Choosing Men to Serve and Stephen Accused of Blasphemy
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እዚህ ላይ የቤተ ክርስቲያንን የጊዜ/የዘመን መዋቅር እናወራለን ፡፡ ወንጌላትን ስናጠና ያልተገለጠዉ ኢየሱስ ነበረን - የእግዚአብሄር መገኘት በሚታይ መልኩ ከእኛ እያለ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለዘላለም ከእነርሱ ጋር እንደ ማይሆን ነገራቸው ፤ በተጨማሪም “ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል “ አላቸው (ዮሐ 16፡ 7) ፤ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ኢየሱስ ይህን ለምን እንዳለ ያሳያል ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 1 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከማረጉ በፊት አስታጠቃቸዉ/አዘዛቸው ፤ በሐዋሪያት ስራ 2 በበዓለ ኃምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ መጣ ሰዎስት ሺህ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 3 ጴጥሮስና ዮሐንስ አንድ ሰዉ በመፈወሳቸዉ ታስረዉ ነበር ፤ በሐዋሪያት ስራ 4 ትልቅ ትምህርት በመስማታቸዉ እና ታምራትን በማየታቸዉ 5000 ሰዎች አመኑ ፡፡ ለሐዋሪያት ስራ መፅኀፍ ቃላችን ስልጣን ነው፣ ስልጣን ድፍረትንና መልካም የሆነ ስራ አመጡ ፤ ወደ ምዕራፍ 6 ስንገባ ወደ ተለያዩ ሁኔታዎች እናገኛለን ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (6፡ 1)፡ አስታዉሉ የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር እየበዛ ሄደ (እየተጨመረ አይደለም) ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሺዎችን እየጨመሩ ነበር ፤ ነገር ግን የግሪክ አማኞች በዕብራዊ አይሁዶች ላይ ቅሬታ አቀረቡ ምክንያቱም በየቀኑ አገልግሎቶቻቸዉ መበለቶቻቸው ችላ የተባሉ ስለሆኑ ፡፡ በዚህ ጊዜ አማኞች ነገሮችን በጋራ በማድረግ እርስ በእርሳቸዉ ተጠባበቁ/እንክብካቤ ይደራረጉ ነበር (ሐዋ 2፡ 44-46) ነገር ግን ግሪኮች መበለቶቻቸዉ ችላ እንደ ተባሉ ተሰማቸው ፡፡ ኪንግ ጀምስ ዕትም “ በየቀኑ ክፍፍል “ የሚለዉ ቦታ ላይ “ በየቀን አገልግሎት “ የሚል ይጠቀማል ፡፡ “ አገልግሎት “ የሚለዉ ቃል የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከሆነዉ ዲያኮን ከሚለዉ የመጣ “ ዲያቆን “ የሚል የግሪክ ቃል ነው ፡፡ በእያንዳንዱ ቀን ሲያገለግሉ ሐዋሪያቱ ሁሉንም ፍላጎቶች ማሟላት ስላልቻሉ እርዳታ አስፈለጋቸው ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (6፡ 2-7)፡ አስራ ሁለቱ (ሐዋሪያቱ) ለእርዳታ “ መላዉ የሀዋሪያት ጓድ “ጠሯቸው ፤ ሐዋሪያቱ ዋናዉን ነገር ይጠብቃሉ ዋናዉ ነገር -የእግዚአብሄር ቃልን መስበክ ላይ ያተኩራሉ ፡፡ ሐዋሪያቱም አማኞቹን የዚህን ተግባር ኃላፊነት