጣዩ ቀን የጊዜ እቅድ የወጣለት ቢሆንም ጴጥሮስ ተኝቶ ነበር (ቁጥር 6) ፤ ጴጥሮስ በእስራቱ ሰላም አግኝቶ ነበር (ፊል 4፡ 6-7) ፡፡ ከዚያም ብርኃን ሲበራ የእግዚአብሄር መለዓክ ተገለጠ ፤ መለዓኩም እንዲነቃ የጴጥሮስን ጎን መታዉ እንዲነሳ፣ እንዲለብስና እንዲከተለዉም ነገረው ፡፡ ሰንሰለቶቹም በቀላሉ ከጴጥሮስ እጆች ላይ ወደቁ (ቁጥር 7-8) ፡፡ ቶማስ ዋትሰን “ መለዓኩ ጴጥሮስን ከእስር ቤት ሄዶ አመጣዉ ነገር ግን መለዓኩን ያመጣዉ ፀሎት እንደ ነበር “ ተናግሯል ፡፡ ጴጥሮስና መለዓኩ ከእስርቤት ወጥተዉ ሄዱ፣ ጥበቃዎቹንም በማለፍ በራሱ የተከፈተላቸዉ የብረት መዝጊያ በር አጠገብ ደረሱ ፤ መንገዱም ላይ በደረሱ ጊዜ መለዓኩ ተለየው (ቁጥር 10) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (12፡ 11-14)፡ ጴጥሮስ እግዚአብሄር በመለዓኩ አማካኝነት ከሄሮድስ እንደ ታደገው ተረዳ (ቁጥር 11) ፤ ከዚያም ጴጥሮስ ለፀሎት ከአማኞች ብዙዎች ወደ ተሰበሰቡበት ወደ ማሪያም ቤት ሄደ (ቁጥር 12) ፡፡ የፀሎት ለዉጥ ይህን ይመስላል/እንደዚህ ነው፡
- ሰዎቹ እየፀለዩ ነበር ፡፡
- በኃይል እየፀለዩ ነበር ፡፡
- ቀንና ሌሊት ምናልባትም ለአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ እየፀለዩ ነበር ፡፡
- ፀሎታቸው በተለዬ ሁኔታ በጴጥሮስ ነፃ መዉጣት ላይ ያተኮረ ነበር ፡፡
ጴጥሮስ በሩ ላይ አንኳኳ አገልጋይቱም መለሰች (ቁጥር 13) ፤ አገልጋይቱም በጴጥሮስ መገኘት በጣም ደንግጣ ስለ ነበር በሩን መክፈቷን ረሳቸው ይልቁንም ጴጥሮስ በር ላይ እንዳለ ለሌሎቹ ለመናገር ሮጠች (ቁጥር 14) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (12፡ 15-17)፡ ከሚፀሉይት አንዳንዶቹ አገልጋይቱን እብድ እንዳበደች ነገሯት ምክንያቱም ጴጥሮስ ሊሆን ስለ ማይችልና መለዓኩ ሊሆን ይችላል በማለት (ቁጥር 15) ፡፡ ማክአርቱር “ በአይሁዶች አጉል አምልኮ/ልማድ መሰረት እያንዳንዱ ሰዉ ያ ሰዉዬ ተሰርቶበት ሊሆን ይችላል ብለዉ የሚያስቡት የየራሱ ጠባቂ መለዓክ እንደ ነበረው “ ይገልፃል ፡፡ በሩን ለመክፈት በቂ እምነት አልነበራቸዉም ፡፡ ከእኛ ዉስጥ ምን ያክላችን እግዚአብሄር ፀሎታችንን ሲመልስልን እንደነግጣለን ? ( “ አምናለሁ ! አለማመኔን እርዳው “ (ማር 9፡ 24)) አሁንም ጴጥሮስ እስኪመልሱለት ድረስ በሩ ላይ ማንኳኳቱን ቀጠለ (ቁጥር 16) ፡፡ ጴጥሮስ በእስርቤት ሆኖ የነበረዉን ነገራቸው፣ የሰሙትንም ለሌሎች ሐዋሪያት ሪፖርት አድርጉላቸዉ አላቸው ከዚያም ሄደ (ቁጥር 17) ፡፡ አንዳንዶች ጴጥሮስ ከሚስቱ ጋር እንደሄደና እንደተጓዘ ያመለክታሉ/ይናገራሉ (1ቆሮ 9፡ 5) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (12፡ 18-19)፡ የጴጥሮስ መጥፋት ሲነጋ ተደረሰበት/ታወቀ (ቁጥር 18) ፡፡ ከፍለጋዉም በኋላ ሄሮድስ ጠባቂዎቹን እንዲገደሉ በመፍረድ ወደ ቂሳሪያ ሄደ (ቁጥር 19) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (12፡ 20-25)፡ ሄሮድስ በቂሳሪያ በሰሜን ባህር ዳርቻ ከነበሩት ሁለት ከተሞች ከጢሮስና ከሲዶና ጋር ተጣልቶ ነበር ፤ የጢሮስና የሲዶና መሪዎች የንጉሱ ብትወደድ/ንብረት ክፍለ እና የንጉሱ የመኝታ ክፍል ኃላፊነት ከነበረባት ባላስጦስ ጋር አንድነትን/ህብረትን አሳደጉ ፡፡ በተቀጠረም ቀን ላይ ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሕዛቦች ፊት ተናገራቸው (ቁጥር 20-21) ፡፡ ታሪክ ፀኃፊዉ ጆሴፍ የሄሮድስ ካባ ከብር የተሰራ እንደ ነበር ፅፏል ፡፡ የሚያዳምጠዉም ሕዝብ ሄሮድስ አማላክ እንጂ ሰዉ አይደለም እያሉ ጮኹ (ቁጥር 22) ፤ ለእግዚአብሄር ክብር ከመስጠት ይልቅ ለራሱ ክብር በመፈለጉ ምክንያት ሄሮድስን የእግዚአብሄር መለዓክ በመቅሰፍት መታው (ቁጥር 23) (ኢሳ 42፡ 8) ፡፡ “ የእግዚአብሄር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር “ (ቁጥር 24) (1ጴጥ 3፡ 12) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ በአገልግሎት ለመሄድና ለመቀጠል “ በእግዚአብሄር ልዓላዊ ፍቃድ በኩል “ የጴጥሮስ ህይወት ዳነች ፡፡
መደምደሚያ
ሐዋሪያት ስራ 12 መጨረሻ ላይ የሐዋሪያት ስራ ታሪክ ከሐዋሪያት ስብከትና ወንጌል ሰበካ/ስርጭት ወደ ጳዉሎስ አገልግሎት/የሰባኪነት ጉዞ ይሸጋገራል ፡፡
7.Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1391.
