Historical Books Nehemiah

The Surprise Ending of Nehemiah

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 331 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በነህምያ ይህ የመጨረሻ ክፍል ነው ፡፡ እግዚአብሄር የኢየሩሳሌምን ቅጥር መልሶ ለመስራት በሕዝቡ በኩል እንዴት እንዳለፈ እና ስራዉ በተጠናቀቀም ጊዜ(ነህምያ 12) ሕዝቡ እንዴት እንደተደሰቱና እግዚአብሄር እንዳመሰገኑ አጥንተናል ፡፡ በምዕራፍ 12 እና 13 መካከል ነህምያ ለ12 አመታት በይሁዳ እንደ አስተዳደር አገለገለ (ነህ 5፡ 14) ፡፡ ነህምያም ለንጉስ አርጤክስስ ቃል ገብቶት እንደ ነበረው ምናልባትም ለአንድ አመት ያክል ወደ ፋሪስ ተመለሰ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ነህምያ ከተመለሰ በኋላ የመፅሀፉ መጨረሻ ላይ በስም በጉጉት የሚሰሩትና የተቀደሱት ሰዎች ተጉዘዉ የነበሩትን፣ ኃጢዓት ዉስጥ ወድቀዉ የነበሩትን እና በአለመታዘዝ ወድቀዉ የነበሩትን በማግኘት የሚያስደንቅ እንደሆነ “ ገልፃል ፡፡ በምዕራፍ 12 ሕዝቡ በኑሮአቸዉ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን በማክበር በምስጋናና በአምልኮ አመለኩት ፡፡ ለአንድ አመት በነህምያ አለመኖር ሕዝቡ ሙሉ ለሙሉ መንገዳቸዉን አጥተዉት ነበር ፡፡ የዳስ ደህንነት ሰራዊት ጀነራል ዊልያም “ ወጣት ሰዎች በሀሳባቸዉ ለመዉጣት የእሳት ተፈጥሮ እንደ ሆነ እንዲሸከሙት እፈልጋለሁ ፤ ተስፋ ባለመቁረጥና በማስቀጠል አመዱን ማስወገድ መጠበቅ (ማድረግ) አለባችሁ ብሏል “ ፡፡

ትምህርት

ነህምያ (13፡ 1-3)፡ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቁጥሮች ዉስጥ የተሰበሰቡት ካህናት በሕዝቡ ፊት ከሙሴ የሕግ መፅኀፍት ዉስጥ አነበቡ ፤ አሞናዊያን እና ሞዓባዊያን የእግዚአብሄር ጉባኤ አካል መሆን በፍጹም እንዳልተፈቀደላቸዉ አገኙ ምክንያቱም የእስራኤል ልጆችን በሰላም ከመቀበል፣ ምግብ ከማብላት (ከመስጠት) ይልቅ እስራኤላዊያንን እንዲረግም በለዓምን ቀጠሩባቸው (ዘኁ 22፡ 1-24፡ 25) ፡፡ አይሁዶች ህጉን ሲሰሙ ከመካከላቸዉ ድብልቁን ሕዝብ ለዩ (ቁጥር 3) ፤ በኦሪት ታዘዉ ወደ ነበረዉ እየተመለሱ ነበር (ዘዳ 23፡ 3-4) ፡፡

በአብርሃም ኪዳን መሰረት እግዚአብሄር ከአብርሃም ጋር እንዳደረገው እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን የሚባርኩትን እንደሚባርክ የሚረግሟቸዉን ደግሞ ይረግማል (ዘፍ 12፡ 3) ፤ አሞናዊያንና ሞዓባዊያን እስራኤላዊያንን ረግመዉ ነበር ፡፡ ይህ ድርጊት የኢየሱስ የበጎችና የፍየሎች ትምህርት ላይ ጥላ ነው (ማቴ 25፡ 31-46) ፡፡ እስራኤልን ባልደገፉት ሕዝቦች ላይ ፍርድ እንደሚሆን አምናለሁ ፤ እስራኤልን የሚደግፉ ሕዝቦችን መፈለግ አለብን ፡፡

