The Deliverance of the Jews
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Despised One Esther 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ የአስቴር የመጨረሻዉ ክፍል እና በአስራ ሁለቱ የታሪክ መፅኀፍት የመጨረሻዉ ነው፡ ኢያሱ -አዛዥ፣ መሳፍንት- ዳኛ፣ ሩት - ተቤዢ ዘመድ፣ 1ሳሙኤል - የተቀባ፣ 2ሳሙኤል - ዘላለማዊ ዙፋን፣ 1ነገስት - የሚበልጠዉ ነገር፣ 2ነገስት - የተረፈዉ ዘር፣ 1ዜና መዋዕል - የዳዊት ልጅ፣ 2ዜና መዋዕል - ንጉሳዊ ዙፋን፣ ዕዝራ - ቃል ኪዳን ጠባቂ፣ ነህምያ - ሰራተኛ/ግንበኛ እና አስቴር - የተናቀዉ ፡፡ እነዚህ ሁሉ ሐረጎች/ቃሎች ወደ መጣዉ መሲህ ያመለክታሉ ( ማቴ 5፡ 17) ፡፡ በአስቴር እግዚአብሄር በፋሬስ አይሁዶችን ከጥፋት ለማዳን የተናቀዉን መርዶክዮስን እና የአጎቱን ልጅ አስቴርን ተጠቀመ (1ቆሮ 1፡ 28-31) ፡፡ አይሁድን ለመግደል የመጀመሪያዉ አዋጅ ሊፈፀም አልቻለም ነገር ግን ሁለተኛዉ አዋጅ የአይሁዶችን ሁኔታ ቀየረ ፡፡ ኮንስታብል “ ንጉሱ አይሁዶችን ጠላቶቻቸዉን በመግደል ራሳቸዉን እንዲከላከሉ ፍቃድ ሰጣቸው ፤ በትክክል ይህ ማለት በመከላከል ያጠቃሉ ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ሁኔታ እንደሚያጠፉአቸዉ በሚያዉቋቸዉ ላይ በመነሳሳት ይገድሏቸዋል “ በማለት ይገልፃል ፡፡
ትምህርት
አስቴር (9፡ 1-4)፡ ሁለቱም አዋጆች በተመሳሳይ ቀን ወደ ተግባር ሄዱ ነገር ግን የአይሁድ ጠላቶች በአይሁዶች ላይ መብለጥ የሚችሉ ስላልነበሩ በአይሁዶች ተበለጡ(ቁጥጥር ስር ሆኑ) (ቁጥር 1-2) ፡፡ የአይሁድ ሕዝቦች በግልፅ የተሻለ መሳሪያ ነበራቸው - ሕዝቦቹ አይሁዶችን ፈርተዉ ነበር (አስ 8፡ 17፣ ኤር 30፡ 16) ፤ የዚህ ምሳሌ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ የሚያካትታቸው፡
- ያዕቆብ ከሴኬም ወደ ቤቴል መንገድ ላይ እያለ በዙሪያቸዉ በነበሩት ከተሞች የነበሩት ሁሉም ህዝቦች እግዚአብሄርን በመፍራት ብቻቸዉን ትተዋቸዉ ሄዱ (ዘፍ 35፡ 5) ፡፡
- እስራኤል ተስፋይቱ ምድር በገባ ጊዜ በምድሪቱ የሚኖሩት ሕዝቦች ፈርተዋቸዉ ነበር (ዘዳ 2፡ 25፣ ኢያ 2፡ 8-11፣ 5፡ 1፣ 9፡ 24) ፡፡
በሚያናድድ ሁኔታ ያ ተመሳሳይ ፍርሃት በአሁኑ ጊዜ በአብዛኞቹ ሰዎች ላይ የለም ፡፡ ሮሜ (3፡ 18) “ በዓይኖቻቸዉ ፊት እግዚአብሄርን መፍራት የለም “ ይላል ፤ ፈርዖንም “ ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሄር ማነው ? እግዚአብሄርን አላዉቅም እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም አለ “ (ዘጸ 5፡ 2) ፡፡
