Pride Before the Fall
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Despised One Esther 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምዕራፍ (5-6) የሚሸፍን በእነዚህ ምዕራፎች ዉስጥ የሚታይ ምልከታ መስጠት የሚችል ታላቅ የቀድሞ ፊልም አለ ፤ በተጨማሪም በተለያየ ትኩረት በየዕለት ፅሁፉ ላይ እንድትመለከቱ ሊመራችሁ የሚችል የላዉራ የዕለት ቃል መንፈሳዊነት አለ ፡፡ ከእነዚህ ፅሁፎች ጋር እንድንገናኝ እግዚአብሄር የሚመራብን ብዙ መንገዶች አሉ ፡፡ ትናትና ሁሉም አይሁዶች በመንግስቱ ዉስጥ በአንድ ቀን እንዲጠፉና ንብረታቸዉ እንዲመዘበር በንጉሱ ድንጋጌ ደብዳቤዎች ለሁሉም ክፍለ ሀገር እንደ ተላኩ አይተናል ፡፡ መርዶክዮስም ሰማ ምን እየተካሄደ እንደ ነበርም አስቴርን አሳወቃት ፡፡ ምዕራፍ 4 መጨረሻ በቁጥር 14 ላይ መርዶክዮስ ለአስቴር ለእንደዚህ አይነት ጊዜ እግዚአብሄር በቤተ መንግስት አስቀምጦች እንደሆን ማን ያዉቃል አላት ፤ አስቴርም በንጉሱ ፊት ከመሄዷ በፊት ለእርሷ እንዲፆሙ በሱሳ ሁሉንም አይሁድ እንዲሰበስብ ነገረችዉ ፡፡
ትምህርት
አስቴር (5፡ 1-8)፡ በፆምና በፀሎት ሰዎስተኛዉ ቀን ላይ አስቴር የንግስትነት ልብሷን በመልበስ ንጉሱ እርሷን ማየት በሚችልበት በአደባባዩ (በወለሉ) ላይ ቆመች (ቁጥር 1) ፡፡ ንጉሱም አያት፣ በበትሩም ወደ ፊቱ በማንቀሳቀስ ምን እንደ ምትፈልግ ጠየቃት (ቁጥር 2-3) ፡፡ ንጉሱም እስከ መንግስቱ ግማሽ ድረስ ማንኛዉንም ነገር እሰጥሻለሁ አላት (ማር 6፡ 22-23) ፡፡ ሀማ እያደረገ ስለነበረዉ ነገር አስቴር ለምን ወዲያዉኑ አልነገረችዉም ?ዋይርስቤ የሚያመለክተዉ፡ 1) ለማሳወቅ ትክክለኛዉ ጊዜ አልነበረም ምክንያቱም ይህን ለመስማት የተዘጋጀ አልነበረም፣ 2) በንጉሱ ዙፋን ክፍል ላይ የሀማን ድርጊት ለማጋለጥ ትክክለኛዉ ስፍራ አልነበረም፣ 3) አስቴር ሀማ አድርጎት የነበረዉን ንጉሱን ስትነግረዉ ከእርሷ እና ከንጉሱ ጋር ብቻዉን እንዲቀርብ ፈለገች እና 4) ንጉሱ እስካሁን መርዶክዮስን ከአምስት አመታት በፊት የንጉሱን የግደያ ሴራ በማጋለጡ በፍፁም የተሸለመ እንዳልነበር ባለመስማቱ የአስቴርን ዜና ለመስማት ንጉሱን ለማዘጋጀት ፡፡ ይህን የተዘጋጀን በመሆን ወደ እርሱ መገኘት እንድንመጣ እንደ ንጉሱ ኢየሱስ የመጠበቅ ስዕል ማየት እንችላለን ፡፡ ሁሉንም ነገር አደጋ ዉስጥ ጣለች ፡፡
አስቴር ንጉሱና ሀማ ብቻ ለእነርሱ አዘጋጅታዉ በነበረዉ ግብዣ ላይ እንዲመጡ ጠየቀቻቸው (ቁጥር 4) ፡፡ አስቴር በፍጥነት ወደ ግብዣዋ እንዲመጡ ለንጉሱና ለሀማ ብቻ ተዘጋጀች ፤ ንጉሱና ሀማ ለመገኘት ፈጠኑ (ቁጥር 5) ፤ እንደ ገና ንጉሱ አስቴር የምትፈልገዉን እንደ ገና የመንግስቱን ግማሽ እንኳን ሳይቀር በማቅረብ ጠየቃት (ቁጥር 6)፡፡ አስቴር ንጉሱና ሀማ ለሌላ ግብዣ ነገ እንዲመለሱ ብቻ ጠየቀችዉ (ቁጥር 7-8) ፡፡ ዋይርስቤ የአስቴር ድርጊት ለእግዚአብሄር ሉዓላዊነት ማስረጃ እንደሰጠ ይናገራል፡ 1) እግዚአብሄር አስቴርን ንጉሱን ስለ ሀማ ማታለለን ቶሎ ከመናገር ከለከላት፣ 2) እግዚአብሄር የንጉሱን ምላሽ ለአስቴር ለሁለተኛዉ ግብዣ ጥሪዋን እንዲቀበል በማድረግ መራው እና 3) እግዚአብሄር አስቴርን ያዉቋት የነበሩትን ማንኞቹንም ሰዎች ከሀማ ጋር መረጃዉን እንዳይጋሩ ከለከላቸው ፡፡
