ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሐዋ (8፡ 1-3) ሳዖል የቤተ ክርስቲያንን አደገኛ ድብደባ፣ ቤቶችን በመስበርና አማኞችን ወደ እስር ቤት የማስገባትን ሂደት እየመራ የነበረ ክፉ/እብድ አይሁዳዊ ነበር ፡፡ ሳዖል ስለ ኢየሱስ ሁሉም ነገር በጣም ከለመደዉ የህይወት ኃይማኖት በተቃሪኒ የሚሄድ እንደ ሆነ አመነ ፤ ነገር ግን በሐዋሪያት ስራ 9 መጨረሻ ላይ ሳዖል ኢየሱስን አገኘዉ ሕይወቱም በፍፁም ተመሳሳይ አልነበረም ፡፡ ዋይርስቤ “ ልክ እንደ አገሩ ብዙ ሰዎች በመስቀሉ ተሰናከለ ምክንያቱም በእግዚአብሄር ፅድቅ ሳይሆን በራሱ ፅድቅ ተደግፎ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 10 ከሳዖል ቃለ ምልልስ በኋላ የአሕዛብ ሰዎች ቃለ ምልልስ ነው ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (9፡ 1-9)፡ በሐዋሪያት ስራ 8 ፊልጶስ በጥሪዉ እየተጓዘ ሳዖል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እያሳደደ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ “ ደቀ መዝሙር “ የሚለዉ ቃል ጌታ/አገልጋይ ከነበረዉ ወደ ቀዱት ክርስቲያን ተከታዮች ያመለክታል ፡፡ ሳውልም ከደማስቆ ሙክራቦች ማምጣት እንዲችል ደብዳቤዎችን ለማምጣት ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ በዚህም በዚያ ያሉትን ክርስቲያኖችን መፈለጉን ቀጠለ (ቁጥር 2) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህን የቅርብ አማኞች አሁንም በምኩራብ እየተንቀሳቀሱ ነበር ምክንያቱም አይሁዶችን እየቀየሩ እንደ ነበር አመለከተ ፡፡ በዚያ ጊዜ በደማስቆ ከ30 እስከ 40 ያክል የምኩራብ ተግባራት እንዳሉ የተገመተ ነው ፡፡ ሳዖል ወደ ደማስቆ ሲጓዝ ከሰማይ ታላቅ ብርሃን ዙሪያዉን አንፀባረቀ “ ሳዉል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ ? “ የሚል ድምፅ ሰማ (ቁጥር 3-4) ፡፡ በሐዋ (22፡ 6) በኋላ ጳዉሎስ ብርሃኑ በፀኃይ/በቀትር እንደ ሆነ ተናግሯል ፡፡ ጳዉሎስ ንጉስ አግሪጳን “ ..በዙሪያዬና ከእኔ ጋር በሄዱት ዙሪያ ከፀሐይ ብሩህነት የበለጠ ብርሃን ከሰማይ ሲበራ አየሁ “ በማለት ነገረው (ሐዋ 26፡ 13) ፡፡ ሳዖል ፈጣን ለዉጥ ያስፈልገዉ ነበር ኢየሱስም በነበረበት ስፍራ ወዲያዉኑ አገኘው ፤ ሳውልም መሬት ላይ በመዉደቅ የጌታ ድምፅ እንደ ሆነ አስተዋለ ነገር ግን ማን እንደ ነበር ጠየቀ (ቁጥር 5) ፤ በምላሹም ኢየሱስ ሳውል የሚያሳድደዉ እርሱ እንደ ነበር በመናገር ሳውልን መጥራቱን እንዲያደርግ ወደ ደማስቆ ላከው (ቁጥር 5) ፡፡ ሳውል ኢየሱስን እንዴት ነበር እያሳደደዉ የነበረው ? 1ቆሮ (12፡ 27) አማኞች የክርስቶስ አካል ናቸዉ ይላል ስለዚህ የሱ አካል በመሆናቸው ሳውል በቀጥታ ኢየሱስን እያሳደደዉ ነበር ፡፡ ከሳውል ጋር የነበሩት ሰዎች ድምፁን ሰሙ ምንም ነገር ግን አላዩም (ቁጥር 7) (ሐዋ 22፡ 9) ፡፡ ሳውል ከመሬት ተነሳ ስለታወረም ምንም ነገር አላየም ፤ ወደ ደማስቆም በእጅ ተመራ ለሰዎስት ቀናትም አልጠጣምም አልበላምም (ቁጥር 8-9) ፡፡ ዊልያም ባርክልይ “ እንደ ኃይለኛ ተበቃይ ወደ ደማስቆ መግባት ያስፈልገዉ የነበረዉ ሳዖል ወደ ዚያች ከተማ እንደ ልጅ እረዳት እንደሌለዉ በመታወር በእጅ እንደ ተመራ “ ፅፏል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (9፡ 10-19)፡ ኮንስታብል “ ሳውል በክርስቲያኖች አደን ላይ ነበር ነገር ግን አሁን ወደ ክርስቶስ እየፀለዬ እንደ ነበር “ ይፅፋል ፡፡ ወንጌላዊ ቻርለስ ሱፐርጌዮን “ ፀሎት በታደሰ ልብ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ፊርማ እንደሆነ “ ገልፃል ፡፡ ቁጥር 10 በሌላ በተቀየረ ሁኔታ ይጀምራል ፡፡ ጌታም በደማስቆ ሐናንያ ለሚባል አንድ ደቀ መዛሙርቱ በራዕይ በኩል ተናገረው (ይህ ማለት በጊዜዉ ሐናንያ ተኝቶ ነበር ማለት ነው) ፤ ጌታም ሐናንያን ቅን በሚባለዉ መንገድ ወደ ይሁዳ ቤት በመሄድ በዚያ ይፀልይ የነበረዉን ከጠርሴስ የነበረዉን ሳዖል የሚባለዉን ሰዉ እንዲጠይቅ ነገረው (ቁጥር 10-11) ፤ በተጨማሪም ሐናንያ የሰዉየዉን አይን መልሶ እንዲያ እንዲያደርገዉ ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ በመሰረቱ ሐናንያ ስለ አሳይመንቱ ከጌታ ጋር ተከራከረ ምክንያቱም የሳዖል ቤተ ክርስቲያንን የማሳደድ ዜና በደማስቆ ቀድሞ ደርሶ ስለ ነበር ፤ ቤተ ክርስቲያንም ኢየሱስን የተከተሉትን ሁሉና በስሙ ተጠርተዉ የነበሩትን ለማሰር ስልጣን ያላቸዉ ደብዳቤዎች ሳዖል ማምጣቱን ታዉቃላች (ቁጥር 13-14) ፡፡ ጌታም ሐናንያን እንዲሄድ ነገረዉ ምክንያቱም ሳዖልን ስሙን “ በአሕዛብ፣ በነገስታት እና በእስራኤላዊያን ፊት “ ስሙን እንዲሸከም ስለመረጠው (ቁጥር 15) ፡፡ እግዚአብሄር ሳዖል ስለ ኢየሱስ ስም መከራን ይቀበላል አለ (ቁጥር 16) ፡፡ 2ቆሮ (11፡ 23-31) እና ፊል (3፡ 10) ስለ ክርስቶስ የጳዉሎስን መከራዎች መግለጫ ያካትታል ፡፡ በጌታ መንፈስ ስንጓዝ ምንም የሚያስፈራን የለም ! ሐናንያ ለእቅዱ ከተጠቀመባቸዉ የተደበቁ ቅዱሳን አንዱ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር በይሁዳ ቤት በዝምተኛ መገናኘት/ስብሰባ ታላቁን የሕዝብ/የታወቀን ተዓምራት እንደ አመጣጠነው “ ያመለክታል ፡፡ እግዚአብሄር ወደ አንድ ሰዉ ለመምጣት ሐናንያን ተጠቀመ - ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ ተብሎ ወደ ታወቀዉ ሰዉ ፤ ዋይርስቤ “ ወደ ክርስቶስ የመጣን የአንድ ሰዉ ዋጋ በፍፁም ልናሳንሰዉ እንደ ማይገባ “ አፅዕኖት ይሰጣል ፡፡
ሐናንያ በድፍረት ወደ ይሁዳ ቤት በመግባት እጆቹን በሳዖል ላይ በማስቀመጥ ሳዖልን የሳዖልን አይን መልሶ እንዲያይ እንዲያደርግ ኢየሱስ እንደ ላከው ነገረው በዚህም በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ቻለ (ቁጥር 17) ፡፡ ቅርፊቱም ከሳዖል አይኖች ወደቁ እይታዉንም እንደ ገና አገኘ ከዚያም ተጠመቀ ፤ ሳዖል መብላት ጀመረ ጥንካሬዉንም እንደ ገና አገኘ (ቁጥር 18-19) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (9፡ 20-25)፡ ሳዖል በደማስቆ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጥቂት ቀናትን በማሳለፍ ወዲያዉኑ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ሆነ በምኩራብ መናገር/ማወጅ ጀመረ (ቁጥር 20) ፡፡ ሳዖል በምኩራብ ያሉትን ለማሰር ደብዳቤዎችን ለማድረስ የተሾመ ነበር በዚያ ፋንታም ለእነርሱ የህይወትን መልዕክት አደረሰላቸው ፤ ሳዖል አድርሶት የነበረዉ መልዕክት በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ በስም ማጥፋት ተበሳጭቶበት ከነበረዉ ጋር ተመሳሳይ ነበር ነገር ግን አሁን ቤተ ክርስቲያን ከነበራት መልዕክት ተመሳሳይ መልዕክት ተናገረ ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ቀሪዎቹን ለማስተማር በቂ ጊዜ የለም ፤ በራሳችሁ አንብቡት ፡፡
መደምደሚያ
የዚህን ታሪክ ዋና ነገር ስትመለከቱ የትኛዉ የተሸለ ይሆናል ? ሐናንያ እግዚአብሄር በማዳመጥ በአካላዊና በመንፈሳዊ በሁለቱም የሳዖልን እይታ ለመመለስ በእግዚአብሄር ተመርጧልን ? ወይስ ሳዖል ለእግዚአብሄር የሚያስደንቅ ነገርን ለማድረግ ራዲካሊይ/በሙሉነት ተንቀጠቀጠ ? አንድኛዉ መንገድ ሐዋሪያት ስራ 9 ላይ ለሁላችንም ይተገበራል ፡፡ ዋናዉ ነገር ሁለቱም ሳዖልና ሐናንያ ተመሳሳይ ነገር አደረጉ - የኢየሱስ ክርስቶስን መልዕክት ተናገሩ/አወጁ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Acts (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 438.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Acts (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1385.
Wiersbe, p. 154.
William Barclay, The Acts of the Apostles (Edinburgh: Saint Andrew Press, 1962), p. 215; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Notes on Acts, p. 154, at https://planobiblechapel. org/tcon/notes/pdf/acts.pdf.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Notes on Acts, p. 216; at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/acts.pdf.
Charles Spurgeon, “Behold He Prayeth”; available at https://biblehub.com/sermons/auth/spurgeon/behold_he_prayeth.htm.
Wiersbe, p. 440.
Wiersbe, p. 440..
ጥያቄዎች
-
በሐዋ (9፡ 3-4) ኢየሱስ እርሱን ሲናገረው ሳዉል ምን እንደ ተሰማዉና እንዳሰበ ምን ታስባላችሁ ? ከእርሱ ጋር የነበሩትስ ሰዎች ?
-
እይታዉን ካጣ በኋላ ሰዉል ሰዎስት ቀን ለምን ምግብ እንዳልበላ ምን ታስባላችሁ ? (ሐዋ 9፡ 9)
-
በግል አስተያየታችሁ እግዚአብሄር ሐናንያን ወደ ሳዉል እንዲሄድ በጠራዉ ጊዜ ለመሄድ ያልፈለገበት ምክንያት ምን ነበር፣ ከፍራት የመነጨ ነበር ወይስ ይህ ሰዉ በእዉነት እንደ ተቀየረ አላመነም ነበር ? (ሐዋ 9፡ 10-14)
-
እግዚአብሄር ሳዉልን “ ስሙን ለአሕዛብ እንዲሸከም እንደ ተመረጠ መሳሪያ ለመጠቀም “ ለምን እንደመረጠዉ ምን ታምናላችሁ ? አሁንም እግዚአብሄር ለመንግስቱ ታላቅ ነገር ለማድረግ ዛሬም ያልተወደዱ ሰዎችን ይጠቀማል ? አንዳንድ /ጥቂት ምሳሌዎችን ማሰብ ትችላላችሁ ?