ቁጥር 3-4 በፋሪስ ሁሉም ክፍለ ሀገሮች ያሉት ሰራተኞች(አለቆች) አይሁዶችን አገዙአቸዉ ምክንያቱም በቤተ መንግስት ታላቅ ኃይል የነበረዉን እና በመላዉ ፋሪስ ዉስጥ ኃይልኛ እየነበር ያለዉን መርዶክዮስን ይፈሩት ስለ ነበር ፡፡ የተናቀዉ መርዶክዮስ ኃይለኛ የሚሆን ነበር ፤ ይህ የተናቀዉ፣ በመስቀል ላይ በመሞት በክብርና በኃይል የተነሳዉ የክርስቶስ ስዕል ነው (1ቆሮ 15፡ 54-57) ፡፡
አስቴር (9፡ 5-10)፡ አይሁዶች ጠላቶቻቸዉን በሰይፍ አጠፉዓቸው ፡፡ በሱሳ ግንብ የሀማን አስር ልጆችን ጨምሮ 500 ሰዎችን ገደሉ (ቁጥር 5-10) ፤ ይሁን እንጂ አይሁዶች በድላቸዉ ምንም ምርኮ አልወሰዱም ፡፡ እግዚአብሄር ሳዖልን ሁሉንም አማሌቃዊያንን እንስሳቶቹን ጨምሮ እንዲያጠፋ እንደ ነገረዉ ነገር ግን ሳዖል ባለመታዘዝ ለምርጦቹ እንሰሳቶችና ለንጉስ አጋግ እንዲኖሩ እንደ ፈቀደላቸዉ ታስታዉሳላችሁ (1ሳሙ 15፡ 17-23) ? በፋሪስ አይሁዶች አማሌቃዊያንንም በማግኘት ጠላቶቻቸዉን አጠፉ ነገር ግን የእነርሱ የሆነዉን ነገር ወይም ማናኛዉንም እንስሳት ለመጠበቅ አልፈለጉም ፡፡ አይሁዶች በፋሪስ በጊዜአቸዉ ተምረዉ ነበር ፡፡ ሀተታ ሰጪ ባልድዊን “ በጠላቶቻቸዉ ወጪ ራሳቸዉን ላለማሳደግ ትክክለኛዉ ዉሳኔ ድሎች ቆሻሻ ይወስዷሉ ተብለዉ ተጠብቀዉ ስለነበር በባህል ሳይነቃበት አይሄድም ፤ እራሳን እንደመካድ አይነት አዲስነት የታሰበ እና የሚታወስ የሚሆን የአይሁድ ማህበረሰብ ትክክለኛነትን እንደ ሚያረጋግጥ የሚወሰድ እንደሚሆን “ ይገልፃል ፡፡
አስቴር (9፡ 11-32)፡ ንጉሱ ተገድለዉ የነበሩትን በመናገር አስቴርን ሌላ የምትፈልገዉን ጠየቃት (ቁጥር 11-12) ፡፡ በሱሳ ያሉት አይሁዶች በጠላቶቻቸዉ ላይ አዋጁን እስኪጨርሱ እና የሀማን ልጆች አካል በዛፍ ላይ እስኪሰቅሉ ተጨማሪ አንድ ቀን እንዲሰጣቸዉ ጠየቀች (ቁጥር 13) ፡፡ ንጉሱም ጥያቄዋን መለሰላት (ቁጥር 14) ፡፡ በማግስቱ አይሁዶች በመሰብሰብ ተጨማሪ 300 ሰዎችን ገደሉ ነገር ግን አሁንም ምርኮ አልወሰዱም (ቁጥር 15) ፤ አይሁዶች በመላዉ በክፍለ ሀገሮች ዉስጥ ከጠላቶቻቸዉ 75,000 ሰዎች ገደሉ ነገር ግን ምንም ምርኮ አልወሰዱም (ቁጥር 16)፡፡ በክፍለ ሀገሮቹ ያሉ አይሁዶች አዳር በሚባለዉ ወር አስራ ሰዎስተኛዉ ቀን ላይ ተዋጉ በአስራ አራተኛዉ ቀን አረፉ ፡፡ በሱሳ ከተማ ያሉ አይሁዶች በአስራ ሰዎስተኛዉ ቀን እና በአስራ አራተኛዉ ቀን ታገሉ ከዚያም በአስራ አምስተኛዉ ቀን አረፉ (ቁጥር 17-18) ፡፡ እያንዳንዱ ቡድን በአረፉበት ቀን ላይ ድሉን አከበሩ ፡፡ መርዶክዮስም በአዉራጃዎቹ ሁሉ ላሉት አይሁዶች ደብዳቤዎችን በመላክ በዓሉ በእያንዳንዱ አመት በአዳር ወር በአስራ አራተኛዉ እና አስራ አምስተኛዉ ቀን “ ኃዘናቸዉ ወደ ደስታ እና ከለቅሶም ወደ መልካም ቀን እንደ ተቀየረበት ቀን “ (ቁጥር 20-22) እንዲያከብሩት አዘዘ ፡፡ በዓሉ ፆምን፣ ስጦታ መስጠትን እና መደሰትን ያካትታል (ቁጥር 22) ፡፡
