ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አዲስ ህይወት፣ ትምህርት፣ ቀኖኒያል ህብረት እና የሐዋሪያት ስራ 2 የሚያስደስት አምልኮ በሐዋሪያት ስራ 3 ወደ ተካሄደዉ ወደ አለም ለመሄድ አስፈልጓል ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 3 የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ትንሽ ጠብታ ፈዉስ የቀድሞ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ማይቀረዉ ሌላ የእድገት እርምጃ መራ - በሐዋሪያት ስራ 4 የመጀመሪያዉ መስዋዕትነት ገጠማት ፡፡ እንደ ኢየሱስ ንግግር መሰረት ሰማዕትነት የማይቀር ክፍል ነበር (ዮሐ 15፡ 18-20) ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 4 የቀድሞ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ለተቃዉሞ ምላሽ እንደ ሰጠች ነው ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (4፡ 1-4)፡ ጴጥሮስና ዮሐንስ በቤተ መቅደሱ ኮሪደሮች ስር እና አደባባዮች ላይ እያስተማሩ ነበር በምላሹ በደስታና እየዘለለና እየፈነጠዘ የነበረዉ ተፈዉሶ የነበረዉ ሽባዉ ሰዉዬም ነበር (ሐዋሪያት ስራ 3) ፡፡ በካህናቱ፣ በቤተ መቅደሱ ፖሊስ አዛዦች እና በሰዱቃዉያን(ፈሪሳዉያን ግን በዚያ አልነበሩም) ተቃዉሞ ገጥሟቸዉ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ በዚህ ሁኔታ ስለ ነበሩ ሰዎች ስናስብ፡
- ጴጥሮስና ዮሐንስ አሁንም በዚያ ነበሩ ተፈዉሶ የነበረዉ ሽባዉ ሰዉዬም በደስታ እየፈነጠዘም ነበር ፡፡
ካህናቱ በቤተ መቅደስ አመታዊ አገልግሎትን የሚሰጡ ሌዋዊያን ነበሩ ፡፡
የቤተ መቅደሱ ፖሊስ አዛዦች ከካህናት አለቆች ቀጥለዉ የተቀመጡና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ላይ ትዕዛዞችን የመጠበቅ ኃላፊነት ነበረባቸው ፡፡
ሰዱቃዉያን የተማሩ፣ የበለፀጉ እና የክህነት ምሁራኖች እንደ መፅሀፍ አምስቱን የብሉይ ኪዳንን ክፍል የተቀበሉ፣ የመለዓክት መኖርን የካዱ (ሐዋ 23፡ 8) እና ከሞት በኋላ ትንሳኤን የካዱ (ማር 12፡ 18) የኃይማኖት ድርጅት ነበሩ ፡፡ እንዲሁም በምሁራኑ ስር እና በአይሁድ ፖለቲካዊ እና ኃይማኖታዊ ቁጥጥር ስር ለመቀመጥ ከሮማዉያን ጋር የተባበሩ ነበሩ ፡፡ በሐዋሪያት ስራ የቀድሞ ቤተ ክርስቲያን ሰመዓትነት በብዛት በሰዱቃዉያን ነበር ምክንያቱም የቀድሞን ቤተ ክርስቲያን እንደ ፖለቲካዊ መዋቅር ማስፈራሪያ ስለ አዩ ፡፡
