ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሐዋሪያት ስራ 8 ማንበብ ለኔ በትንሹ ወደ “ ቀድሞ ት/ቤት” መሄድ የሚመስል ነው ፤ ይህ ፅሁፍ የመነቃቃት ጊዜን ለመጀመር የሚረዳ ነው ፡፡ በሐዋ (1፡ 8) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በእስራኤል ብቻ ሳይሆን በመላዉ አለም ምስክሮቹ እንዲሆኑ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይልን እንደሚቀበሉ ተስፋ ገባላቸው ፡፡ ሐዋሪያቱ ይህን ተስፋ ከልባቸዉ በመዉሰድ መንፈስ ቅዱስ ተሞልተዉ የነበሩና ስራዉን መስራት የሚችሉ ሰባት ሰዎችን አገኙ ስለዚህም እንደ ምስክር የተሰጣቸዉን ማድረግ ይችላሉ (ሐዋ 6፡ 3-5) ፡፡ ከእነዚህ ከሰባቱ ለአገልግሎት ከተመረጡት አንዱ ፊልጶስ ነበር ፤ ፊልጶስ ለአገልግሎቱ የተመረጠ ቢሆንም በሐዋሪያት ስራ 8 ተግባሩ/ሚናዉ ተቀየረ ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (8፡ 1-4)፡ የቁጥር 1 የመጀመሪያዉ ክፍል ለእኛ አስፈላጊ ነው፡ “ ሳዖል በእስጢፋኖስ ሞት ተስማማ “ ፤ ያ በሐዋሪያት ስራ መጽኀፍ ለምንሄድበት ደረጃን ያስቀምጣል ፡፡ ቁጥር 1 ከእስጢፋኖስ መወገር በኋላ (ሐዋሪያት ስራ 7) በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ላይ ብዙ ድብደባዎች መድረሳቸዉን እና ሐዋሪያቱ በዙሪያቸዉ በነበሩት አካባቢዎች መበተናቸዉን መግለፁን ይቀጥላል (ቁጥር 1) ፡፡ ሳዖል ቤት ለቤት እየላከ ክርስቶስን የተከተሉትን ሴቶችና ወንዶች እያሰረ በነበረበት ጊዜ የእስጢፋኖስ አካል በተጉ ሰዎች ተቀበረ አዘኑለትም ፡፡ ሉቃስ የሳዖልን ድርጊት “ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሚያፈርስ “ ገልፆታል (ቁጥር 2-3) ፡፡ እዚህ ስፍራ ላይ ሳዖል፣ የተጉ አይሁዶች ቤተ ክርስቲያንን ጠሉ፣ የኢየሱስ ታሪክንም የምታጋራዉን ቤተ ክርስቲያን ጠሩ ፡፡ ሐዋሪያቶቹም እንደ ተበተኑ እንዲያደርጉት ተሰጥቷቸዉ የነበረዉን አደረጉ - የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሰበኩ (ቁጥር 4) ፡፡ እግዚአብሄር ሰዖልንና የአይሁዶችን ድብደባ እንዴት ወንጌል ለማሰራጨት ቸእንደ ተጠቀመበት አስታዉሉ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (8፡ 5-8)፡ እንዲያገለግል ተመርጦ የነበረዉ ፊልጶስ ወደ ሰማሪያ ከተማ በመሄድ መስበክ ጀመረ (ቁጥር 5) ፤ ሕዝቡም አዳመጡት፣ መልዕክቱን ሰሙ በተጨማሪም ያደረገዉን መልዕክቶችም አዩ - ክፉ መናፍስትን ወጡ፣ ሽባዎችና በሽተኞችም ተፈወሱ (ቁጥር 6-7) ፡፡ ባዩት ነገር በምላሹ ሕዝቡ ተደሰቱ (ቁጥር 8) ፡፡ ፊልጶስ በእግዚአብሄር ምስክርነቱ እየተጓዘ ነበር ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (8፡ 9-13)፡ ፊልጶስን ከሚሰሙት ሰዎች አንዱ ሲሞን ነበር፣ ጥንቆላን የሚያደርግ ሰዉ ነበር ከእግዚአብሄርም ታላቅ ኃይል እንደ መጣ ተናገረ ፡፡ ሲሞን ሕዝቡን ለረጅም ጊዜ ያስደንቅ ነበር (ቁጥር 9-10) ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የፊልጶስን መልዕክት በሰሙ ጊዜ ፊልጶስ ስለ እግዚአብሄር መንግስትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እየሰበከ እንደ ሆነ አስተዋሉ ፤ ይህን ሲሞንን ጨምሮ ብዙዎችም ተጠመቁ (ቁጥር 13) ፡፡ ከዚያም ሲሞን ከፊልጶስ ጋር ሁሉም ቦታ በመሄድ ፊልጶስ ሲያደርግ ባያቸዉ ምልክቶችና ተዓምራቶች በእዉነት ተደነቀ (ቁጥር 13) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (8፡ 14-25)፡ አሁንም በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋሪያት ፊልጶስ ለሰማሪያ መልዕክቱን እንደ ሰበከና ሰማሪያዊያንም የእግዚአብሄርን መልዕክት በጥሩ እንደ ተቀበሉት በሰሙ ጊዜ በዚያ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኳቸው (ቁጥር 14) ፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስ እዉነት እንደ ነበር ሊያዩ ወይስ የእግዚአብሄር ንቅናቄ እየተካሄደ ስለ ነበር በመርዳት የነበሩትን ለማጠንከር ነበር የሄዱት ? ሪቻርድ ብላክብይ ሁል ጊዜ እንደ ሚለው “ እግዚአብሄር የሚሰራበትን ስፍራ ስታገኙ ተቀላቀሉት “ ፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሲደርሱ እስካሁን ሆኖ ያልነበረዉን ሰማሪያዊያን መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ፀለዩ (ቁጥር 15-16) ፤ ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸዉን ጫኑባቸዉ ሰማሪያዊያንም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ (ቁጥር 17) ፡፡ በስነ መለኮት ይህን የመንፈስ ቅዱስ መካፈል አላገኘሁም ፤ የኢየሱስ ተከታዮች ከማረጉ በፊት መንፈስ ቅዱስን ከኢየሱስ ተቀበሉ ፤ ስለዚህ ፊልጶስ መንፈስን አላስተላለፈላቸዉም /አልነገራቸው ? ሰማሪያዊያን ሲጠመቁ መንፈስን አልተቀበሉም ? ምንም ይሁን ምክንያቱ ሆኗል ፡፡ ሲሞን በማየት ተመሳሳይ ኃይል እንዲሰጡት ለመግዛት ሐዋሪያቱን ጠየቀ (ቁጥር 18-19) ፡፡ ለቀድሞዉ ጠንቋይ ለሲሞን መስጠት ብናዘነብል አስቸጋሪ ጊዜ ነዉ ነገር ግን በትክክል የፈለገዉ ተመሳሳይ ነገር የማድረግ ችሎታ እንዲኖረዉ ነበር ፤ የሲሞን ኃጢዓት ኃይሉን መግዛት እንደሚችል በማሰቡ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ ከእግዚአብሄር እንደ ስጦታ የመጣዉን ለመግዛት በመሞከሩ ምክንያት የሲሞን ብር ከእርሱ ጋር እንደ ሚጠፋ ተናገረው (ቁጥር 20) ፤ ጴጥሮስ የሲሞን ልብ በእግዚአብሄር ፊት ትክክል እንዳልነበር ተናገረ (ቁጥር 21) ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ ይህ የብልፅግና አስተሳሰብ ስዕል ነው - ወንጌል ንፁኅ በሆነበት ቦታ በሁኔታው ገንዘብ ለማግኘት መመኮር ፡፡ ጴጥሮስ ሲሞንን ክፉ የሆነዉን የልቡን ፍላጎት ንስሀ እንዲገባ ይህን ካደረገም እግዚአብሄር ይቅ ሊለዉ እንደ ሚችል ነገረው (ቁጥር 22-23) ፡፡ ጴጥሮስ ስለ ሲሞን መቀየር ሲጠይቅ ፊልጶስ ግን አልጠየቀም ፡፡ እንደ ምስክር ስራችን በቀላሉ መልካሙን ዜና ማድረስ ብቻ ነው ፤ መልካሙን ዜና በትክክል ተቀብለዉታል ወይ ብሎ መዳኘት/መፍረድ ስራችን አይደለም ፡፡ ሲሞን የመለወጡን እዉነት ለእርሱ እንዲፀልይለት ጴጥሮስን በመጠየቁሰ አሳየ/ገለጠ (ቁጥር 24) ፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም በሰማሪያ መንደሮች ሁሉ በመስበክ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ (ቁጥር 25) ፡፡ ፊልጶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱት ቡድኖች ጋር አብሮ እንደሚኖር ማሰብ ልክ ነዉ የሚሆነው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (8፡ 26-40)፡ ከዚያም ሁኔታዉ በፍጥነት ተቀየረ ፤ እየሄዱ እንዳለ መለዓክ ፊሊጶስን ከደቡብ ኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያስከደዉ መንገድ ላይ እንዲሄድ ነገረው (ቁጥር 26) ፤ ፊሊጶስም ታዘዘ (27) ፡፡ የንግስቲቱ ታላቅ ሰራተኛ የነበረ እና ለስግደት ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ የነበረ አንድ ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ ወደ ኢትዮጲያ በሰረገላዉ እየተመለሰና የኢሳያስን መፅሀፍ እያነበበ ነበር (ቁጥር 27-28) ፤ መንፈሱም ሰረገላዉን እንዲቀርበዉ ነገረዉ ፊልጶስም ታዘዘ (ቁጥር 29) ፡፡ እግዚአብሄር በብዙ መንገድ ሊናገረን እንደሚችል አስታዉሉ - በመለዓክት በኩል፣ በእግዚአብሄር ቃል በኩል፣ በሚሰማ ድምፅ በኩል፣ በሌሎች በኩል እና በራዕይ በኩል፣ በምልክት በኩል እና በሕልም በኩል ፡፡
ፊልጶስ በመሮጥ እንዲሄድ ወደ ተነገረበት ስፍራ ሄደ ፡፡ ፊልጶስ “ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት “ መለሰለት (ቁጥር 29) ፤ የኢትዮጲያዉን ንባብ በሰማ ጊዜ ፊልጶስ “ የምታነበዉን ታስተዉለዋለህን “ የሚል ጥያቄ ጠየቀው (ቁጥር 30) ፡፡ ኢትዮጲያዊዉ ለወንጌል ክፍት እንደ ነበር የሚለይ እና የሚመራ መንፈስ ፊልጶስ ነበረው ፤ ፊልጶስ ስለ ኢሳያስ የኢትዮጲያዊዉን ጥያቄዎች ለመመለስ የተዘጋጀ ነበር (ቁጥር 30-35) ፡፡ ፊልጶስ በምስክርነቱና በሰማሪያ በስብከቱ ዉስጥ ለዚህ አጋጣሚ የተዘጋጀ ነበር ፤ ጃንደረባዉ ፊልጶስን ነቢዩ ስለማን እያወራ እንደ ነበር በጠየቀዉ ጊዜ ፊልጶስ ስለ ኢየሱስ እንደሆነ ነገረው (ኢሳ 53፡ 7-8) ፡፡ ይህ ሁሉንም መፅሀፈት ለመረዳት አስፈላጊ እንደሆነ ያሳያል ምክንያቱም ሁሉም አንድን ሰዉ ወደ ክርስቶስ ለመምራት የሚጠቅም ይሆናል ፡፡
