Historical Books Esther

Finding the King's Favor

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Despised One Esther 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 332 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ በመጨረሻዉ የታሪክ መፅሀፍ መጀመሪያ ነው ፡፡ ይህ የዚህ አመት 332 ክፍላች ነው ፡፡ አስቴር የሚያስደንቅ መፅሀፍ ነው ፡፡ ለአስቴር መፅሀፍ አንድ ቃላችን የተናቀ የሚል ነው ፡፡ መርዶክዮስ አንድ አይሁዳዊ ነበር የተናቀም ነበር ፤ በመጨረሻም የተናቀ ወደ ሆነዉ ወደ መሲሁ ስዕል ያመጣል ፡፡

በብሉይ ኪዳን በሴት ተሰይመዉ የነበሩት መፅኀፍት መፅሀፈ አስቴርና መፅሀፈ ሩት ብቻ ነበሩ ፡፡ በአዲስ ኪዳን ከአስቴር የተጠቀሰ የለም ፤ ይህ በመኃለይ መኃለይ ሰለሞን፣ አብዲዩ እና ናሆምም እዉነት ነው ፡፡ የአስቴር ስም በዕብራዊ ሀዳስ ሲሆን (አስ 2፡ 7) “ ትንሽ ለምለም “ ወይም “ ለምለም ዛፍ “ ማለት ሲሆን ምናልባትም “ ለኮኮብ “ ከሚለዉ የፋሪሳዊያን ቃል የመጣ ወይም ባቢሎናዊያን ወደዉ አስቴር ብለዉ ከሚጠሯት ጣዖት መጥቷል ፡፡

ምሁራን የአስቴርን መፅሀፍ ማን እንደ ፃፈው አያዉቁም መርዶክዮስ፣ ዕዝራና ነህምያ ሊሆኑ የሚችሉት ናቸው ፡፡ ማክአርቱር “ ማንኛዉም አስቴርን የተጣበቀ (የቀረበ) ስለ ፋሪሳዊያን ልምድ፣ ባህሪይ እና ታሪክ እንዲሁም በተጨማሪ በሱሳ ቤተ መንግስት የተወሰነ ቤተሰባዊነትን ጥልቅ እዉቀት እንደሚያገኝ “ ይፅፋል ፡፡ በተጨማሪም ፀሀፊዉ የዕብራዊያንን ቀን አቆጣጠር፣ የዕብራዊያንን ልምድ እና የአይሁድን ብሄርተኝነት ስለተረዳ ወደ እስራኤል የተመለሰ አንድ ፋሪሳዊ አይሁድ ነበር ፡፡ መፅሀፉ የታሪክ መፅኀፍትን የዘጋ ሲሆን ዕዝራ (7-10) ብቻ፣ የነህምያ መፅሀፍት እና ሚልክያስ ቆይተዉ በታሪካዊነት የተቀመጡ ናቸው ፡፡ የአስቴር መፅሀፍ በፋሪሳዊያን ታሪክ ጊዜ ከ539 እስከ 331 ከክርስቶስ ልደት በፊት ከንጉስ አርጤክስስ መገደል በፊት 473 ከክርስቶስ ልደት በፊት አካባቢ ያበቃል ፡፡ አርጤክስስ ከ486-465 እስከ ከክርስቶስ ልደት በፊት አስተዳደረ ፤ የአስቴር መፅሀፍ 483-473 አመትን ከክርስቶስ ልደት በፊት ይሸፍናል ፡፡ አርጤክስስ በግሪክ ስሙ ለነህምያ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለስ የፈቀደለት የአርጤክስስ አባት በነበረው በአርጤክስ መፃፋችን አስፈላጊ ነው ፡፡ በአስቴር ተመዝግቦ የነበሩት ክስተቶች በባቢሎናዊያን 70 አመታት ምርኮ በመከተል በዘሩባቤል ከተመራዉ ከመጀመሪያዉ የአይሁድ ቡድን በኋላ እና በዕዝራ እየተመራ ከተመለሰዉ ከሁለተኛዉ የአይሁድን ቡድን በፊት ተካሄደ ፡፡ ዘሩባቤል አይሁዶችን ቤተ መቅደሱን መልሶ ለመስራት መራቸው የአስቴርም ክስተቶች ሆኑ ፡፡ የአይሁድ ሁለተኛዉ ቡድን ከተማዋን መልሶ ለመስራት ተመለሱ ከዚያም ሰዎስተኛዉ ቡድን በነህምያ ስር የከተማዋን ቅጥር መልሶ ለመስራት ተመለሱ ፡፡

