ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሐዋሪያት ስራ 7 ምንም ነገር ያላጣዉን የአንድ ሰዉ ምስክርነት ላይ ተመልክተናል ፡፡ ይህ የእስጢፋኖስ ህይወት የመጨረሻ ቀን ነው ፤ በብዛት ሞቱ ላይ ወይም መወገሩ ላይ እናተኩራለን ነገር ግን ከዛ በፊት እስጢፋኖስ እስከ መጨረሻ ድረስ ለኢየሱስ ክርስቶስ የተሸነፈ ልብ ያለዉን በመግለጥ ምስክርነት ሰጠ ፡፡ ስሙም ለክብር ዘዉድ ወይም በኦሎፒክ ጨዋታ ለድል ዘዉድ ከሚጠቅም ከግሪክ ቃል ጋር ተመሳሳይ የሆነ ዘዉድ ወይም በአበባ ያጌጠ ማለት ነው ፡፡ ይህ ሰዉ በመንፈስ ቅዱስ እንደ ተሞላ ተገልፃል፣ በጣም እንደ ትልቅ/እንደ አረጀ አይደለም ነገር ግን ለኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያዉ ሰመዓትነትን ዘዉድ በመጫን በሚገባ ዘዉድ ጭኖ የተሰየመ ነው ፡፡ በታላቅ ፍርድ፣ በታላቅ መካከል እንደ ታማኝና እዉነተኛ እንቆማለን ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (6፡ 14)፡ የእስጢፋኖስ ሐሰተኛ ከሳሾች ኢየሱስ “ ቤተ መቅደሱን በማጥፋት ሙሴ አዉርዶት የነበረዉን ልምድ ይቀይረዋል “ ብሏል በማለት በመክሰስ እዉነቱን ጠመዘዙት (የታወቀዉ የሰይጣን ስልት) ፡፡ እስቲፋኖስ ሙሉ ለሙሉ ያን ሲገስፀዉ አናየውም ነገር ግን አፈፃፀሙን/ትርጉሙን እዚህ ገሰፀዉ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (7፡ 1)፡ የሸንጎዎቹ 70 ሰዎች “ የመለዓክት ፊት መስሎ የነበረዉን “(ሐዋ 6፡ 15) እስጢፋኖስ ፊት ላይ አትኩረዉ በመመልከት “ ይህ አዉነት ነው ? “ በማለት ጠየቁ፣ የእስጢፋኖስ መልስ - ምስክርነቱ - የአይሁዶች ታሪክ ማጠቃለያ ነው ፤ ነገር ግን ከዚያም የሚበልጥ ነው ፡፡ ምስክርነቱ እግዚአብሄር ከሰጣቸዉ አይሁዶች እንዴት ወደ ጣዖት እንደ ዞሩ ያሳያል ፡፡ ለሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ቃላችን ስልጣን እንደሆነ አስታዉሱ ፤ በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ስልጣን ስር እስጢፋኖስ አይሁዶች የእግዚአብሄር ስልጣንና በረከት ተቀብለዉ ወደ ጣዖት ቀየሩት አለ፡፡ እስጢፋኖስ ስለ አይሁዶች ኃይማኖት አጥባቂዎች ሰዎስት ታላቅ ነገሮች ላይ አትኩሯል፡ መጀመሪያዉ ምድሪቷን (ቁጥር 2-36)፣ ሁለተኛ ህጉን (ቁጥር 37-43) እና ሰዎስተኛ ትልቅ የሆነዉ ቤተ መቅደሱ ላይ (ቁጥር 44-53) ፡፡ ቀድሞ ኢየሱስ ስለነዚህ ሁሉ ነገሮች ተናግሮ ነበር ፡፡