ነህምያ (13፡ 4-9)፡ ካህኑ ኤልያሴብ ከሰንበላጥ ጋር በኢየሩሳሌም ቅጥር ስራ ላይ ተቃዎ ከነበረዉ ከጦብያ ጋር ግንኙነት ነበረው (ነህ 2፡ 19፣ 4፡ 3፣ 6፡ 10-14፣ 13፡ 4) ፡፡ ኤልያሴብ ለጦብያ (ለጠላቱ) በቤተ መቅደሱ ዉስጥ እንዲቀመጥ ትልቅ ስፍራ አዘጋጅቶለት ነበር ፤ ነህምያ ከኢየሩሳሌም ርቆ በነበር ጊዜ ታላቁ ካህን ኤልያሴብ በእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ዉስጥ በብዙ ክፍሎች ዉስጥ እንዲያድሩ ጠላቶቹን ፈቀደላቸው ፡፡ ነህምያ ከአርጤክስስ ወደ ኢየሩሳሌም የመመለሻ መልቀቂያ እስኪቀበል ድረስ ስለ ኤልያሴብ ድርጊት አልሰማም (ቁጥር 6-7) ፤ ነህምያም ሁሉንም የጦብያን ንብረት ከቤተ መቅደሱ አዉጥቶ በመወርወር ክፍሎቹ እንዲነፁና ወደ እነዚህ ክፍሎች የእግዚአብሄር ቤት እቃዎች የተመለሱ እንዲሆኑ አዘዘ (ቁጥር 8-9) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ መንፃት “ መታጠብን፣ ማሸትንና በደም መረጨትን “ ያካትታል ፡፡

ነህምያ (13፡ 10-14)፡ በተጨማሪም ነህምያ ሌዋዊያኑንና ዘማሪዎቹን ድርሻቸዉ ተሰጥቷቸዉ ስላልነበር ወደ እርሻቸዉ ተመልሰዉ አገኛቸው (ቁጥር 10) ፤ ነህምያም የቤተ መቅደሱን አለቆች ለቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ጥንቃቄ ባለማድረጋቸዉ ገሰፃቸው አገልጋዮቹንም በመሰብሰብ ወደ ስራቸዉ መልሶ አስቀመጣቸው (ቁጥር 11) ፡፡ በግልፅ ይህ መንፈሳዊ ጉዳይ ነበር ፤ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሄር የሆኑትን ከእርሱ የሚይዙትን መገሰፅ ያስፈልጋታል ! ነህምያም ቀደም ብሎ ሕዝቡ ያላመጡትን አስራታቸዉን እንዲያመጡ ጠራቸው (ነገራቸው) ፤ ለቤተ መቅደሱም አገልጋዮች አስራታቸዉን በመቀበል የሚሰበስቡ የታመኑ ሰዎችን ሾመ (ቁጥር 12-13) ፡፡ ነህምያ ወደ እግዚአብሄር በመፀለይ ድርጊቱን እንዲያስታዉስለት ጠየቀው (ቁጥር 14) ፡፡

ነህምያ (13፡ 15-22)፡ ከዚያም ነህምያ የሕዝቡን አለመታዘዝ አዬ - በወይን ስፍራቸዉ መስራታቸዉን፣ ለመሸጥ የመደብርን ፍሬዎች ማጓጓዛቸዉን እና አሳዎችን ይሸጡና ከጢሮስ ሸቀጣሸቀጦችን ማስገባታቸዉን - እነዚህን ሁሉ በሰንበት አደረጉ (ቁጥር 15-16) ፡፡ በነህምያ ይህ ፍሬ ነገር (ጭብጥ) ይሆናል ፤ ለዉጥ (ተሀድሶ) ለማምጣት የመገሰፅ ጊዜ አስፈላጊ ነበር ፤ ነህምያ ይህን የፈቀዱትንና የእግዚአብሄርን ቀን የናቁትን የኢየሩሳሌም መኳንንትን ገሰፀ (ቁጥር 17-18) ፡፡ ነህምያ ሰንበት ከመጀመሩ በፊት የከተማዋ በሮች እንዲዘጉና ሰንበቱ እስኪያበቃ ድረስ እንዳይከፈት አዘዘ ፤ በሁሉም በሮችም ላይ ጠባቂዎችን ስላቆመ ምንም ሸቀጥ ወደ ከተማዋ መግባት አልቻለም (ቁጥር 19) ፡፡ አንዳንድ ነጋዴዎች ከቅጥሩ ዉጪ ለመሰብሰብ ሞከሩ ነገር ግን ነህምያ በኃይል ሲያስፈራራቸዉ በሰንበት ላይ አልተመለሱም (ቁጥር 20-21) ፡፡ ነህምያ ሰንበትን ቅዱስ ለማድረግ ሌዋዊያንና ጠባቂዎቹን የነፁ እንዲሆኑ አዘዛቸው ፡፡ እንደ ገና ነህምያ ድርጊቱን እግዚአብሄር ስራዉን እንዲያስብ በመፀለይ ጨረሰ (ቁጥር 22) ፡፡