ለመዉሰድ/ለመቀበል መንፈስ ቅዱስ የሞላባቸዉና ጥበበኞች የሆኑ የታወቁ ሰባት ሰዎችን እንዲመርጡ አዘዟቸው ፡፡ ይህ ከሆነም ሐዋሪያቱ ለፀሎትና ለስብከት ራሳቸዉን የሰጡ መሆን ይችላሉ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ቅድሚያን ይህን ማድረግ ያስፈልጋታል - ኃላፊነትን በመምራት ያለሟቋረጥ ለፀሎትና ቃሉን ለማገልገል ራሳቸዉን የሰጡ ሰዎች መኖር አለባቸው ፡፡ ይህ ዉሳኔ ሁሉንም ሰዎች አስደሰተ ለዚህ አገልግሎትም ሰዎችን በመምረጥ በሰባቱ ላይ እጃቸዉን ጫኑባቸው ፡፡ ሰባቱን ሰዎች በመዘርዘር እስጢፋኖስን “ እምነትና መንፈስ ቅዱስ እንደ ሞላበት “ ተገለፀ (ቁጥር 5) ፡፡ እነዚህ ሰዎች በመፅኀፍት ደግመን ደግመን የምንጠቀመዉ ቃል የመጀመሪያዎቹ ዲያቆን ነበሩ ፤ በ 1ጢሞቲዎስ 3 ለዲያቆን መመልመያዎችመስፈርቶች ልክ በሐዋሪያት ስራ 6 እንዳሉት የተዘረዘሩ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከመንፈሳዊ ይልቅ በይበልጥ የቤተ ክርስቲያን አካላዉ ፍላጎቶችን አገለገሉ ፤ በዚህ መንገድ አገልግሎቶቹ በቤተ ክርስቲያን እየተሰጡ ቢሆንም እንኳን ፀሎትና ስብከት ችላ አይባሉ ወደፊት ይጓዛሉ ፡፡ ምሳሌአቸው በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የሚያስፈልግ ነገር ሲኖር ፍላጎቶችን ለማሟላት እቅድ ማስቀመጥ ተገቢ እንደሆነ ያሳያል ፤ በቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልግ ነገር ሲኖርያን ለማድረግ እግዚአብሄር ጥበብ፣ ሰዎችና ፋይናንስ ይሰጣል ፡፡ በሐዋ (14፡ 21-23) ቤተ ክርስቲያን ስታድግና ስትሰፋ ፍላጎቶችን ለማሟላት እንዲረዱ ዲያቆኖችን ለመሾም እና በትምህርት እንዲረዱ ሽማግሌዎችን ለመምረጥ ትክክለኛ የሆነ እንቅስቃሴ ነበር ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (6፡ 8-12)፡ እስጢፋኖስ በሕዝቡ መካከል ታላቅ ድንቅ ያደረገ የታላቅ እምነትና ኃይል ሰዉ ነበር ፤ በነበረዉ በሁሉም ነገር እግዚአብሄርን ለመከተል ወስኖ የነበረ ሰዉ ነበር ፡፡ ዛሬም ቤተ ክርስቲያናችን “ እስጢፋኖስ “ ያስፈልጋታል ፡፡ ከኪልቅያና ከእስያ የሆኑ ሰዎች ከእስጢፋኖስ ጋር ተከራከሩ ነገር ግን ጥበቡን እና ይናገርበት የነበረዉን መንፈስ ሊቋቋሙት አልቻሉም ፤ በዚህም ምክንያት እነዚህ ሰዎች በሙሴ እና በእግዚአብሄር ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተነዋል በማለት ሌሎችን አስከተሉበት/አስነሱበት ፤ ከዚያም እስጢፋኖስን ለመያዝ ሰዎችን፣ ፃፎችንና ሽማግሌዎችን በመምራት በሸንጎዎች ፊት ፎከሩበት ፡፡
በቀደመዉ ክፍል እንደ ገለፅ ነው ሰዎች በማስፈራራት ድርጊት በሸንጎ ፊት መጥተዉ ነበር ፡፡ በመካከላችን ያሉ ኃይማኖተኞች በትክክል በመንፈስ ኃይል የሚሰሩትን ማስፈራራት ይፈልጋሉ ፤ ለምን ? ምክንያቱም መቅዳት እንደማይችሉ ስለሚያዉቁ ያስፈራራሉ ፡፡ ዛቻን/ማስፈራራትን ስናይ እና መመልከት ስንችል ልክ እንደ እስጢፋኖስ በእምነት ዕና በኃይል የተሞላን እንሁን ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (6፡ 