Hasten With The Message
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Despised One Esther 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለአስቴር መፅሀፍ ሀረጋችን/ቃላችን የተናቀዉ የሚል ነው ፡፡ በተጨማሪም መፅሀፉ በፋሬስ የሁሉንም አይሁዶች ኑሮ የታደገችዉን የአስቴርንም ስም ይዟል፣ አጎቷ መርዶክዮስም በታሪኩ ጠቃሚ (አስፈላጊ) ድርሻ ነበረው ፡፡ መርዶክዮስ የተናቀ ነበር ፡፡ ሁሉም አይሁዶች ስለ ሚያጠፋዉ አዋጅ የሰማዉ መርዶክዮስ ነበር ፤ በማዘን ከንጉሱ በር ዉጪ በአመድ እና ማቅ በመልበስ የተቀመጠው መርዶክዮስ ነበር፣ በፋሬስ የአይሁድን ሰዎች ለማዳን የምትችለዉን ሁሉ እንድታደርግ ያሳመናት መርዶክዮስ ነበር ፡፡ አይሁዶችን ገጥሟቸዉ የነበረዉ ችግር የንጉስ ሰራተኛና የንጉስ አጋግና የአማሌቃዊያን ዘር የነበረዉ በማክበር በፊቱ ስግደትን እምቢ ባለዉ በመርዶክዮስ የተበሳጨው የሀማ ዉጤት ነበር፡፡ በመናደድ ሀማ መርዶክዮስን ብቻ ለማጥፋት አልፈለገም በፋሬስ የሚኖሩትን ጠቅላላ አይሁዶችንም እንጂ ፡፡
በምዕራፍ 6 ንጉሱ ለእርሱና ለሀማ ካዘጋጀችዉ ከአስቴር ሁለተኛ ግብዣ በፊት ምሽቱን የዕለት ተዕለት ክስተቶች መፅሀፍን በማንበብ አሳለፈ ፤ በዚያም ንጉሱ በህይወቱ ላይ የግድያ ሙከራዉን መርዶክዮስ ተከላክሎለት እንደ ነበር አገኘ (ቁጥር 1-2) ፤ ንጉሱም ለመርዶክዮስ ምን ክብር ተሰጥቶቷል ብሎ በጠየቀ ጊዜ ምንም እንዳልተደረገለት ተነገረው (ቁጥር 3) ፡፡ በእንጨቱ ላይ መርዶክዮስን ለመስቀል ንጉሱን ለመጠየቅ ሀማ በተዘጋጀዉ አዳራሽ ላይ ደርሷል (ቁጥር 4-5) ፤ ይልቁንም ንጉሱ ሀማን አንድን ሰዉ ለማክበር ምን ታደርግለታለኽ አለው ፤ ሀማም ክብሩ ለእርሱ እንደሚሆን በማሰብ ንጉሱን የንጉስን ልብስ እና ንጉስ ተቀምጦበት የነበረዉን ፈረስ፣ ዘዉድ የለበሰዉን ፈረስ በመስጠት በንጉሱ የተከበረዉ እንዲህይደረግለታል በማለት በከተማዋ እንደሚዞር ነገረው (6-9) ፡፡ ንጉሱ የሀማን እቅድ ተቀበለ ነገር ግን ሀማን ያን ክብር ለመርዶክዮስ እንዲያደርግለት ነገረው (ቁጥር 10) ፤ ሀማ እንደ ተባለዉ አደረገ ፡፡ ከከበረ በኋላ መርዶክዮስ በንጉሱ በር ላይ በስፍራዉ ተመለሰ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ይሁን እንጂ ሀማ ቤት በመመለስ ለሚስቱና ለወዳጆቹ ተፈጥሮ የነበረዉን ነገራቸው (ቁጥር 12-13) ፤ ሀማንም መዉደቁ እርግጥ እንደ ነበር ነገሩት (ቁጥር 13) ፡፡ እያወሩ ወደ ንግስቲቱ አስቴር ግብዣ ሊወስዱት የንጉሱ ጃንደረቦች ደረሱ ፡፡
ትምህርት