ከፊልጶስ ገለፃ በኋላ ወደ ዉሃ መጡ ጃንደረባዉም ከመጠበቅ የሚከለክለዉ ነገር እንዳለ ጠየቀ (ቁጥር 36) ፤ ጃንደረባዉ በዉሃ ስለመጠመቅ አስፈላጊነት እንዴት አወቀ ? ፊልጶስ የክርስቶስ መልካም ዜናን ሲገልፅለት ከጃንደረባዉ ጋር ተጋርተዋል/አካፍሎታል ፡፡ ይህ መስተጋብራቸዉ ምን ያክል ቀናትና ሰዓታት እንደ ወሰደ እርግጠኞች መሆን አንችልም ? ምናልባትም ስለነዚህ ዝርዝር ስላልተመዘገብልን በአንድ ምሽት የሆነ አልነበረም ፡፡ ፊልጶስ ሰረገላው እንዲቆም በማዘዝ ጃንደረባዉን አጠመቀው (ቁጥር 38) ፡፡ ፊልጶስ ከጃንደረባዉ ጋር ወደ ዉሃዉ ዉስጥ ገባ ፤ ከዉሃዉ በወጡ ጊዜ መንፈስ ፊልጶስን ወሰደዉ ጃንደረባዉም እንደ ገና አላየዉም (ቁጥር 39) ፡፡ ፊልጶስ በአዛጦን በመገኘት ወደ ቂሳርያም እስኪመጣ ድረስ በዚያ ከተሞች ወንጌልን ሰበከ (ቁጥር 40) ፡፡
መደምደሚያ
በመነቃቃት ጊዜ የሆነን ሰዉ እንዴት መቅረብ እንዳለብን አራት ቃሎች አሉን ፤ ሁሉም አራቱም በፊልጶስ አቀራረብ ሊታዩ ችለዋል፡
- ፍቅር፡ ፊልጶስ የኢትዮጲያ ጃንደረባዉን ወደ እርሱ ስለሮጠ እንደሚወደው አሳየው ፡፡
- ማዳመጥ፡ ፊልጶስ ኢትዮጲያዊዉ ጃንደረባ እያነበበ የነበረዉን በማዳመጥ በጥያቄ ለቃለ ምልልስ ጋበዘው፡፡
- መረዳት፡ ፊልጶስ ኢትዮጲያዊዉ ለወንጌል ክፍት እንደ ነበር አስተዋለ/ተረደ ፡፡
- ምላሽ መስጠት፡ ፊልጶስ ከጃንደረባዉ ጋር ወደ ሰረገላዉ በመሄድ ስለ ኢየሱስ አወራው ፡፡
ፊልጶስ ጃንደረባዉን ወደ ክርስቶስ ከመራ በኋላ ምስክርነቱ የተፈፀመ እንደሚሆን አልተመለከተም ፤ መጓዙንና መስበኩን ቀጠለ ፤ መጓዙንና ማጥመቁን ቀጠለ ፡፡ መጓዙንና የኢየሱስ ክርስቶስን መልዕክት ማሰራጨቱን ቀጠለ ፡፡ ስራችን በዚህ በመጓዝ ቃሉን በማሰራጨት ለእነርሱ በጊዜዎ አንድን ሰዉ በመዉደድ፣ በማዳመጥ፣ በመረዳትና ምላሽ መስጠት ፡፡
1 Richard Blackaby, Experiencing God
ጥያቄዎች
-
ሲሞን ማን ነበር፣ በሐዋ (8፡ 1) እያደረገ ስለ ነበረዉ መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል ? (ሚክ 5፡ 12, ዘሌ 20፡ 6, ዘጸ 22፡ 18)
-
በሐዋ (8፡ 18-19) ሲሞን የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ወይም ስልጣን ለመግዛት እየሞከረ ነበር ፤ ብዙ ጊዜ በህይወታችሁ በተሳሳተ አሳብ ወይም ፍላጎት የእግዚአብሄርን ኃይል ወይም ሌላ ስጦታ ለማግኘት እንዴት ትሞክላችሁ ?
-
በሐዋ (8፡ 26 እና 29) የእግዚአብሄር መለዓክ ለፊልጶስ ተናገረው ፤ መንፈስ ፊልጶስ እንዲያደርግ ምን ነገረው ? እግዚአብሄር ለኢትዮጲያዊዉ ጃንደረባ ለመናገር አንድ እንግዳን ለምን እንደተጠቀመ ምን ታስባላችሁ ? እግዚአብሄር ለማታዉቁት ሰዉ እንድትነግሩት ወደ ሌላ ሰዉ በመላክ ተጠቅሞባችሁ ያዉቃል ወይስ በተመሳሳይ መንገድ ወደ እናንተ ሌላ ሰዉ ተልኮላችሁ ያውቃል ?
