The Joy of Jerusalem
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዚህ ሳምነት የመጨረሶቹን የነህምያን ሁለት ምዕራፎችና የአስቴርን ጠቅላላ መፅሀፍ እንጨርሳለን ፤ ይህ ማለት የታሪክ መፅኀፍት ጥናታችንን የምንጨርስ ይሆናል ማለት ነው ፡፡ ለነህምያ መፅሀፍ አንዱ ቃል ገንቢ(ሰራተኛ) ነው ፡፡ ነህምያ ቤተ ክርስቲያንን መልሶ የሚሰራዉን መሲሁን ኢየሱስን የሚያሳይ በኢየሩሳሌም የከተማዋን ቅጥር መልሶ እንዲሰራ የተጠራ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ቅጥሩን ለመስራት ነህምያን እንደ ተጠቀመው ቤተ ክርስቲያኑን ለመስራት ሊጠቀምብን ይፈልጋል (ማቴ 16፡ 18) ፡፡ ዋይርስቤ “ በዚህ አለም ላይ ስራዊ እንዲሰራለት እግዚአብሄር በተለያየ ስጦታና ችሎታ ብዙ የተለያዩ ሰዎችን ተጠቅሟል ….ስለዚህም ለእግዚአብሄር ሰዉነታችንን ስንሰጠው ስራዉን ለመፈፀም እንደ መሳሪያ ሊጠቀምብን እንደ ሚችል “ አስቀምጧል ፡፡ የምዕራፍ 12 የመጀመሪያዎች 26 ቁጥሮች ከዘሩባቤል ጋር ቤተ መቅደሱን እና ቅጥሮቹን መልሶ ለመስራት ተመልሰዉ የመጡትን ሁሉንም ሰዎች ይዘረዝራል ፡፡ እነዚህ ሁሉም ሰዎች ራሳቸዉን ለእግዚአብሄር ሰጡ ይህ ደግሞ ስማቸዉ የተመዘገበ እንዲሆን ለነህምያ አስፈላጊ (ጠቃሚ) ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ይህን ምዕራፍ ወደ ሁለት ክፍል ይከፋፍለዋል፡ ለእግዚአብሄርን ራስን መስጠት እና ለእግዚአብሄር ምስጋና መስጠት ፡፡
ትምህርት
ነህምያ (12፡ 1-2)፡ራሳችንን ለእግዚአብሄር መስጠት፡ ዘሩባቤልና ኢያሱ ከፈራረሰ በኋላ የሰለሞንን ቤተ መቅደስ መልሰዉ ለመስራት ተመልሰዉ የሄዱትን መሩ ፤ ከእነርሱ ጋር 22 አለቆች (ቁጥር 1-7) እና ስምንት ሌዋዊያን (ቁጥር 8-9) መጡ ፡፡ ሌዋዊያን እርስ በእርሳቸዉ በተቃራኒዉ በመቆም የምስጋና መዝሙሮችን መሩ ፡፡ በቁጥር (10-11) የኢያሱ ዘር ተጠቅሰዋል ፡፡ በቁጥር 12 መጀመሪያ ላይ ካህናቱ ተጠቅሰዋል (ቁጥር 12-21) ፡፡ በቁጥር 22 ላይ ካህናቱም ተጠቅሰዋል በተጨማሪም ነህምያ ምናልባትም የቤተ መቅደሱን ወጪ በመክፈል ስለረዳዉ የፋሪስን ንጉስ የዳሪዮስን ዘመን ጠቀሰዉ ፡፡ ነህምያ የሌዊ ልጆች በዜና መዋዕል መፅሀፍ ላይ እንደ ተፃፉ አብራራ (ቁጥር 23) ፡፡ በቁጥር 24 የሌዋዊያን አለቆች በቁጥር 25 ከበር ጠባቂዎች ጋር የተጠቀሱ ናቸው ፡፡ እነዚህ በኢዮአቂም እና በነህምያና በዕዝራ ዘመን ነበሩ (ቁጥር 26) ፡፡
ነህምያ (12፡ 27-47)፡ምስጋናችንን ለእግዚአብሄር መስጠት፡ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለዉን ቅጥር ለመቀደስ እንደ ተዘጋጁ መቀደሱን በደስታ፣ በምስጋና እና በዝማሬ እንዲመሩ ከመላዉ እስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ሌዋዊያንን ጠሩዓቸው (ቁጥር 27) ፡፡ በተጨማሪም የዘማሪዎች ልጆች ተሰበሰቡ (ቁጥር 28-29) ፡፡ ቶም ኮንስታብል “ ነህምያ ሌዋዊያንን ከመላዉ ይሁዳ የመቀደስ ስርዓቱ በትክክል እንዲሆን ዋስትና ለመስጠት እንደጠራቸው(እንደሳባቸዉ) “ ይገልፃል ፡፡ ካህናቱ እና ሌዋዊያኑም ራሳቸዉን፣ ሕዝቡን፣ በሮቹን እን ቅጥሩን አነፁ (ቁጥር 30) ፡፡ ዋይርስቤ ይህን በቅጥሩ ላይ የሰሩና የጠበቁ በቅጥሩ ላይ አምላኪዎች የሆኑበት እንቅስቃሴ እንደሆነ ይገልፃል ፡፡