13-15)፡ ከዚያም በዚህ የተቀደሰ ስፍራ እና ሕግ ላይ እስጢፋኖስ የስድብ ቃል መናገሩን አይተዉም በሚል የከሰሱ ኃሰተኛ ምስክሮችን አቀረቡ ፡፡ የሰዎቹ አንዱ ቡድን እስጢፋኖስን በእምነት፣ በኃይል እንደ ተሞላ ሰዉና የመንፈስ ቅዱስን መልካም ዝና እና ተዓምራትን ማየታቸው ሌላዉ ደግሞ በተመሳሳይ ስፍራ በእግዚአብሄር ላይ የስድብ ቃል እንደ ተናገረና ነገሮችን በቀድሞዉ ነገር እንደሚያደርግ ማየታቸው አያስደንቅም ? ይህ መንፈሳዊ ዉጊያ ነበር ፡፡ መንፈሳዊ ዉጊያ መጠበቅ አለብን ምክንያቱም ከመንፈስ የተወለድን እኛ በጠላታችን እንታወቃለን እንዲሁም ደግሞ በራሳቸዉ መንፈስ ምን እንደሚደረግ እንዴትም የማያዉቁት የሌሎች ክፉ መንፈስ በእኛላይ ይነሳል ፡፡ ይህን በሕዝባችንና በቤተ ክርስቲያናችን እናየዋለን ፤ ሁል ጊዜ ሁከትን የሚያማስሉ ሀሰተኛ ምስክር እና ከሳሽ የሚሆኑ ሰዎች ይኖራሉ ፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ላይ ለማደግ መጠበቅ፣ በፀሎት መጠበቅ እና እንድታፈራ ለቤተ ክርስቲያን መሳሪያዎችን መስጠት አለብን ፡፡
እስጢፋኖስ ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን በማፍረስ ሙሴ ሰጥቷቸዉ የነበረዉን ልምድ አጠፋዋለሁ ብሏል በማለት የከሰሱትን ኃሰተኛ ምስክሮችን አመጡዓቸው ፤ ነገር ግን የሸንጎ አባላት ወደ እርሱ ትኩር ብለዉ ተመለከቱ ፊቱም የመለዓክት ፊት መስሏል አሉ ፡፡
የእስጢፋኖስ በራስ መተማመንና ድፍረት ከእርሱ ከራሱ ዉስጥ አልመጣም ፤ ሙሉ ለሙሉ ተቋጣጥሮት ከነበረዉ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስለመጣ እስጢፋኖስም አልፈራም ፡፡ በምድር ላይ በጣም አደገኛዉ ሰዉ ምንም ነገር ያላጣ ሰዉ ነው፣ ስለዚህም ምንም ነገር ላለማጣት የምንሆን ሰዎች እንድንሆን የተሰየመን ሰዎች ነን - የክርስቶስ ተከታዮች ፡፡ ጳዉሎስ “ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና “ እንዳለዉ ምንም ነገር አናጣም (ፊል 1፡ 21) ፤ ነገር ግን አብዛኞቻችን ይህ ከሰማይ የተሸለ በማድረግ እዚህ ህይወታችንን እንወደዋለን ፤ ነገር ግን ይህ እንደሚሆን የሚል በመፅኀፍት ላይ ምንም የለም ፡፡ በመፅሀፍት በዚህ በምድር ላይ ከህይወታችን የተሸለ ነገርና የሚያስደንቅ በሰማይ እንዳለ የሚናገር ሁሉም ነገር አለ - ከዚህ ከሚሞት አካል ህይወት፣ ከተበላቸዉ ከዚህ ምድር እና በሀሳብ ከሚያስጨንቀ ነፃ መዉጣት የሚሉት ሁሉ አሉ ፡፡ እነዚህ ሰዎች እነዚህን ሁሉ ክሶች በእርሱ ላይ እየተናገሩበትም እንኳን እስጢፋኖስ ፊቱ የመለዓክት ፊት መሰለ ተብሎ ሲገለፅ ሰማያዊ ነፃነት ምን እንደሚመስል አመላካች ሰጠ ፡፡
መደምደሚያ
ተመሳሳይ ሰዎች እንሆናለን ፡፡ ሁሉንም ክሶች አንመልሳቸዉም /መመለስ አይጠበቅብንም ፤ በማን እንዳመን ማወቅ ያስፈልገና እናም እስከ መጨረሻ ሁሉንም መንገድ ስለ እርሱ ስንፈፅም ሊጠብቀን እንደሚችል ማወቅ አለብን ፤ ያ ካለን ምንም አናጣም ፡፡ በዚያ ስፍራ ራሳችንን ማየት ከቻልን በምድር ላይ በጣም አደገኛ ሰዎች እንሆናለን ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 343.
