Historical Books Esther

Called For Such a Time As This

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Despised One Esther 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 333 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬም የአስቴርን መፅሀፍ ማጥናት እንቀጥላለን ፡፡ በምዕራፍ (1-2) ባሏን ንጉስ አርጤክስስን በማዋረዷ ዘዉዷን ስለወሰደባት ስለ ንግስት አስጢን አንብበናል ፡፡ በፋሪስ በጣም የሚያምሩ ቆነጃጅት ወጣት ሴቶች ንጉሱ በመመልከት አስጢን ለመለካት በንጉሱ ፊት ለመሄድ አንድ አመት በሴቶች መሰብሰቢያቤት ዉስጥ ለመዘጋጀት እንዲያሳልፉ ተመርጠዉ ነበር ፡፡ አንድ የአይሁድ ወጣት ሴት አስቴር በንጉሱ ፊት ለመቅረብ ከተመረጡት ዉስጥ ነበረች፣ ቀጣይ ንግስትም ለመሆን ተመረጠች ፡፡ የአስቴር አጎት እና አሳዳጊ አባቷ በንጉሱ በር ላይ የስልጣን ስፍራ ተሰጥቶት ነበር ፤ በዚያ እያለ ንጉሱን የመግደል አንድ ሴራን ሰማ ፤ ንጉሱን ለነገረችዉ ለአስቴርም መረጃዉን አስተላለፈው ፣ ሴረኞቹም ጥፋት ተገኘባቸዉ ተሰቀሉም ፡፡ ለአስቴር ሀረጋችን (ቃላችን) የተናቀዉ ሲሆን በምዕራፍ (3-4) ወደ ጨዋታ መምጣት ይጀምራል ፡፡

በምዕራፍ 3 ንጉስ አርጤክስስ የአይሁድ ጠላት የነበረውን አንድ አጋጋዊዉን እና አሜሌቃዊዉን ሀማን አከበረው ፤ ሀማ በሌሎቹ በሁሉም ሰራተኞች ላይ ከፍ አለ (ቁጥር 1) ፡፡ ንጉሱም ሁሉም አገልጋዮቹ ለሀማ እንዲሰግዱና ክብር እንዲሰጡ አዘዘ ነገር ግን መርዶክዮስ ለማድረግ እምቢ አለ (ቁጥር 2) ፡፡ ሌሎች የሰራተኞች አባላት ለምን እምቢ እንዳለ መርዶክዮስን ጠየቁት፣ ከብዙ ቀናትም በኋላ የመርዶክዮስን ድርጊት የሚታገሰዉ እንደሆነ እንዲያየዉ ለሀማ እምቢታዉን ሪፖርት አደረጉለት ፡፡ መርዶክዮስ ለመስገድ እምቢ አለ ምክንያቱም አይሁድ ስለ ነበር (ቁጥር 3-4) ፤ ሀማ ሲሰማ በመበሳጨት መርዶክዮስ አይሁድ በመሆኑ ምክንያት በመንግስቱ ሁሉንም አይሁዶች ለማጥፋት አቀደ (ቁጥር 5-6) ፡፡ መርዶክዮስ ለመስገድ እምቢ በማለቱ ምክንያት ሀማ ንጉሱን በመዋሸት “ የማይታዘዙትን ሕዝቦች “ እንዲጠፉ አዋጅ እንዲደነግግ በመጠየቅ ሀማ ንጉሱን በምላሹ 375 ቶን ብር ወደ ንጉሱ ግምዣ ቤት እንደሚያስገባ ቃል ገባለት (ቁጥር 8-9) ፡፡ ንጉሱም በመስማማት የጣቱን ቀለበት ለሀማ ሰጠው ፤ አዋጁም በመፃፍ ሀማ ፍላጎት ታተመ (ቁጥር 10-12) ፡፡ ደብዳቤዎቹም “ በአንድ ቀንም ያጠፉና ይገድሉ ዘንድ ይደመስሱም ዘንድ ምርኮአቸዉንም ይዘርፉ ዘንድ “ ለእያንዳንዱ ክፍለ ሀገር ተላኩ ፡፡ በመላዉ ፋሬስ አገዛዝ ዉስጥ ለመገደል ታልመዉ የነበሩት ጠቅላላ የአይሁድ ቁጥር ከ15ሚሊዮን ይበልጣል ፡፡

ትምህርት

አስቴር (4፡ 1-4)፡ መርዶክዮስ ስለ አዋጁ በሰማ ጊዜ ማቅ በመልበስና አመድ በመነስነስ አዝኖ በመጮኽ እና በታላቅ ምሬት እያለቀሰ ወደ ከተማዋ ሄደ (ቁጥር 1) ፡፡ ከንጉሱ በሮች በላይ(አልፎ) መሄድ አልቻለም ምክንያቱም ማቅ ልብስ ለብሶ ስለ ነበር (ቁጥር 2) ፤ የአይሁድ ሰዎችም በመላዉ መንግስት ዉስጥ በማዘን ፆሙ (ቁጥር 3) ፡፡ እድሙንድ ብሩክ “ ሁሉም የክፉ ደስታ ሆታ መልካም ሰዉ ምንም እንዳያደርግ አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራል “ ፡፡ መርዶክዮስ ወዲያዉኑ ክፉዉ እንዲያሸንፈዉ ከመፍቀድ ይልቅ የሆነ ነገር ማድረግ ጀመረ (ምሳ 24፡ 11-12) ፡፡ እንደ አማኝ ገለልተኞች መሆን አንችልም !

በቁጥር 3 የነበረዉ ፆም የህብረት ፆም ነበር ፡፡ ለፆም የዕብራዊ መሰረት “ ከምግብ መቆጠብ “ እና “ በጊዜዉ ከመጠጥ፣ ከመታጠብ፣ በዘይት ከመቀባት ወይም ደግሞ ከወሲብ ግንኙነት መቆጠብ ማለት ሲሆን ፤ መፆም የሰዉን ድካም በእግዚአብሄር ፊት እዉቅና የሚሰጥ እና ምህረቱን መጠየቅ ነው “ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ፆም በቀድሞዉ አለም በብዛት የተፈፀመ እና “ ለሞቱት ለማዘን፣ ለአማላጅነት ፀሎት፣ ስለ ኃጢዓት ንስኃና ፀፀት እና በጭንቀት ጊዜ “ ተጠቅመዉት እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ በብሉይ ኪዳን የፆም ምሳሌ የሚያካትታቸዉ፡ የስርየት ቀን (ዘሌ 16፡ 31) እና የኢየሩሳሌም መፈራረስ መታሰቢያ (ዘካ 8፡ 19) ፡፡ ፆም አንድ ቀን ሊቆይ ይችላል (1ሳሙ 7፡ 6)፣ ሰባት ቀን ሊቆይ ይችላል (1ሳሙ 31፡ 13)፣ ወይም ደግሞ 40 ቀን ሊቆይ ይችላል (ዘጸ 34፡ 28) ፡፡

አስቴር (4፡ 5-12)፡ አስቴር መርዶክዮስ እያደረገ የነበረዉን ሰማች የማቅ ልብሱንም እንዲቀይር ልብስ ላከችለት (ቁጥር 4) ፤ መርዶክዮስ ልብሱን እምቢ ባለ ጊዜ አስቴር ምን እየተከናወነ እንደ ነበር ለመስማት ከንጉሱ ጃንደረቦች አንዱን አክራትዮስን ላከችዉ (ቁጥር 5) ፡፡ መርዶክዮስም አክራትዮስን ስለ አዋጁ እና ስለ አይሁድ መጥፋት በምላሹ ስለሀማ ገንዘብ ስጦታ ሁሉንም ነገር ነገረው (ቁጥር 6-7) ፤ መርዶክዮስ ለአስቴር እንዲሰጣትና ሕዝባቸዉን ለማዳን ንጉሱን እንድትለምነዉ በመጠየቅ የአዋጁንም ኮፒ ለአክራትዮስ ሰጠዉ (ቁጥር 8-9) ፤ ይሁን እንጂ አስቴር መልሳ አክራትዮስን መርዶክዮስን ሳይጠራት በንጉሱ ፊት የምትሄድ ከሆነ ልትገደል እንደ ምትችል እና ለ 30 ቀናት ንጉሱ እንዳልጠራት እንዲያሳዉቀዉ ላከችው (ቁጥር 10-12) ፡፡