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary, New Testament, Vol. 1 (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989) p. 451.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson, 2005), p. 1456.
MacArthur, pp. 1456–1457.
Wiersbe, p. 452.
MacArthur, p. 1457.
MacArthur, p. 1457.
ጥያቄዎች
-
የዮሐንስ ወንድም ያዕቆብ ለመሞት የመጀመሪያዉ ሐዋሪያ ነበር ? ይሁዳን እንደ ተከዉ እንደ ማቲያስ በሌላ ተተክቶ ነበር ?
-
በሐዋ (12፡ 6) የእግዚአብሄር መለዓክ በእስርቤት ሲገለጥለት ጴጥሮስ ተኝቶ ነበር ፤ በሰላም መተኛት ለምን ችሎ እንደነበር ምን ታስባላችሁ (ዮሐ 21፡ 18, ዘዳ 31፡ 6) ? እንደምትሞቱ እያወቃችሁ በሰላም መተኛት እችላለሁ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በሐዋ (12፡ 22) ሕዝቡ ሄሮድስን አምላክ እንጂ ሰዉ አይደለም ያሉት ለምን ነበር ? ከእግዚአብሄር የተቀበለዉ ቅጣት ምን ነበር ? ለምን ?
-
በሐዋሪያት ስራ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 12:5
“So Peter was kept in prison, but prayer was being made earnestly to God for him by the church.”
ንጉሥ ሄሮድስ የቤተ ክርስትያን በሆኑት በአንዳንዶቹ ላይ እጁን አሳረፈ ፣ ያዕቆብንም ገደለው ደግሞም ጴጥሮስን እንዲሁ ያደርግበት ዘንድ አሰረው ፡፡ ጴጥሮስም በእስር ቤት ተቀምጦ ሳለ ፤ ብዙዎች ተሰብስበው እግዚአብሔር የጴጥሮስን ህይወት ያተርፍ ዘንድ አጥብቀው ይጸልዩ ነበር ፡፡ በድንገትም በአንድ ምሽት የጌታ መልአክ ለጴጥሮስ ተገልጦ “ ተነስ ! “ አለው ፤ ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ መልአኩም ከእስር ቤት እስከ ከተማው መውጫ ሸኘው ፡፡ እግዚአብሔር የሰዎቹን ጸሎት መለሰ ጴጥሮስንም በታምራት አስመለጠው ! ሰዎቹ ምንም እንኳ ጴጥሮስ እንድፈታ እግዚአብሔርን ቢለምኑም ነገር ግን ጴጥሮስ በደጅ በቆሞ ጊዜ ተገርመው ነበር ፡፡
እግዚአብሔር ጸሎታችሁን እንደሚመልስ ተናግሯል ፡፡ ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ልክ እንደጓደኛ ማውራት ማለት ነው ፡፡ እግዚአብሔርን በደንብ ስታውቁ ጸሎታችሁ ንጹህ እየሆነ ይመጣል ፡፡ ቅን ጸሎት ማለት ከልብ በሚመነጭ ስሜት ፣ ያለማወላወል ፣ በኃይልና በማስተዋል መጸለይ ማለት ነው ፡፡ ወንድማችሁ ወደ ክርስቶስ እንድመለስ እየጠበቃችሁ ነውን ? ትዳራችሁ እንድመለስ እግዚአብሔርን እየለመናችሁ ነውን ? ስለ ስራ እግዚአብሔርን እየጠየቃችሁ ነውን ? አስቡት እስኪ በቅንነት በጸሎት እግዚአብሔርን መፈለግ በእንባ እንድሁም አጥብቆ ወንድሞችን ሳይቀር ከእናንተ ጋር እንድጸልዩ በመሰብሰብ መጸለይን ፡፡ ይህንን እያደረጋችሁ ሳለ እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ሲመልስ እንዳትገረሙ ! እርሱ ይገለጣልና የእርሱም ፍቃድ ይፈጸማል ፡፡
“ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር ።”
- ሐዋርያት ሥራ 12፡5
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 34:15 — “የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና ። “
- ቆላስይስ 4:2–3 — “ ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ ፤ በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምሥጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ ፡፡ “
- ያዕቆብ 5:16 — “ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።