አንዳንዶች አስቴር የሚያወዛግብ መፅሀፍ እንደሚሆን ያስባሉ ፡፡ በአስቴር መፅሀፍ ዉስጥ የእግዚአብሄር ስም በፍፁም የተጠቀሰ አይደለም ፤ ይሁን እንጂ አስቴር ከመኃልዬ መኃልየየ፣ ከሩት፣ ከመክብብ እና ከሰቆቃዉ ኤርምያስ ጋር በምኩራብ ከሚሰበኩት (መጊላህ) ጋር የተካተተ ነው ፡፡ እነዚህ አምስት መፅሀፍቶች መጊላህ ሲሆኑ በአምስት በተለዩ በዓላት ጊዜ በምኩራብ ላይ ያነቡዓቸዋል ፡፡ አስቴር ከኃማ መገደል ነፃ መዉጣትን በሚያከብሩበት ጊዜ የሚነበብ ነው ፡፡

የአስቴር አጎት መርዶክዮስ ከቢንያም ነገድ ሲሆን የእርሱ ጠላት የሆነዉ ሀማ ደግሞ አጋጋዊዉ ነበር (አስ 3፡ 1) ፡፡

እነዚህ ሁለቱ ከመገናኘታቸዉ ከአንድ ሺህ አመት በፊት እስራኤላዊያን በአማሌቃዊያን ባቻ የተጠቁ ለመሆን ከግብፅ ወጥተዉ ነበር (1445 ከክርስቶስ ልደት በፊት) (ዘጸ 17፡ 8-16) ፡፡ ንጉስ ሳዖል ሁሉንም አማሌቃዊያንን እንዲገድል ቢነገረዉም እንዲኖር ንጉስ አጋግን ፈቀደለት ፤ ቆይቶም ነቢዩ ሳሙኤል በሰይፍ አጋግን ገደለዉ (1ሳሙ 15፡ 32-33) ፡፡ የአጋግ ዘር ስለ ነበር ሀማ አይሁዶችን ጠላቸው ፡፡ በአስቴር መርዶክዮስና ሀማ የዘጸዓቱን ዉጊያ መኖር ቀጠሉ ፤ ማክአርቱር የአስቴርን መፅኀፍ በእግዚአብሄርና በሰይጣን መካከል መርዶክዮስን፣ አስቴርንና ሀማን እንደ ችዝ መጋጠሚያ ነጭና ጥቁር ነገሮች በመጠቀም እንደ ችዝ ግጥሚያ ይገልፀዋል ፡፡ በአስቴር መፅኀፍ ስለ ተናቀዉ ስናወራ ስለ መጣዉ መሲህ ጥላ ስለ ነበረው ስለ መርደክዮስ እያወራን ነው (መዝ 121፡ 4) ፡፡

በአስቴር (1፡ 1-12) ንግስቲቱ አስጢን በንጉሱ ፊት መገኘትን እምቢ አለች ፤ ንጉሱም በመበሳጨቱ ምን እንደሚያደርግ ለመወሰን ከጥበበኞች ሰዎች ጋር ተማከረ ፤ አስጢንንም ከንጉሱ ፊት አስወግዷት ዘዉዷን ለሌላ እንዲሰጠዉ መከሩት (ቁጥር 13-22) ፡፡ ምዕራፍ 2 ሌላ ንግስት ለማግኘት የንጉሱን እቅድ ያቀርባል ፡፡