ይህ ቡድን ተበሳጭቶ ነበር (ተረብሾ ነበር) ፡፡ “ መበሳጨት “ የሚለዉ ቃል መናደድ፣ መቆጣት ወይም መበሳጨት ማለት ነው ፡፡ የኃይማኖት መሪዎች ጴጥሮስና ዮሐንስ የኢየሱስን ሞትና ትንሳኤ እንደ ራሳቸዉ ምሳሌ በመጠቀም ከሞት ትንሳኤ እንዳለ እያስተማሩና እያወጁ ስለ ነበር ተበሳጩ (ቁጥር 2) ፤ ነገር ግን አድርገዉት የነበረዉን ማጥፋት አልቻሉም ምክንያቱም የሽባዉ ሰዉዬ መፈወስ እና ተከትለዉት የነበረው ስብከታቸው ምስክሮቹን ቀድሞ ተፅዕኖ አድርጎባቸዉ ነበር ፡፡ ጴጥሮስንና ዮሐንስን በማሰር ለህጋዊ ቀጠሮ ዘግይተዉ ስለ ነበር ምሽቱኑ በወህኒ አስቀመጧቸው ፤ የተፈወሰዉም ሰዉዬ በማግስቱ ከጴጥሮስና ከዮሐንስ ጋር ስለ ነበር በእስር ቤት አስቀመጡት ፡፡ ይሁን እንጂ የጴጥሮስንና የዮሀንስን መልዕክት የሰሙ ከአምስት ሺህ በላይ ወንዶች አመኑ (ቁጥር 4) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (4፡ 5-12)፡ በቀጣዩም ቀን የአይሁድ አለቆች አሁንም በስልጣን ላይ ከነበረዉ ከቀድሞዉ ታላቅ ካህን ከሐናም፣ ከሊቀ ካህኑ ከቀያፋ እና ከሐናም ቤተሰብ አባሎች ጋር በኢየሩሳሌም በአንድ ላይ መጡ (ቁጥር 5-6)፡፡ የምሁራን ምክር በሮማዉያን ህግ ጣልቃ ያልተገባበትን ኃይማኖታዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን እንዲቆጣጠሩ በሮማዉያን አስተዳደሮች ተፈቅዶላቸዉ ነበር ፡፡ የ70 የዳኞች አባል በማዕከላዊ ግማሽ ክብ እያንዳንዳቸወ 35 በመሆን ተሰበሰቡ ስለሆነም ጉባኤዉ መድረስ ያለባቸዉ ቦታ ላይ በግልፅ ማትኩር ይችላሉ ፡፡ ሊቀ ካህኑ ታስረዉ በነበሩት ላይ የገሊላዊያንን ጉዳዮች ለመመልከት ማስፈራራትን ለመጠቀም በመፍቀድ በመካከል ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ እና የተፈወሰዉ ሰዉዬ በጥያቄዎች በመታሰር “ በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ ? “ በማለት ጠየቋቸው፣ ጥያቄዉ ንቀትን የሚገልፅ እና ጮሌነት፣ የተማረረ ወጥመድ ነበር ምክንያቱም ከሳሾቹ ከእግዚአብሄር ዉጪ ፈዉሱን ከሌላ ኃይል እንዳደረጉ ጴጥሮስና ዮሐንስ አመለካከት ኖሯቸዉ ካገኙአቸው በሞት ሊቀጡዓቸዉ ይችላሉ (ዘዳ 13፡ 1-5) ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል (ሉቃ 21፡ 14-15) ጴጥሮስ ከሳሾቹ በሰቀሉት እግዚአብሄር ደግሞ ከሞት ባስነሳዉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፈዉሱን አድርገዉ እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 8-10) ፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስ እነርሱ ንቀዉት የነበረ የማዕዘን ድንጋይ እንደ ነበር አሳሰባቸው (ቁጥር 11)፣ በመዝ (118፡ 22) መሰረት ለኃይማኖት መሪዎች ሰበከላቸው ፡፡ ጴጥሮስ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዉጪ ከሌላ ከማንም ሰዉ ድነት እንዳልነበር አወጀ (ቁጥር 12) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (4፡ 13-22)፡ ኃይማኖት መሪዎች በእነዚህ ባልተማሩ ሰዎች ቃል በመደነቅ ጴጥሮስና ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ በማሳየት መፅኀፍን የተጠቀሙበትን መንገድ አስተዋሉ (ቁጥር 13) ፡፡ በአገባቡ “ እነዚህ ያልሰለጠኑ “ ሰዎች የህግ ስልጠናዎች እጥረት እንዳለባቸዉ ለማሳየት ከተማሩ ይልቅ እንዳልተማሩ ይታዩ የነበሩ ናቸው ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ የኃይማኖት መሪዎቹ ለማዉራት ምንም ነገር ማግኘት አልቻሉም (ቁጥር 14) ፡፡ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ እና የተፈወሰዉ ሰዉዬ ከተለቀቁ በኋላ የኃይማኖት መሪዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸዉ ጠየቁ ምክንያቱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ሊካድ የማይችል “ ግልፅ የሆነ ምልክት “ እንዳደረጉ አስተዋሉ (ቁጥር 15-17) ፡፡ መሪዎቹ ፍላጎታቸዉን ለመጠበቅ በመፈለጋቸዉ ጴጥሮስንና ዮሐንስን መልሰዉ በመጥራት “ በኢየሱስ ስም “ እንዳይሰብኩና እንዳያስተምሩ አዘዟቸው (ቁጥር 18) ፡፡ በዚያም ሆነ በሌላ ጊዜ ሁኔታ ኢየሱስ ከሞት እንደ ተነሳ የሐዋሪያትን ማረጋገጫ ዉሸት ለማድረግ ከባድ የሆነ ድርጊት ባለስልጣኖች እንዳልወሰዱ ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስና ዮሐንስ በድፍረትና በኃይል፣ በአንድነት ባለማመቻመች የኢየሱስ ምስክሮች በመሆን ይቀጥላሉ (ቁጥር 19-20) ፡፡ ይህ የቀድሞ ቤተ ክርስቲያን ለተቃዉሞ ምላሽ ትሰጥበት የነበረበት መንገድ ነበር - በአንድነት ! አለቆቹም/አዋቂዎቹ ምንም ነገር ማድረግ አልቻሉም ደቀ መዛሙርቱንም መቅጣት አልቻሉም ምክንያቱም “ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነዉ ነገር እግዚአብሄርን ያከብሩ ነበርና ፡፡ ይህ የመፈወስ ምልክት የተደረገለት ሰዉ ከአርባ ይበልጥ ነበርና “ (ቁጥር 21-22) ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (4፡ 23-31)፡ ጴጥሮስና ዮሐንስ በተለቀቁ ጊዜ ለህዝባቸዉ ለእነርሱ ተደርጎላቸዉ የነበረዉን ነገሯቸው (ምስክርነት ሰጡ)፣ ህዝቡም እግዚአብሄርን በማመስገን የመንፈስ ቅዱስ ስራን እዉቅና ሰጡ (ቁጥር 23-26) ፡፡ በመፀለይ እግዚአብሄርን በሙሉ ድፍረት ቃሉን እንዲናገሩ ችሎታ እንዲሰጣቸው ጠየቁት እግዚአብሄርም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሆኑ ፈዉሶችን፣ ምልክቶችንና ድንቆችን መስጠት/ማድረግ ቀጠለ (ቁጥር 27-30) ፡፡ ከፀሎት በኋላ ስፍራዉ ተንቀጠቀጠ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት በድፍረት ቃሉን መናገር ጀመሩ (ቁጥር 31)፡፡ ድፍረት ከሐዋሪያቶች ምስክርነትና ከቀድሞ ቤተ ክርስቲያን አንፃር አስፈላጊ ሀሳብ ነው (ሐዋ 4፡ 13፣ 29, 9፡ 27፣ 29, 14፡ 3, 18፡ 26, 19፡ 8) ፡፡ “ ፓረሺያሽ “ የሚለዉ የግሪክ ቃል እዚህ ቁጥር 31 ላይ “ ድፍረት “ በመባል ሲተረጎም በሐዋ ( 2፡ 29) “ በነፃነት “ በመባል ተተርጉሟል እንዲሁም ደግሞ በሐዋ (28፡ 31) ላይ “ በሙሉ በራስ መተማመን “ በመባል ተተርጉሟል ፡፡
