Wanting To Look Good Before Others
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሐዋሪያት ስራ መፅሀፍት የመሲሁን ስዕል የሚወክልልን ቃላችን ስልጣን ነው ፡፡ ኢየሱስ ስልጣን ነው፣ በሁሉም ነገር ላይ በኃላፊነት ላይ ነዉ - በትዳራችን፣ በቤተሰባችን፣ በስራችን፣ በአገልግሎታችን እና በፋይናንሳችን ፡፡ በኑሮአችን እንደ ስልጣን ኢየሱስ ለሌሎች ሰዎች በእኛ ላይ ለመወከል ይጠራናል ፤ እንደ አዳኛችን እና እንደ ጌታችን ካወጅን/ከተቀበልን በኋላ ኢየሱስ በኑሮአችን ስራ/ኃላፊነት ከሌለው ግብዞች ነን ፡፡ ዋይርስቤ ግብዝነትን እንደ “ ጭምብል ልብስ “ ወይም “ እንደ ተጫዋች ተዋናይ “ ይገልፃል ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 5 ግብዞች የነበሩ የሁለት ሰዎች ታሪክ ነው ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (5፡ 1-6)፡ ሐናንያ እና ሚስቱ ሰጲራ ንብረታቸዉን የሸጡ አማኞች ነበሩ (ቁጥር 1) ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 4 በርናባስ መሬቱን በመሸጥ የተቀበለዉን ሁሉንም ነገር ለሐዋሪያቱ ሰጠ (ሐዋ 4፡ 36-37) ፡፡ በቁጥር 1 የሚጠበቀዉ ነገር ሐናንያና ሰጲራ ተመሳሳይ ነገር እንደ ሚያደርጉ ነው ፤ ይሁን እንጂ ሐናንያ ሰጲራ እያወቀች ከሸጠዉ በማስቀረት የተረፈዉን ለሐዋሪያቱ ሰጣቸው (ቁጥር 2) ፡፡ ጴጥሮስም ሐናንያን ስለ ሽያጩ እንዲዋሽ ለምን ሐናንያን ሰይጣን ልቡን ሞልቶት እንደ ነበር ጠየቀው ፤ ጴጥሮስም መንፈስ ቅዱስን ዋሽቶ እንደ ነበር አመለከተዉ (ቁጥር 3-4) ፡፡ ሐናንያ በቃሎቹ ወድቆ ሞተ፣ ሁሉም ፈሩ (ቁጥር 5) ፡፡ በዚያ የነበሩ ጎበዞቹም የሐናንያን አካል በመሸፈን ቀበሩት (ቁጥር 6) ፡፡
ጴጥሮስ እንዴት አወቀ ? በመንፈስ ቅዱስ ስልጣን እየተጓዘ ስለ ነበርና የመለየት ስጦታ ተሰጥቶት ስለነበር አወቀዉ፡፡ በግልፅ ሐናንያ የእግዚአብሄር የሆነዉን መደበቅ እንደ ሚችል አሰበ ነገር ግን በሌሎች አማኞች ፊት መልካም ለመሆን ፈለገ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ከሰይጣን አምባገነንነት ነፃ የወጡ የእግዚአብሄር ልጆች ማን እንዲቆጣጠራቸዉ ለመፍቀድ የመምረጥ ችሎታቸዉ አላቸው ፤ ኃጢዓትን ስንመርጥ በሩን ለሰይጣን እንደምንከፍት “ ይናገራል ፡፡ ሐናንያና ሰጲራ በእግዚአብሄር ፊት በዉሸት እንዲፈትናቸዉ ሰይጣንን ፈቀዱለት፣ በደንብ በማድረግም ፈትኗቸዉ የነበረዉን በብዙ ባህሪም ወሰዱት - “ ዉሸታም እና የዉሸት አባት “ (ዮሐ 8፡ 44) ፡፡ ኦሊቨር ወንዴል ሆልሜስ እንዳለዉ “ ኃጢዓት ብዙ መሳሪያ አለው ነገር ግን ዉሸት የሚገጥም መያዣ ነው “ ብሏል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (5፡ 7-11)፡ ከሰዎስት ሰዓት በኋላ ሰጲራ መጣች ምን ተፈጥሮ እንደ ነበርም አላወቀችም (ቁጥር 