Acts Acts

Even to the Gentiles

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 347 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዳችን ዉስጥ እያለፈ/እየተንቀሳቀሰ ነው ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 10 መንፈስ ቅዱስ ራሱን በቆርኔሌዎስ ላይ ብቻ ሳይሆን በቆርኔሌዎስ ሙሉ ቤተሰቦች ላይ አፈሰሰ ፤ በሐዋሪያት ስራ (1-9) ወንጌል የአይሁድ ሰዎችን ብቻ ደርሶ ነበር ፡፡ በቆርኔሌዎስ ላይ የሆነዉ ቃል ሲሰራጭ ለአንዳንድ ሙግቶች መነሻ መሆን ጀመረ ፤ ሰዎችም አልወደዱትም ፡፡ በምዕራፍ 11 ዉስጥ ዋይርስቤ ለአሕዛቦች ቃለ ምልልስ የአይሁዶችን ሰዎስት ምላሾች ተመልክቷል፡

  1. አሕዛቦችን ተቀበላቸው (ቁጥር 1-18) ፡፡
  2. አሕዛቦችን አበረታቷቸው (ቁጥር 19-26) ፡፡
  3. ከአሕዛቦች ርዳታ /እገዛ ተቀበሉ (ቁጥር 27-30) ፡፡

ትምህርት

ሐዋሪያት ስራ (11፡ 1)፡ ሁሉም ይሁዳ 30 ማይል ያክል ያጠቃልላል ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን በሌሉበት አለም እንኳን ሲጓዝ ቃሉ ይሰማል ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (11፡ 2-3)፡ የተፈጠረዉ ዜና ጴጥሮስ ሊጓዝ ከሚችለዉ ይልቅ በፍጥነት ተሰራጨ ፤ በጊዜዉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፣ በቆርኔሌዎስ ቤት ተፈጥሮ የነበረዉ ቀድሞ ታዉቋል ፡፡ አንዳንዶች ጴጥሮስ ወደ አልተገረዘዉ ሰዉ ቤት በመግባቱና አብሮ በመብላቱ ጴጥሮስ አድርጎት በነበረዉ ነገር ላይ ተናደዱ ፤ አሕዛቦች በስፋት እንደ “ ዉሾች “ ይታዩ ነበር (ማቴ 15፡ 26) ፡፡ ማክአርቱር “ የአይሁድ አማኞች በእንዲህ አይነቱ የአይሁድ የቅሬታ ልፍለፋ ልምድ ላይ ተበሳጩ አለ “ ፤ የአይሁድ ልምዶት የተሰበሩ ከሆኑ ይህ ማለት ጴጥሮስ በኃይማኖታቸዉ እየቆሸሸ ነበር ማለት ነው ፡፡ ዋይርስቤ አይሁዶች ለመጀመሪያ ጊዜ አይሁዶች አሕዛቦችን ሲቀበሉ በመጀመሪያዎቹ 18 ቁጥሮች እንዳየን መፃፉን አስታዉሱ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ብዙ ተቀባይነት አልነበረም ነገር ግን በዚያ እንዴት እንዳገኘነው ማየት የሚያስደንቅ ነው ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (11፡ 4-11)፡ ጴጥሮስ ለራሱ ለአይሁድ አድማጮቹ ወደ ቆርኔሌዎስ ቤት ምን እንደ መራዉና በዚያ እንደ ነበር ደግሞ ተፈጥሮ የነበረዉን በትክክል ገለፀላቸው ፡፡ ጴጥሮስ አድርጎት ለነበረዉ ነገር ምክንያቱ እግዚአብሄር እንደ ነበር ብዙ ማስረጃዎችን ሰጠ ፤ መጀመሪያ ጴጥሮስ ራዕዩን ከእግዚአብሄር ጋር አገናኘው (ቁጥር 5-11) ፤ ጴጥሮስ ራዕዩን ለእርሱ እንደ እግዚአብሄር ምስክርነት ማስረጃ እንደ ገና ተናገረ ፡፡ ይህን በማድረግ እግዚአብሄር ጴጥሮስ ባደረገዉ ክብርን ተቀበለ ፡፡ ጴጥሮስ ተቃዋሚዎቹ/ባላንጣዎቹ እንደገለፁት ራዕዩን ለመቀበል ተመሳሳይ ግትርነት እንደገለፀ አገናኘው ፤ በፍፁም ንፁህ ያልሆነ ነገር እንዳልበላና እንዳልነካ በመግለፅ ፤ ነገር ግን ሀሳቡን ለማጠንከር እግዚአብሄር ራዕዩን ሰወስት በተለያዩ ጊዜ ላከለት ፤ ከዚያም በኋላ ጴጥሮስ ከእንቅልፉ ሲነቃ እርሱን ወደ ቆርኔሌዎስ ለመዉሰድ ሰዎስት ሰዎች እርሱን እየጠበቁት ነበር ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (11፡ 12-15)፡ ጴጥሮስ የቆርኔሌዎስ ቤተሰብ ለምን እንዳገለገለ ለመግለፅ ያገናኘበት ሁለተኛዉ ማስረጃ የመንፈስን ምስክረነት እንደ ገና መግለፅ ነበር (ቁጥር 12-15) ፡፡ በመንፈስ ፈጣን ምላሽ ላይ ጴጥሮስ ስድስቱን ሰዎች እርሱን ለማዳን በመላክ ያዛቸው ፤ የቆርኔሌዎስን ቤት ለማግኘት በአንድ ላይ 30 ማይል ያክል ተጓዙ ፡፡ ጴጥሮስ ደርሶ በቆርኔሌዎስ ቤተሰቦች ወንጌልን ማካፈል ሲጀምር ጴጥሮስ በበዓለ ኃምሳ ቀን ላይ የአይሁድ አማኞች ቡድን ላይ እንደ ነበረዉ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱም ላይ እንደሚመጣ በግልፅ መሰከረ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (11፡ 16-18)፡ ጴጥሮስ የቆርኔሌዎስን ቤት ለምን እንዳገለገለ ለመግለፅ ያገናኘበት ሰዎስተኛው ማስረጃዉ የጴጥሮስ ቃል ነበር (ቁጥር 16) ፤ ጴጥሮስ ተከታዮቹ “ በመንፈስ ቅዱስ እንደሚጠመቁ “ (ቁጥር 16) የሚለዉን የኢየሱስን ትምህርት አስታወሰ ፡፡ “ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ “ የሚለዉ ሀረግ በአዲስ ኪዳን በስድስት ሌሎች ጊዜ ይገኛል፡

