Acts Acts

Pentecost and the Holy Spirit

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 338 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በትናትናዉ በሐዋሪያት ስራ 1 ጥናታችን ሐዋሪያት ስራ በጠቅላላ ስለምን እንደ ሆነ እንድናወራ በሩ ተከፍቷል ፡፡ በሪቫይቭ ት/ቤት ሁሉም የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ወደ ኢየሱስ እንዴት እንደሚያመለክቱ መረዳታችሁን እያሰፋን ነው ፡፡ ሐዋሪያት ስራ 2 በተለያዩ ብዙ መንገዶች ሊተረጎም ይችላል ነገር ግን ዛሬ መፅሀፍት ምን እንደሚል እናተኩራለን ፡፡

ትምህርት

ሐዋሪያት ስራ (2፡ 1)፡ “ በዓለ ኃምሳ የተባለዉ ቀን ደረሰ “ ፤ በዓለ ኃምሳ ቀን አሁን ጥቂት ሺህ አመታቶች አካባቢ ሆኖታል ፡፡ አብዛኞቻችን ከበዓለ ኃምሳ ቀን ጋር በምንም ነገር አንዛመድም ነገር ግን ስለዚህ ቀን ማመሳሰልን መስራት እፈልጋለሁ ፡፡ ዘሌዋዉያን 23 የበዓለ ኃምሳ ቀን ሀሳብን ይዟል ነገር ግን በዓለ ኃምሳ ቀን አል ነበረም ፡፡ በአዲስ ኪዳን በቀላሉ በተለየ የተሰየሙ ነገሮች በብሉይ ኪዳን ነበሩ ምክንያቱም የብሉይ ኪዳን ዕብራዊ እና አረማይክ ፅሁፍ ወደ ግሪክ ስለ ተተረጎመ ፡፡ በዓለ ኃምሳ ቀን ማለት 50 ቀን ማለት ነው ፡፡ በዘሌዋዉያን 23 በዓለ ኃምሳ የማይባል ቀን -አንድ ድግስ ነበር ፤ የበኩራት ወይ የመጀመሪያ መከር መሰብሰቢያ ድግስ ነበር ፡፡ ፍሬዎችንና አትክልትን ስታሳድጉ የበኩራት ፍሬንና ሁሉንም ምርት ሁለቱንም ዕዉቅና መስጠት በጣም አስፈላጊ ለምን ይሆናል ? እስራኤላዊያን በኩራታቸዉን በመሰብሰብ ሰንበት ካለፈ በኋላ በመጀመሪያዉ ቀን ለካህናቱ ወሰዱላቸዉ ካህናቱም የበኩራት ፍሬዉን በእግዚአብሄር ፊት ወዘወዙት ፤ ከዚያም በ50 ቀን ለመምጣት ሰባት ሰንበቶችን ወይም ሙሉ ሰባት ሳምንታትን ሲደመር አንድ ቀን ቆጠሩ ፡፡

በሐዋሪያት ስራ (2፡ 1) “ የበዓለ ኃምሳ ቀን በመጣ ጊዜ “(ኪንግ ጀምስ ዕትም) የሚለዉ ሀረግ ሙሉ መከር መጥቶ ነበር ወይም የድግሱ መጨረሻ ማለት ነው ፤ ስለዚህ 50 ቀን አልፎ ነበር ፡፡ ከበዓለ ኃምሳ 50 ቀን በፊት መን ተፈጥሮ ነበር ? የኢየሱስ ትንሳኤ ፡፡ ያ ለምን ነበር ያስፈለገዉ ? በዚህ ድግስ በመጀመሪያዉ ቀን ላይ ካህናቱ የበኩራት ፍሬ የመወዝወዝ መስዋዕት አደረጉ ፤ እዚህ ከሞት ህያዉ የሆነ፣ በሞት ፊት የተወዘወዘዉ እና የመከር መጀመሪያዉ መጥቷል የሚለዉ ኢየሱስ አለ ፡፡ ይህ የበዓለ ኃምሳ ቀን ድግስ ስለ ሚባለዉ በጠቅላላ ነው ፤ ስለዚህም ከትንሳኤ ሀምሳ ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በአንድ ላይ በሰገነቱ ላይ ነበሩ ፤ ይህ የመሰብሰብ ሙሉ በዓል የሚከበርበት ቀን ነው፣ እንዲሁም በተጨማሪ ቤተ ክርስቲያን የተወለደችበት ቀን በመባል ይጠራል ፡፡