ይህ ከሀማ ጭፍጨፋ ያመለጡበት መታሰቢያ በዓል የተፈጠረበት ነበር (ቁጥር 23) ፡፡ ክፉዉ ሀማ እጣ በማዉጣት አይሁዶችን ለማጥፋት ቀንን መርጦ ስለነበር ከዚያ በኋላ ነበር የተሰየመው (ቁጥር 24፣ ምሳ 16፡ 33) ፡፡ ቁጥር 25 የአስቴርን መፅኀፍ ማጠቃለያ ይጀምራል - ሀማ ለአይሁዶች አሲሮት የነበረዉ ለእርሱና ለልጆቹ ሆነ ፡፡ የፑሪም(ከሀማ ጭፍጨፋ የተረፉበት) መታሰቢያ ፆም እነዚህ ሁሉ ነገሮች በፋሪስ ለአይሁዶች እና ለሁሉም አይሁዶች ይመጣል (ቁጥር 26-32) ፡፡ የፑሪም(ከሀማ ጭፍጨፋ የተረፉበት መታሰቢያ በዓል) ፆም በአሁኑም ጊዜ የሚከበር ነው ፡፡
2 Joyce G. Baldwin, Tyndale Old Testament Commentary: Esther (Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1984), p. 105; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Esther, p. 65; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/esther.pdf.
መደምደሚያ
የተናቀዉ ለእግዚአብሄር ህዝብ ነፃ መዉጣትን አመጣ ፡፡ ትሁቱ ሰዉ መርዶክዮስ ከንጉስ አርጤክስስ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከፍ አለ፣ ስለ ሕዝቡም መናገር እና ደህንነታቸዉን መፈለግ ቀጠለ (አስ 10፡ 3) ፤ በአሁኑ ጊዜ ለእግዚአብሄር ሰዎች ነፃ መዉጣትን የሚያመጣዉ እና ስለ እኛ የሚማልደዉ የተናቀዉ የኢየሱስ ትክክለኛ ስዕል ነው፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Esther, p. 61; available online at v.
ጥያቄዎች
-
በአስቴር (9፡ 1) በንጉሱ ምን አዋጅ ወይም ትዕዛዝ ተሰጠ (አስ 8፡ 11-12) ? ንጉሱ ይህን አዋጅ ለምን አደረገ ?
-
መርዶክዮስ የማን ዘር ነበር ለአስቴርስ እንዴት ነበር የሚዛመዳት (አስ 2፡ 5-7) ? መርዶክዮስ ምን ስፍራ ያዘ ?
-
በምዕራፍ 9 ንጉሱን የአስቴር ጥያቄ ምን ነበር ? ንጉሱ የአስቴርን ጥያቄ መለሰላት ? ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ?
-
አይሁዶች ከጠላቶቻቸዉ ነፃነትን በማግኘታቸዉ ለማክበር ምን ድግስን መሰረቱ ? ይህን እንዴት አከበሩት ? አይሁዶች ይህን እስከ አሁን ድረስ ያከብሩታል ? ይህ በዓል ከጠላታቻን የራሳችንን ነፃ መሆናችንን እንዴት ያንፀባርቃል ?
-
በአስቴር (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Esther 9:21–22
“He ordered them to celebrate the fourteenth and fifteenth days of the month Adar every year because during those days the Jews got rid of their enemies. That was the month when their sorrow was turned into rejoicing and their mourning into a holiday. They were to be days of feasting, rejoicing, and of sending gifts to one another and the poor.”