አስቴር (4፡ 13-17)፡ መርዶክዮስ ለአስቴር ሌላ ምላሽ በመላክ በቤተ መንግስት ስለምትኖር በእዉነት እድናለሁ ብላ እንዳሰበች ጠየቃት ፤ በንግስትነት ስፍራ በዚህ ጊዜ ጣልቃ መግባት እንድትችል እግዚአብሄር አስቀምጧት እንደሆን እንድታስብ ጠየቃት (ቁጥር 13-14) ፡፡ መርዶክዮስ ሰዎስት እዉነቶችን አስቀመጠ (አመለከተ)፡ 1) የቤተ መንግስት ነዋሪ መሆን ከሞት ሊያድናት ዋስትና እንደማይሆናት፣ 2) ዝምታዋ ከሌላ ምንጭ የሚመጣዉን መዳናቸዉን እንደማይከለክል እና 3) በቤተ መንግስት ዉስጥ መሆኗ “ ለእንደዚህ አይነት ጊዜ “ እንጂ አጋጣሚ እንዳልነበር (ቁጥር 14) (ዘፍ 50፡ 20) ፡፡

ብዙ ምሁራን ስሙ እንኳን ባይጠቀስ እግዚአብሄር በዚህ መፅሀፍ እንደዳለ ያምናሉ ፡፡ ሁይ “ መፅሀፉ የእግዚአብሄር ሰዎች ከእርሱ የራቁና ያልታዘዙ ቢሆኑም እንኳን አሁንም የእርሱ ሀሳብና ፍቅር አላማ በመሆናቸው በእነርሱ በኩል አላማዉን እየሰራ እንደሆነ እንደሚያሳይ “ ይናገራል ፡፡ አሁን መርዶክዮስ የአስቴር እርዳታ ነበረው ፣ ለሰዎስት ቀናትም በሱሳ እንዲፆሙ ሁሉንም አይሁዶች እንዲሰበስብ ጠየቀችው ፡፡ አስቴርና ሴት አገልጋዮቿም ፆሙ፣ ከፆሙም በኋላ ህይወቷንም የሚያስከፍል ቢሆን አስቴር ንጉሱ ፊት ትሄዳለች (ቁጥር 16) ፤ አስቴር እንደጠየቀችዉ መርዶክዮስ ሁሉንም ነገር አደረገ (ቁጥር 17) ፡፡ ዋይርስቤ ይህን ለአስቴር የመሞትና የመኖር ጉዳይ እንደ ነበር አመልክቷል ምክንያቱም ሁሉም ነገር ከእርሷ ተቃራኒ ነበር - የፋሬሳዊያን ህግ፣ የመንግስት አዋጁ እና ለሴቶች ባለዉ በንጉሱ አመለካከት ምክንያት ፆታዋ ተቃራኒ (አስከፊ የሚያደርጉባት ነገሮች) ነበሩ ፡፡

መደምደሚያ

በመፅሀፍ ቅዱስ ምንም ቢያስከፍል የእግዚአብሄር ፍቃድ ለማድረግ ፍቃደኛ የነበረችዉ አስቴር ብቻ አልነበረችም ፤ ጳዉሎስ እግዚአብሄር በህይወቱ አድርጎለት የነበረዉን መመስከሩን እስከቀጠለ ድረስ ለህይወቱ ደንታ እንደሌለዉ ፅፏል (ሐዋ 20፡ 24) ፡፡ አስቴር የእግዚአብሄርን ፍቃድ ለማድረግ ሁሉንም ነገር ለመተዉ ፍቃደኛ ነበረች - ዘዉዷን፣ መንግስቷን እና ህይወቷንም እንኳን ሳይቀር (ሉቃ 14፡ 33) ፡፡ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን እርሱን ለመከተል ራሳቸዉን መካድ እንደ ሚያስፈልጋቸዉ ነገራቸው (ማቴ 16፡ 24) ፡፡

ይሁሉ የጀመረዉ መርዶክዮስ ለሀማ ባለመስገዱ እንደ ነበር አስታዉሱ ፡፡ ምንም ይሁን ምንም ዉጤቱ የሚወስደዉን ሁሉ ለመስራት ፍቃደኝነት ደረጃ ላይ እንዴት ትደርሳላችሁ ? ሮሜ (8፡ 31) ይህን ጥያቄ ይመልሳል፡ “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል ? “

5 F. B. Huey, Jr., “Esther,” in The Expositor’s Bible Commentary: 1 Kings—Job, ed. Frank E. Gaebelein and Richard D. Polcyn (Grand Rapids, MI: Zondervan Publishing House, 1998); quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expositional Bible Study: Esther, p. 46, available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/esther.pdf.

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 722.