“ ዮሐንስ በዉሃ አጥምቆ ነበርና እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስትጠመቃላችሁ “ (ሐዋ 1፡ 5) ፤ አይሁዶች ኢየሱስ ይህን ቃል ከተናገረበት “ ብዙ ቀን “ ሳይቆይ በበዓለ ኃምሳ ቀን በመንፈስ ቅዱስ ተጠመቁ ፡፡

“ እኔስ ለንስሐ በዉኃ አጠምቃችኋለሁ ፤ ጫማዉን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣዉ ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል ፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትምያጠምቃችኋል “ (ማቴ 3፡ 11) ፤ እዚህ ላይ በመንፈስ መጠቀም ከእሳት ከመጠመቅ ጋር የተገናኘ ነበር ፤ ይህ በብዛት በአንደበት ከመናገር ጋር ሲገናኝ በስፋት ለጌታ በማገልገል በመንፈሳዊ ስጦታዎቻችሁ ለመሄድ እንድትዘጋጁ ዋጋ ቢስ የሆነዉን ህይወታችን ለማቃጠል በመምጣት የእግዚአብሄር መገኘትን ያመለክታል ፡፡

“ እኔ በዉኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር “ (ማር 1፡ 8) ፡፡

“ ዮሐንስም መልሶ እኔስ በዉኃ አጠምቃችኋለሁ ፤ ነገር ግን የጫማዉን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል ፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል “ (ሉቃ 3፡ 16) ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ እሱ ከደረገዉ የሚበልጥ ነገር ያደርጋል አለ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቲያኖች እርሱ ካደረገዉ ይበልጥ ያደርጋሉ አለ ምክንያቱም በኑሮአችን ላይ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄር እሳት ስለሚያስቀምጥ ፡፡

“ እኔም አላዉቅም ነበር ዳሩ ግን በዉኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየዉ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነዉ አለኝ “ (ዮሐ 1፡ 33) ፡፡

“ አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና ፡፡ ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናልና “ (1ቆሮ 12፡ 13) ፤ ይህ ጥቅስ በኃይል ከሐዋሪያት ስራ 11 ይተሳሰራል ፡፡ ሁሉም አማኞች ከየትም እንምጣ ወደ አንድ አካል በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀናል ፡፡