በእርሱ ላይ የተነሱት ክሶች ትክክል እንደ ነበር በጠየቁት ጊዜ እስጢፋኖስ ጣዖቶቻቸዉ አድርገዉ ሰርተዋቸዉ የነበሩ አይሁዶች ናቸዉ አለ ፡፡ ወደ አንድ ከሚያመለክተዉ ይልቅ እንዲያተኩሩ አድርገዋቸዉ ነበር ፡፡ እስጢፋኖስ እነዚህን የተቀደሱ ላሞች አድርገዉ በመስራታቸዉ ብቻ አላጠቃም ነገር ግን ብሉይ ኪዳንን በመጥቀስ ሁሉም የተመሰቃቃለዉን ቀየረው ፤ ይህን እንዴት እንዳደረጉ ከቃሉ አሳያቸው ፡፡ በነፃ መለቀቅን ወይም ከችግር መዉጣትን ከመፈለግ ይልቅ እስጢፋኖስ ለድርጊታቸው ለማምለክ በእግዚአብሄር በተመረጠዉ መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም እምነት ተከላከላቸው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (7፡ 2-8)፡ እስጢፋኖስ ስለ ምድሪቱ ትክክል እንዳልነበሩ በመናገር ጀመረ ፡፡ እግዚአብሄር በተስፋይቱ ምድር ለሚኖሩት የተለዬ እድልን ሰጣቸው ፤ ነገር ግን እስጢፋኖስ ከቅዱስ ምድር ዉጪ እንኳን እየኖሩ እግዚአብሄር ሕዝቡን እንደተጠነቀቀላቸዉና እንዳገኛቸዉ አመለከተ ፡፡ ያንን ሐሳብም ለማረጋገጥ በአብርሃም ጀመረ ፤ “ ወንድሞችና አባቶች ሆይ “ (ቁጥር 2) ብሎ በመናገር እስጢፋኖስ አክብሮትን አሳያቸው ፡፡ ከዚያም እስጢፋኖስ እግዚአብሄር በተስፋይቱ ምድር ከመሆኑ በፊት ለአብርሃም እንደ ተገለጠለት አብራራ (ቁጥር 2-8) ፤ እግዚአብሄር አብርሃምን ከቅድስቲቱ ምድር እርምጃ እንኳን ሳይዝ ባረከው ፡፡ የምድሪቱ ባህሪይ በረከት አልነበረም፣ በምድሪቱ ላይ የእግዚአብሄር በረከት ነው ፤ እዚህ ስፍራ ላይ እስጢፋኖስ የሸንጎዎቹ አባላት ይዘዉት የነበረዉን እዉነት እየጠቀሰና አጉልቶ እያሳዬ ነበር ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (7፡ 9-16)፡ እስጢፋኖስ ይህ ስልጣንና ዝምድና ለ12ቱ የያዕቆብ ልጆች በእግዚአብሄር የተደረገ ነዉ አለ ፡፡ ፓትሪያሪኮቹ/ቤተሰቦቹ በዮሴፍ በመቅናት በግብፅ ለባርነት የሸጡት ቢሆንም እንኳን እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ነበር፣ ከችግሮቹ ሁሉ በማዳን በፈርዖን ፊት ሞገስን ሰጠው ፡፡ እግዚአብሄር የቅድስቲቱ ምድር የያዙት ብቸኛዉ አካል የአባቶቻቸዉ መቃብር ቢሆንም እንኳን በግብፅ በዮሴፍ በኩል ቤተሰቦቹን ባረካቸው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (7፡ 17-36)፡ ከዚያም እስጢፋኖስ ወደ ሙሴ ዘመን አመለከታቸው ፤ ዮሴፍን የማያዉቀዉ ያስጨነቃቸዉ ፈርዖን እስኪነሳ ድረስ በግብፅ አይሁዶች አፍርተዉ/በዝተዉ ነበር ፡፡ በዚያን ጊዜ የተለመደዉ የሕዝቡ ድርጊት