አስቴር (7፡ 1-6)፡ ንጉሱና ሀማ ንግስት አስቴር ግብዣ ላይ በደረሱ ጊዜ እንደ ገና ንጉሱ አስቴርን የምትፈልገዉን ነገር ሁሉ እስከ መንግስቱ እኩሌታ እንኳን ቢሆን እንደሚሰጣት ነገራት (ቁጥር 1-2) ፡፡ ንግስቲቱም የንጉሱ ማረጋገጫ ከነበራት ህይወቷና የህዝቧ ህይወት እንዲድን ብቻ እንደምትፈልግ አለች (ቁጥር 3) ፡፡ አስቴር ቃሏን ለንጉሱ ለመናገር ትክክለኛዉ ጊዜ መቼ እንደ ነበር ለመረዳት ትብ/የፈራች ነበረች ፡፡ አስቴር ሕዝቧ “ ለመጥፋትና ለመገደል ለመደምሰስም “ ተሸጧል በማለት ገለፀች ፤ ሕዝቧ ለባርነት ብቻ ተሸጠዉ በነበር እንደ ማታስጨንቀዉ ለንጉሱ ባልተናገርኩ አለች (ቁጥር 4) ፡፡ ንጉሱ ስለ ማንና ስለ ምን እያወራች እንደ ነበር ሀሳቡ አልነበረው (ቁጥር 5) ፤ አስቴርም ህዝቧን የማጥፋት እቅድ ጥፋተኛዉ ሀማ እንደ ነበር አመለከተች ፡፡ ሀማ በንጉሱና በንግስቲቱ ፊት ደነገጠ (ቁጥር 9) ፡፡
አስቴር (7፡ 7-10)፡ ንጉሱም በሰማዉ ነገር በጣም ተበሳጭቶ ስለነበር ግብዣዉን በመተዉ ወደ አትክልት ስፍራዉ ሄደ ፤ ይሁን እንጂ ሀማ ከአስቴር ጋር ተቀመጠ ምክንያቱም ንጉሱ ለእርሱ መጥፎ ነገር እያቀደ እንደ ነበር ስለተረዳ (ቁጥር 7) ፡፡ ንጉሱ ሲመለስ አስቴር በምትጋደምበት ስፍራ ላይ ወድቆ ሲያየዉ በመደነቅ ንጉሱ በቤተ መንግስት እያለ ንግስቲቱን ትጋፋታለህን አለ ፡፡ ንጉሱ ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ የሀማ ፊት ተሸፈነ (ቁጥር 8) ፤ ከጃንደረቦቹ አንዱ ንጉሱን ሀማ በቤቱ መርዶክዮስን ለመስቀል እንጨት እንዳዘጋጀ ነገረው ፤ ንጉሱም እንጨቱ ሀማን ለመስቀል እንዲጠቀሙበት አዘዘ (ቁጥር 9) ፡፡ ሀማ በእንጨቱ ላይ ተሰቀለ የንጉሱም ቁጣ በረደ (ቁጥር 10) ፡፡
ሀማ ቢሞትም የንጉሱ አዋጅ አሁንም በተፅዕኖ ነበር ፤ ሁሉም ግዛቶች በተወሰነ ቀን ሁሉንም አይሁዶች መግደል ይችላሉ የሚለዉን አዋጅ ኮፒ ተቀብለዉ ነበር ፡፡ በዘፍ (12፡ 1-3) ላይ የሚገኘዉን የአብራሃምን ኪዳን ለማጥፋት ሰይጣን እየሞከረ ቢሆንም የእግዚአብሄር እጅ በተመረጡ ሕዝቦቹ ላይ ነበር ፤ ይህ የአይሁዶችን ብዙ ቁጥር በማጥፋት ፀረ-ሴሜቲካዊያን የሞከሩበት ጊዜ ነበር ፡፡ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ባንወስድም ወደ ፊት ወደ ዘመናዊዉ ጊዜ ስናመጣው የአስቴርንና የመርዶክዮስን ታሪክ አለማንበብና ስለ እልቂቱ( በሁለተኛዉ አለም ጦርነት ጊዜ በሂትለር የአይሁዶች ጭፍጨፋን) አለማሰብ የማይቻል ነው ፤ በዕልቂቱ ጊዜ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች ተገድለዉ ነበር ፡፡ አንድ ሰዉ ልክ እንደ ሂትለር አይሁዶችን ለማጥፋት