-
በኢሳያስ ጃንደረባዉ ስለማን ነበር እያነበበ የነበረው ? ስለ ኢየሱስ ከሰማ በኋላ ጃንደረባዉ ለመጠመቅ ለምን እንደፈለገ ምን ታስባላችሁ፣ ፊልጶስ መጀመሪያ ምን ማድረግ እንዳለበት ነገረው ? ተጠምቃችኋል ? ካልተጠመቃችሁ ከማድረግ/ከመጠመቅ ምን ከለከላችሁ ?
-
ቁጥር 39 “ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን እንደ ነጠቀዉ “ ይናገራል ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ አንድ ሰዉ በድንገት የተነጠቀዉ ሌላ የት ነው ? (ዘፍ 5፡ 24, 2ነገ 2፡ 11)
-
በሐዋሪያት ስራ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 8:26–29
“An angel of the Lord spoke to Phillip: ‘Get up and go south to the road that goes down from Jerusalem to Gaza.’ (That is the desert road.) So he got up and went. There was an Ethiopian man, a eunuch and high official of Candace, the Queen of the Ethiopians, who was in charge of her entire treasury. He had come to worship in Jerusalem and was sitting in his chariot on his way home, reading the prophet Isaiah aloud. The Spirit told Phillip, ‘Go and join that chariot.’”
ፊልጶስ እየሄደ ሳለ የጌታ መልአክ በደቡብ በኩል ወዳለው ምድረ በዳ መንገድ ሂድ አለው። ወድያውኑም ፊልጶስ ሄደ ፤ በሰረገላም ላይ የተቀመጠ ኢትዮጵያዊ ሰው አየ ፡፡ መንፈስም ፊልጶስን ሰረገላውን እንድገናኝ ነገረው ፤ አሁንም እንደገና ፊልጶስ መንፈስ እንዳዘዘው አደረገ ፡፡ ኢትዮጵያዊውም ጃንደረባ ከነቢዩ ኢሳይያስ ክፍል ያነብ ነበር ፤ ግራም ተጋብቶ ነበር ፡፡ ሁለቱም ሰዎች በሰረገላ ላይ ተቀምጠው ፊልጶስ ጃንደረባው የጠየቀውን ክፍል አብራራና ከዚያ የኢየሱስን ወንጌል ወደ ማካፈል አመራ ፡፡
ለአማኞቹ የጌታ ፍቃድ መንፈስ ቅዱስን እንድያደምጡትና ለእርሱም ወድያው እንድታዘዙ ነው ፡፡ ከመንፈስ የሆነ ነገር በምትሰማበት ጊዜ ፣ አድርገው ፡፡ የሰማኸውን አትመርምር ወይም አትጠራጠር ይልቁንም ታዘዝ ፡፡ በቃ መሄድ ፣ ማድረግ ፣ መስጠት ወይም የሰማኸውን ማንኛውንም ነገር መቀበል ብቻ ፡፡ መጽሀፍ ቅዱስን ካልተቃረነ ፣ በቃ እመን ከእግዚአብሔር ነው ፡፡ ለማዳመጥና ለመታዘዝ ትፈቅዳለህ ? ምንድን ነው ወደ ኋላ ያስቀረህ ? ዛሬ ሂድና መንፈስ የሚልህን አድርግ ፤ በምድረ በዳ መንገድ መሄድ ቢሆን እንኳ ……. ጌታ ከአንተ ጋር ይሆናል ! እርሱ በእያንዳንዱ የወደፊት እርምጃህ በታማኝነት ይመራሃል ፡፡ ይህ ከኢየሱስ ጋር ወደ ታላቅ ጀብዱ ይመራሃልና ደስ ይበልህ ፡፡
“ የጌታም መልአክ ፊልጶስን፦ ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ አለው ። ተነሥቶም ሄደ ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር ፤ ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር ። መንፈስም ፊልጶስን፦ ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ አለው ። “
- ሐዋርያት ሥራ 8፡26-29
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 30:21 — “ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ ። “
ማቴዎስ 7:24 — “ ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል ። “
ያዕቆብ 1:22 — “ ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።