ፅንስን ወደ ዉጪ እንዲሞቱ መጣል ነበር ፤ ነገር ግን ሙሴ በተጣለ ጊዜ የፈርዖን ልጅ እንደ ጉድፈቻ እንደ እራሷ ልጅ አነሳችዉ ፡፡ ሙሴ በግብፃዊያን ጥበብ የተማረ ነበር (ቁጥር 20-22) ፡፡ እስጢፋኖስ ታሪኩን መናገር በመቀጠል ከዘጸዓት (2፡ 14) እና ከዘጸዓት (3፡ 6) እና 15 ሙሴ ገጥሞት የነበረዉን ነገር ለመገንባት በመጥቀስ ሕዝቡን ወደ ምድሪቱ መልሶ ያመጣቸዋል ፡፡ ከዚያም በሐዋ (7፡ 33) ሙሴ ጫማዉን እንዲያወልቅ ተነገረዉ ምክንያቱም የቆመበት ስፍራ ቅዱስ ምድር ስለ ነበር ፤ በዚያን ክስተት ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ቆሞ ነበር ፡፡ እስጢፋኖስ የእግዚአብሄርን ጥሪ ለሙሴ እንደ ገና በመቁጠር ከዘጸዓት 3 እንደ ገና ጠቀሰ ፡፡ አይሁዶች ሙሴን ባይቀበሉትም እግዚአብሄር እንደ አስተዳዳሪና እንደ ተቤዢ መርጦት ነበር ፤ እግዚአብሄር ሙሴን ከግብፅ በቀይ ባህር በኩል ሲመራቸው ለ40 አመታት በምድረበዳ ድንቅና ታዓምራትን አደረገ ፡፡ በኦሪት መፅኀፍት ዉስጥ እግዚአብሄር በቅዱሱ ተራራ ላይ ጠራው ፡፡ የትም ቢሆን ቅዱስ ቦታ እግዚአብሄር ህዝቡን የሚያገኝበት ነው ፡፡ ሙሴ ከተስፋይቱ ምድር ድንበር ዉጪ ነበር - በፍፁም ተስፋይቱ ምድር አልገባም ፡፡ ህዝቡን ወደ ምድሪቱ ሲመሩ እግዚአብሄር በሁሉም ስፍራ ከሙሴ ጋር ነበር ፡፡ እስጢፋኖስ ሸንጎዎቹ ሀሳቡን ተሳስተዉ እንደ ነበር አብራራላቸው ፡፡ ምድሪቱ ከእግዚአብሄር በረከት ነበራት እንጂ ምድሪቱ የእግዚአብሄር በረከት ነበራት ፤ የትም ቦታ እግዚአብሄር ከህዝቡ ጋር በሚገናኝበት አለ - ወደ ኢየሱስ የሚያመክተዉን ፡፡
ሐዋሪያት ስራ ( 7፡ 37-43)፡ እስጢፋኖስ ህጉን በመጠበቅ እና በመቋቋም ከሰዉ የነበሩትና ሕጉን ጣዖት አድርገዉት የነበሩትን ሸንጎዎቹን ነገራቸው ፤ እስካሁን እስጢፋኖስ ባልተስማሙበት ነገር ምንም አላለም ነበር ነገር ግን አሁን በእግሮቻቸዉ እርምጃዎች ላይ ነበር ፡፡ በእርሱ ላይ ማጉረምረም እንደሚጀምሩ ጥርጥር የለዉም ፤ እስጢፋኖስ በሙሴ ንግግር “ እግዚአብሄር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል “ (ቁጥር 37) በሚለዉ ጀመረ ፤ ይህ ነቢይ ክርስቶስ ነበር ፡፡ በሙሴ ጊዜም እንኳን እግዚአብሄር ወደ ክርስቶስ እያመለከተ ነበር ፡፡ እስጢፋኖስ ሕዝቡን ለመታዘዝ ፍቃደኛ እንዳል ነበሩና፣ በልባቸው ወደ ግብፅ ተመልሰዉ እንደ ነበር ለማሳየት የወርቅ ጥጃ በመስራት መስዋዕት ማቅረባቸዉን በመግለፅ ከዘጸዓት መጥቀሱን ቀጠለ ፡፡ ጣዖታቸው በመላዉ በብሉይ ኪዳን በመጠቀስ እስጢፋኖስ በቁጥር (42-43) በጠቀሰዉ በነቢዩ አሞፅ ተጠቃለለ (አሞ 5፡ 25-27) ፡፡ እስጢፋኖስ ከኦሪት መፅኀፍት በሁሉም መንገድ በታሪክ መፅኀፍቶች አልፏል/ተናግሯል ፤ እስጢፋኖስ ጣዖቶቻቸዉን እያመለከታቸዉ ነበር ፡፡ የሙሴ ህግ እና የእግዚአብሄር ቃል ነበራቸዉ ነገር ግን አልጠበቁትም/አላከበሩትም ፤ የሙሴ ህግ ሊያድናቸዉ አልቻለም ነገር ግን ወደ ሚችለዉ አንዲ ነቢይ አመለከታቸው ፡፡ የቤዛነት/የመዋጀት ተስፋ በሙሴ ህግ አልነበረም በኢየሱስ እንጂ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (7፡ 44-50)፡ ቀጥሎም እስጢፋኖስ ስለ ቤተ መቅደሱ ስህተት እነደ ነበሩ ተናገረ ፤ እግዚአብሄር “ የሰዉ እጅ በሰራቸዉ ቤተ መቅደስ አይኖርም “ (ቁጥር 48) በማለት አመለከታቸው ፡፡ በቁጥር 49-50 እስጢፋኖስ ጉዳዩን/ትኩረቱን በኢሳ (66፡ 1-2) ፈፀመ ፡፡ መማክርቱ/አማካሪዎቹ ይገናኙበት የነበረዉ የድንጋይ ክፍል ስፍራ/ቤት በቤተ መቅደሱ አጠገብ ነበር - እስጢፋኖስ ወደ ጣዖት አድርጋችሁታል ያላቸዉ ቤተ መቅደስ ፤ በኢየሱስ የአዲስ ቤት ተስፋዉ በትክክል ተፈፅሞ ነበር ፡፡ ኤፌ (2፡ 19-22) ይህ አዲስ ቤት “ በሐዋሪያትና በነቢያት መሰረት ላይ ታንፃችኋልና የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ “ እንደሆነ ይናገራል ፤ በዚህ ጊዜ በቤተ መቅደስ ያለዉ መጋረጃ ወደ ሁለት ተቀደደ ፡፡ ፈጣን የሆነ ለዉጥ ነበር፣ ጠቅላላ ሕዝቡ ትኩረት እየሰጡት አልነበረም ፤ በትንሳኤዉ የሱስ ሁሉንም ነገር ቀይሮታል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (7፡ 51-53)፡ እርግጠኞች ለመሆን ሸንጎዎቹ ምንም ነገር አልሳቱም፣ እስጢፋኖስ የተነሳበትን ሀሰብ አደረሰ ፡፡ ይህ ሰዉ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት፣ በመለዓክት ፊት/የመለዓክት ፊት በመምሰል እና ምንም ባለማጣት በአይኑ በመመልከት ሁሉንም ነገር ተሳስታችኋል አላቸው ! በአሁኑ ጊዜ ለኛ ይህ እንዴት ይተገበራል ? እግዚአብሄር ሕዝባችንን ስለ ባረከ የእግዚአብሄርን በረከት እንደ ምንወርስ ማሰብ እንችላለን ፡፡ እኛም የህግ ጣዖቶችን አድርገናል ፤ በእግዚአብሄር ቃል ዙሪያ አለን ነገር ግን አንኖርበትም ፡፡ ልክ ለቤተ መቅደሱ እንደ ሆነው እግዚአብሄር ህዝቡን ወደ ሚያገኝበት ማንኛዉም ስፍራ ከሄድን የተለዬ በረከት እንደ ምንቀበል እናስታዉላለን ፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ግንኙነት ችግር ዉስጥ በሚጥል በብዙ ህፃዉ ላይ እናተኩራለን ፡፡ የእስጢፋኖስ ቃል