በሐዋ (1፡ 4) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አባቱ ተስፋ የገባላቸዉን በኢየሩሳሌም እንዲጠብቁ የነገራቸዉን አስታዉሱ ፡፡ ሁል ጊዜ የእግዚአብሄር እቅድ አሁን እግዚአብሄር እየሰራ በነበረው ላይ በማተኮር ወደ ኋላ ሳይሆን ወደ ፊት መመልከት ነበር ፡፡ በዮሐ (14፡ 15-17) ኢየሱስ አብን ለደቀ መዛሙርቱ በእነርሱ ዉስጥ እና ከእነርሱ ጋር የሚኖረዉን ሌላ መካሪ የሆነዉን የእዉነት መንፈስ እንዲሰጣቸዉ እጠይቅላችኋለሁ አላቸው ፡፡ በሉቃ (24፡ 49) ኢየሱስ ከላይ ኃይል ለማልበሰ ለደ ቀመዛሙርቱ አብ ተስፋ የገባዉን እልክላችኋለሁ አላቸዉ ፤ ሰዎስት ጊዜ በአብ ተስፋ ተገብቶ ነበር ፤ ይህ የኢየሱስ ሀሳብ ወይም በአንድ ቀን ያደረገዉ የሆነ ነገር አልነበረም ፤ ይህ የእግዚአብሄር እቅድ አካል ነበር ፡፡ በዘሌዋዉያን የመኸር በዓል በአዲስ ኪዳን ወደ በዓለ ኃምሳ ቀን አመልክቷል ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (2፡ 2)፡ በዚህ ጊዜ 120 አካባቢ የሚሆኑ ሰዎች በአንድ ላይ ተሰብስበዉ ነበር ፤ ይህ ኃይለኛ ንፋስ ልክ እንደ ኃይለኛ ንፋስ ወይም አዉሬ ንፋስ ድምፅ የሆነ ነዉ ፡፡ ንፋሱ ሲሄድ(ሲንቀሳቀስ) የሚሰሙት ኃይለኛ ድምፅ አለው ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (2፡ 3-4)፡ በሐዋሪያት ስራ መፅሀፍት ለኢየሱስ ቃላችን ስልጣን ነዉ ምክንያቱም ስልጣን የተሰጠዉ እሱ ብቻ ስለሆነ በንሄድበት በማንኛዉም ስፍራ ምስክሮቹ መሆን እንችላለን ፡፡ የሜንዴ ስዕል ለዚህ መፅሀፍት ገፅታዎች የተከፋፈሉ ልላባዎች ናቸው ፤ ላባዎች የእግዚአብሄርን መገኘት ሲወክል እሳት ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ይወክላል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ስንጓዝ ከእያንዳንዳችን ጋር የሚሄድ ኃይለኛ መገኘት አለን ፡፡

ቁጥር 3 በአንድ ላይ ተሰብስበዉ በነበሩት በእያንዳንዳቸዉ ላይ “ ምላስ የሚመስሉ የእሳት ልሳኖች “ ተቀመጡባቸዉ ይላል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ መንፈስም እንደ ሰጣቸዉ ችሎታ በምላሶቻቸዉ ቋንቋዎችን መናገር ጀመሩ ፡፡ በመፅሀፍት እሳት በሆነ ሰዉ ላይ መቼ እንደ ሆነ ታስባላችሁ ? የእስራኤል ልጆች በምድረበዳ ሲንከራተቱ ቀን በደመና አምድ እና ማታ በእሳት አምድ ተመሩ ፤ በዚያን ጊዜ እሳት የሰዎችን ቡድን መራ ፤ አሁን በአዲስ ኪዳን ላይ በእምነታቸዉ እንዲጓዙ ስልጣን ለመስጠት በእያንዳንዳቸዉ በግል መንፈስ ሰራባቸው ፡፡ ኢሳ (28፡ 11) “ በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል “ ይላል ፤ ኢሳያስ በዓለ ኃምሳ ቀንን ተንብዩአል ፡፡ በማቴ (3፡ 11) መጥምቁ ዮሐንስ እኔ በዉሃ አጠምቃችኋለሁ ነገር ግን ከእርሱ በኋላ የሚመጣዉ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል አላቸው ፡፡ በማር (16፡ 17) ተከታዮቹን ወደ አለም በመሄድ ወንጌልን እንዲሰብኩ ካዘዛቸዉ በኋላ ኢየሱስ የሚያምኑትን የሚከተሏቸዉን ምልክቶች ገለፀ፡- አጋንንትና ያስወጣሉ፣ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፣ እባቦችን ይይዛሉ፣ የሚገድል ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸዉም እንዲሁም እጃቸዉን በድዉዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (2፡ 5-13)፡ ለበዓለ ኃምሳ ቀን አይሁዶች ከማንኛዉም ሀገር ወደ ኢየሩሳሌም ይሰበሰቡ ነበር ፤ እግዚአብሄር ወደ ኢየሩሳሌም አምጥቷቸዉ ስለ ነበር በእግዚአብሄር ኃይል የሆነዉን ተዓምራት ያያሉ ፡፡ በተሰበሰበዉ ዉስጥ የነበሩት ሰዎች ደቀ መዛሙርቶቹ በቋንቋቸዉ ሲናገሩ ሰሙ “ እንዴት ሊሆን ይችልል ? “ በማለትም ተደነቁም ተገረሙም ፤ የእግዚአብሄር መንፈስ ከደቀ መዛሙርቱ የወንጌልን መልዕክት በራሳቸዉ ቋንቋ መስማት እንዲችሉ አደረገ ፤ አንዳንዶች ሲደነቁ ሌሎች ደግሞ በደቀ መዛሙርቱ በመቀለድ በወይን ተሞልተዉ ነዉ አሏቸው ፡፡