  2. Wiersbe, p. 723.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 608.

  4. Nelson’s, p. 608..

  5. Wiersbe, p. 725.

ጥያቄዎች

  1. በሀማ ፊት መርዶክዮስ ለምን ተደፍቶ ክብር አልሰጠውም ? ለዚህ የሀማ ምላሽ ምን ነበር ?
  2. አይሁዶችን የማጥፋት የሀማን አዋጅ ከዘፍጥረት (49፡ 10) ጋር እንዴት ታወዳድሩታላችሁ ? ይህ ተስፋ ምን ይነግረናል ?
  3. የሱሳ ግንብ/የሱሳ ከተማ ለምን ነበር ግራ የሚያጋባው ? ለመጠጣት በመቀመጥ ንጉሱና ሀማ በራሳቸዉ ታብየዉ ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልነበረም ?
  4. በአስቴር (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Esther 4:14–16

“‘If you keep silent at this time, liberation and deliverance will come to the Jewish people from another place, but you and your father’s house will be destroyed. Who knows, perhaps you have come to your royal position for such a time as this.’ Esther sent this reply to Mordecai: ‘Go and assemble all the Jews who can be found in Susa and fast for me. Don’t eat or drink for three days, day or night. I and my female servants will also fast in the same way. After that, I will go to the king even if it is against the law. If I perish, I perish.’”

ንጉሡ አርጤክስስ አጋጋዊውን ሐማን በስልጣን ከፍ ከፍ አደረገው ከዚያም አልፎ ሐማ ውሳኔን ያስፈጽም ዘንድ የፊርማ ቀለበቱን ሰጠው ፡፡ የአስቴር አጎት መርደክዮስ እንደታዘዘው ለሐማ ከመስገድ እምቢ አለ ፣ ይህም ሐማን አስቆጣ ፡፡ ስለዚህም ሐማ ሁሉም አይሁዳዊ ህዝቦች እንድጠፉ አዘዘ ፡፡ መርደክዮስ ይህን አዋጅ ሰማ አስቴርም እንድትሰማ አደረገ ፡፡ መርደክዮስም አስቴር በንጉሡ ፊት እንድትቀርብና ህዝቧን ያድንላት ዘንድ እንድትለምን ነገራት ፡፡ ምንም እንኳ ይህ ድርጊት የራሷን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ቢሆንም አስቴር ንግሥት ሆና የተቀመጠችው እንደዚህ ላለ ጊዜ መሆኑን ተገነዘበች ፡፡ እርሷም “ ከጠፋሁ ልጥፋ “ በማለት በድፍረት በንጉሡ ፊት ህዝቧን ለማዳን ለመቅረብ ተስማማች ፡፡

ለወንጌል የምትቆምበት እድል ይኖርህ ይሆናል ፤ ነገር ግን ዝናህን አደጋ ላይ የሚጥል ፣ የገንዘብ ወይም የስራ እድገትህን ፣ ጓደኝነትህን ምናልባትም ህይወትህንም ጭምር ሊያሳጣህ ይችላል ፡፡ ዝም ማለትን ወይም ለኢየሱስ በድፍረትና በጀግንነት የተሞላ ልክ በአስቴር ጭንቅላት ውስጥ እንደነበረው “ ከጠፋሁ ልጥፋ “ የሚል ቁርጥ ያለ አቋም መያዝ ትችላለህ ፡፡ እንደ አማኝ የተጠራኸው ራስህን ልትክድ ፣ መስቀልህንም ተሸክመህ ኢየሱስን ልትከተል ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይህ ማለት አስቸጋሪውን ነገር ማድረግ ማለት ነው ፡፡ መስዋዕትነቱ ምንም ይሁን ፣ እግዚአብሔርን እመን ፡፡ ህይወትህን ለእግዚአብሔር ስትል አሳልፈህ መስጠት በምትችልበት አኗኗር ኑር ፡፡ ልክ እንደዚህ ላሉ ጊዜዎች ሲል እግዚአብሔር ዛሬ ያለህበት ቦታ ላይ አስቀምጦሃል ፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንደሆነ አስታውስ ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ ይህ ሁሉ ይገባዋል ፡፡

“ በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል ? አስቴርም እንዲህ ብሎ ለመርዶክዮስ እንዲመልስ አዘዘችው ። ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን፤ ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ፤ ብጠፋም እጠፋለሁ ። “

አስቴር 4፡14-16

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ማቴዎስ16:24 — “ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ። “
  • ሐዋርያት ሥራ 20:24 — “ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ ። “
  • ሮሜ 8:31 — “እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል ? “