ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በኢየሱስ ስልጣን ላይ ስንመለከት እና እንዴት በመንፈስ ቅዱስ በኩል ያ ስልጣን እንዳለን እንዴት እንዳወቅን ስንመለከት አስቂኝ ጅማሬ ነው ፡፡ አንዴ የእግዚአብሄር መገኘት፣ የእግዚአብሄር እሳት እና የእግዚአብሄር ጥበቃ እንዳላችሁ ስታስታዉሉ ምንም አላጣችሁም ፡፡ ሄደን ወንጌልን የማናጋራበት ምክንያት የእግዚአብሄርን እሳት ስለረሳን ይመስለኛል ፤ በመንፈስና በእሳት ተጠምቀናል ፡፡ ለሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ አንድ ቃላችን ስልጣን ነው ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 3 የክርስቶስን ስልጣን ተቀብለዉ የነበሩት ሰዎች ቁጠር መጨመሩን ታያላችሁ ፤ ጴጥሮስንና ዮሐንስን በፍጥነት በዚህ ስልጣን ሲጓዙ እናያቸዋለን ፡፡ እግዚአብሄርን ማየት ከፈለጋችሁ ተንቀሳቀሱ፣ ፀልዩ እንዲሁም ደግሞ ፅኑ ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (3፡ 1)፡ ጴጥሮስና ዮሐንስ ለመፀለይ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ ነበር ፡፡ በእነዚህ ቀናት ጊዜ የአይሁድ ሰዎች እንዴት እንደሚፀልዩ መመልከት እፈልጋለሁ ፡፡ በመዝ (55፡ 17) አይሁዶች በቀን ሰዎስት ጊዜ ይፀልያሉ፡ 1) ሰዎስተኛዉ ስዓት ቀን 9ሰዓት ላይ፣ 2) ስድስተኛዉ ስዓት ምሽት 12 ሰዓት ላይ እና 3) ዘጠነኛ ሰዓት ምሽት 3 ሰዓት ላይ ፡፡ ሀሳቡ በኑሮአቸዉ ፀሎትን ማጠንከር ነበር ፤ በስልጣን ስንጓዝ በደንብ የፀሎት ሰዎች እንሆናለን ፡፡ ያለማቋረጥ ከእግዚአብሄር ጋር የተገናኘን መሆን አለብን ፡፡
በጴጥሮስና በዮሐንስ መካከል አለዉ ቅርርብ ላይ ስንመለከት ፤ ጴጥሮስና ዮሐንስ ለትንሽ ጊዜ ጓደኞች ነበሩ፡
- በሉቃ (5፡ 10) ዮሐንስ በአሳ ማጥመድ ስራ ላይ የጴጥሮስ የስራ አጋር ነበር ፡፡ ጸሀፊዉ ሉቃስ ሁለት ፅሁፍ እንደ ፈጠረ እናስታዉሳለን ፤ የሉቃስ ወንጌል የመጀመሪያዉ ፅሁፍ ሲሆን ሐዋሪያት ስራ ደግሞ ሁለተኛዉ ፅሁፍ ነው ፡፡ በመጀመሪያዉ ፅሁፍ ሉቃስ ለአገልግሎት የዮሐንስን ጥሪና የጴጥሮስን ጅማሬ መዝግቧል ፡፡ በሁለተኛዉ ፅሁፍ ዮሐንስና ጴጥሮስ በእምነታቸዉ መጓዝ ጀመሩ ፡፡
- በሉቃ (22፡ 8) ጴጥሮስና ዮሐንስ በጋራ የመጨረሻዉን የፋሲካ እራት አዘጋጁ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከጥሪያችን ግንዛቤ ጋር የማይጣጣሙ ድርጊቶችን ለመዉሰድ (ለማድረግ) እናመነታለን ፤ ጴጥሮስና ዮሐንስ በአገልግሎት የተለያዩ ተግባራትን በማድረግ የሚያስደንቁ ምሳሌ ናቸዉ ምክንያቱም የእግዚአብሄር መንፈስ እንዲያደርጉ ስለመራቸው ፡፡
- በዮሐ (20፡ 3-4) ጴጥሮስና ዮሐንስ በአንድ ላይ ወደ ኢየሱስ ባዶ መቃብር የሮጡ ነበሩ ፤ እንደ ተጠቀሰዉ ወደ መግቢያዉ ዮሐንስ ጴጥሮስን አሸነፈዉ በሁለቱ መካከል ትንሽ ፉክክር ያለ ይመስላል ፡፡ እነዚህ ሁለቱ በሁሉም ነገር አብረዉ ነበሩ ፤ ህይወትን በአንድ ላይ ፈፅመዋል ፡፡