7) ፤ ጴጥሮስም አንቺና ሐናንያ ለመሬቱ ይህን ያክል ገንዘብ ነበረ የተቀበላችሁት ብሎ ጠየቃት፣ እርሷም አዎ አለችዉ (ቁጥር 8) ፤ ጴጥሮስም “ የእግዚአብሄርን መንፈስ ለመፈተን “ ለምን ከሐናንያ ጋር እንደተስማሙ ጠየቃት ከዚያም ባሏን ቀብረዉት ወደ ነበሩት ሰዎች በማመልከት የእርሷንም አካል ተመሳሳይ ሰዎች እንደሚወስዱት ነገራት (ቁጥር 9) ፡፡ ሰጲራ በመዉደቅ ወዲያዉኑም ሞተች ጎበዛዝቱ ሰዎችም አካሏን በመዉሰድ ከሐናንያ አጠገብ ቀበሯት (ቁጥር 10) ፡፡ በሙሉ በቤተ ክርስቲያን ላይ እና ተፈጥሮ የነበረዉን በሰሙት ላይ ታላቅ ፍራት መጣ (ቁጥር 11) ፡፡
ዋይርስቤ “ በድነት ታሪክ በአዲሱ መጀመሪያ ጊዜ ላይ እግዚአብሄር ኃጢዓትን በሀይለኛዉ እንደ ዳኘ/እንደ ፈረደ “ አመልክቷል ፡፡ የሚያካትቷቸዉ ምሳሌዎች፡
- የድንኳኑ ማደሪያ ከተሰራ በኋላ ናዳብና አብዩድ “ ትክክል ያልሆነ እሳት “ ለማቅረብ ሞከሩ እግዚአብሄርም ገደላቸዉ (ዘሌዋዉያን 10) ፡፡
- ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲመጡ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ባለመጠበቁ አካን እግዚአብሄር ገድሎት ነበር (ኢያሱ 7) ፡፡
በ 1ቆሮ (10፡ 11-12) መሰረት “ ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገስፀን ተፃፈ “ እግዚአብሄርም ይጠቀምበታል ፡፡ በሐዋ (2፡ 42-47) ለቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን ሂደት የተቋቋመችበት፡- ለመማር፣ ለህብረት እና ለፀሎት በየቀኑ በአንድ ላይ መጥተዋል ፤ ሁሉንም ነገር በጋራ ባለቤትነት በመያዝ በጉባኤዉ ላሉ የሚያስፈልጋቸዉን ለመስጠት ያላቸዉን ሁሉ ሸጡ ፤ በቁጥራቸዉም ላይ በየቀኑ ጨመሩ ፡፡ ሐናንያና ሰጲራ የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት ለመሸወድ ሲወስኑ እግዚአብሄር ኃጢዓታቸዉ ሳይቀጣ እንደሄድ ለመፍቀድ አልፈለገም የሚጓዝበትን የጴጥሮስን ስልጣን ተጠቀመ ፡፡ እግዚአብሄር የሆነን ነገር በቦታዉ ሲያስቀምጥ እንዳትነኩ !
ሐዋሪያት ስራ (5፡ 12-16)፡ ሐዋሪያቱ በክርስቶስ ስልጣን ስር በሰለሞን ደጅ ላይ ብዙ ምልክቶችንና ድንቆችን እያደረጉ ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ የቀሩት ቤተ ክርስቲያኖች በዚያ ከእነርሱ ጋር ለመተባበር በጣም ፈሩ ነገር ግን ሕዝቡ በኅይል አከበሩዓቸው (ቁጥር 13) ፡፡ ብዙ ሰዎች ማመናቸዉን ቀጠሉ፣ ለመጀመሪያም ጊዜ ሉቃስ አማኞቹ ሴቶችንም እንዳካተቱ ፃፈ (ቁጥር 14) ፡፡ ጴጥሮስ በሚያልፍበት መንገድ አጠገብ በአንዱ ላይ ጥላዉ ያርፋል ብለዉ ተስፋ በማድረግ በሽተኞችን በአልጋ ላይ አድርጎ ይዘዉ ይመጣሉ (ቁጥር 15) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በቀደመዉ አለም ብዙ ሰዎች የአንድ ሰዉ ጥላ አስማታዊ የመፈወስ ኃይል ሊኖረዉ እንደ ሚችል እንደ ሚያምኑ “ ይናገራል ፡፡ ሌሎች ከኢየሩሳሌም ዙሪያ ከተሞች በሽተኞችንና ክፉ መንፈስ ያደረባቸዉን አመጡ “ ሁሉም ተፈወሱ “ (ቁጥር 16) ፡፡
