ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ አንድ ቃላችን ስልጣን ነው ፡፡ በመፅኀፉ ሁሉም ነገር ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካል፣ ሐዋሪያቱና መንፈስ ቅዱስ እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣን እንደሚሰሩ ያመለክታል ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 9 የሳዖልን መቀየር ይመዘግባል በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ የምዕራፉ ዋና ነገር ሁሉም አይሁዶች እንዲቀየሩ ነበር ፤ ነገር ግን በሐዋሪያት ስራ 10 ወንጌሉ ወደ አህዛብ ተወሰደ ፤ ወንጌል ወደ አሕዛብ ሲሄድ በአይሁድ አማኞች ለፍጭት ምክንያት ሆኑ - አሕዛቦች ነገሮችን በተለየ መልኩ ያደርጋሉ የተለዩም ነገሮች ይበላሉ፣ ከአይሁድ አማኞች የተለዩ ነበሩ ፤ ይሁን እንጂ የእግዚአብሄርን እንቅስቃሴ ማየት ስትፈልጉ ነገሮች በተለየ መልክ ማድረግ አለባችሁ ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ በህይወት ዘመናችን ብሄራዊ የእግዚአብሄርን ንቅናቄ አላየንም ፡፡ ምናልባት ፀሎታችን ነገሮችን እንዴት በተለየ መልኩ ማድረግ እንዳለብን እግዚአብሄርን መጠየቅ ነው ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (10፡ 1-8)፡ የሮማዉያን መቶ አለቃ በመሆን የሚያገለግል ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ አሕዛብ ነበር ፤ ቆርኔሌዎስ የተሰጠና እግዚአብሄርን የሚፈራ ነበር - ለሙሉ ቤተሰቦቹ እንደሚያደርገው ፡፡ ለአይሁዶች ምፅዋቶችን ያደርግ እና ወደ እግዚአብሄር ይፀልይ ነበር (ቁጥር 1-2) ፤ ቆርኔሌዎስ ስድስት መቶ የጦር ጓድ ኃላፊነት ከነበረባቸዉ ስልሳ አለቆች ዉስጥ አንዱ ነበር ፡፡ አንድ የወታደሮች ክፍለ ጦር ከአስር የጦር ጓዶች ወይም ከስድስት ሺህ ሰዎች የተሰራ ነበር ፡፡ ቂሳርያ ቆይቶ በሐዋሪያት ስራ ታሪክ በጣም አስፈላጊ ከምትሆነዉ ከኢዮጴ በሰሜን በኩል 30 ማይል ያክል እና ከኢየሩሳሌም ሰሜን ምዕራብ 60 ማይል ርቀት ላይ የምትገኝ ስፍራ ነበረች ፡፡ ማክአርቱር “ እግዚአብሄርን የሚፈሩ “ የሚለዉ ቃል “ አይሁዶች በእግዚአብሄር አምላክ በስግደት/በአምልኮ ሞገስ ጣዖቶቻቸዉን ትተዉ የነበሩትን አሕዛቦች ለመግለፅ አይሁዶች ይጠቀሙበት ነበር ፤ እንዲህ አይነት ሰዉ የብሉይ ኪዳንን ስርዓት ሲከተል በመገረዝ በኩል ብቻ/ስላልተገረዘ ለአይሁዳዊነት ሙሉ አዲስ አባል እንደማይሆን “ ይገልፃል ፡፡ እነዚህ እግዚአብሄርን የሚፈሩ ተመሳሳይ እግዚአብሄርን አመለኩ አይሁዶች የሚያደርጉትንም ተመሳሳይ ሕጎችን ፈፀሙ/አደረጉ ነገር ግን ሙሉ አዲስ አባል ከመሆን ሳይሆኑ እግዚአብሄርን የሚፈሩ ሆነዉ ተቀመጡ ምክንያቱም ተገርዘዉ ወይም ተጠምቀዉ ስላልነበር ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 8, 9 እና 10 በክርስቶስ እዉነትን ለማግኘት በመጡት ታሪክ ላይ ይቀጥላል - ኢትዮጲያዊዉ ጃንደረባ፣ አሳዳጁ ሳዖል እና እግዚአብሄርን የሚፈራዉ ቆርኔሌዎስ ፡፡ ለእያንዳንዳቸው እግዚአብሄር ስለ እዉነቱ እየፈለጉ ከነበሩት ጋር እንዲጓዙ አንዳንዶችን ላከላቸው ፡፡ ለመሄድ እምቢ በማለት ይልቁንም እግዚአብሄር ለእነርሱ ለእያንዳንዳቸው የላካቸዉን ቢሳደቡ ኖሮ ምን ይሆናል/ይፈጠራል ? በሚያናድድ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ብዙ ጊዜ ይህ ሁኔታ ነው - ወደ እኛ እንዲመጡ እየጠበቅን ነው ፡፡
ከቀኑም ዘጠኝ ስዓት ቆርኔሌዎስ በመጥራት ፀሎቱና የምፅዋት ተግባሩ በእግዚአብሄር ፊት እንደ መታሰቢያ መስዋዕት ተቀባይነት እንዳገኘ የነገረዉን መለዓክት በራዕይ አየ (ቁጥር 3-4) ፡፡ የእዉነተኛ ፈላጊዎች ሁሉም ፀሎቶች ዉጤታማ ናቸው ፡፡ መለዓኩም ቆርኔሌዎስን ወደ እርሱ እንዲመጣ ወደ ኢዮጴ በባህር አጠገብ በስምዖን ቤት ተቀምጦ እነበረዉ ጴጥሮስ ጋር እንዲልክበት ነገረው (ቁጥር 5-6) ፡፡ በሐዋሪያት ስራ መፅኀፍ ራዕይ ጠቃሚ ሚና ተጫዉቷል ፤ ማክአርቱር በሐዋሪያት ስራ እግዚአብሄር በራዕይ በኩል የተናገራቸዉን ይለያል፡ ጳዉሎስ በሚያሳዉር ብርሃን ራዕይ በኩል ወደ ክርስትና ተቀየረ (ሐዋ 9፡ 3-9)፣ ሐናንያ ሳዖልን(በኃላ ጳዉሎስ የተባለዉን) እንዲያገለግል ተላከ (ሐዋ 9፡ 10-16)፣ ቆርኔሌዎስ ወደ እርሱ እንዲመጣ ወደ ጴጥሮስ እንዲልክ ተነገረው (ሐዋ 10፡ 3-6)፣ ጴጥሮስ ንፁህ ያልሆኑትን እንስሳቶች እንዲበላ ተነገረው (ሐዋ 10፡ 9-18)፣ ጳዉሎስ በመቄዶንያ ለአገልግሎት ስራ ተጠራ (ሐዋ 16፡ 9)፣ ጶዉሎስ የእግዚአብሄር መገኘት ተረጋገጠለት (ሐዋ 18፡ 9-10) እና ጳዉሎስ ወደ ሮም ሲጓዝ የእግዚአብሄር መገኘት ቃል ተገባለት/ተስፋ ተሰጠው (ሐዋ 23፡ 11) ፡፡ ቆርኔሌዎስ ለራዕዩ ከቤቱ አገልጋዮች ዉስጥ ሁለቱን እና አንድ የሚተጋዉን ወታደር ለጴጥሮስ ከትዕዛዞቹ ጋር ወደ ኢዮጴ በመላክ ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 7-8) ፡፡ ጴጥሮስ ከአንድ ቆዳ ፋቂ ጋር በመቀመጥ በኢዮጴ መሰናክሎችን መሰባበር ጀምሮ ነበር፣ “ ስፍራዉ በአይሁድ ማህበረሰብ ተናቀ ምክንያቱም ቆዳ ፋቂዉ በሞቱ እንስሳቶች ቆዳ ስለሚሰራ ፤ ምናልባትም የአካባቢዉ ምኩራብ ስምዖንን ትቶታል “ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (10፡ 9-19)፡ ሰዎቹ ወደ ኢዮጴ በተጓዙ ጊዜ ጴጥሮስ ለመፀለይ በቤቱ ጣሪያ ላይ ወጣ (ቁጥር 9) ፡፡ በጣም ተራበ ለመብላትም ፈለገ ነገር ግን ምግቡ እንደ ተዘጋጀለት ጴጥሮስ “ወደ ራዕይ ሁኔታ ዉስጥ ገባ “ (ቁጥር 10) ፤ ጴጥሮስ ሰማይ ተከፍቶ አንድ ትልቅ ሸማ በአራቱም መዓዘኑ ተይዞ ሲወርድ አየ ፡፡ በሸማዉ ላይ ሁሉም አራት እግር እንስሳቶች፣ ሁሉም ተሳቢዎች እና ሁሉም የምድርና የሰማይ አዕዋፍት ነበሩ ፤ አንድ ድምፅም ጴጥሮስን ከእነዚህ እንስሳቶች በመግደል እንዲበላ ነገረው (ቁጥር 11-13) ፡፡ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ጴጥሮስ ያስበዉና ይከተለዉ ከነበረዉ የምግብ መመሪያ በተቃራኒ ስለ ሄደ/ስለሚቃረን (ዘሌ 11፡ 25-26) ጴጥሮስ ጮኾ “ ጌታሆይ አይሆንም ! “ አለ (ቁጥር 14) ፡፡ ድምፁም ጴጥሮስን እግዚአብሄር ንፁህ አድርጎ የፈጠረዉን አታርክሰዉ በማለት ነገረው (ቁጥር 15) ፡፡ ይህ ልዉዉጥ ሰዎስት ጊዜ ተከሰተ ከዚያም ሸማ ወደ ሰማይ ተመልሶ ተወሰደ (ቁጥር 16) ፤ በቆርኔሌዎስ የተላኩት ሰዎች ጴጥሮስን በመፈለግ በስምዖን ቤት ቆመዉ ሳለ ጴጥሮስ ስለ ራዕዩ ግራ ተጋባ (ቁጥር 17-18) ፡፡ ስለ ራዕዩም እያሰበ መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስን እርሱን ለማየት በዚያ ከነበሩት ሰዎች ጋር እንዲሄድ ነገረዉ ምክንያቱም መንፈስ ወደ ጴጥሮስ ሰዎቹን ልኳቸዉ ስለ ነበር (ቁጥር 19-20) ፡፡