- በሐዋ (8፡ 14) ጴጥሮስ እና ዮሐንስ በሰማሪያ በኢየሱስ ያመኑትን አገለገሉ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (3፡ 2)፡ በሚከተሉት ቁጥሮች ጴጥሮስና ዮሐንስ ኢየሱስ በአካል ሳይኖር አገልግሎትን መስራት ተለማምደዋል ፤ እዚያ ስፍራ እንዴት ደረሱ ? የክርስቶስ ስልጣን ምስክሮች ነበሩ እናም አሁን በእነርሱ ላይ የእግዚአብሄርን እሳት እየተለማመዱት ነበር ፡፡ በጥሪያችሁ ስትጓዙ የእግዚአብሄርን እሳት ትለምዳላችሁ ፤ በጥሪያችሁ ላይ ስትተኙ እሳቱ ይጠፋል ፡፡
ጴጥሮስና ዮሐንስ ከዉልደቱ ጀምሮ ሽባ ወደ ነበር አንድ ሰዉ መጡ ፤ ይህ ሽባ ሰዉዬ መልካም በር በሚባለዉ በቤተ መቅደስ ስፍራ ላይ ሰዎች እንዲሸከሙት በግልፅ አሳማኝ ነበር ፡፡ ፈዉስን አይለምንም ነበር ነገር ግን ገንዘብ ይለምን ነበር ፤ ሁልጊዜ ሰዉየዉ በበጎ አድራጎትነት ይሰጥ ስለ ነበረዉ ገንዘብ ለምፅዋት ይጠይቃል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (3፡ 3-6)፡ ሽባዉም ሰዉዬ ጴጥሮስንና ዮሐንስን በማየት ለእርዳታ ጠየቃቸው ፤ ጴጥሮስ ሰዉየዉን ወደ እርሱና ወደ ዮሐንስ እንዲመለከት አዘዘዉ ፤ ጴጥሮስ የሚሰጡት ብር ወይም ወርቅ እንዳልነበራቸዉ ገለፀለት ነገር ግን ጴጥሮስ “ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳና ተመላለሰ አለው ! “ ጴጥሮስና ዮሐንስ በማቴዎስ፣ በማርቆስ፣ በሉቃስና በዮሐንስ ወንጌል ባዩት ስልጣን እየተጓዙ ነበር ፡፡ ስልጣናቸዉ በክርስቶስ ስም መጣ (ሐዋ 3፡ 16) ፡፡ ይህ ፈዉስበክርስቶስ ስም በኩል በእምነት መጣ (ሐዋ 4፡ 7-10) ፡፡ በኢየሱስ ስም ኃይል አለ ! የኔልሰን ማብራሪያ “ በኢየሱስ ስም የሚለዉ ሀረግ ለፀሎት ማረጋገጫ ወይም መልስ ለመስጠት ጥቅም ላይ የሚዉል የማጅክ ቀመር አይደለም ፤ በኢየሱስ ስም በሚለዉ ላይ ያለዉ ኃይል መንፈስ ቅዱስ ከሚያደርገዉ ይመጣል በዚያ ስም ምክንያት “ እንደሆነ ይናገራል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (3፡ 7)፡ ይህ ሽባ ሰዉዬ ተወልዶበት የነበረዉ ክስተት ሌሎች ሰዎች እንዲሸከሙት አድረጎት ነበር ፡፡ ጴጥሮስም በቀላሉ እጁን በመያዝ ሰዉዬዉን እንዲነሳና እንዲቀሳቀስ ረዳው ፡፡
ከትምህርት ቀጥዬ በመሄድ ወደ መዘጋጀት እቀሳቀሳለሁ ፡፡ ለፈዉስ ወንጌልን ለማጋራትና ለመፀለይ የሚወጡ ሰዎች በግል አስተያየቴ መጥፎ ዕድል ነው ፡፡ ሁላችንም ሰዎች በኢየሱስ ስም ለፈዉስ ሲፀልዩ እና ከዚያም ይህ ሰዉ ለምን ፈዉስ አስፈለገዉ እንዴት የተፈወሱ መሆን አስፈለጋቸዉ የሚለዉ ወገን ሲይዙ አይተናል ፡፡ ጴጥሮስ ፈዉስ እንዲከናወን ስለ አደረገዉ ነገር ምንም አልተናገረም፣ ሰዉዬዉን ተነስቶ እንዲሄድ ብቻ ነገረው ፡፡ የክርስቶስ ስም ቀለል ማለት በቂ ነው ፤ ስልጣን አለን - ስለዚህ ግልፅ እንደሆነ አጥብቀን እንያዝ ፡፡ ስለ ሐዋሪያት ስራ መፅኀፍ በማንበብ እንዴት በአሁኑ ጊዜ እንደ ምንተገብር ስናስብ በጣም መጥፎዎች የነበረነዉ ለዚያ ነው ፡፡ የክርስቶስ ስም በቂ ሲሆን ይህን ሁሉ ተግባርና እርምጃ መጨመር እንፈልጋለን ፤ ቀላል/ነፃ በመሆን በስልጣን ተጓዙ ፡፡ ባለመጥፎ እድል ሆኛለሁ ? በትክክል ፤ ሁሉንም የተለያዩ ዘዴዎች ሞክሬአለሁ ? አዎ ፡፡ ማለት የምችለዉ ሁሉም እስካሁን ካልተሰራ ነገሮችን በእምነት መጓዝን መሞከር ቀጥሉ ፡፡
ዋይርስቤ “ በዚህ ሰዉ ላይ ድነት ምን እንደ ሚመስል ለማሳየት ቀላል ነው ፤ ሽባ ሆነ ተወለደ፣ ሁላችንም እግዚአብሄርን በማመስገን መጓዝ የማይችል ሆነን ተወለድን፤ አባታችን አዳም ዉድቀት ስለ ነበረው ወደ ሁሉም ዘሮቹ ሽባነቱን አስተላለፈ (ሮሜ 5፡ 12-21) ፡፡ እንዲሁም ሰዉዬዉ ድሀ ነበር፣ በእግዚአብሄር ፊት እንደ ኃጢዓተኛ በራሳችን ላይ ያለብንን ብዙ እዳችንን መክፈል የማንችል የከሰርን ነን (ሉቃ 7፡ 36-50) ፡፡ ከቤተ መቅደስ ዉጪ ነበር፣ ለበሩ የቀረቡ ቢሆኑም ችግር የለዉም ሁሉም ኃጢዓተኞች ከእግዚአብሄር የተለዩ ናቸው ፡፡ ሰዉዬዉ በእግዚአብሄር ፀጋ በጠቅላላ ተፈወሰ፣ ፈዉሱም ወዲያዉኑ ነበር (ኤፌ 2፡ 8-9) “ ፅፏል ፡፡ ይህን ታሪክ ብዙ ጊዜ አንብቤዋለሁ እዚህ ላይ ያለዉን የድነት ስዕልን አላየሁም ፡፡ በእዉነት የሚያስደንቅ እንደ ሆነ አስባለሁ ፤ ወዲያዉኑ ይህ ሰዉ ተፈወሰ ፡፡ የተጓዘበት ምንም ነገር አልነበረም ፤ ጸጋን ለማግኘት ማድረግ የምችለወ ነገር ምንም የለም ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (3፡ 8)፡ ሰዉዬዉ ከተፈወሰ በኋላ ዘለለ መሄድም ጀመረ ፡፡ ሰዉዬው እየዘለለ፣ እየፈነጠዘ እና እየተንቀሳቀሰ ነበር ፤ አዲስ ህይወት ነበረው ! አዲስ ማንነት ሲኖራችሁ፣ አሁንምልክ ሽባ እንደ ነበረዉ ሰዉዬ ትተገብራላችሁ ወይስ ህይወት እንዳላችሁ ትኖራላችሁ - በመፈንጠዝ እና በዝላይ ? እግዚአብሄር በእነዚህ አዲስ ማንነቶች እንድንጓዝ ይፈልጋል በዚህም ክብር ያገኛል ፡፡ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ በክርስቶስ ስልጣን እንደ ነበራቸዉ በማመን ተግባር ላይ አዋሉት ፡፡ በእምነት መጓዝ አለብን ፡፡ በእምነታችን ለመኖር ራሳችንን ስናሰለጥን አኗኗራችንን ለመዉደድ እንማራለን ፡፡ በጊዜዉና ከጊዜዉ ዉጪ ምስክሮች ለመሆን ተጠርተናል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (3፡ 9-11)፡ ሰዉዬዉ እየዘለለና እግዚአብሄርን እያመሰገነ ነበር ይህን ሲሆን ያዩት ሰዎች በመደነቅ ተሞሉ ፡፡ ይህ ታሪክ ጴጥሮስና ዮሐንስ ስልጣናቸዉን ባይዙና በተሰጡት እሳት ባይጓዙበት አይሆንም ነበር ፡፡ ድርጊታቸው መላዉን ማህበረሰብ ቀየረው ፤ ይህ ሰዉ ቀድሞ ሽባ የነበረው በጴጥሮስና በዮሐንስ ላይ የተያዘ ነበር፣ ሰዎችም ወደ እነርሱ እየሮጡ ነበር ፡፡ ለምን ወደ እነርሱ ሮጡ ? ምክንያቱም እግዚአብሄር ስለ ተገለጠባቸው !