የጴጥሮስን ጠቅላላ ታሪክ በመስማት ለአሕዛቦች ዘላለማዊ ህይወት በመስጠቱ የአይሁድ አማኞች እግዚአብሄርን አመሰገኑ ፡፡ ማክአርቱር ይህ “ በአይሁድ ታሪክ አንዱ የሚያስደንቅ ቅበላ/አዎንታ “ እንደ ነበር ፅፏል ፤ አይሁዶች መሲሁ ለአሕዛቦችም እንደ ነበር አስተዋሉ ፤ ይህ ነገር ተተንብዮ ነበር (ኢሳ 41፡ 1, 6፣ 49፡ 6) ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (11፡ 19-26)፡ የአይሁድ አማኞች የአሕዛብ አማኞችን ከመቀበል ወደ ማበረታታት ሄዱ/ተጓዙ ፡፡ ከእስጢፋኖስ መሰዋት/መገደል በኋላ መጀመሪያ ተበትነዉ የነበሩት የአይሁድ አማኞች ወንጌል ከአይሁዶች ጋር ብቻ ተጋሩ ፤ አሁን ግን ከቆጵሮስና የቀሬና የሆኑ ሁለት ስማቸዉ ባልተጠቀሰ ሰዎች በኩል በአንፆኪያ ወደ አሕዛብ ማህበረሰብ ዉስጥ ወንጌል ተሰበከ ፡፡ ይህን ሲሰሙ የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ነገሮቹን እንዲያረጋግጥ በርናባስን ላኩት ፤ ሲመጣም “ የእግዚአብሄርን ፀጋ አየ “ (ቁጥር 23) ፡፡ አሁን ጳዉሎስ ብለን የምናዉቀዉን ሳዖልን ከጠርሴስ ለመፈለግ በርናባስ ሄደ፣ ሁለቱም በማበረታታት ለሚመጣዉ አንድ አመት በአንፆኪያ አዲስ ቤተ ክርስቲያን አስተማሩ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (11፡ 27-30)፡ አሕዛብን ከተቀበሉና ካበረታቱ በኋላ አይሁዶች ከአሕዛቦች አርዳታን ለመቀበል ተንቀሳቀሱ/ሄዱ ፡፡ ከአንፆኪያ አንድ አጋቦስ የሚባል ነቢይ በግዛቱ/በዓለም ሁሉ ርሃብ እንደሚሆ ተነበዬ ፡፡ በአንፆኪያ ደቀ መዛሙርቱ በኢየሩሳሌም ያሉትን አማኞች ለመርዳት በሽማግሌዎቻቸዉ የሚልኩትን ሰበሰቡ ፤ ይህ የእግዚአብሄር ጥብቅ ንቅናቄ ማስረጃ ነው ፤ ከቆጵሮስና ከቀሬና የሆኑት ስም የሌላቸዉ ሁለቱ ሰዎች ይህ ጠቅላላ ንቅናቄ ጀምረዉታል (ሮሜ 15፡ 25-27) ፡፡

መደምደሚያ

ሐዋሪያት ስራ 11 በደንብ በጳዉሎስ በሮሜ 15 በሚገባ ተጠቅልሏል፡ “ አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ ፡፡ መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ቅዱሳን መካከል ያሉትን ድሆች ይረዱ ዘንድ ወደዋልና ፡፡ ወደዋልና የእነርሱም ባለዕዳዎች ናቸው ፤ አሕዛብ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ተካፋዮች ከሆኑ በስጋዊ ነገር ደግሞ ያገለግሉዓቸው ዘንድ ይገባቸዋል “ (ቁጥር 25-27) ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 11 በመንፈሳዊ ቅርሳቸዉ ምክንያት አሕዛቦች ለአይሁዶች ባለዳዎች እንደሆኑ ተረዱ ፤ እኛም የአይሁዶችን ቁሳዉ ፍላጎቶች ላለመከልከል በተመሳሳይ እምነት ስር ነን ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary, New Testament, Vol. 1 (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989) pp. 447–450.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson, 2005), p. 1456.