ጴጥሮስ ሰዎቹ በዚያ ለምን እንደ ነበሩ ጠየቃቸው መለዓኩ በመለኮት ቆርኔሌዎስን ወደ ቤቱ እንድትመጣ ጴጥሮስን እንድንጠራዉ አዘዘን በማለት ገለፁለት (ወደ አሕዛብ ቤት መግባት አይቻልም የሚለዉን የአይሁድ ባህል መሰናክል በመስበር) (ቁጥር 21-22) ፡፡ ጴጥሮስ ሰዎቹን ወደ ቤት በመግባት ምሹቱን እንዲያሳልፉ ጋበዛቸው (ሌላ የባህል መሰናክል የሆነዉን የሰባበረውን ) ከዚያም ሰዎቹ በማግስቱ/በቀጣዩ ቀን ከጴጥሮስና በኢዮጴ ከነበሩት ወንድሞቹ ጋር ከኢዮጴ ሄዱ (ቁጥር 23) ፡፡ ቆይተን እንደምናየው እነዚህ ወንድሞች ከኢዮጴ ጴጥሮስን ያጀቡ ስድስት አማኞች ነበሩ ፡፡
ከቀኑም በኋላ ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስ ከቤተሰቡና ከጓደኞቹ ጋር በሚጠብቅበት ስፍራ ደረሰ (ቁጥር 24) ፡፡ ቆርኔሌዎስ ምን አይነት ታላቅ እምነት ነበር የነበረዉ፣ የጴጥሮስን መልዕክት ለመስማት በጓጉ ሰዎች በሞላ ክላስ የሚጠብቁት ፤ ጴጥሮስ ክፍሉ ዉስጥ ገባ ቆርኔሌዎስም በመስገድ በእግሩ ስር ወደቀ (ቁጥር 25) ፤ ጴጥሮስም ቆርኔሌዎስን እንዲነሳ በመርዳት እሱ (ጴጥሮስ) ሰዉ እንደ ነበር ቆርኔሌዎስን ነገረው ( ቁጥር 26) ፡፡ ጴጥሮስ ብዙዎች ሊያገኙት እንደመጡ አገኛቸው (ቁጥር 27) ፤ ጴጥሮስ የአይሁድ ህግ ወይም ወደ ቆርኔሌዎስ ቤት እንዳይመጣ ለእርሱ ተገቢ ያልሆነ እንዳደረገው ነገር ግን እግዚአብሄር ማንንም ንፁህ ያልሆነ አድርጎ መጥራት እንዳይችል እንዳሳየዉ /እንደገለጠለት ገለፀ (ቁጥር 27) ፡፡ ማክአርቱር እንደ “ታላቅ እርም “ “ ህገወጥ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ ጴጥሮስም በዚያ ለምን እንደፈለጉት ጠየቀ (ቁጥር 29) ፤ በቁጥር (30-33) ቆርኔሌዎስ ታሪኩን ለጴጥሮስ ነገረው ፤ “ እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሄር ዘንድ የታዘዝኸዉን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሄር ፊት በዚህ አለን “ በማለት አጠናቀቀ (ቁጥር 33) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (10፡ 34-48)፡ ጴጥሮስ መልካሙን ዜና ከአሕዛብ ጋር በመጋራት እግዚአብሄር በማንኛዉም ሕዝብ/ብሄር መሰረት አድሎ እንዳላሳዬ ማመልከት ጀመረ ፤ የእግዚአብሄር መልዕክት ለአይሁዶች ብቻ አልነበረም (ቁጥር 34-35) ፡፡ ጴጥሮስም የሁሉ ጌታ በሆነው በክርስቶስ በኩል ለእስራኤል ሰላም እንዲያመጣ ስለተሰጠው መልዕክት ነገራቸው (ቁጥር 36) ፤ መጥምቁ ዮሐንስ ሲሰብክ፣ እግዚአብሄር በመንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ሲያጠምቀዉ እና ኢየሱስ ሲያስተምርና በሰይጣን ቁጥጥር ስር ያሉትን ሲፈዉስ በይሁዳ የሆኑትን ክስተቶች ነገራቸው (ቁጥር 37-38) ፡፡ ጴጥሮስ በሐዋሪያት ስራ (1፡ 8) እንደ ምስክር ተጠርቶ እንደ ነበር እየመሰከረ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስ በእንጨት ተሰቅሎ እንደ ነበር ነገር ግን በሰወስተኛዉ ቀን ወደ ህይወት በመነሳት በብዙ ምስክሮች እንደ ታዬ ነገራቸው (ቁጥር 39-41) ፡፡ ጴጥሮስ ሐዋሪያቱ እንዲሰብኩና ኢየሱስ በሕያዋንና በሙታን ላይ ብቻዉን የሚፈርድ እንደ ነበር እንዲመሰክሩ ታዝዘዉ እንደ ነበርና ሁሉም ነቢያት ስለ እርሱ እንደመሰከሩ አብራራላቸዉ (ቁጥር 42-43)፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደ መሲህና እንደ ሁሉም ጌታ የሚያመለክቱትን የብሉይ ኪዳንን መልዕክቶች ሰበከ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (10፡ 44-48)፡ ጴጥሮስ ሲናገር መንፈስ ቅዱስ የጴጥሮስን መልዕክት በሚሰሙት ላይ ወረደባቸው (ቁጥር 44) ፤ ይህ የአሕዛብ በዓለ ኃምሳ ቀን ነው ፡፡ ዋይርስቤ ይህን እንደ “ ነፃ መዉጣት “ ጊዜና በአሕዛብ ማህበረስ ዉስጥ ወደ ማረጋገጫነት ያመለክታል ምክንያቱም ወንጌልን ስለያዙ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ ከጴጥሮስ ጋር የመጡት አማኞች አሕዛቦች በሌላ ቋንቋ ሲናገሩና እግዚአብሄርን ሲያመሰግኑ በመስማት የመንፈስ ቅዱስ በአሕዛቦች ላይ ስለ መፍሰሶ መሰከሩ (ቁጥር 45-46) ፡፡ ጴጥሮስም ቀድመዉ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስለተቀበሉ “ እነዚህን የተጠመቁ እንዳይሆኑ ማንም ዉሃ ሊከለክላቸዉ አይችል “ አመለከተ (ቁጥር 47) ፡፡ አሕዛቦቹም በዚያዉ ቀን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፣ ለጥቂት ጊዜም ከእነርሱ ጋር እንዲቆይ ጴጥሮስን ጋበዙት (ቁጥር 48) ፡፡
መደምደሚያ
ሕዝቡ ልምድን በመስበር ስለ ተሳተፈ ይህ ሁሉ ሆነ ፤ እንደ ልምድ ያዩት የነበረዉን በኃይማኖት፣ በባህል እና በማህበራዊ መሰናክል በእነርሱ መካከል የነበረዉን በመግፋት ሰበሩት ፡፡ ቆርኔሌዎስ እግዚአብሄርን በመፈለግ ቤተሰቡ እግዚአብሄርን እንዲያዉቅ በመፈለጉ ይህ ሁሉ ሆነ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Acts (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1387.
Nelson’s Commentary, p. 1387.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: TN: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1455.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Acts (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 445.
MacArthur, p. 1453.
MacArthur, p. 1455.
MacArthur, p. 1455.
Wiersbe, p. 447.
ጥያቄዎች
-
ዘጠኝ ሰዓት ላይ በቆርኔሌዎስ ላይ ምን ተፈጠረ ? ያየዉ ምን ነበር ? የቆርኔሌዉስ ምላሽ ምን ነበር ?
-
ቆርኔሌዎስ ራዕይ ካየ ከምን ያክል ጊዜ በኋላ ጴጥሮስ የእሱን ራዕይ አየ ? በዚህ ራዕይ እግዚአብሄር ጴጥሮስን ምን አሳየው ? በጴጥሮስ ልብ ላይ እግዚአብሄር ምን እየሰራ እንደ ነበር ታስባላችሁ ?