ሐዋሪያት ስራ (3፡ 12-21)፡ ጴጥሮስ እነዚህን ሰዎች አያቸዉና “ ለምን ትደነቃላችሁ ? “ በማለት ጠየቃቸው ፤ ጴጥሮስና ዮሐንስ ይህን ተዓምራታዊ ነገር ማድረግ የቻሉበት ብቸኛዉ መንገድ ኢየሱስ ነው ፡፡ ጴጥሮስ እያንዳንዱን ነገር መልሶ ከብሉይ ኪዳን ጋር አስተሳሰረው ፡፡ በሌላ አነጋገር/ቋንቋ “ እንዲሰቀል አሳልፋችሁ በሰጣችሁት በኢየሱስ በፊት እነዚህ ሁሉ ነገሮች እንዳሉ አይታችኋል “ ማለት ነው ፤ ፃድቁንና ቅዱሱን ክደዉ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ “ የህይወትን ምንጭ ከደላችሁት….ለዚያ ደግሞ ምስክሮች ነን አለ ! “ የጴጥሮስ በክርስቶስ በኩል ባለዉ ስልጣን በራስ መተማመን ከፍራት ወይም ከስጋት ዉጪ ከባዱን እዉነት ለመናገር ፈቀደለት ፡፡ የኢየሱስ ስም ለዚህ ሽባ ሰዉ ፍፁም ጤንነት የመስጠት ስልጣን ተሰጥቶት ነበር ፤ በአይሁዶች በእነዚህ በቀድሞዉ ድርጊት ምክንያት ጴጥሮስ ሕዝቡን ንስሀ በመግባት ወደ ኢየሱስ እንዲመለሱ ጠራቸው ፡፡
መደምደሚያ
ጴጥሮስ ይህን ቸጋጣሚ በጥንካሬ ጨረሰ ፡፡ በስልጣን ስትጓዙ፣ በክርስቶስ ስም ስትጓዙ ሁሉም ነገር ሊሆን ይችላል እንዲሁም ሁሉም ነገር ቀላል ነው ፡፡ ሁል ጊዜ በፀሎት ላይ በመመስረት በስልጣን መጓዝ እንድትጀምሩ አበረታታችኋለሁ ፡፡ በመፀለይ መፅናት ፤ በዚያ ነዉ እግዚአብሄር እንዴት በህይወታችሁ እንደሚጓዝ ታያላችሁ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Acts (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1372
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: Acts (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 412.
ጥያቄዎች
-
ሐዋ (3፡ 2-8) ስታነቡ ኢየሱስ ህይወታችሁ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ለማድረግ እንደሚፈልግ ታስባላችሁ ? ስለዚህ ሰዉዬ እምነት ይህ ፅሁፍ ምን ይላል ? እምነት በማጣታችን ምክንያት ኢየሱስ በእኛ ላይ ማፍሰስ የፈለገዉን በረከት በመተዉ በህይወታችን ዉስጥ ላነሰ ነገር እንዴት እንረጋጋለን/እንቀመጣለን ?