ጴጥሮስ በክርስቶስ ስልጣን በመጓዙ ክብር አመጣለት ( ዮሐ 14፡ 13-14) ፡፡ ዋይርስቤ ኢየሱስ ምልክቶችንና ድንቆችን የሚያደርግበት ሰዎስት አላማዎች እንደ ነበሩት ይገልፃል፣ እነዚህ አላማዎች የሐዋሪያታዊ ተዓምራቶችንም ያካትታሉ፡- “ 1) ርህራሄ ለማሳየትና የሰዉን ፍላጎት ለማሟላት፣ 2) እንደ እግዚአብሄር ልጅ መረጃዉን/ሹመቱን ለማቅረብ እና 3) መንፈሳዊ እዉነትን ለማሳየት/ለማቅረብ “ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (5፡ 17-21)፡ በቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን እድገት እንዲሁም ምልክት እና ተዓምራት እየሆነ በምላሹ የኃይማኖት መሪዎች በመቅናት ሁሉንም ሐዋሪያቶች በማሰር በወኅኒ ቤት አስቀመጧቸው (ቁጥር 18) ፤ ይሁን እንጂ የእግዚአብሄር መለዓክ የወኅኒዉን በር በመክፈት በምሽት አስወጣቸው (ቁጥር 19) ፡፡ በብሉይ ኪዳን ሁል ጊዜ “ የእግዚአብሄር መለዓክ “ ተጠቅሷል ይህም ቅድመ ክርስቶስን/ክርስቶስ ስጋ ለብሶ ከመገለጡ በፊት አመልክቷል ፤ በመፅሀፍት የዚህ ድጋፍ ባይኖርም ይህ የተነሳዉ ክርስቶስን አመልካች እንደሚሆን ማሰብ አስደናቂ ነው ፡፡ መለዓኩም ወደ ቤተ መቅደስ በመመለስ ስለ ክርስቶስ እንዲሰብኩ ነገራቸው (ቁጥር 20) ፤ በመታዘዝም ምላሽ በመስጠት ሲነጋም ማስተማር ጀመሩ (ቁጥር 21) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (5፡ 21-33)፡ ሐዋሪያቱ በታሰሩ ጊዜ ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሸንጎዉን በመጥራት ከወኅኒ እንዲያመጧቸዉ ወደ ሐዋሪያቱ ላኳቸዉ (ቁጥር 21) ፤ የቤተ መቅደሱ ፖሊሶች/ሎሌዎቹ ወኅኒዉ አሁንም በሚገባ እንደተዘጋና የወኅኒዉ ጠባቂዎችም በደጆቻቸዉ ቆመዉ እንደ ነበር ነገር ግን ወኅኒዉ ባዶ እንደ ሆነ ነገሯቸው (ቁጥር 22-23) ፡፡ የቤተ መቅደሱ ፖሊሶች አዛዥ እና የካህናት አለቆች ግራ ተጋቡ (ቁጥር 24) ፡፡ ከዚያም አንድ ሰዉ መጥቶ ሸንጎዎቹን ሐዋሪያቶ በቤተ መቅደስ እያስተማሩ እንደ ነበር ነገራቸው (ቁጥር 25) ፤ አዛዡና የቤተ መቅደስ ፖሊሶች/ሎሌዎች ሐዋሪያቱን በሸንጎዎቹ ፊት ከኃይል ዉጪ አመጧቸዉ ስለሆነም ሕዝቡ አይወግራቸዉም (ቁጥር 26) ፡፡ በዚያም ሊቀ ካህኑ ሐዋሪያቱን በኢየሱስ ስም እንዳታስተምሩ አዘናችሁ አልነበረምን አላቸዉ ነገር ግን ሐዋሪያቱ በትምህርታችሁ ኢየሩሳሌምን በመሙላት ኢየሱስን በመግደል ሸንጎዎቹን እየከሰሷቸዉ ነበር (ቁጥር 28) ፤ ጴጥሮስም ሐዋሪያት እግዚአብሄርን እንጂ ሰዉን ልንታዘዝ አይገባም አላቸው (ቁጥር 29) ፡፡ በመጨረሻም ሐዋሪያቱ የሐዋ (1፡ 8) አስፈላጊነትን ተረዱ ፡፡ ሐዋሪያቱም እግዚአብሄር ሸንጎዎቹ አስቀምጠዉበት