አማኞች እንዳደረጉት ለምን መለሱ ? መልሱ በሚያስደንቅ ሁኔታ ግልፅ ነው፡ “ ከኢየሱስ ጋር ነበሩ “ (ቁጥር 13) “ በመንፈስ ቅዱስም ተሞልተዉ ነበር “ (ቁጥር 8) ፡፡ በስቅለቱ ዋዜማ ላይ የኢየሱስ አደገኛ/ቁርጠኛ መጠይቅ/ምርመራ በአዋቂዎቹ/በአለቆቹ አባላት ላይ የማይረሳ ዱካ ሰርቶ ነበር ፤ በማስታወሻነት “ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ “ እንዳስተዋሏቸዉ መረዳት እንችላለን ፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣን ታይቶ ነበር፣ ለዉጡም ታይቷል ! አለቆቹ/ህግ አዋቂዎቹ በዚህ ክስተት ላይ ሐዋሪያቱ በዉስጣቸዉ ባለዉ መንፈስ ቅዱስና በክርስቶስ በኩል አሁንም የኢየሱስ ዘማቾች/አገልጋዮች እንደ ነበሩ መረዳት አልቻሉም (ሮሜ 8፡ 8-10) ፡፡ የሕግ አዋቂዎቹ እነርሱን ብቻ ሳይሆን በእነርሱ ዉስጥ እያዩት የነበረዉ ኢየሱስ የጴጥሮስና የዮሐንስ አካል ጌታ ነበር ፤ ያብቻ ሳይሆን ጴጥሮስና ዮሐንስ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ከጌታ ጋር ያላቋረጠ ንግግር/ግንኙነት ላይ ነበሩ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (4፡ 32-37)፡ በቤተ መቅደስ ከሽባዉ ሰዉዬ መፈወስ በኋላ ተከታዮቹ ተከታዮቹ በሀይል ማደግን ቀመሱ/ለመዱ ፡፡ በአንድ ልብ፣ በአንድ ሀሳብ አንድ ነበሩ፣ ንብረታቸዉን በመካፈል ሁሉንም ነገር በጋራ አስቀመጡ (ቁጥር 32) ፡፡ ሐዋሪያቱም በታላቅ ፀጋና ኃይል የኢየሱስን ትንሳዔ ምስክርነት መስጠት ቀጠሉ (ቁጥር 33) ፤ በመካከላቸዉ ድሀ ሰዉ አልነበረም ምክንያቱም ለእያንዳንዱ ሰዉ መሰረታዊ ፍላጎቶች እንዲያሰራጩት ለሐዋሪያቱ ተሰጥቶ ነበር (ቁጥር 35) ፤ ያ ዕድገት ለኢየሱስ ስም ኃይል እና በግላቸዉ ላይ ለነበረዉ ተፅዕኖ በአምልኮ የተሰየመ/የተመለከተ/የተገኘ ነበር ፡፡
በርናባስ የራሱ የሆነዉን መሬት በመሸጥ ገንዘቡን ለሐዋሪያቱ አመጣ (ቁጥር 36-37) ፤ ይህ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች ሙሉ በሆነ መሰጠት መልስ የሰጠው የእግዚአብሄርን ጥሪ የተረዳዉ የሌዋዊዉ የበርናባስ መታወቅ/ትዉዉቅ ነው ፡፡
መደምደሚያ
ለእኛ እነዚህ ሁሉ ምን ማለት ነው ?
በመንፈስ ቅዱስ ስንሞላ ክርስቶስ የኑሮአችን ትኩረት ይሆናል ፡፡
መንፈስ ቅዱስ ራሱን አያስተዋዉቅም /ከፍ አያደርግም ፤ ክርስቶስን ከፍ ያደርጋል/ያስተዋዉቃል ፡፡
በዚያም ከኢየሱስ ጋር ጊዜን በማሳለፍ ከኢየሱስ ጋር እንሆናለን ፡፡
ጥያቄዎች
-
ጴጥሮስና ዮሐንስ በሚናገሩበት ጊዜ ማን ነበር የተቃወማቸው ? በኃይል ለምን ነበር የተረበሹት ?