-
በሐዋ (9፡ 40) ጴጥሮስ ዶርቃን ከሞት አስነሳት ፤ ከኢየሱስ ሌላ /እንደ ኢየሱስ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሰዎች ከሞት ሲነሱ ሌላ የት ላይ ታያላችሁ ? (2ነገ 4፡ 32-37, ሉቃ 7፡ 12-15, ዮሐ 11፡ 37-44)
-
በሐዋሪያት ስራ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 9:17
“So Ananias left and entered the house. Then he placed his hands on him and said, ‘Brother Saul, the Lord Jesus, who appeared to you on the road you were traveling, has sent me so that you can regain your sight and be filled with the Holy Spirit.’”
ሳውል የክርስቶስን ደቀ መዛሙርት ይፈልግና አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ ወደ ደማስቆ በሚወስደው መንገድ ሄደ ፡፡ ነገር ግን የሰማይ ብርሃን ነጸብራቅ መንገዱን ገታ ፤ ኢየሱስም በቀጥታ ለሳውል ተናገረ ፣ ቀጥሎም ወዴት እንደሚሄድ ነገረው ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሳውል አይኑ ታውሮ ነበር ለሶስት ቀናትም ማየት አልቻለም ነበር ፡፡ ሐናንያ የተባለ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የጌታን ትዕዛዝ ሰምቶ በመታዘዝ ሳውልን በደማስቆ ለመጎብኘት ሄደ ፡፡ እግዚአብሔር ከሳውል አይን ላይ በኢየሱስ ስም ቅርፊትን ያስወግድ ዘንድ ሐናንያን ተጠቀመ ፡፡ ከዚያም ሳውል አማኝ ሆነ በሐናንያም እጅ ተጠመቀ ፡፡ ከዚያም በኋላ በደማስቆ ካሉ ደቀ መዛሙርት ጋር ጊዜን አሳለፈ ከዚያም በምኩራቦቹ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ሰበከ ፡፡
የሳውል ህይወት በትልቁ “አስደናቂ ጸጋ “ የሚለውን የመዝሙር ቃል ያሳያል ፡ “ ማየት አልችልም ነበር አሁን ግን አያለሁ ፤ ጠፍቼም ነበር አሁን ግን ተገኝቻለሁ ፡፡ “ ምናልባት በጣም የተበላሸ ፣ በኃጢአት የተሞላ ፣ መታዘዝ የሌለበት ትላንትና እንዳለህ እንድሁም ማንም መቼም እንደማይቀበልህና በአንተም ውስጥ ምንም ነገር እንደማያይ ታስብ ይሆናል ፡፡ እንድሁም ደግሞ ህይወትህ በአጠቃላይ ያለ አዳኝ ሰላም እንደሆነ ታምንም ይሆናል ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስን አግኝተኸው አታውቅም ፡፡ ኢየሱስ ኃጢአትህን ይቅር ይላል ስላገኘኸው ወይም ደግሞ ስለሚገባህ አይደለም ፡፡ ነገር ግን ስለሚወድህና የጸጋን ፣ የፍቅርንና የተስፋን ነጻ ስጦታ እንድሁም መታወቅን ሁሉ የሚያልፈውን የእርሱን ሰላም ስለሰጠህ ነው ፡፡ ይህን መቀበል ብቻ ነው ያለብህ ፡፡ ይህ በእውነትም የሚያስደንቅ ጸጋ ነው ፡፡ ለኢየሱስ አወ ብለህ የማታውቅ ከሆነ ፣ ዛሬ አንድ ደቂቃ ውሰድና እርሱን ወደ ህይወትህ ተቀበል ፡፡ በክርስቶስ አማኝ ከሆንክ ደግሞ ለሆነ ሰው እንዴት ከአለማየት ወደ ማየት እንደመጣህ ታሪክህን አካፍል ፡፡ በኢየሱስ ታላቅ ፍቅርና አስደናቂ ጸጋ ውስጥ ኃይል አለ ፡፡
“ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ አለ ። “
— ሐዋርያት ሥራ 9:17
ተጨማሪ ጥቅስ
- ሮሜ 11:6 — “ በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል ። “
- ኤፌሶን 2:8–9 — “ ለዓመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል ። ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ ደግሞም በግሪክ ሰው ፡፡ “
- 1ኛ የጴጥሮስ 2:9 — “ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።