ለምን ፈለገ ? ሀማ ለምን አይሁዶችን ለማጥፋት ፈለገ ? በናዚ በደቡብ ምዕራብ ፖላንድ ላይ ትልቅ መጠራቀሚያ ስፍራ በሆነው ከአንድ ሚሊዬን በላይ አይሁዶች ተገደሉ ፡፡ በተርቢልካ ከ925,000 በላይ አይሁዶች ተገድለዋል ፤ በሶቢቤር 50,000 አካባቢ የሚሆኑት ጠፉ፣ በፖላንድ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተገደሉ በተጨማሪም በሶቭየት ህብረት ሌላ ሁለት ሚሊዮን ተገደሉ ፡፡ ዝርዝሩ ሊቀጥል ይችላል፣ እነዚህ በብዙ በህይወት ዘመናችን የተገደሉ ህዝቦች ነበሩ ፡፡ በአጠቃላይ በእልቂቱ ጊዜ ከስድስት ሚሊዮን በላይ አይሁዶች ተገድለዋል፣ ሰይጣንም አይሁዶችን ከምድር ለማጥፋት ሂትለርን እንደተጠቀመበት አምናለሁ ፡፡ በአሁኑ ዘመንም የእግዚአብሄር ምርጫ ህዝቦችን ለማጥፋት ሰይጣን ሌላ ሀማን፣ ሌላ የፀረ-ክርስቶስ መንፈስ ለማግኘት እየሞከረ ነው ፡፡ የቀድሞዉ የኢራን አምባገነን አህመድነጃ “ በፍልስጤም አዲሱ ንቅናቄ እስራኤልን ከእስላሙ አለም ፊት እንደ ምትጠፋ ጥርጥር የለም ብሏል “ ፡፡ እስራኤል አገራችሁ ብትሆን ሁል ጊዜ ኢራን መላዉ ህዝባችሁን ከካርታ ላይ ለማጥፋት እንደምትፈልግ ስታዉቁ እንዴት ይሰማችኋል ? በተናቀዉ ምከንያት ይህ ክፉ መንፈስ በአሁኑም ጊዜ አለ ፡፡ እስራኤል መኖሯን እንኳን እዉቅና ለመስጠት እምቢ የሚሉ ፀረ ሴሜቲካዊ ቋንቋ አሉ ፤ ለዚያም ነዉ መርዶክዮስ የሚመጣዉን መሲሁን እዉነተኛ ስዕል ፡፡ ለጠላቱ ተደፍቶ ስግደትን ለመስጠት እምቢ ያለዉ መርዶክዮስ ነበር ፤ የተናቀ ቢሆንም እንኳን ክርስቶስ ያደረገዉ ያንኑ ነው (ማር 12፡ 10፣ ዮሐ 1፡ 11፣ 1ጴጥ 2፡ 4) ፡፡ መርዶክዮስ ወደ ክርስቶስ አመልክቷል (1ቆሮ 1፡ 28-31) ፡፡
አስቴር (8፡ 1-8)፡ ሀማ በተሰቀለበት ቀን ንጉሱ የሀማን ቤት ለንግስት አስቴር ሰጣት (ቁጥር 1) ፤ ከዚያም ንጉሱ ከሀማ የጣቱን ቀለበት ከሀማ በመዉሰድ ለመርዶክዮስ ሰጠው፣ በንጉሳዊ ቤትም ከፍተኛ ስፍራ ላይ መርዶክዮስን ሾመዉ (ቁጥር 3) ፡፡ ንጉሱም ለአስቴር በትሩን ሲዘረጋላት በእርሱ ፊት በመቆም ሀማ ልኮት የነበረዉን ደብዳቤ ለመገልበጥ የንጉስ አዋጅ እንዲልክ ለመነችዉ (ቁጥር 4-6) ፡፡ የመጀመሪያዉን አዋጅ መገልበጥ የማይቻል ስለነበር ንጉሱ የምትፈልገዉን ማንኛዉንም ነገር በንጉሱ ስም መፃፍና በንጉሱ የጣት ቀለበት ማተም እንደምትችል እና የሚቀየር እንደማይሆን ነገራት (ቁጥር 7-8) ፡፡ አስቴር በመስማማት ህዝቧን ለማዳን የምትችለዉን ሁሉ አደረገች (ኢሳ 62፡ 2-6) ፤አስቴር ለመጠየቅ አልፈራችም ነበር ! ለሁላችሁም፣ ለኔም፣ ለሁላችንም የምፈልገዉ ያንን ነው - አትፍሩ ፡፡ ለመጠየቅ በሚገባ ደፋር ሁኑ !
