The Holy Spirit Promised, Jesus' Ascension, Matthias Chosen
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Authority Acts 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሐዋሪያት ስራ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ አዝናኝ መፅሀፍ ነው ፡፡ ብዙ ሰዎች የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍን እንወደዋለን ይላሉ ምክንያቱም በዚያን ጊዜ እግዚአብሄር ስለ አደረገዉ ነገር መስማት ስለሚወዱ ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ እንደሚችል እንድታዩ ተስፋ አደርጋለሁም እፀልያለሁም ፡፡ በዚህ መፅሀፍ በእኛ ዉስጥ ስለሚያድረዉ ስለ መንፈስ ቅዱስ እናወራለን ፡፡ በህይወታችን ዉስጥ ሊኖር እንዴት እንደሚመጣ መማር እንችላለን ምክንያቱም ለመስራት በሐዋሪያት ህይት ዉስጥ ሊኖር እንዴት ህያዉ ሆኖ እንደመጣ ስለምናይ ፡፡
ሐዋሪያቶች ለመስራት ታጥቀዉ በነበረዉ ተጓዙ ምክንያቱም ኢየሱስ ስልጣን ሰጥቷቸዉ ስለ ነበር ፡፡ በማቴዎስ ለኢየሱስ ተጠቅመነዉ የነበረዉ ቃል ንጉስ ነበር ፤ በማርቆስ ቃሉ አገልጋይ ነበር ፤ በሉቃስ የሰዉ ልጅ ነበር፣ በዮሐንስ ደግሞ የእግዚአብሄር ልጅ ነበር ፡፡
በማቴዎስ (28፡ 18) ኢየሱስ ለሐዋሪያቱ የጨዋታዉን እቅድ በመግለፅ በሰማይ እና በምድር ላይ ስልጣን ተሰጠኝ አላቸው ፡፡ የኢየሱስ ስልጣን የተወሰነ አይደለም ፡፡ ለሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ቃላችን ስልጣን ነው ፡፡ በተመሰረተ ስልጣኑ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ሁሉም ሕዝብ በመሄድ ደቀ መዛሙርቱ እንዲያደርጉ ነገራቸው (ማቴ 28፡ 19-20) ፡፡ የሚከናወነዉን ስንረዳ ኢየሱስ ስልጣን እንዳለዉ እና ለእኛም እንደሰጠን እንረዳለን ፡፡ እንዴት ? የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ስልጣን እንደሰጠን ያሳየናል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የሰጠን ነገሮች የተመቻቸን እንዳንሆን ያደርጉናል ፤ ነገር ግን ከእርሱ ብቻ መምጣት የሚችል ስልጣንና ኃይል ያስፈልገናል ፡፡ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍን ስናጠና ሁሉም ብሉይ ኪዳን ወደ ዚህ እንደሚያመለክቱ እናስታዉላለን ፡፡
ሐዋሪያት ስራ የሉቃስ ወንጌልን በፃፈዉ በሉቃስ የተፃፈ ሁለተኛ መፅሀፍ/ክፍል ነው ፡፡ ልክ እንደ ሉቃስ ወንጌል ሐዋሪያት ስራ ለቴዎፍሎስ ተፃፈ (ሐዋ 1፡ 1) ፡፡ የመጀመሪያዎቹ 12 ምዕራፍ በደንብ ስለ ጴጥሮስና ስለ ቤተ ክርስቲያን ናቸው ፤ በምዕራፍ (13-28) በይበልጥ የሚታየዉ ገፀ ባህሪይ ጳዉሎስ ነው ፡፡ የመፅሀፉን ርዕስ እንደ “ የመንፈስ ቅዱስ ስራ “ በሚል ስንቀጥል፣ ዮሐናስ ማክአርቱር “ ቤተ ክርስቲያንን በማጠንከር በቁጥር፣ በመንፈሳዊ ኃይል እና በተፅዕኖ ለማደግ ምክንያት የመንፈስ ምሪት፣ የመንፈስ ቁጥጥር እና የመንፈስ አገልግሎትን ማሳደግ እንደ ነበር “ ተናግሯል ፡፡ ጸሀፊዉ ሉቃስ በመፅሀፍ ሰዎስት ጊዜ የተገለፀ ነው ፤ በቆላ (4፡ 13) ሉቃስን እንደ “ ተወደደ ባለ መድኃኒት “ የተገለፀ ነበር ፡፡ በ 2ጢሞ (4፡ 11) ጳዉሎስ በእስርቤት እንደ ነበር ሉቃስ ከእርሱ ጋር ነበር ፡፡ ሉቃስ የሀዋሪያትን ተግባር ለመመዝገብ መሆን በሚያስፈልግበት ስፍራ ሁል ጊዜ ነበር ፡፡ በፊልሞን (1፡ 24) ጳዉሎስ ደግሞ ሉቃስ አጋር ሰራተኛዉ እንደ ነበር ጠቅሷል ፤ ሉቃስ ሀኪም ስለ ነበር በጥልቅ የተዘጋጀ (የሚመዘግብ) ነበር ፤ የጳዉሎስ የቅርብ ወዳጁ፣ የጉዞ ጓደኛዉ እና የግል ሀኪሙ ነበር ፡፡ በሉቃ (1፡ 1-4) ሉቃስ እንደ ጠንቃቃ ጥናት አድራጊ የተገለፀ ነበር ፤ ሉቃስ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን እና የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን አካል የነበሩትን ሌሎችን ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ ለሁለት አመት በእስር ቤት እንደ ነበር ሉቃስ ፊልጶስንና ሴት ልጁን ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል ፡፡ በሐዋሪያት ስራ ዉስጥ ሉቃስ የዚያ ወይም የዚህ የሆነ በመለት የፃፈው ብዙ “ እኛ “ የሚሉ ክፍሎች አሉ ፤ ስለዚህ ሉቃስ ሰዎችን ብቻ ቃለ መጠይቅ አላደረገም ነገር ግን ሉቃስ ይሳተፍባቸዉ የነበሩ ወቅቶችም ነበሩ ፡፡
ምናልባትም ሐዋሪያት ስራ የጳዉሎስ የመጀመሪያ የሮም እስራት ከ60 እስከ ከ62 ኤ.ዲ በፊት ተፅፏል ምክንያቱም ሉቃስ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ስለ ያዕቆብ ሰመዓትነት አልፃፈም ፡፡ ሉቃስ ለቴዎፍሎስ ኢየሱስ እዚህ በምድር ላይ ስላደረጋቸዉ ነገሮች መግለጫ/ትረካ ለመስጠት ፃፈው ፤ በዚህ ሂደት ሉቃስ የኢየሱስን ማረግ፣ ጴንጤ ቆስጣን እና የቤተ ክርስቲያንን መመስረትና ማደግ ገልፃል ፡፡ ሉቃስ የሁሉንም ጊዜ የተለዬ መነቃቃትን መስክሯል ፡፡ መቼም ቢሆን በሐዋሪያት ስራ የቤተ ክርስቲያንን እድገት ስንመለከት ተቃርኖም እንመለከታለን ፤ ሉቃስ በሐዋሪያት ስራ የመዘገበዉ ለታላቁ ተልዕኮ የመነሻ ምላሽ ነበር (ማቴ 28፡ 18-20) ፡፡ በተልዕኳቸው በመሄዳቸዉ ስለ ነፍሳቸዉ በማይጨነቁት በ12 ሰዎች ምክንያት ስለ ኢየሱስ በመስማት በተሰጠን ስልጣን ተጓዝን ፡፡ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ኢየሱስ የእስራኤል የሚጠበቅ መሲህ ነበር ፤ ኢየሱስ በሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ በእዉነት የእስራኤል ተስፋ ሆኗል ፡፡ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ በደንብ ከብሉይ ኪዳን ይጠቅሳል ፤ ሉቃስ መግለጫዉን መልሶ ከኢዩኤል ጋር፣ መልሶ ከመዝሙር ጋር እና መልሶ ከኢሳያስ ጋር አስተሳሰረዉ ፡፡ ለምሳሌ ሐዋ (2፡ 35) ከመዝ (110፡ 1) የተወሰደ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ብሉይ ኪዳንን ያጠፋል ማለት አይደለም ምክንያቱም አሁን አዲስ ኪዳንን እና አዲስ ኪዳና እያጠናን ስለሆነ ፤ ይልቁንም ኢየሱስ ህግንና ነቢያትን ልፈፅም መጣሁ ብሏል - ሊያጠፋ ወይም ሊያስወግድ አልመጣም (ማቴ 5፡ 17) ፡፡
ትምህርት
ሐዋሪያት ስራ (1፡ 1-3)፡ ሉቃስ በመጀመሪያ ፅሁፉ (በሉቃስ ወንጌል) ሸፍኖት የነበረዉን መልሶ ተመለከተ ፡፡ ይህን ፅሁፍ ሲጀምር ሉቃስ ኢየሱስ እንደ ተሰቃዬ፣ እንደ ሞተ ከዚያም ወደ ህይወት እንደ ተመለሰ እና ለአራት ቀናት ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ተገለጠላቸዉ ያብራራል ፡፡ ኢየሱስ ህያዉ እንደ ነበር “ ብዙ ማሳመኛ ማረጋገጫዎችን “ ሰጥቷል፣ ለደቀ መዛሙርቱም ስለ እግዚአብሄር መንግስት አወራቸው ፡፡ ይህ በአሁኑ ጊዜ መሆን ያለብን መልዕክት ነው ፤ ከራሳችን ወይም ከዋጋችን ይልቅ በይበልጥ ለእግዚአብሄርን መንግስት መሆን ያስፈልገናል ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (1፡ 4-5)፡ ኢየሱስ እነዚህን 40 ቀናት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደ ነበር ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ ነገራቸው ፡፡ ኢየሩሳሌም ኢየሱስ የተገደለባት ስለ ነበር ምናልባትም ትዕዛዙን ጠይቀዋል ነገር ግን ኢየሱስ አብ ተስፋ የገባዉን ጠብቁ አላቸዉ ፡፡ ኢየሱስ አብ በመንፈስ ቅዱስ እንደሚያጠምቃቸዉ ነግሯቸዉ ነበር ፤ በሉቃ (11፡ 13) ኢየሱስ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን እንደ ሚሰጣቸዉ ገልፆላቸዋል ፡፡ በሉቃ (24፡ 49) ከሞት ከተነሻ በኋላ ኢየሱስ “ አባቴ የሰጠዉን ተስፋ እኔ እልክላችኋላ “ አላቸው ፤ ደቀ መዛሙርቱ በኢየሩሳሌም ኢየሱስና እግዚአብሄር አብ ተስፋ ገብቶላቸዉ የነበረዉን ለእነርሱ እስኪሰጣቸዉ ድረስ እንዲጠብቁ የሚያዘዉን የፀና መልዕክት ሰሙ ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (1፡ 6-8)፡ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ የእስራኤል መንግስት ለመመለስ አስቦ እንደ ነበር ለማወቅ ፈለጉ ፤ የእስራኤል መንግስት እንደ ገና ተቋቁሞ እንደ አስተዳዳሪ ንጉስ ኢየሱስን ለማየት ዝግጁ ነበሩ ፡፡ ደቀ መዛሙርት ሕዝቅኤል 36 እና ኢዩኤል 2 በመንፈስ ቅዱስ መዉረድ የመንግስቱ መምጣት ጋር እንደ ተገናኘ ያውቃሉ ፡፡ ኢየሱስም ይህን እንዲያዉቁ ለእነርሱ የተሰጠ እንዳልነበርናእንዲያደርጉት ተጠርተዉ ወደ ነበረዉ እንደ ገና አዘዛቸው (አስተካከላቸው) ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በተሰጣቸዉ ጊዜ “ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማሪያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ “ (ቁጥር 8) ፡፡ “ ምስክር “ የሚለዉ ቃል “ ለእምነቱ የሚሞት ሰዉ “ የሚል ትርጉም ያለዉ የግሪክ ቃል ነው ፡፡ ኢየሱስ እያለ የነበረዉ ስልጣንና ኃይል ሊሰጠን መንፈስ ቅዱስ እንደሚመጣ ተስፋዉን ስናምን ለእርሱ እንሞታለን ፤ በአንዳንድ ምክንያት በሰንበት ት/ቤት ትምህርት ዉስጥ መልካም ዜና መቀበል ስራ ወይም የቤት ስራ ነው ፡፡ በእዉነታው የክርስቶስ ተከታዮች ከሆንን ባለንበት በየትም ስፍራ በክርስቶስ ለእምነታችን ለሚሞተዉ ምስክር ለመሆን ፍቃደኞች መሆንችንን የተጠየቅን መሆን አለብን ፡፡ ለሚኖረዉ ንጉስ እንደ አምባሳደር ለመጓዝ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ በመጣ ጊዜ ስልጣንና ኃይል ተሰጥቶናል ፤ ነገር ግን እንደ ምንፈልግ ወይም እንደ ማንፈልግ እንወስናለን ፡፡ በተሰጠን ስልጣን ለመጓዝ ፈሪዎች ነን ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (1፡ 9-14)፡ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ከእይታቸዉ በደመና ሲያርግ ተመለከቱ ፤ እኛም ወደዚህ አለም (ሁኔታ) እና ወደ ዚህ ምድር የእግዚአብሄርን ወንጌልን እና መንግስትን ማን እንዳመጣዉ ምስክሮች እንሆናለን ፡፡ በክርስቶስ ስልጣን የመጓዝ ስልጣን አለን፣ እንዴት እንደ ምናደርግም የሚያስደንቅ ሞደል አለን ፡፡ ከዚያም ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ቀደ ሰማይ እየተመለከቱ በዚያ ለምን ቆመዉ እንደ ነበር ደቀ መዛሙርቱን ጠየቋቸው (ቁጥር 11) ፡፡ ሁለቱ ነጭ ልብስ የለበሱት ሰዎች ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳዩት በተመሳሳይ መንገድ ተመልሶ እንደሚመጣ ገለፁላቸው ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱ - ከግማሽ ማይል በላይ ስለ ማይበልጥ በሰንበት ላይ መጓዝ የሚችሉትን ያክል የራቀ ነበር (ቁጥር 12) - ቃለ ምልልሳቸዉን አስባችሁታል ? እንደ ታዘዙት ደቀ መዛሙርቱ ተስፋ የተገባዉን መንፈስ ቅዱስ በኢየሩሳሌም ጠበቁ፡፡
ሐዋሪያት ስራ (1፡ 15-26)፡ በሰገነትም ላይ እንደ ተሰበሰቡ ደቀ መዛሙርቱ ይሁዳን ለመተካት ማትያስን ለመምረጥ እጣ ጣሉ እንደ ገናም 12 ደቀ መዛሙርት ነበሩ ፡፡
መደምደሚያ
ሐዋሪያት ስራ 1 መጨረሻ ላይ ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሄርን መንፈስ እስኪመጣ እየጠበቁ ነበር ስለዚህም ምስክሮች መሆን ይችላሉ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1429
MacArthur, p. 1429.