ሐዋሪያት ስራ (2፡ 14-21)፡ ጴጥሮስ በመንፈስ ተሞልቶ በመቆም ለቃሉ ትኩረት እንዲሰጡት የይሁዳንና የኢየሩሳሌም ሰዎችን ተጣራ ፤ ጴጥሮስ እነዚህ ክስተቶች በነቢዩ ኢዩኤል ተነግረዉ ነበር አለ ፡፡ በቁጥር (17-21) የጴጥሮስ መልዕክት ከኢዩ (2፡ 28-32) የተወሰደ ነበር ፡፡ በዮሐ (20፡ 22) ከሞት በተነሳበት ቀን ላይ ኢየሱስ ከ 11 ደቀ መዛሙርቱ ጋር በመገናኘት “ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ “ በማለት እፍ አለባቸው ፡፡ በሉቃስ መግለጫ ኢየሱስ “ መጻሕፍትን ያስተዉሉ ዘንድ አይምሮአቸዉን ከፈተላቸው “ (ሉቃ 24፡ 45) ፤ መንፈስ ቅዱስ መጻሕፍትን እንድንረዳ የሚረዳን መለኮታዊ ተርጓሚ ነው ፡፡ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ እንደሚመጣባቸዉ ተስፋ ሰጥቷቸዉ ነበር (ሐዋ 1፡ 8) ፤ በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ለአገልግሎት ለሆነ ጊዜ ለማዘጋጀት በሰዎች ላይ መጥቷል ፡፡ መንፈስ በንጉስ ሳዖል ላይ በመጣ ጊዜ የተለዬ ሰዉ ነበር ፤ መንፈስ በሳምሶን ላይ በመጣ ጊዜ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ጥንካሬ ነበረው ፡፡ መንፈስ በመጣብን ጊዜ ምስክሮቹ የመሆን ችሎታ አለን ምክንያቱም የክርስቶስ ስልጣን ለግላችን ተሰጥቶናል ፤ ለዚያ ነዉ ይህ ሁሉ የሚሆነው ፡፡ ኢየሱስ ሙሉ ምርት ይፈልጋል ፤ እንደ እርሱ መከር ሰብሳቢዎች ወደ እርሻ ስፍራ በመሄድ የመከር ሰራተኞች እንድንሆን ችሎታ የሰጠን በኩር ነበር ፤ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የታጠቅነዉ ለዚያ ነው ፡፡

በቁጥር (19-21) ጴጥሮስ ከበዓለ ኃምሳ ቀን ወደ ስለዚህ ምድር የፍጻሜ ቀን ተንቀሳቀሰ ፡፡

መደምደሚያ

ኢየሱስ የሚገባዉን ምን ላድርግ ? የአብ ተስፋ ምን ነበር ? የእግዚአብሄር እቅድ ምን ነበር ? ወደዚህ ዉስጥ እንዴት እዋሀዳለሁ ? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ለራሳችን ለመመልከትና ለማጥናት የሚያስቸግሩ በዚህ ፁሁፍ ብዙ ናቸው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), pp. 325–326.