በነህምያ 6 በቅጥሩ ላይ የነበረዉ ስራ ተጠናቀቀ ከዚያም በምዕራፍ (8-10) መነቃቃት ፈነዳ ፡፡ በነህምያ (7፡ 4-5) ነህምያ ኢየሩሳሌም በዉስጧ ጥቂት ሕዝቦች ይኖሩባት እንደ ነበር አስቀምቷል ፡፡ በምዕራፍ (11፡ 1-2) ከተማዋን በሕዝብ እንደ ገና ለመሙላት ወደ ኢየሩሳሌም ማን እንደሚጓዝ ለመወሰን እጣ ጣሉ ፤ የቅጥሩ መቀደስ ዘግይቶ የነበረዉ በእነዚህ ምክንያቶች ነበር ፡፡ ሁሉም ነገር በቦታዉ ሲቀመጥ መቀደሱ ተካሄደ ፡፡ በዕብራዊ “ መቀደስ “ የሚለዉ ቃል በሶሪያዊያን ከረከሰ በኋላ የቤተ መቅደሱ ከመቀደሱ ሂደት የሚመጣ “ መቀደስ “ ማለት ነው ፡፡ በዚህ መቀደስ የምስጋና መዝሙሮችን መዘመር ስምንት ጊዜ፣ ምስጋና መስጠት ስድስት ጊዜ፣ መደሰት ሰባት ጊዜ እና የመሳሪያዎች ጥቅም ሰዎስት ጊዜ ተጠቅሷል ፡፡ አከባበሩ ትልቅ ነበር ! ምስጋና የመስጠት ድርጊት ማለት “ በአደባባይ ለሌሎች ጮኾ በማወጅ የአደባባይ እዉቅና መስጠት ማለት “ ፡፡
ከመንፃቱ በኋላ ነህምያ የይሁዳን አለቆች በቅጥሩ ላይ በማምጣት በቅጥሩ ላይ በተለያዬ አቅጣጫ በመሄድ በሁለት ታላቅ ተርታዎች ላይ ምስጋና እንዲሰጡ ሾማቸው (ቁጥር 31) ፡፡ ነህምያ ተጨማሪ ሰዎችን የመጀመሪያዉን ተርታ እንዲቀላቀሉ በዕዝራ ተመርተዉ የነበሩትን አንዳንዶችን ከዳዊት መሳሪያ ጋር የነበሩት ጠራቸው (ቁጥር 31-36) ፤ ከዚያም ሁለተኛዉ ተርታ በቅጥሩ በሌላኝዉ አቅጣጫ ከነህምያ ኋላ የሄዱትን ሰረገሎች አካትቷል (ቁጥር 37-39) ፡፡ ሁለቱም ተርታዎች በቅጥሩ አጠገብ ሲጓዙ ምስጋና ሰጡ (ቁጥር 40-42) ፡፡ ሁለቱም ቡድን መስዋዕትን አቀረቡበትና እተደሰቱበት ስፍራ ቤተ መቅደሱላይ በአንድ መጡ (ቁጥር 43) ፡፡ ዋይርስቤ “ ሕዝቡ እግዚአብሄር ሰርቶላቸዉ እንደ ነበር እና ብቻዉ እንደሚያከብራቸው ለሚመለከታቸዉ አለም ምስክር እያቆሙ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ በኃይል ስለተደሰቱ “ በታላቅ ከሩቅ ተሰማ “ (ቁጥር 43) ፡፡ ቻርለስ ፈንሻም የቀኑን አስፈላጊነት “ አዲሱ የተሰራዉ የኢየሩሳሌም ቅጥር መቀደስ ለዕዝራና ለነህምያ መፅሀፍ ጫፍ ነዉ “ በሚል በዚህ መንገድ ይገልፀዋል ፡፡ በቁጥር (44-47) ከመቀደሱ በኋላ ሕዝቡ ለካህናቱ፣ ለሌዋዊያኑ፣ ለዘማሪዎቹ እና ለበር ጠባቂዎች ዕድል ፋንታቸዉን ለማምጣት እርምጃ ወሰዱ ፡፡
መደምደሚያ
አይሁዶች በዕጣ በኩል አልፈዉ እንደ ነበር ስላወቁ በሁሉም እንደ ገና ማለፍ አልፈለጉም ፤ ኮንስታብል የዚህን ክስተት ጥቅም አብራርቷል፡
“ ይህ በማህበረሰቡ መታደስ ዉስጥ ታላቅ ታሪክ ነበር ፡፡ አሁን እስራኤል የመጀመሪያዉ ስደተኞች ተመልሰዉ ከነበረው ይበልጥ ደህንነቱ በተጠበቀና መፅሀፍ ቅዱሳዊ ወደ ሆነዉ ምድር ተመልሰዉ ነበር ፤ ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር መልሶ በመስራት፣ እንደ እስራኤል ስልጣን የሙሴን ሕግ መልሶ በማቋቋም እና ከእግዚአብሄር ፍቃድ ጋር በመስማማት የቤተ መቅደሱን አገልግሎት በማስተዋል ተሳክቶለት እንደ ነበር” በማለት አብራርቶታል ፡፡
እንድንመለከተዉ ለእኛ ጥያቄ አለ፡ እግዚአብሄር በፍፁም ኑሮአችንን ሲቀይረው እንዴት ርቀን ዝም ብለን መቀመጥ እንችላለን ? ይህ የመቀደስ ስዕል እግዚአብሄር እንዴት እንድናመልከዉ እንደሚፈልገን ስዕል(መልክ) ነው ፡፡
William Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Nehemiah (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 690.