አስቴር (8፡ 9-17)፡ መርዶክዮስ የንጉሱን ፀሀፊዎች በመሰብሰብ ለእያንዳንዳቸዉ ክፍለ ሀገሮች በራሳቸዉ ቋንቋ አዲስ አዋጅ በመፃፍ ላከ (ቁጥር 9) ፡፡ አዋጆቹ በንጉሱ የጣት ቀለበት የታተሙ ነበሩ (ቁጥር 10) ፡፡ አዋጁ ሁሉንም አይሁዶች በመንግስቱ ራሳቸዉን እንዲከላከሉ፣ እንዲገድሉና የሚጠላቸዉን ማንኛዉንም እንኳን የመጀመሪያዉ የንጉሱ ድንጋጌ ይሙቱ ብሎ ተናግሮበት በነበረዉ ቀን እንዲያጠፉ ተፈቀደላቸው (ቁጥር 11-12) ፡፡ በችኮላ መልዕክተኞቹ በመመንግስቱ ሁሉ ፈረሶችን በመጋለብ የመጀመሪያዉ አዋጅ ዋጋ እንደሌለዉ የሚናገሩትን የአዲሱን አዋጅ ግልባጮች አደረሱ (ቁጥር 13-14) ፡፡ መርዶክዮስ ከንጉሱ ፊት በንጉሱ ሀምራዊና ነጭ ልብስ እና የወርቅ ዘዉድ በማድረግ ወጣ፣ የሱሳ ከተማም ተደሰተች ፡፡ አይሁዶች በሁሉም ክፍለ ሀገርና ከተሞች በመደሰት አከበሩ (ቁጥር 15-17) ፡፡ ቀድመዉ እያከበሩ ነበር ምክንያቱም ቀድመዉ አሸንፈዉ እንደ ነበር ስለሚያዉቁ ፤ ይህ የሌሎች ህዝቦች ቡድኖች አይሁዳዊ ለመሆን ያወጁበት ብቸኛዉ ጊዜ መሆኑን ታያላችሁ ፡፡
መደምደሚያ
ኋይትኮምብ “ ይህ (እነዚህ አስራራት ጥቅሶች) በአሁኑ ጊዜ ስለ መልዕክተኛን ስራ ሚያስደንቅ አጥጋቢ መግለጫ እንደሚሰጥ ብዙ ጊዜ እንደሚያመለክት ፤ የአምላክ ሞት ኃጢዓት በሰራዉ ሰዉ ቅጣት ላይ ተሰቀለ ነገር ግን ለሁሉም ምድር የድነትን መልዕክት እንድናፈጥን እንዳዘዘን ፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ስለ ኃጢዓት የመጀመሪያዉ አስፈሪ የአለማቀፋዊዉ ኩነኔ ዉጤት መቀየር እንደሚችል የሁለተኛዉን የሚያድን ፀጋ አዋጅ በእዉቀት ብቻ መመለስ “ በማለት ፅፏል ፡፡ ለእያንዳንዳችን የመጀመሪያዉ አዋጅ ለኃጢዓትና ለሞት የወሰነን ነን ፤ ነገር ግን ሁለተኛዉ አዋጅ ክርስቶስ ወደ ምድር በመምጣት ለድነታችን በመስቀል ላይ እንደ ሞተ መልካም ዜናን አወራ (ተናገረ/ጮኸ) ፡፡ መልዕክተኞች መሆን አለብን (ሉቃ 2፡ 20) ! ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን እንድትሄድ ነግሯታል (ማቴ 28፡ 19-20) ፡፡
1 United States Holocaust Memorial Museum; available at https://www.ushmm.org/.
2 John C. Whitcomb, “Esther,” in The Wycliff Bible Commentary, ed. Charles F. Pfeiffer and Everett F. Harrison (Chicago: Moody Press, 1962), p. 107; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Esther, p. 59; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/esther.pdf.
ጥያቄዎች
-
አስቴር ምዕራፍ 7 ካነበባችሁ በኋላ መዝሙር (26፡ 24-27) አንብቡ ፤ እነዚህ ጥቅሶች በምሳሌ ላይ ሀማን እንዴት ይገልፁታል ?
-
መልካሙን ዜና በመላዉ ግዛት ዉስጥ ለማሰራጨት በእያንዳንዱ የንጉሱ ትዕዛዝ አዋጁ በፍጥነት ተፈፀመ ፤ ለሚጠፉት መልካሙን ዜና እንዴት ማድረስ አለብን ?
-
በአስቴር መፅሀፍ የተናቀ የነበረዉ ከፍ ከፍ በማለት ጨረሰ ፤ የክርስቶስ አይነት የሆነዉ እንዴት ነበር ? (ኢሳ 53፡ 3፣ ዮሐ 15፡ 24-25፣ ሐዋ 2፡ 36፣ 5፡ 30፣ ፊል 2፡ 8-9)
-
በንጉሱ ስም የተፃፈና በንጉሱ ቀለበት የታተመ ሊቀየር የማይችል አዋጅ የሜንዴና የፋሪሳዊያን ህግ ነበር ፡፡ አይዶችን ለማጥፋት የነበረዉን አዋጅ አቅም የሌለዉ ለማድረግ ንጉሱ አርጤክስስና መርዶክዮስ እንዴት አደረገ (አስ 8፡ 8-12) ? ይህን በኃጢዓት ምክንያት ከሰዉ ልጅ የመገደል ፍርድ ጋር እንዴት ታወዳድሩታላችሁ፣ እንዴት አቅም የሌለዉ ተደረገ ?