ለእያንዳንዳችን ነዉ ምክንያቱም ሰይጣን በ 85 ፐርሰንት እዉነት እና ያን በመጠምዘዝ መስራት ስለሚወድ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (7፡ 54-60)፡ ሸንጎዎቹ ቀድመዉ የእስጢፋኖስን ንግግር ላይ አዳምጠዋል ምክንያቱም ስለተስማሙ ነገር ግን ሲቀጥል/በመቀጠሉ እስጢፋኖስ በግልፅ እየኮነናቸዉ ነበር ፡፡ ያለዉን በሰሙ ጊዜ ተበሳጩ ፡፡ እስጢፋኖስ የእግዚአብሄርን ክብርና ኢየሱስን በእግዚአብሄር ቀኝ ቆሞ አየዉ (ቁጥር 56) ፡፡ በመፅኀፍ በሙሉ በሙባል ምሳሌዎች ላይ ኢየሱስ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠ ነዉ ነገር ግን እዚህ ኢየሱስ ከዙፋኑ በመነሳት በሁሉም ኃያላን ሰዎች ፊት ክርስቶስን እንዳከበረዉ ኢየሱስ በማክበር እስጢፋኖስን ሰላም የማለት ምስል ነው ፡፡ ከዚያም የሸንጎ ሰዎች በመጮኽ በእርሱ ላይ ቸኮሉበት/ተጣደፉበት ፤ ከከተማዋም በማሳደድ በድንጋይ ወገሩት ፡፡ እስጢፋኖስ በዚህ ክስተት ኢየሱስን ሞደል በማድረግ በጣም በኢየሱስ ፍቅር ነበር ፤ ለገደሉትም ፀለየላቸው ፡፡
መደምደሚያ
እዚህ የምንማራቸዉ ትምህርቶች አሉ ፡፡ እግዚአብሄር ምቾትን አያቀርብልንም ጥንካሬን እንጂ ፤ ጥሪያችን ለክርስቶስ መታዘዝ ነው ፡፡ በዚህ ህይወት ምቾትእንደምንፈልግ እናስባለን ነገር ግን በሚመጣዉ ህይወት ምቾት ይኖረናል ፡፡ ምንም ነገር በማናጣ ጊዜ በእርሱ በኩል ጥንካሬ ሊኖረን ይችላል ፤ አምላካችን ተስፋ በገባልን ነገር ሁሉ የታመነ ነው ፤ የኛ ስራ ለእርሱ የታመንን መሆን ነው ፡፡ የእስጢፋኖስ ፈተና ምሳሌዎች ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች እንድንሆን እንዴት እንደ ሚያዘጋጁን ራሳችንን መጠየቅ አለብን ፡፡ ሉቃስ የኢየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮ መቀጠሉን እንደምናዉቀው እርግጠኛ መሆኑን አስታዉሉ ምክንያቱም የእስጢፋኖስን ምስክርነት የሰማዉንና በዚያን ጊዜ የካደዉን ጳዉሎስ የሆነዉን ሳዖልን ስላስተዋወቀ ፤ ይሁን እንጂ መለማመድ/መቅመስ ወደ ሳዖል የመጣበት የደማስቆ መንገድ ነበር ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላን ድፍረትና ስልጣን ለመጓዝ ልክ እንደ እስጢፋኖስ የታመንን መሆን ያስፈልገናል ፡፡
ጥያቄዎች
-
በሐዋሪያት ስራ 7 እስጢፋኖስ ብዙ የተለያዩ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች ተናገረ ፤ ያን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ?