ትምህርት

አስቴር (2፡ 1-4)፡ ንጉሱ ከብስጭቱ እና በአስጢን ጥያቄዉን ባለመቀበሏ ቅር ከመሰኘቱ ከተረጋጋ በኋላ የንጉሱ ረዳቶች በሱሳ ለቆነጃጅት ወጣት ሴቶች በሚኖሩበት(በሚሰበሰቡበት) ስፍራ ላይ ሀገራዊ ፍለጋ ለማድረግ መከሩ ፤ በሚሰበሰቡበት ቤት እያሉ ንጉሱን ለማግኘት በዝግጅት የቁንጃ መጠበቂያን ስለሚቀበሉ ንጉሱ ያስደሰተችዉን ይመርጣል (ቁጥር 1-4) ፡፡ ይህ የዉበት መዝናኛ አልነበረም ምክንያቱም ሴቶቹ እንደ በጎፍቃደኞች አልመጡም ስለ ወደፊታቸዉም ምርጫ አልነበራቸዉም ፡፡ ንግስት ለመሆን ያልተመረጡት ሴቶች የቀረዉን ኑሮአቸዉን በተሰበሰቡበት ስፍራ ያሳልፋሉ ፤ “ ለንጉሱ ደስታ ብቻ እያመጡ “ በተሰበሰቡበት ቤት ኖሩ ፡፡

አስቴር (2፡ 5-11)፡ መርዶክዮስ በዳዊት እና በአጃቢዎች ላይ እርግማኖችን ጭኖ የነበረዉ የሳሚ (2ሳሙ 16፡ 5-13) እና የሳዖል አባት ተብሎ የተጠቀሰዉ የቄስ (1ሳሙ 9፡ 1) ዘር ነበር ፡፡ መርዶክዮስ ወደ ኢየሩሳሌም በምርኮ ተወስዶ ነበር ከዚያም ወደ ባቢሎን ተወሰደ (ቁጥር 5-7) እናም እንደ ሴት ልጁ ያሳደጋት እናት አባት የሌላት የአጎቱ/የአክስቱ ልጅ የሀዳስ/የአስቴር ህጋዊ ጠባቂዋ ነበር (ቁጥር 7) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በምርኮ ያሉት ወይም በሌሎች ምድር የሚኖሩት ብዙ ጊዜ ሁለት ስም ነበራቸው፣ የዕብራዊ ስማቸዉ እንደ ተቀደሰ የሚታሰብ ሲሆን ሌለኛዉ ስማቸዉ ደግሞ ያደጉበትን(የለመዱትን) ባህል ያንፀባረቀ እንደ ነበር ገልፃል ፡፡ አስቴርና ሌሎቹ ወጣቶች ሴቶች ወደ ሚሰበሰቡበት ስፍራ በመወሰድ ከሄጌ ቁጥጥር ስር ተቀመጡ (ቁጥር 8) ፡፡ አስቴር ሄጌን በመሳብ ከፍተኛ ሞገስን አገኘች ፤ ሄጌ ለአስቴር የመዋብ ሂደቷን ለማፋጠን እንዲያገለግሏት ሰባት ሴት አገልጋዮችን በመምረጥ እሷንና አገልጋዮቿን ምርጥ መዋቢያዉን ሰጣቸው (ቁጥር 9) ፡፡ አስቴር በመርዶክዮስ ጥያቄ መሰረት አይሁድ እንደ ነበረች ለማንም አልተናገረች (ቁጥር 10) ፤ እስከዛዉ ሴቶቹን ለማረጋገጥ ለመርዶክዮስም በሴቶቹ መሰብሰቢያ ቤት አደባባይ አጠገብ በየቀኑ ተመላለሰ (ቁጥር 11) ፡፡