  3. Wiersbe, p. 448.

  4. Wiersbe, p. 448.

  5. Wiersbe, p. 448.

  6. MacArthur, p. 1456

ጥያቄዎች

  1. በይሁዳ የነበሩት ሐዋሪያት አሕዛቦች የእግዚአብሄርን ቃል እንደ ተቀበሉ በሰሙ ጊዜ ምን ተፈጠረ ? እግዚአብሄርን እንዲያመሰግኑ ምን አሳመናቸው ? (ሮሜ 10፡ 12-13, 15፡ 9-12, 16)
  2. በመሰደድ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ላይ ምን ተፈጠረ ? ካለ ምን አይነት ስደት የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ ደረሰባት ? ስደቱ ሰዎችን ወደ ጌታ ያመጣል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  3. በዚህ ምዕራፍ በርናባስ እንዴት ነበር የተገለፀው ? በተመሳሳይ መንገድ ሊገለፅ የቻለ የምታዉቁት ሌላ ሰዉ አለ ? ማነው ? ለምን ?
  4. በአንጾኪያ ይኖር በነበረዉ በኒቆላዎስ ፋንታ በርናባስ በጠርሴስ የነበረዉን ጳዉሎስን ለመርዳት ለምን ተዘረዘረ (ሐዋ 6፡ 5) ? ጳዉሎስ እንዲያደርገዉ እግዚአብሄር ጠርቶት የነበረዉን በርናባስ ተረድቶታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ሐዋ 9፡ 15, 22፡ 21, 26፡ 17)
  5. ለመጀመሪያ ጊዜ “ ክርስቲያን “ የሚለዉ ቃል ጥቅም ላይ የዋለዉ የት ላይ ነበር ? ሲጀምር ይህ ክብር የሚነካ ወይም የሚያቃቂል ስም ማለት ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? በአዲስ ኪዳን ዉስጥ “ ክርስቲያን “ የሚለዉ ቃል ሌላ የት ላይ ጥቅም ላይ ዉሏል ? (ሐዋ 26፡ 28, 1ጴጥ 4፡ 16)
  6. በሐዋሪያት ስራ 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 11:17–18

“‘Therefore, if God gave them the same gift that He also gave us when we believed on the Lord Jesus Christ, how could I possibly hinder God?’ When they heard this they became silent. Then they glorified God, saying, ‘So God has granted repentance resulting in life even to the Gentiles.’”

ቆርነሌዎስና ቤተሰቡ የወንጌልን መልዕክት ከተቀበሉ በኋላ ጴጥሮስ የእነዚህን አህዛብ ወደ ጌታ መምጣት ለሐዋርያትና በይሁዳ ላሉ ወንድሞች ማስረዳት ነበረበት ፡፡ ከጌታ ስላየው ራዕይ እንድሁም የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ምስክር አንደሆነ መሰከረላቸው ፡፡ ጴጥሮስ ለማመን ከባድ እንደሆነ ተረድቶ የአይሁድ ጓደኞቹን እንድህ ብሎ ጠየቃቸው “ እግዚአብሔርን መከልከል እንዴት ይቻለናል ? “ የጴጥሮስንም ማብራርያ ከሰሙ በኋላ ዝም አሉ ፡፡ እናም ከዚያ ለአህዛብ እንኳ የዘላለምን ህይወት ስለ ሰጠ እግዚአብሔርን አመሰገኑ ፡፡ ለመጀመርያ ጊዜም ወንጌል አይሁድ ባልሆኑ ህዝቦች ዘንድ ደረሰ እግዚአብሔርም ስለዚህ ተመሰገነ ፡፡

እግዚአብሔር በማይታመን መንገድ ማለት ልታምነው በማትችለው መንገድ እንደሰራ ሰምተህ ታውቃለህ ? ለእግዚአብሔር ሁሉም ይቻላል ! የወንጌል መልዕክት ለሁሉም ነው በዚህ አለም ለሚኖር ሁሉ ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ህዝቦችን ወደ ስሙና ወደ ፍቅሩ ለማምጣት የማይቻሉትን ፡- ህልሞች እና ራዕዮች ፤ ምልክትንና ድንቆችን ይጠቀማል ፡፡ ምናልባትም አንተ ይህን ታምን ይሆናል ይህንንም በራስህ ህይወት ትፈልግ ይሆናል ! ሌሎች ላይ አትፍረድ ፣ በአለማመንም አትኑር ፣ እግዚአብሔርንም አትከልክል ፡፡ ወንጌል ፣ የእግዚአብሔር ኃይል እና የእርሱ ስልጣን ለሁሉም ናቸው ፤ ተስፋን ለተራቡና ለተጠሙ ሁሉ ፡፡ ምናልባት አንተ ይህን ታላቅ እውነት ከሚያምንና ከሚያራምድ ትውልድ አካል ትሆናለህ ፡፡

“እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ ? ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ ። “

  • ሐዋርያት ሥራ 11፡17-18

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 19:26 — “ ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፦ ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው ። “

ሉቃስ 18:16 — “ ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠርቶ፦ ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው አትከልክሉአቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና ። “

ያዕቆብ 5:9 — “ ወንድሞች ሆይ፥ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ፤ እነሆ፥ ፈራጅ በደጅ ፊት ቆሞአል ። “