ከነበረዉ መስቀል ኢየሱስን አስነስቶት እንደ ነበርና እንደ ገዢ እና የኃጢዓትን ይቅርታና ንስሃ እንዲያደርግ ከፍ ከፍ እንዳደረገዉ ነገሯቸው (ቁጥር 31-32) ፤ ሐዋሪያቱም የዚህ ሁሉ ምስክሮች ነበሩ አሁን በአማኞቹ ላይ የሚመጣዉ መንፈስ ቅዱስም ምስክር ነበር (ቁጥር 32) ፡፡ ሸንጎዎቹም በጣም ተበሳጩ ሐዋሪያቱንም ሊገድሏቸዉ ፈለጉ (ቁጥር 33) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (5፡ 34-37)፡ የሳዖል/የጳዉሎስ መምህር አንድ ፈሪሳዊ ገማልያል ገን በሁሉም የተከበረ ነበር ፡፡ በሸንጎዎ በመቆምም በሐዋሪያቱ ላይ ስለ ሚያደርጉት ነገር የተጠነቀቁ እንዲሆኑ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 34-35) ፡፡ ገማልያል የተነሱና ብዙዎች የተከተሏቸዉ ነገር ግን በፍጥነት የተበተኑ ሰዎችን ብዙ ምሳሌዎችን ነገራቸው (ቁጥር 36-37) ፤ ሸንጎዎቹን ሐዋሪያቱን ብቻቸዉን እንዲዋቸው ነገራቸዉ ምክንያቱም ሐዋሪያቱ ከእግዚአብሄር ካልነበሩ ስራቸዉ ስለሚጠፋ ፤ ነገር ግን ሐዋሪያቱ ከእግዚአብሄር ከነበሩ እንደማይጠፉና ሸንጎዎቹ ከእግዚአብሄር ጋር ትጣላላችሁ አላቸው (ቁጥር 38-39) ፡፡ ከሸንጎዎቹ አንዳንዶች አመኑ ፤ ሸንጎዎቹም ሐዋሪያትን በመጥራት ገረፏቸዉ፣ በኢየሱስም ስም እንዳያስተምሩ በማዘዝ ለቀቋቸው (ቁጥር 40) ፡፡ ይህ በሐዋሪያት ስራ የተመዘገበ ትክክለኛዉ የአማኞች የመጀመሪያ ስቃይ/ግርፋት ነበር ፡፡ ሐዋሪያቱም “ ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ “ ዋጋቸዉ እንደሆነ ስላገኙት ደስ እያላቸዉ ወጡ (ቁጥር 41) ፡፡ ሐዋሪያቱም ኢየሱስ መሲህ እንደ ነበር በቤተ መቅደስና በቤታቸዉ ማስተማርና ማወጅ ቀጠሉ (ቁጥር 42) ፡፡
መደምደሚያ
በማቴ (5፡ 10-12) ኢየሱስ ተከታዮቹን ስለ እርሱ እንደሚገረፉ፣ እንደሚሰደቡና እንደ ሚጣሉ ነግሯቸዋል ፤ ነገር ግን ይባረካሉም (ፊል 1፡ 29፣ 2ጢሞ 2፡ 12) ! እነ ማናችሁ/ማናችሁ ? በሌሎች ፊት መልካም ለመሆን የፈለጉት ግብዞቹ ሐናንያና ሰጲራ ናችሁ ? ወይስ ማስፈራራቱ፣ዉሸቱን እና የገጠማቸዉን ግርፋት በመተዉ እንደ አዳኝና እንደ ጌታ በድፍረት የኢየሱስን መልካም ዜና በድፈረት መስበክ እንደ ቀጠሉት ጴጥሮስና ሐዋሪያት ናችሁ ?
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Acts (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 421.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Acts (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1374.
Nelsons, p. 1374.
Wiersbe, p. 421.
Nelson’s, p. 1375.
Wiersbe, p. 423.
ጥያቄዎች
-
በሐዋ (4፡ 36-37) በተጠቀሰዉ በርናባስና በሐናንያና ሰጲራ መካከል ልዩነቱ ምን ነበር ?