አስቴር (5፡ 9-14)፡ ሀማ የመጀመሪያዉን ግብዣ በሙሉ ደስታና በንግስት አስቴር የተከበረ በመሆኑ በመልካም መንፈስ ወጣ ነገር ግን አሁንም በእርሱ ፊት ለመነሳት እምቢ ወዳለዉ ወደ መርዶክዮስ በንጉሱ በር መጣ ፡፡ የሀማ መልካም መንፈስ በመርዶክዮስ ላይ ወደ ብስጭትና ንዴት ተቀየረ (ቁጥር 9) ፡፡ በሀማና በመርዶክዮስ መካከል ያለዉ ጥላች አማሌቃዊያን በእስራኤላዊያን ላይ ከግብፅ መዉጣታቸዉ ላይ ባደረጉት ድርጊት መሰረት እንደ ነበር እናስታዉሳለን ፤ ሀማ የአማሌቃዊዉ የንጉስ አጋግ ዘር ሲሆን መርዶክዮስ ደግሞ የብንያም ነገድ ዘር ነበር (ዘጸ 17፡ 8-16) ፡፡
ሀማ ቤቱ እስከሚደርስ ድረስ ብስጭቱን ተቆጣጠረ ከዚያም ለወዳጆቹና ለቤተሰቦቹ መጥተዉ ምን ይክል ባለፀጋ እንደ ነበር፣ በሌሎቹ ንጉሳዊ ሰራተኞችና አለቆች ላይ እንዴት ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ነበርና እንዴት ንግስት አስቴር እርሱን ብቻ ከእርሷና ከንጉሱ ጋር ግብዣ ጠርታዉ እንደ ነበር እንዲሰሙት ላከባቸው (ቁጥር 11-12) ፡፡ ለእርሱ ተደርገዉለት የነበሩት መልካም ነገሮች እያሉ ሀማ መርዶክዮስ ለእርሱ የሚገባዉን አክብሮት ባለማሳየቱ ሀማ የተጨነቀ ነበር (ቁጥር 13) ፡፡ ተዋናይ ዮሐንስ ብራይሞር “ በትያትር አመታቶቼ ጊዜ ዋና ፀፀቴ በተመልካች መካከል በመቀመጥ ራሴን መመልከት ባለመቻሌ ነው “ ብሏል ፤ እናም ይህ ተሰጥቶት ስለነበረዉ ኃይልና ስልጣን በሙሉ መታበይ እና ከእርሱ በታች ካሉ ሰዎች ከክብሩ ያነሰ ማንኛዉንም ነገር ለመቀበል ፍቃደኛ ካልነበረው ከሀማ ጋር አይመሳሰልምን (ዘፍ 3፡ 4-5፣ ምሳ 6፡ 16-19፣ 16፡ 18፣ 29፡ 23) ?
የሀማ ሚስት እና ወዳጆቹ 75 ጫማ ርዝመት የሆነ መስቅያ ዛፍ እንዲሰራና በቀጣዩ ቀን ንጉሱን በዚያ ላይ መርዶክዮስን ለመስቀል እንዲጠይቀዉ ነገሩት ፡፡ ሀማን እንዲሄድና በቀጣዩ ቀን ግብዣ እንዲደሰት አበረታቱት ፤ ሀማ ምክሩን ስለወደደው በዚያ ቀን በመሄድ መስቀያ ዛፉን አዘጋጀ፣ ንጉሱ እንደ ፈለገዉ ሊያደርግለት እንደሚችል እርግጠና ነበር (ቁጥር 14) ፡፡ ስጋ ሁል ጊዜ በራሱ አጀንዳ ዉስጥ ለመግፋት ትግስት የሌለዉ መሆኑን ነገር ግን የሆነ ነገር የእግዚአብሄር ከሆነ የሚያጠፋዉና የሚቋቋመዉ ምንም ምክንያት እንዴሌለ አስታዉሉ ፡፡ ሀማ ሁሉንም ነገር ወደፊት ስለገፋ ወዲያዉኑ መርዶክዮስን ሊያጠፋዉ ይችላል ፡፡
መደምደሚያ
ዋይርስቤ ሀማ ሀሰተኛ በሆነ በራስ መተማመን፣ በትዕቢትና በክፋት ቁጥጥር ስር እንደ ነበር አመልክቷል ፤ ዊልያምባርክለይ “ ትዕቢቱ ሁሉም ኃጢዓቶች የሚያድጉበት መሰረት እና ሁሉም ኃጢዓቶች የሚመጡበት ቤተሰብ እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡ ክፋት ወደ በቀል ይቀየራል ያም በትክክል መንፈስ ቅዱስን ያሳዝናል (ኤፌ 4፡ 30-32፣ ቆላ 3፡ 8) ፡፡ በአስቴር 6 ሀማ መርዶክዮስን ባከበረዉ በንጉሱ የተዋረደ ነው ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 729.