-
አስደናቂ ነገሮች ሲሆኑ በማየታችሁ ብቻ ወደ ኢየሱስ ሮጣችሁ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ጌታን ካገኛችሁት በኋላ ስለ እርሱ በይበልጥ ለማወቅ እንዴት ትፈልጉታላችሁ ? በህይወት ዉሃ ወንዝ እና በመልካም ነገሮች ታመሰግኑታላችሁ ?
-
ለሽባዉ ለማኝ እንዳደረገዉ በተመሳሳይ መንገድ ባልተጠበቀ ወይም ተዓምራታዊ በሆነ መንገድ ሲመጣላችሁ የኢየሱስን ምስጋና እንዴት ታሳያላችሁ/ትገልጣላችሁ ?
-
ጴጥሮስ በሐዋ ( 3፡ 21) “ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለዉ ዘንድ ይገባልና “ ባለ ጊዜ ምን እየጠቀሰ ነበር ? (ማቴ 17፡ 11-12፣ ማር 9፡ 11-13፣ 2ጴጥ 3፡ 3-13፣ ራዕ 22፡ 6-7፣ 12-15) ዛሬ ተመልሶ ቢመጣ በኢየሱስ ፊት ለመቆም ዝግጁ ነን ብላችሁ ታምናላችሁ ?
-
በሐዋ (3፡ 22-25) ጴጥሮስ በቀድሞዉ ጊዜ እግዚአብሄር ስለ ጌታ መምጣት ትንቢት የሚናገሩ ሰዎችን እንደ ላከ ተናገረ ፤ የተጠቀመባቸዉ ጥቂት ሰዎች እነ ማን ነበሩ ይህንንስ በመፅኀፍ ቅዱስ ላይ የት ታገኙታላችሁ ? (ዘዳ 18፡ 15-19፣ ዕብ 1፡ 1-2፣ ሐዋ 7፡ 37፣ ሉቃ 24፡ 19)
-
በሐዋሪያት ስራ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 3:6
“But Peter said, ‘I don’t have silver or gold, but what I have, I give you: In the name of Jesus Christ the Nazarene, get up and walk!’”
ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ እየወጡ ሳለ አንድ አንካሳ ሰው አዩ ፡፡ እነርሱም ለሰውየው ብርና ውርቅ አልሰጡትም ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተናገሩት እንድህም አሉት ፡- “ ተነስና ተመላለስ ! “ ፡፡ ወድያውኑም ቀኝ እጁን ይዘው ባነሱት ጊዜ እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና ! ዘሎም ቆመ ፣ ይመላለስም ጀመር እየዘለለም እግዚአብሔርን እመሰገነ ! ልክ ሌሎችም ይህን ታምራዊ ፈውስ ባዩ ጊዜ ፤ ጴጥሮስ ክብርን ሁሉ ለኢየሱስ እንድሰጡ ተናገራቸው ፡፡ አንካሳው ሰው መሄድ የቻለው በኢየሱስ ስም ላይ ባለ እምነት ነው ፡፡
በኢየሱስ እምነት ካላችሁ ፣ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው ያ ኃይል በእናንተም ውስጥ አለ ፡፡ ስለዚህም በኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣን መራመድ ትችላላለህ ፡፡ በስሙ ውስጥ ኃይል አለ ፡፡ ኢየሱስ በስሙ የምትለምኑት ማንኛውም ነገር እንደሚሰጣችሁ ተናግሯል ፡፡ ስትጸልዩ እግዚአብሔር ኃይሉን የምትጠቀሙበትን እድል ይሰጣችኋል ፡፡ በኢየሱስ ስልጣን መራመድ የማይታሰብ ወይም ከባድ መሆን የለበትም ፡፡ ቀለል አድርገውና በእምነት እንድህ በል “ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስና ተመላለስ “ ፡፡ ክብር ሁሉም ለአንተ ሳይሆን ፣ ለኢየሱስ ስም ይሁን ፡፡ የተሰጠህን የኢየሱስ ስልጣን ምን እያደረክበት ነው ? መጠቀምህን ጀምር የሆነ ነገርም ይሆናል ፡፡
“ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው ። “
- ሐዋርያት ሥራ 3፡6
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ 14:13 — “ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ ። “
ሐዋርያት ሥራ 3:16 — “ በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፥ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው ። “
ፊልጵስዩስ 2:9–11 — “ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው ፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።