Wiersbe, pp. 688–690.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expositional Notes: Nehemiah, p. 57; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/nehemiah.pdf
Wiersbe, p. 690.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 599.
Nelson’s, p. 599.
Wiersbe, p. 691.
F. Charles Fensham, New International Commentary on the Old Testament: The Books of Ezra and Nehemiah (Grand Rapids, MI: Wm. B. Eerdmans Publishing Co., 1983), pp 257–258.
Constable, p. 58.
ጥያቄዎች
-
በምድሪቱ የነበሩት ሌዋዊያን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ የተጠየቁት ለምን ነበር ?
-
በየትኛዉ የሰልፍ ተርታ ላይ ዕዝራ መራ ? በየትኛዉ መንገድ በመሄድ ቤተ መቅደሱን በመከተል በፊቱ በምን በሮች አለፉ ? (ነህ 12፡ 31-37)
-
ስለ አገልግሎቱ መቀደስ በጣም አስፈላጊ ስለነበረዉ ነገር ምን ታስባላችሁ ? (መዝ 68፡ 32-35፣ ዕብ 13፡ 15)
-
ስፍራ በመያዝ ለዚህ መቀደስ አገልግሎት በጣም ኃላፊነት የነበረበት ማን ነበር ?
-
የእግዚአብሄር ደስታ ምን እንድንሰራ ይመራናል (ነህ 12፡ 44-47) ? በራሳችሁ ጉባኤ ዉስጥ ለእግዚአብሄር ይህን የሚመስል አይታችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አላያችሁም ?
-
በነህምያ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ ያስረዳችኋል (ያሳያችኋል) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Nehemiah 12:43
“On that day they offered great sacrifices and rejoiced because God had given them great joy. The women and children also celebrated, and Jerusalem’s rejoicing was heard far away.”
ነህምያ ህዝቡን ወደ ኢየሩሳሌም ቅጥር ደስታ በተሞላበት ቁርጠኝነት መራ ፡፡ ከግዞት መውጣት ነበረባቸው ፤ በህብረት መስራት እና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደገና መስራትም እንዲሁ ፡፡ ጊዜው የመደሰት ጊዜ ነበር ! በአንድነት እንደ ንጹህ ህዝብ ሆነው ተሰበሰቡ በመዝሙርና በመለከት ድምጽ ምስጋናንም አቀረቡ !
ሁልጊዜ ከእንቅልፍህ ለአዲስ ቀን ስትነቃ እናም ህይወትህን ለእግዚአብሔር እንደ ህያው መስዋዕት አድርገህ ለማቅረብ እድሉን ስታገኝ ፤ ስለዚህ ህይወት የሰጠህን አምላክ ! ተስፋ የሰጠህን አምላክ ! ታላቅ ደስታና ኃይልን የሰጠህን አምላክ ! እግዚአብሔርን አመስግን ! ጌታ በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ የደህንነትንና የዘላለማዊ ሕይወትን ነጻ ስጦታ አቅርቧል ! ምናልባት አዲስ ልጅ ይኖርህ ይሆናል ፣ አዲስ ቤት ፣ አዲስ ስራ ወይም አዲስ ፕሮጀክት ቢሆንም ግን ይህን አዲሱን ጊዜህን ለእግዚአብሔር አሳልፈህ ስጥ ፡፡ አዲስ ዝማሬን ለእርሱ ዘምር ፡፡ መለከትን ንፋ ወይም ደግሞ ጊታር አንሳ እንድሁም ለእግዚአብሔር የደስታን ድምጽ አሰማ ፡፡ ህይወትህን አሳልፈህ ስትሰጥ ሌሎች ቢሰሙስ……. እና ምን ? ደስታ የተሞላበት የምስጋና ጩኸት ምን እንደሆነ እንድሰሙና እንድደነቁ አድርግ ፡፡
“እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ ። “
- ነህምያ 12፡43
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ሳሙኤል 7:29 — “ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ተናግረሃልና አሁን እንግዲህ ለዘላለም በፊትህ ይሆን ዘንድ የባሪያህን ቤት፥ እባክህ፥ ባርክ፤ በበረከትህም የባሪያህ ቤት ለዘላለም ይባረክ ። “
መዝሙር 98:4–6 — “ ምድር ሁሉ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ አመስግኑ፥ ደስ ይበላችሁ፥ ዘምሩም ። ለእግዚአብሔር በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ ። በዋሽንትና በመለከት ድምፅ በንጉሥ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ ። “
ሮሜ12:1–2 — “ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው ። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።