ጥያቄዎች
-
ሐዋ (6፡ 1-4) ዘመናዊዋ/የአሁኗ ቤተ ክርስቲያን እንዴት መሄድ እንደሚገባት ያሳያል ብላችሁ ታስባላችሁ ? እንደ አጠቃላይ ከዚያ ሞደል እርቀናል ? ለምን ወይም ለምን አርቅንም ?
-
ለታማኝ ወንዶች ሪፖርት ቁጥር ሰባት አስፈላጊ ነዉ ብላች ታስባላችሁ ? ቁጥር ሰባት ሌላ የት ላይ አስፈላጊነትን ወክሏል ? (ዘፍ 2፡ 2-3, ዘጸ 12፡ 15, ኢያ 6፡ 4)
-
በተመረጡት ሰባት ሰዎች ላይ ሐዋሪያቱ ለምን እጃቸዉን ጫኑባቸው (ሐዋ 6፡ 6) ? ስለ እጅ መጫን ሌላ የት ላይ አንብበናል ? (ዘኁ 27፡ 18-23, 1ጢሞ 4፡ 14, 2ጢሞ 1፡ 6)
-
በሐዋ (6፡ 8-15) ሐሰተኛ ምስክሮች በእስጢፋኖስ ላይ ተናገሩ ፤ ይህ ሌላ የት ላይ ሆነ በማን ላይስ ሆነ ? (1ነገ 21፡ 8-13፣ ማቴ 26፡ 57-68)
-
በሐዋሪያት ስራ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 6:2–4
“Then the Twelve summoned the whole company of the disciples and said, ‘It would not be right for us to give up preaching about God to handle financial matters. Therefore, brothers, select from among you seven men of good reputation,full of the Spirit and wisdom, whom we can appoint to this duty. But we will devote ourselves to prayer and to the preaching ministry.’”
የአማኞች ቁጥር እየጨመረ በሄደ ጊዜ መበለቶች የቀን ድርሻቸውን አለማግኘታቸውን ሰዎች አወቁ ፡፡ አስራ ሁለቱ ሐዋርያትም እነርሱ በጸሎትና በማስተማር ቢቀጥሉ የተሻለ እንደሆነ ወሰኑ ፡፡ ስለዚህ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች መርጠው በዚህ ጉዳይ ላይ ለመሾም አቀዱ ፡፡ እነዚህንም ሰዎች መረጡ ፤ የእግዚአብሔር ቃል ስብከትም እየሰፋ ሄደ በተጨማሪም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ ጨመረ ፡፡
እግዚአብሔር የክርስቶስን አካል የሰራው አንድ አካል ከብዙ ክፍሎች ጋር እያንዳንዱም ክፍል የተለያየ ተግባር ያለው አድርጎ ነው ፡፡ አንድ ሰው ሁሉንም ነገር ማከናወን የለበትም ፡፡ ሁሉንም ነገር በራስህ ለማድረግ መሞከሩን አቁም ፡፡ በስራዎቹ ላይ አሳብህ እንደተበታተና ካወቅህ ፣ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ጥበብን እንድሰጥህ ጠይቅ ፡፡ ልትተማመንባቸው የምትችላቸውን መልካም ስም ያላቸውን ፣ መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን “ እስጢፋኖሶችን “ በዙሪያህ ፈልግ ፡፡ ከዚያም በመታዘዝ በእምነት እግዚአብሔር የሰጠህን አቅድ ተከተል ፡፡ አዎ ምናልባት ይሄ መቆጣጠርህን መተው ማለት ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ለመተው መታዘዝህ ፣ ሌሎች እንድተጉ ቢያስችልስ ? ልክ ይህ ሲሆን አንተም ለጌታ ታብለጨልጫለህ ፡፡ ይህ የሆነ እምነት ይፈልግ ይሆናል ፤ ነገር ግን እያንዳንዷን የመንገድህን እርምጃ ጌታ አብሮህ እንደሚራመድ ተናግሯል !
“ አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው፦ የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም ። ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን ፤ እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን ። “
- ሐዋርያት ሥራ 6፡2-4
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ 12:4–5 — “ በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን ። “
1ኛ ቆሮንቶስ 7:17 — “ ብቻ ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ከፈለለት እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይመላለስ። እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እደነግጋለሁ ። “
ኤፌሶን 2:10 — “ እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።