-
ጴጥሮስና ዮሐንስ የተናገሩት እዉነት አስደናቂ ዉጤት ነበር ?
-
ጴጥሮስን በሐዋ (4፡ 8-12) ከጴጥሮስ በዮሐ (18፡ 13-27) ፤ ልዩነቱ ምንድን ነው ? በዚህ አይነት ድፍረትና በራስ መተማመን መናገር ለምን ነበር የቻለው ?
-
በሐዋ (4፡ 12) ስለ ኢየሱስ የጴጥሮስ ንግግር ምን ነበር ? (ማቴ 1፡ 21፣ ሐዋ 10፡ 43፣ 1ጢሞ 2፡ 5) የመማክርቱ አባላት በጴጥሮስና በዮሐንስ ለምን ነበር የተደነቁት ? ሰዎች እናንተን ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበረ ሰዉ ይለያችኋል ?
-
የሸንጎዎቹ/የመማክርቱ አባላት ጴጥሮስንና ዮሐንስ የሚያደርጉትን እንዲያቆሙ ለምን አስጠነቀቋቸው ? የጴጥሮስና የዮሐንስ ምላሽ ምን ነበር ? ጴጥሮስና ዮሐንስ ወዲያዉኑ እንደ ተፈቱ ምን ተፈጠረ ?
-
በሐዋሪያት ስራ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 4:13
“When they observed the boldness of Peter and John and realized that they were uneducated and untrained men, they were amazed and recognized that they had been with Jesus.”
አለቆች ፣ ሸማግሌዎችና ጻፎች በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ጠየቁአቸው ፡፡ በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ? ብለው ጠየቁአቸው ። ጴጥሮስ በራሱ ብርታት ወይም ብልኃት አልነበረም የመለሰው ፤ ይልቁንም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንጅ ፡፡ የሀይማኖት መሪዎቹም የጴጥሮስን ግልጠኝነት አዩ ፤ ከኢየሱስ ጋርም እንደነበር አወቁ ፡፡ የሚመልሱትም ምንም ነገር አልነበራቸውም ፡፡
በኢየሱስ ላይ ስላለህ እምነት ሰዎች በሚጠይቁህ ጊዜ ምን መመለስ እንዳለብህ ተጨንቀህ ታውቃለህ ? ልትጨነቅ ወይም ልትፈራ አይገባህም ፡፡ በውስጥህ ባለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሌሎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትመሰክር ዘንድ ስልጣን ተሰጥቶሃል ፡፡ እርሱ ያስታጥቅሃል ፤ በድካምህ እንኳ የእርሱ ጸጋ ብርቱ ነው ፡፡ ልክ ሰዎች ሲያዩህ ፣ ከኢየሱስ ጋር እንደነበርክ ያውቁ ይሆን ? ከኢየሱስ ጋር ጊዜን ስታሳልፍ ፣ እግዚአብሔር ህይወትህ እንደሚቀየር ተናግሯል ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ከኢየሱስ ጋር ጊዜን ውሰድ ፣ በተስፋውም እረፍ እናም በውስጥህ ለሚኖረው ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋናን አቅርብ ፡፡ ልክ እንደ ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር ጊዜን ካሳለፍክ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመንገድህ ለሚመጣው ለማንኛውም ነገር ዝግጁ ትሆናለህ ፡፡ በእምነት ተራመድ ለመናገርም አትፍራ ! የሚያስፈልግህንም ቃል እግዚአብሔር ይሰጥሃል ፡፡
“ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው “
- ሐዋርያት ሥራ 4፡13
ተጨማሪ ጥቅስ
ሉቃስ 21:14–15 — “ ስለዚህ እንዴት እንድትመልሱ አስቀድማችሁ እንዳታስቡ በልባችሁ አኑሩት ፤ ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና ። “
ዮሐንስ 15:4 — “ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም ። “
ሐዋርያት ሥራ 4:7–8 — “ እነርሱንም በመካከል አቁመው፦ በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ? ብለው ጠየቁአቸው ። በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።