  2. Wiersbe, pp. 325–326.

ጥያቄዎች

  1. በበዓለ ኃምሳ ቀን ጊዜ ራሳችሁን በክፍሉ ዉስጥ አድርጋችሁ አስቡት ፤ ምን ታስባላችሁ ምንስ ይሰማችኋል ? አንዳንድ ሰዎች በመንፈስ ተሞልተዉ የነበሩትን ለምን እንደ ሰክረዋል ብለዉ እንዳሰቧቸዉ ምን ታስባላችሁ ? ሊገለፅ የማይችል ወይም ተዓምራታዊ ነገር ሲሆን እንዴት አድርገን ተመሳሳይ ነገር እናደርጋለን ?
  2. እግዚአብሄር በበዓለ ኃምሳ ቀን የተፈጠረዉን እና አሁን በምንኖርበት ጊዜ የሚሆነዉን ቀድሞ ለመናገር ነቢዩ ኢዩኤልን ተጠቀመ (ሐዋ 2፡ 17-21) ፡፡ በአሁኑ ጊዜም ነቢያት አሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? በዚህ ፅሁፍ ተተንብዮ የነበረዉ ሁሉም ነገር ሆኗል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  3. በሐዋ (2፡ 23) ጴጥሮስ “ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት “ ሲል ምን ማለቱ ነበር ?
  4. ሐዋ (2፡ 21) “ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል “ ይላል ፤ ስለዚህ ዳዊትና ታላቅ የብሉይ ኪዳን ሰዎች ወደ መንግስተ ሰማይ መሄዳቸዉን እንዴት እናውቃለን? (ሐዋ 2፡ 26-28)
  5. ስንኖርበት በአሁን ጊዜ የምንኖረበት አለም የተለየ የሚሆነዉ እንዴት ነው ሐዋ (2፡ 38-47) ? ይህ በቤተ ክርስቲያን ስለ ንስኃ፣ ስለ አንድነት፣ ስለ ፀሎት፣ ስለ ህብረት እና ስለ ለጋስነት አስፈላጊነት ምን ይላል ?
  6. በሐዋሪያት ስራ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Acts 2:37–39

“When they heard this, they came under deep conviction and said to Peter and the rest of the apostles: ‘Brothers, what must we do?’ ‘Repent,’ Peter said to them, ‘and be baptized, each of you, in the name of Jesus Christ for the forgiveness of your sins, and you will receive the gift of the Holy Spirit. For the promise is for you and for your children, and for all who are far off, as many as the Lord our God will call.’”

ጴጥሮስን ያደመጡት ኢየሱስ መሲሁና ለእስራኤል የድነት ተስፋ የሚሆን ጌታ እንደነበር አመኑ ፡፡ ይህንንም በተረዱ ጊዜ በደንብ ተነክተው ነበርና ጴጥሮስን “ ምን ማድረግ አለብን ? “ ብለው ጠየቁ ፡፡ ጴጥሮስም ፦ “ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ ። “ የጴጥሮስንም መልዕክት ሲቀበሉ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው እናም በሐዋርያት ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በጸሎትም ይተጉ ነበር ። የእግዚአብሔርንም ስራ መለኮታዊ በሆነ መንገድ አዩ ፡፡ እግዚአብሔርም ቁጥራቸውን በየቀኑ ይጨምር ነበር ፡፡

ከእምነት ውጭ ነገሮች ወጋ ቢስ ናቸው ፡፡ እምነት ጥልቅ መታመንን ፣ ውስጣዊ ስሜትንና ራስን አሳልፎ መስጠትን ያስገኛል ፡፡ ኢየሱስ የህይወትህ ጌታና መሲህ እንደሆነ እምነት አለህ ? በየቀኑ የምታደርጋቸው ተግባራት እና ንግግሮችህ እምነትህን ያንጸባርቃሉ ? ኢየሱስን ማመን አንድ ነገር ነው ፤ ይህንን እምነት ማንጸባረቅ ደግሞ ሌላ ነገር ነው ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ከማንበብ ፣ ከመጸለይ እንድሁም ደግሞ ከሌሎች አማኞች ጋር ህብረት ለማድረግ ጊዜን ከመስጠት ይልቅ ለማህበራዊ ሚድያ መረጃ ወይም ለሆነ የተለየ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የበለጠ ጊዜህን ትሰጣለህን ? ህይወትህን ኢየሱስ ላይ በሆነ ጽኑ እምነት ኑር እናም ይህን በእምነት ስታደርግ የመንፈስ ቅዱስን መገኘትና ኃይል ጠብቅ ፡፡ በእምነት ህይወት ይቀየራል ፡፡

“ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት፦ ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው ። ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው ። “

  • ሐዋርያት ሥራ 2 ፡ 37-39

ተጨማሪ ጥቅስ

ሐዋርያት ሥራ 2:42 — “ በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር ። “

ኤፌሶን 3:19–20 — “ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ ። እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው “

1ኛ ተሰሎንቄ 1:5 — “ ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ ። “