-
መዝ (37፡ 10-11) በማንበብ በአስቴር ምዕራፍ 8 እንዴት ሲረጋገጥ እንደምታዩት ግለፁት ፡፡
-
በአስቴር (7-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Esther 7:3
“Queen Esther answered, ‘If I have obtained your approval, my king, and if the king is pleased, spare my life—this is my request; and spare my people—this is my desire.’”
ንግሥት አስቴር ከንጉሡና ከሐማ ጋር በድግሱ ውስጥ ተቀምጣ ነበር ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜም ንጉሡ ለንግሥቲቱ እንድህ አላት “ የምትለምኚኝ ምንድር ነው? ይሰጥሻል የምትሺውስ ምንድር ነው? እስከ መንግሥቴ እኵሌታ እንኳ ቢሆን ይደረግልሻል አላት ።“ በዚህ ጊዜ አስቴር ቀጥታ የምትፈልገውን ተናገረች ሁለት ነገሮችን ፡- ህይወቷ እንድትተውላትና ህዝቧም እንድተርፍላት ጠየቀች ፡፡ እግዚአብሔርም ንጉሡ አስቴር የጠየቀችውን ሁሉና ከጠየቀችውም በላይ እንድሰጣት አደረገ ፡፡ አይሁዳውያንም ዳኑ ፤ አስቴርም ዳነች ፡፡ እንድሁም የአስቴር አጎት መርዶክዮስ ጭምር በቤተ መንግስቱ ውስጥ የክብር ቦታን አገኘ ፡፡ ጊዜው ልክ ነበር ፤ አስቴርም የጸለየችበትንና የጾመችበትን መልስ ተቀበለች ፡፡
እግዚአብሔር ዛሬም የማይቻለውን ማድረግ ይችላል ፡፡ እግዚአብሔር የዚህ ትውልድ “ አስቴሮች “ በድፍረት ፣ በጀግንነትና በእርሱ ላይ ብቻ በመታመን ሲነሱ ይነሳል ፡፡ አስቴር በውበቷ ላይ አልተደገፈችም ነበር ፤ በስልጣኗም ላይ አልተደገፈችም ነበር ፡፡ ጾመች እንድሁም ጸለየች ደግሞም ህዝቡ ሁሉ ከእርሱዋ ጋር አንድሆኑ ጠየቀች ፤ ይህን ሁሉ ግን በታማኙ አምላክ ላይ በመታመን አደረገች ፡፡ እምነት ሲኖርህ እምነትህ እንደ ሰናፍጭ ዘር ትንስ የሆነ ቢሆን እንኳ እግዚአብሔር የማይቻለውን ነገር ያደርጋል ፡፡ ትክክለኛ እና ቀጥተኛ ጸሎት ጸልይ ፣ ጹም ፣ እግዚአብሔርን ፈልግ እናም የእርሱን ጊዜ ጠብቅ ፡፡ አንተ አንድ የእምነት እርምጃን እስከምትራመድ ድረስ እግዚአብሔር ምን ያህል ትልቅ እርምጃን እንደሚራመድ ላታውቅ ትችላለህ ፡፡ አይዞህ አትፍራ ፡፡ ወደ ፊት ተራመድ እናም “ ግን ባይሆንስ………. ? “ እንድትል የሚያደርግህን የእምነት እርምጃ ተራመድ ፡፡ እምነት ይኑርህ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ፡፡
“ ንግሥቲቱም አስቴር መልሳ፦ ንጉሥ ሆይ፥ በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ንጉሡንም ደስ ቢያሰኘው፥ ሕይወቴ በልመናዬ ሕዝቤም በመሻቴ ይሰጠኝ “
- አስቴር 7፡3
ተጨማሪ ጥቅስ
ማቴዎስ 14:27–29 —“ ወዲያውም ኢየሱስ ተናገራቸውና፦ አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው ። ጴጥሮስም መልሶ ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው ። እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ ። “
ማቴዎስ17:20 —“ ኢየሱስም፦ ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም ። “
ዮሐንስ 14:14 —“ ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።