Wiersbe, pp. 729–730.
Quoted in Wiersbe, p. 730.
Wiersbe, pp. 730–731.
Quoted in Wiersbe, p. 731.
ጥያቄዎች
-
አስቴር በንጉሱ ፊት ለመግባት እየተዘጋጀች በነበረበት ጊዜ ምንድን ለበሰች (አስ 5፡ 1) ? እንደ አማኝ በንጉሱ ፊት ለመገኘት ራሳችንን እንዴት እናለብሳለን ? (ሮሜ 13፡ 14፣ ገላ 3፡ 27፣ ቆላ 3፡ 12-14፣ 1ጴጥ 5፡ 5፣ ራዕ 19፡ 8)
-
ሀማ ሀብቱንና በንጉሱ ከፍ ከፍ ተደርጎበት የነበረዉን ደግሞ እንደቆጠረ በዚህ ሞገስ እንዳይደሰት ምን አሳሰበዉ (ከለከለው) (አስቴር 5፡ 11-13) ? በተባረካችሁበት የረካችሁ እንዳትሆኑ ምን ይከለክላችኋል ?
-
ሀማ በመርዶክዮስ ሞት ላይ ለምን አሴረ ? በመዝ (37፡ 12-13) መሰረት እግዚአብሄር ለእንደዚህ አይነት ባህሪይ እንዴት ምላሽ ይሰጣል፣ ለምን ?
-
በአስቴር (6፡ 2-3) ንጉሱ መርዶክዮስ እንዴት ህይወቱን አድኖት እንደ ነበርና ለድርጊቱ አመስግኖትም አክብሮትም እንዳልነበር አገኘ ፤ ይህ እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ?
-
ንጉሱ መርዶክዮስን ከፍ ከፍ ሊያደርገዉ ፈለገ ስለዚህም ሀማ በአደባባይ እንዲያከብረዉ ተገደደ (አስ6፡ 10-11) ፤ በፊል (2፡ 9-11) ይህ የክርስቶስ ጥላ እንዴት እንደሚሆን ታዩታላችሁ ?
-
በአስቴር (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Esther 6:6
“Haman entered, and the king asked him, ‘What should be done for the man the king wants to honor?’ Haman thought to himself, ‘Who is it the king would want to honor more than me?’”
መርዶክዮስ በንጉሡ ደጅ ላይ የግድያ እቅድ እንዳለ ከሰማ በኋላ የንጉሥ አርጤክስስን ህይወት ታድጎ ነበር ፡፡መርዶክዮስም ለህይወት አድን ተግባሩ ምንም አይነት እውቅናን አልፈለገም እንድሁም ደግሞ አልተቀበለም ፡፡ መርዶክዮስ በትህትና እና በታማኝነት መሄድን መረጠ ፡፡ በሌላ በኩል ሐማ ለራሱ ፍላጎት ብቻ ነበር የሚያስበው ፡፡ ንጉሡ ሐማን እንዴት አድርጎ የሆነን ሰው እንደሚያከብር በጠየቀው ጊዜ ፤ ንጉሡ ሊያከብረው የሚፈልገው እርሱን እንደሆነ በማሰብ ወጣ ያለ አሳብ አቀረበ ፡፡ ሐማ ለራሱ ሽልማትን በመጠበቅ በትዕቢት ተመላለሰ ፡፡ የሐማ እንደ ንጉሥ የመክበር አሳብ ፤ በመጨረሻ ተመልሶ መርዶክዮስን በክብርና በሞገስ በከተማይቱ አደባባዮች ሁሉ አከበረው ፡፡
እንደ ክርስቶስ ተከታይ የራስህን ፍላጎት ልትመለከት ወይም ደግሞ ከሌሎች ይልቅ ስለ ራስህ ልታስብ አይገባም ፡፡ አስተውል እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ፤ ለትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣል ፡፡ እውቅና ማግኘት የሚገባው ስራ መስራትህን ካወቅህ “ ራስህን ከፍ “ ባታደርግ መልካም ነው ፡፡ እግዚአብሔር ያይሃል ፤ ያደረከውን ሁሉ ያውቃል ፡፡ ከእርሱ ክብርን ትቀበላለህ ፡፡ በትህትና ስትመላለስ እርሱ ከፍ ያደርግሃል ፡፡ ዛሬ በመንፈስ ደሀ ሆኖ መመላለስን ምረጥ ከዚያም የእግዚአብሔርን ስራ በህይወትህ ታያለህ !
“ሐማም ገባ፤ ንጉሡም፦ ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ምን ይደረግለታል? አለው። ሐማም በልቡ፦ ንጉሡ ከእኔ ይልቅ ማንን ያከብር ዘንድ ይወድዳል? አለ ። “
- አስቴር 6፡6
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 27:2 — “ ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም፤ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም ። “
ፊልጵስዩስ 2:3 — “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር “
ያዕቆብ 4:6 — “ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።