-
ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስን እንዴት ተመለከተዉ/አየው (ሐዋ 10፡ 1, 11-16, 28) ? ለአሕዛቦች የእግዚአብሄር አሳም ምን ነበር ? (ዘዳ 10፡ 19, ሮሜ 1፡ 16)
-
ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስን ባየበትና እግዚአብሄር ቆርኔሌዎስን ባየበት መካከል የነበረዉ ልዩነት ምን ነበር ? (ሐዋ 10፡ 2, 4, 15, 19-20)
-
በቁጥር (34-43) ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ያስተማራቸዉ/የሰበካቸው ጥቂት ነገሮች ምን ነበሩ ? ጴጥሮስ የሰበከዉ እዉነት ዉጤት ምን ነበር ? እየተናገረ በነበረበት ጊዜ እንኳን ምን ተፈጠረ ?
-
በሐዋሪያት ስራ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 10:33
“Therefore, I immediately sent for you, and you did the right thing in coming. So we are all present before God, to hear everything you have been commanded by the Lord.”
ከቂሳርያ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ አህዛብ የእግዚአብሔር መልአክ በራዕይ ሰዎችን ወደ ኢዮጴ እንድልክና ስምዖን የተባለውን ጴጥሮስን እንድያስጠራ ሲያዘው አየ ፡፡ በኢዮጴም ከጌታ ደቀ መዛሙርት አንዱ የሆነው ስምዖን ጴጥሮስም ከጌታ ራዕይን አይቶ ነበር ፤ ነገር ግን አልተረዳውም ነበር ፡፡ በቆርኔሌዎስም ሰዎች በተጠራ ጊዜ ጴጥሮስ ወደ ቆርኔሌዎስ ቤት ሄደ ፡፡ ከጌታ የሰማውን ነገር በማመን ቆርኔሌዎስ ጴጥሮስ እንደሚመጣና መልዕክቱን እንደሚነግረው ጠበቀ ፡፡ ዘመዶቹንና የቅርብ ጓደኞቹን ሳይቀር ጴጥሮስን እንድሰሙ ሰብስቦ ነበር ፡፡ እግዚአብሔርም ከዚያ በጴጥሮስ ልብ ውስጥ ገለጠ አይሁድ የሆነውም እርሱ ለዚህ አህዛብ ለሆነ ሰውና ለቤተሰቡ ወንጌልን እንደሚሰብክ አረጋገጠ ፡፡ ሁሉም ወንጌልን ተቀበሉ ፤ መንፈስ ቅዱስም ወረደባቸው ተጠመቁም ፡፡
ለአንተ ትርጉም ስላልሰጠህ የተውከው ህልም ወይም ራዕይ አይተህ ታውቃለህ ? አስታውስ እግዚአብሔር ክብሩን ይገልጥና ሌሎችን ወደ ወንጌል ይመራ ዘንድ ለህዝቡ በህልምና በራዕይ እንደሚናገር ፡፡ በሌላ ጊዜ ህልምና ራዕይ ስታይ እንድያስረዳህና ጥበብን እንድሰጥህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ ፡፡ እግዚአብሔርም ከገለጠልህ ፣ ኃይሉ እንደሚገለጥ በመጠበቅ ወድያውኑ ምላሽ ስጥ ፡፡ የህልሙ ወይም የራዕዩ ትርጉም ከሌለህ ፣ ታማኝ ጓደኛ ጠይቅ ፤ በዚህም ቀጥልበት ፤ ጸልይበትም ፡፡ እግዚአብሔርም ትርጉሙን ሲገልጥልህ የለምንም ቅድመ ሁኔታ አድርገው ! ጴጥሮስና ቆርነሌዎስ በራዕያቸው እግዚአብሔርን አመኑ ወንጌልም ኃይል በተሞላበት አዲስ መንገድ ለአህዛብ ደረሰ ! እርሱ እንደሚገለጥ በማመን የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያራምድ አይነት ሰው ሁን !
“እንግዲህ ወደ ኢዮጴ ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስጠራ፤ እርሱ በቍርበት ፋቂው በስምዖን ቤት በባሕር አጠገብ እንግድነት ተቀምጦአል አለኝ ። “
- ሐዋርያት ሥራ 10፡33
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኤርምያስ 33:3 — “ ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ ። “
- ኢዮኤል 2:28 — “ ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ ፡፡ “
- ሐዋርያት ሥራ 10:34–35 — “ ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።