-
ሐዋ (7፡ 51-52) አንብቡ ፤ እስጢፋኖስ በተናገራቸዉና ጌታ በተናገራቸዉ መካከል ያሉ ጥቂት አንድነቶች ምን ነበሩ (ዘጸ 32፡ 9) ? እስጢፋኖስ በቁጥር (59-60) የተናገረዉን ኢየሱስ በሉቃ (23፡ 34) ከተናገረዉ ጋር አወዳድሩ ?
-
መፅሀፍት ኢየሱስ በእግዚአብሄር ቀኝ እንደ ተቀመጠ ይናገራሉ (ኤፌ 1፡ 20) ፤ እስጢፋኖስ ለምን ቆሞ እንዳየዉ ምን ታስባላችሁ ? (ሐዋ 7፡ 55-56)
-
በቁጥር 57 የአይሁድ መሪዎች ጆሮቻቸዉን በመሸፈን ለምን እንደ ጮኹ ምን ታስባላችሁ ( ማቴ 26፡ 64-66) ? በሳዖል እግር ስር ለምን ልብሳቸዉን ያስቀምጣሉ ?
-
በሐዋሪያት ስራ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 7:51
“You stiff-necked people with uncircumcised hearts and ears! You are always resisting the Holy Spirit; as your ancestors did, so do you.”
በእምነትና በመንፈስ የተሞላውን እስጢፋኖስን ሊቀ ካህናቱና ሸንጎው ጠየቁት ፡፡ በፊታቸውም ተናገረ ፤ በድፍረትም እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ እንዴት በስራ ላይ እንደነበረ አወሳ ፡፡ እስጢፋኖስ ስለ እግዚአብሔር መገኘትና ኃይል በርስት ፣ በህግ እና በቤተ መቅደስ ላይ ነበር ያተኮረው ፤ ምንም እንኳ ህዝቡ እነዚህን ነገሮች እግዚአብሔር ክብሩን ለማሳየት የተጠቀመባቸው መሳሪያዎች ሳይሆን ጣዖት ቢያደርጋቸውም ፡፡ የእስጢፋኖስም መልዕክት አድማጮቹን አስቆጣ ፤ ወድያውኑም እስጢፋኖስ እስኪሞት በድንጋይ ተወገረ ፡፡ እስጢፋኖስም የመጀመርያው የወንጌል ሰማዕት ሆነ ፡፡
እግዚአብሔር በእስጢፋኖስ ልብ ውስጥ መልዕክትን አስቀመጠ እርሱም ለሸንጎው በግልፅ ተናገረ ፡፡ ከመልዕክቱ ጋር ምን ታደርጋለህ ? እንደ ጣዖት በእርስት ፣ በህግ እና በቤተመቅደስ ላይ በደንብ ታተኩራለህ ? አለም ሊያውክህና አሳብና ልብህን ሊያሳምን ይችላል ፡፡ ሆኖም ግን ክርስቶስ በድካም ጊዜ ብርታትን እንድሁም ደስታን በስደት ጊዜ እንደሚሰጥህ ተስፋን ሰጥቶሃል ፡፡ በታሪክ ወይም በህግ ብቻ ላይ ሳይሆን በኢየሱስ እውነት ላይ ተቀመጥና እረፍ ፡፡ ሁልጊዜ ጸልይ አመስግንም ፡፡ መንፈስ ቅዱስን አትከልክል ይልቁንም በመንፈስና በእውነት ተመላለስ ፤ የክርስቶስን ሙላት ተለማመድ እናም እርሱ ለአንተ ያለውን ሁሉ !
“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ ። “
- ሐዋርያት 7፡51
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ 2:14 — “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም ። “
ኤፌሶን 4:30–31 — “ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ ። መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ ። “
1ኛ ተሰሎንቄ 5:17–21— “ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና ። መንፈስን አታጥፉ ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ ፡፡
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።