ነህምያ (13፡ 23-31)፡ ነህምያ የገጠመዉ ቀጣዩ ጉዳይ ከጣዖት አምላኪዎች ጋር የነበረዉ መጋበት ነበር ፡፡ በጋብቻዉ የተወለዱት ግማሾቹ ዕብራዊ(ዕብራይስጥ) መናገር አይችሉም ይህ ማለት መፅኀፍን ማንበብ የማይችሉና እግዚአብሄርን አያዉቁም ማለት ነው (ቁጥር 23-24) ፡፡ ነህምያ በመገሰፅ ረገማቸዉም፣ አንዳንድ ወንዶችንም መታ፣ ፀጉራቸዉንም በመንጨት አሕዛቦችን እንዲያገቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸዉን እንዳይፈቅዱ እንዲምሉ አስገደዳቸዉ (ቁጥር 25-27) ፡፡ የኤልያሴብ አንዱ የልጅ ልጅ ለሌላኛዉ የይሁዳ ጠላት ለሰንበላጥ የሕግ ልጅ ቢሆንም እንኳን አባረረው (ቁጥር 28) ፡፡ ነህምያ እግዚአብሄር የክህነቱን ስርዓትና የእግዚአብሄርን ኪዳን አርክሰዉ የነበሩትን እንዲያስታዉሳቸዉ ፀለዬ (ቁጥር 29) ፤ ከዚያም ነህምያ ሁሉንም ነገር በማንፃት ለእያንዳንዱ ካህንና ሌዋዊ የተለዩ ተግባራትን ሰየመ (ሰጣቸዉ) (ቁጥር 30) ፡፡ ነህምያ ሕዝቡን በኩራትን በሚሰጡበት ጊዜ መራቸው - የምርጡን ምርጥ - መልሰዉ ለእግዚአብሄር እንዲሰጡ (ቁጥር 31) ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር ነህምያን ተጠቀመበት ነህምያም በሂደቱ ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሄር ታዛዥ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እያንዳንዳችንም እንደ ነህምያ ሊጠቀምብን ይፈልጋል ፡፡ የእግዚአብሄርን ቤተ ክርስቲያን እንደ ሰራተኛ መስራት ስንጀምር ሰይጣንም እንኳን የሚበልጥ ኃይል ሊኖረዉ አይችልም (ማቴ 16፡ 18) ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 599.

  2. William Booth; quoted in William Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Nehemiah (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 693.

  3. Nelson’s, p. 600.

ጥያቄዎች

  1. አሞናዊያንና ሞዓባዊያን ወደ እግዚአብሄር ጉባኤ እንዲገቡ ለምን ነበር ያልተፈቀደላቸው ? (ዘዳ 23፡ 3-4)
  2. እስራኤላዊያን ለመጠበቅ ያልቻሉት ከእግዚአብሄር ጋር ያደረጉአቸዉ ጥቂት ተስፋዎች ምን ነበሩ ? (ነህ 10፡ 28-31, 39፣ 13፡ 1-11፣ 15-17)
  3. በቁጥር 4-5 ጦብያ የሚባል አንድ ሰዉ ተጠቅሷል ፤ ጦብያ ማን ነበር ነህምያስ ጦብያ ወደ ቤተ መቅደሱ ብዙ ክፍሎች ላይ መግባት በመሰጠቱ ለምን ነበር የተበሳጨዉ ? (ነህ 2፡ 10, 19፣ 4፡ 3 ፤ 6፡ 10-12,17, 19)
  4. የብዙ ዘር ጋብቻ ልጆች ዕብራዊ እንዴት እንደ ሚናገሩ አለማወቃቸው ችግሩ ምን ነበር ? አንድ አማኝ እና አንድ አማኝ ባልሆነ መካከል ያለው ንግግር ልዩነት አለው ? ጥቂት ምሳሌዎች ምንድን ናቸው ? (1ዮሐ 4፡ 5-6)
  5. በነህምያ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Nehemiah 13:6–8