አስቴር (2፡ 12-20)፡ ሴቶቹ አመቱን በጠቅላላ እያንዳንዳቸዉ በንጉሱ ፊት ከመሄዳቸዉ በፊት በመዋብ ስርዓት (መንገድ) ዉስጥ አለፉ (ቁጥር 12) ፡፡ እያንዳንዳቸዉ ሴቶች ንጉሱን ለማየት በእርሷ የሚወሰደዉን የሚፈልጉትን ማንኛዉንም ነገር ተሰጥቷቸዉ ነበር (ቁጥር 13) ፡፡ ሴቲቱ ወሲብ ለመፈፀም በምሽት ወደ ንጉሱ ገባች ከዚያም በጥዋት ከንጉሱ ጃንደረባዉ ጋይ ስር ወደ ሁለተኛዉ መሰብሰቢያ ቤት ትወሰድ ነበር ፤ ሴቲቱ በስሟ ካልጠራት በስተቀር በፍፁም ደግሟ ንጉሱን አታየዉም ነበር (ቁጥር 14) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህ ሴቶች “ በሚቀሩአቸዉ አመታቶች መበለቶች እንደ መበለት ሆነዉ በመኖር እንደሚጨርሱ “ ይገልፃል ፡፡ የአስቴር መመለሻ በመጣ ጊዜ ሄጌ ከመከራት ነገር ጋር ብቻ መጣች ፤ ባዩአት ሁሉም ሰዉ ፊት፣ ከሌሎቹ ወጣት ሴቶች በላይ የወደዳትን ንጉስ ፊት ጨምሮ በማረጋገጥ አሸነፈች (ቁጥር 15-16) ፡፡ ንጉሱም አስቴርን በንግስትነት በማንገስ ለእርሷ ታላቅ ግብዣ በማዘጋጀት ሰራተኞቹንና ባለሟሎቹን ጋበዘ (ቁጥር 18) ፡፡ የአስቴርን ታሪክ (ወገን) ማንም አላወቀዉም (ቁጥር 19-20) ፡፡ “ ጆሴፍና የአይሁድ አዋቂዎች (አስተማሪዎች) ሁለቱም የአስቴርን ዉበት በማጋነን በባህሪዋ እና ቅዱስነቷ ላይ አሰፉት ፤ የአይሁድ አዋቂዎች (አስተማሪዎች) አስቴር በታሪክ ከሳራ፣ ከራሄልና ከአቢግያ ጋር ከአራቱ አንዷ በጣም የምታምር ሴት ነበረች በማለት አስቀምጠዋል ፤ ጆሴፍ አስቴር በሚኖርበት አለም ሁሉ በዉበት ከሴቶች የላቀችን እንደ ነበር አስቀምጧል “ ፡፡

አስቴር (2፡ 21-23)፡ መርዶክዮስ በንጉሱ በር ላይ እንዲቀመጥ ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር ፤ በዚያ ሁለቱ የንጉሱ ጃንደረቦች ንጉሱን ለመግደል እንዳሴሩ ሰማ (ቁጥር 21) ፤ መርዶክዮስም ንግስት አስቴርን ነገራት፣ በመርዶክዮስም ስም ንጉሱን ነገረችዉ (ቁጥር 22) ፡፡ ጃንደረቦቹም ጥፋተኞች ሆነዉ ስለተገኙ ተሰቀሉ (ቁጥር 23) ፡፡ እነዚህ ሰዎስት ቁጥሮች በዚህ መፅኀፍ ለሚከተሉት ሁሉም ደረጃን ያስቀምጣሉ ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር የአጎቷን ልጅ በስልጣን ስፍራ በማስቀመጥ የእስራኤልን ህዝብ አቅጣጫ በሙሉነት ስለ ሚቀይረዉ ኃይለኛ ግድያ እንዲሰማ በመፍቀድ ንግስትን ተጠቀመባት ፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡን ለሚያድን በሚችል ሁኔታ ለራሱ ጊዜና ለራሱ አላማ ሰዎችን በቦታ ማስቀመጥን ቀጥሏል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary: Esther (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 553

  2. MacArthur, p. 553.

  3. MacArthur, p. 553.

  4. MacArthur, p. 554.

  5. MacArthur, p. 554.

  6. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 604.

  7. Nelson’s, p. 606.

  8. Nelson’s, p. 607.

  9. Edwin M. Yamuchi, “The Archaeological Background of Esther,” Bibliotheca Sacra 137:546 (April–June 1980) 99–106; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Exposition Study Notes, p. 33, available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/esther.pdf.

ጥያቄዎች

  1. በአስቴር (1፡ 2) ንግስት አሰጢን የንጉሱ ጥያቄ በአደባባዩ ወደ ፊቱ እንድትመጣ የሚለዉን ለምን እምቢ እንዳለችዉ ምን ታስባላችሁ ? ቅጣቷ ምን ነበር ?
  2. አስቴር የኋላ ታሪኳን (ከየት) እንደመጣች ለማንም ለምን እንዳልተናገረች ምን ታስባላችሁ ? በመጨረሻስ ይህ ስራ በእርሷ ላይ ሞገስን አድርጓል ?
  3. መርዶክዮስ የንጉሱን ህይወት እንዴት አዳነው (አስ 2፡ 19-23) ? በንጉሱ ላይ ባሴሩት ሰዎች ላይ ምን ሆነ ?
  4. በአስቴር (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Esther 2:22–23

“When Mordecai learned of the plot, he reported it to Queen Esther, and she told the king on Mordecai’s behalf. When the report was investigated and verified, both men were hanged on the gallows. This event was recorded in the Historical Record in the king’s presence.”