-
በሐናንያና በሰጲራ ላይ ጴጥሮስ ተናግሯቸዉ የነበሩት ጥቂት ኃጢዓቶች ምን ነበሩ (ሐዋ 5፡ 3, 9) ? ጴጥሮስ የማታለላቸዉ ምንጭ ማን እንደ ነበር ተናገረ/ማን ነዉ አለ (ዮሐ 8፡ 44) ? እግዚአብሄር ከእነዚያ ዉስጥ ምሳሌ ማድረጉ ዉጤቱ ምን ነበር ? (ሐዋ 5፡ 50, 10-11)
-
የቀሩት ሰዎች በስብሰባቸዉ ባያግዟቸዉም ቤተ ክርስቲያን እያደገች የነበረዉ ለምን ነበር ? (ሐዋ 5፡ 13-14)
-
የአይሁድ ሽማግሌዎች በሐዋሪያቱ ላይ ቅናታቸዉ አደገ አስረዉም በወህኒ አስቀመጧቸው ፤ የትኛዉ የኢየሱስ ቃል መፈፀም እየጀመረ ነበር (ዮሐ 15፡ 18-20, 16፡ 2) ? ሐዋሪያቱ ከወኅኒ እንዴት ወጡ ?
-
ሐዋሪያቱ ስለ እምነታቸው ከታሰሩና ከተገረፉ/ከተሰቃዩ በኋላ እምነታቸዉን/አላማቸዉን ቀየሩ (ሐዋ 5፡ 29-32፣ 4፡ 19-20) ? መልዕክታቸዉን ቀየሩ (ሐዋ 3፡ 13-14፣ 4፡ 10) ? አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ለማስደሰት በእግዚአብሄር ላይ ተፈትናችኋል ? በመታዘዛችሁ መንገድ ላይ ስታገኙት ፍላጎታችሁ ይወደዳል ?
-
በሐዋሪያት ስራ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 5:29
“But Peter and the apostles replied, ‘We must obey God rather than men.’”
ሐናንያና ሚስቱ ሰጲራ አንድ መሬት ሸጡ ፡፡ ገንዘቡንም በሐዋርያት ፊት ከማምጣታቸው በፊት በማጭበርበር ግማሹን አስቀሩ ፡፡ ሐዋርያትን ብቻ አልነበረም የዋሹት እግዚአብሔርንም ጭምር እንጅ ፡፡ ስለ ግብዝነታቸውም ሁለቱም ሐናንያም ሰጲራም ወድያውኑ ሞቱ ፡፡ በሌላ በኩል ጴጥሮስና ሐዋርያት በማስተማርና በኢየሱስ ስም ስልጣን በመናገር ጸኑ ፡፡ ሰዎችም በኢየሱስ ስም ሲፈወሱና ሲቀየሩ ያዩ ነበር ፡፡ ምንም እንኳ ስለ ግልጥ እምነታቸው እስራት እና ግርፋት ቢገጥማቸውም ፣ በዚህ ሁሉ እግዚአብሔር አስቀጠላቸው ፡፡ እነርሱም ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን ታዘዙ ፤ በቁርጠኝነት ኖሩ ፡፡ መከራቸው በኢየሱስ ስም ነበርና በመከራቸውም ጭምር ደስ ይሰኙ ነበር ፡፡
እንደ አማኝ ሐናንያና ሰጲራን በማታለልና ከክርስቶስ ሩቅ በሆነ ልብ ትመስላላችሁ ? ወይስ እንደ ጴጥሮስና ሐዋርያት የሚከፈለው ምንም ይሁን ህይወታችሁን ለማጣት ዝግጁ ናችሁ ? በሚስጥር ሰዎችን ደስ ለማሰኘት እየፈለጉ ፤ በሙሉ ልብ ኢየሱስን እየተከተሉ እንደሆነ ማስመሰልን ለማቆም ጊዜው አሁን ነው ፡፡ ለእግዚአብሔር በታማኝነትና በመታዘዝ መኖርን ምረጡ ፡፡ ለእግዚአብሔር ድብቅ የሆነ ምንም ነገር የለም ፤ እርሱ ሁሉን ያውቃል ፡፡ ህይወታችሁን ብታጡ እንኳ ፣ በክርስቶስ ህይወትን ታገኛላችሁ ፡፡ ዛሬ እንዴት መኖርን ትመርጡ ይሆን ?
“ ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል ። “
- ሐዋርያት ሥራ 5፡29
ተጨማሪ ጥቅስ
ማቴዎስ 10:39 — “ ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል ። “
ማርቆስ 7:6 — “ እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች፦ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው ። “
ሉቃስ 6:46 — “ ስለ ምን፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ትሉኛላችሁ፥ የምለውንም አታደርጉም ?
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።