“While all this was happening, I was not in Jerusalem, because I had returned to King Artaxerxes of Babylon in the thirty- second year of his reign. It was only later that I asked the king for a leave of absence so I could return to Jerusalem. Then I discovered the evil that Eliashib had done on behalf of Tobiah by providing him a room in the courts of God’s house. I was greatly displeased and threw all of Tobiah’s household possessions out of the room.”

ከቅጥሩ መጠናቀቅ በኋላ ነህምያ ንጉሥ አርጤክሲስን ለማገልገል ወደ ባቢሎን ተመለሰ ፤ በኋላም ወደ እስራኤል መጣ ፡፡ ነህምያ ባቢሎን ሲሄድ ህዝቡ እግዚአብሔርን እያመለኩና ለአሳቡም እየተገዙ ነበር ፤ ነገር ግን ነህምያ በሌለበት ሰዓት ህዝቡ ፈተና ውስጥ ገብተው ነበር ፤ ከእግዚአብሔር መንገድ ተመልሰው ነበር ደግሞም ለአምላካቸው ባለመታዘዝ ይመላለሱ ነበር ፡፡ አሁንም እንደገና ነህምያ ተስፋን አስገኘ ፡፡ እግዚአብሔርን ፈለገ እንድሁም ከህዝቡ ጎን መቆሙን ሳያቋርጥ ጸለየ ፡፡ በህዝቡ ውስጥ ላለው ለእግዚአብሔር እሳቱን እንደገና እንድያነቃቃ እግዚአብሔር ነህምያን ተጠቀመ እነርሱም ልባቸውን ወደ እርሱ መለሱ ፡፡

የሚነድድ እሳት ከተተወ እንደሚጠፋ ሁሉ ፤ አማኞችም ከተተው ፍላጎታቸውንና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ንጽህና ማጣታቸው የማይቀር ነው ፡፡ ኢየሱስን ስትከተል ትጉ ፣ በመንፈስ የምትቃጠልና ለእግዚአብሔርን የምትገዛ ሆነህ እንድትኖር ነው ፡፡ ብረት ብረትን እንደሚስል ሁሉ ሰውም ሰውን ይስላል ፡፡ ለእግዚአብሔርና ለቃሉ መታመንህን አትተው ፡፡ ከሌሎች አማኞች ጋር ጊዜን አሳልፍ ፡፡ እምነትህን አስፋ ፡፡ ለእግዚአብሔር እሳትህን ለማንደድ ዛሬ ምን ይሆን ማድረግ የሚገባህ ? እግዚአብሔር አለም የእርሱን ታላቅ ፍቅር እንድያውቅ በውስጥህ ያለውን እሳት ማንደድህን ታስቀጥል ዘንድ ይናፍቃል ፡፡

“እኔ ግን በባቢሎን ንጉሥ በአርጤክስስ በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበርና በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም አልነበርሁም። ከጥቂት ዘመንም በኋላ የንጉሡን ፈቃድ ለመንሁ ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጣሁ፤ ኤልያሴብም በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦብያ ጓዳውን በማዘጋጀት ያደረገውን ክፉ ነገር አስተዋልሁ ። እጅግም አስከፋኝ፤ የጦብያንም የቤቱን ዕቃ ሁሉ ከጓዳ ወደ ውጪ ጣልሁ ። “

  • ነህምያ 13፡ 6-8

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 27:17 — “ ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል ። “

ሮሜ 12:11 — “ ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ “

2ኛ ጢሞቴዎስ 1:6 — “ ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፥ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ ። “