MacArthur, pp. 1429–30.
MacArthur, p. 1432.
MacArthur, p. 1433.
ጥያቄዎች
-
በሐዋ (1፡ 3) ሉቃስ ኢየሱስ “በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያዉ ሆኖ ለእነርሱ ራሱን እንዳሳያቸው “ አስፍሯል ፤ ከእነዚህ ማረጋገጫዎቹን ጢቂቶቹን መዘርዘር ትችላላችሁ ?
-
ኢየሱስ ሐዋሪያቱን አብ ተስፋ ገብቶላቸዉ የነበረዉ በእነርሱ እስኪገለጥ እንዲጠብቁ ነገራቸው ፤ ወደ ኃላ ወንጌላት ላይ ተመልከቱ ፤ መቼና በምን ኢየሱስ አብ ተስፋ ገብቶላቸዉ ስለ ነበረዉ ነገር ነገራቸው ?
-
በሐዋሪያት ስራ (1፡ 8) መሰረት እንዲሰሩ ሐዋሪያቱን ምን ኃይል ያስታጥቃቸዋል ? ተመሳሳይ ጥሪ አለን ? መልችሁን በጥቅስ/በመፅሀፍት አስደግፉ ፡፡
-
አማኞች በኢየሩሳሌም እየጠበቁ ምን አደረጉ (ሐዋ 1፡ 13-14) ? በዚህ ሂደት ምን ያክል ቀጠሉ ?
-
በሐዋሪያት ስራ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Acts 1:8
“But you will receive power when the Holy Spirit has come on you, and you will be My witnesses in Jerusalem, in all Judea and Samaria, and to the ends of the earth.”
ከኢየሱስ ሞትና ትንሳዔ በኋላ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ ለ 40 ቀናት ያህል ታያቸው ፡፡ በዚህ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ነገር አስተማራቸው ፡፡ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን መንፈስ ቅዱስ በላያቸው ላይ በመጣ ጊዜ ኃይልን እንደሚቀበሉ ነገራቸው ፡፡ እንድሁም በተጨማሪ የመጨረሻውን ትዕዛዝ በኢየሩሳሌም በይሁዳ ሁሉ በሰማርያ እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቹ ይሆኑ ዘንድ አዘዛቸው ፡፡ ይህንም ከተናገራቸው በኋላ ኢየሱስ ወደ ሰማይ አረገ ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ፣ በህብረትም ይጸልዩ ነበር ፡፡
ኢየሱስ አሁንም ገና ስላልተመለሰ ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ተስፋና የመጨረሻ ትዕዛዝ ዛሬም አማኝ ለሆኑ አሁንም እውነት ነው ፡፡ እንደ አማኝ የእናንተ ስራ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የኢየሱስ ምስክር እንድትሆኑ ነው ፤ በራሳችሁ ኃይል አይደለም ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተቀብላችሁ እንጅ ፡፡ ምናልባት መጠጥ ቤት ውስጥ ፣ ትምህርት ቤት ፣ ከቤተሰብ ጋር ወጣ ብላችሁ ወይም በአለም ዙሪያ በአንድ አገር ውስጥ እንድሁም ደግሞ ከቤት እርቃችሁ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን የትም ቢሆን የኢየሱስ ምስክሮች ትሆኑ ዘንድ ታዛችኋል ፡፡ ልትፈሩት የሚገባ ምንም ነገር የለም ፡፡ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው ያ ኃይል በእናንተም ውስጥ ይኖራል ፡፡ ስለዚህ በስልጣን ውጡ ፡፡ ብርሀናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ይብራ ፤ መንገድ ፣ እውነት እና ህይወት ኢየሱስ መሆኑን መስክሩ !
“ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ ። “
ሐዋርያት ስራ 1፡8
ተጨማሪ ጥቅስ
- ማቴዎስ 28:18–20 — “ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ። “
- ዮሐንስ 14:6 — “ ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ። “
- ሮሜ 8:11 — “ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።