ንግሥት አስጢን ንጉሥ አርጤክስስ እንዳዘዘው ለማድረግ እምቢ አለች ፡፡ ስለዚህም ከንግሥትነቷ ተሻረች ፡፡ አዲስ ንግሥት መፈለጉም ተጀመረ ፡፡ ከብዙ ወራት የውበት እንክብካቤ በኋላ ንጉሡ አባትና እናት የሌላትን ፣ በተወለደች ጊዜ ሀደሳ የሚል የእብራይስጥ ስም የተሰጣትን ያልታሰበችውን አስቴርን ወደደ ፡፡ ያሳደጋት አጎቱዋ መርዶክዮስም ከቤተ መንግስት በር ሆኖ ሳይቀር ይከታተላት ነበር ፡፡ አስቴርም ከሌሎቹ ቆነጃጅት ይልቅ መወደድንና ሞገስን አገኘች ፤ የንጉሡን ክትትልና ክብርም አገኘች ፡፡ ከዚያም መርደክዮስ ሁለት ሰዎች ንጉሡን ለመግደል ማቀዳቸውን በሰማ ጊዜ አስቴር ለንጉሡ እንድተነግር ነገራት ፣ ይህም የንጉሡን ህይወት ታደገ ፡፡

እግዚአብሔር ፍቃዱን ለመፈጸም ያልተጠበቁ ሰዎችን ባልተጠበቁ ጊዜያት ላይ ይጠቀማል ፡፡ ትጠይቅ ይሆናል አሁን ባለህበት ሁኔታ ውስጥ ለምን እንዳለህ ፡፡ ስለዚህም ለአንድ ስራ ወይም ቦታ ብቁ እንዳልሆንክ ይሰማህ ይሆናል ፡፡ ጊዜው መች እንደሆነም ልትጠይቅ ትችላለህ ፡፡ ቢሆንም ግን ተረጋጋ ይህንንም ጊዜ ከእግዚአብሔር በዓላማ የተሰጠህ እንደሆነ አድርገህ ተቀበል ፡፡ እግዚአብሔር ምክንያት አለው እናም አንተ ለእርሱና ለአሳቡ ለመታዘዝ ፍቃደኛ ከሆንክ ፣ እርሱ በጊዜው ለታላቅ ስራ ይጠቀምብሃል ፡፡ አትጠይቅ ፣ ለማወቅ ወይም ሁኔታውን ለመቀየርም አትሞክር ፡፡ በቃ ዝም ብለህ እግዚአብሔርን እመን ፣ በታማኝነት ተመላለስ ቀጣዩንም ትክክለኛ ተግባር ፈጽም ፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን ለተወሰነ ጊዜና ለተለየ ዓላማ ያስቀምጣል ፡፡ በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ ብቻ ውሰድ እናም አትጨነቅ ፤ ይህንን አድርገው ፡፡

“ነገሩም ለመርዶክዮስ ተገለጠ፥ እርሱም ለንግሥቲቱ ለአስቴር ነገራት፤ አስቴርም በመርዶክዮስ ስም ለንጉሡ ነገረች ። ነገሩም ተመረመረ፥ እንዲህም ሆኖ ተገኘ፥ ሁለቱም በዛፍ ላይ ተሰቀሉ ያም በንጉሡ ፊት በታሪክ መጽሐፍ ተጻፈ ። “

  • አስቴር 2፡22-23

ተጨማሪ ጥቅስ

መክብብ 3:1 — “ ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው ። “

ሰቆቃው ኤርምያስ 3:25-26 — “ ጤት። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው ። ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው ። “

ዕንባቆም 2:3 — “ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፤ እርሱ አይዘገይም ። “