አሁንም እንደገና አስቴር ሌላ ነገር ትለምን ዘንድ በንጉሡ ፊት ቀረበች ፡፡ ለአይሁድ ህዝብ ጠላቶቻቸውን የሚገድሉበት ተጨማሪ አንድ ቀን እንድሰጣቸውና የሐማ ልጆች እንድሰቀሉ ጠየቀች ፡፡ ይህም ይደረግ ዘንድ ንጉሡ ትዕዛዝ ሰጠ ፡፡ መርዶክዮስም እነዚህን ክንውኖች መዘገበ እንድሁም በቅርብና በሩቅ ያሉትን ህዝቦች አዳር የሚባለው ወር አሥራ አራተኛውና አሥራ አምስተኛውን ቀን እንድያከብሩ አዘዘ ፤ ምክንያቱም “ በእነዚህ ቀናት አይሁዳውያን ጠላቶቻቸውን አስወግደዋልና “ ፡፡ በዚያ ወር ኀዘን ወደ ደስታ ለቅሶም ወደ በዓል ቀን የተለወጠበት ነውና ፤ ሁለት ቀናት እንድሆኑና የግብዣና የደስታ ፥ እርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚሰጣጡባቸውና ለድሆች ስጦታ የሚሰጡባቸው ቀናት እንድሆኑ ተደረገ ፡፡
እንዴት ታላቅ ይሆን ቀናትን ማክበር ! ለገና የክርስቶስን መወለድ እንድሁም ደግሞ ሞትና ትንሳዔውን ለፋሲካ ታከብራለህ ፡፡ ግን በቃ ከኢየሱስ ጋር ባለህ ግንኙነት የተለየ ቀን ብታከብርስ ? ለኢየሱስ አወ ያልክበትን እንድሁም ከሞት ወደ ህይወት የተሻገርክበትን ቀን ? ምናልባትም ይቅር ካለማለት ፣ ከሀዘን ወይም ከመራራ ህይወት ባርነት ነጻ የወጣህበትን ቀን ? እንደ ክርስቶስ ተከታይ በመንፈሳዊ ጉዞህ እነዚህን ጊዜያት ልደትህን እንደምታከብረው ሁሉ ማክበር ትችላለህ ፡፡ እግዚአብሔር ሀዘንህን ወደ ደስታ አመድህንም ወደ አክሊል እንደሚለውጥ ተናግሯል ፡፡ ቀናትን ማሰብ ወደ ኋላ ለመመልከት እንድሁም እግዚአብሔር በህይወትህ እንዴት እንደሰራ ለማስታወስ ጊዜን ይሰጣል ፡፡ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር በመንገድህ ልታስበው የሚገባ ቀን ካለ አስብ ፤ እናም ከዚያ ጓደኞችህን ሰብስብ ፣ በአምልኮና እግዚአብሔርን በማመስገን ጊዜን አሳልፍ ወይም ደግሞ ኢየሱስ እንደሚወዳቸው ማወቅ ለሚያስፍልጋቸው ሰዎች ስጦታን ስጥ !
“ በየዓመቱም አዳር በሚባለው ወር አሥራ አራተኛውና አሥራ አምስተኛው ቀን ፥ አይሁድ ከጠላቶቻቸው ዕረፍትን ያገኙበት ቀን፥ ወሩም ከኀዘን ወደ ደስታ ከልቅሶም ወደ መልካም ቀን የተለወጠበት ወር ሆኖ ይጠብቁት ዘንድ፥ የግብዣና የደስታም ቀን፥ እርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚሰጣጡበትና ለድሆች ስጦታ የሚሰጡበት ቀን ያደርጉት ዘንድ አዘዛቸው ። “
- አስቴር 9፡21-22
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 30:11–12 — “ ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል ልቅሶዬን ለደስታ ለወጥህልኝ፥ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ ። አቤቱ አምላኬ፥ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ ። “
ኢሳይያስ 61:3 — “ `እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል ። “
ሉቃስ 15:22–24 — “ አባቱ ግን ባሪያዎቹን አለ፦ ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ ፤ የሰባውን ፊሪዳ አምጥታችሁ እረዱት፥ እንብላም ደስም ይበለን ፤ ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።